Get Mystery Box with random crypto!

ዘሪሁን ገሠሠ

የቴሌግራም ቻናል አርማ zerihunkocha — ዘሪሁን ገሠሠ
የቴሌግራም ቻናል አርማ zerihunkocha — ዘሪሁን ገሠሠ
የሰርጥ አድራሻ: @zerihunkocha
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 13.77K
የሰርጥ መግለጫ

በመረጃ እንቀራረብ! በመረጃ እንተሳሰር!

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 8

2023-04-16 15:24:59
እነ ብርሃኑ ጁላ በክፉ የማያነሱት አሸባሪ!

//በጋዜጠኛ - ጌታቸው ሽፈራው//

በፎቶ የምትመለከቱት የከሚሴው "ሸኔ" ነው። የዚህ ቡድን መሪ ትህነግን ከሚሴ ላይ ተቀብሎ ሰራዊቱን የወጋ ነው። በድምፀ ወያነ ቲቪ ዜና የቀረበው የቡድኑ መሪ ከጦርነቱ ቀደም ብሎ በሰራው ወንጀል ደብረብርሃን ላይ ታስሮ ነበር። የኦሮሚያ ብልፅግና መንገድ በክልሉ ፖሊስ አዘግቶ ህዝብ ወደ አዲስ አበባ እንዳያልፍ አድርጎ ነው ያስፈታው።

ከዚህ በኋላ የኦሮሚያ ብልፅግና አጀንዳ ሲፈልግ ይህ ቡድን አጣዬንና አካባቢውን እንዲያጠቃ ያደርገዋል። ሰሞኑን ልዩ ኃይሎችንና ንፁሃንን ያጠቃው ይህ ቡድን ነው። ይህ ቡድን ትጥቅ አልፈታም። እንዲፈታም አይፈለግም። ህዝብና ሰራዊት ሲያጠቃም እነ ብርሃኑ ጁላ ስሙን አያነሱም። በሀሰት ፋኖ ልዩ ኃይል የመታ አስመስለው ሲያቀርቡ ይህ ቡድን በቀደሞ ከሚሴ ላይ የፈፀመውን ዘግናኝ ጥቃት ግን አይናገሩም። ምክንያቱም አጀንዳ ማስፈፀሚያቸው ነው።

በነገራችን ላይ ባለፈው እነ ምሬ ጋር ሰላም የተፈጠረው በአካባቢ ሽማግሌዎችና በቀጠናው ባሉ የሰራዊት መሪዎች እንጅ እነ ብርሃኑማ ችግሩ እንዲፈታ አይፈልጉም። በቀጣይም ሰበብ እየፈለጉ ችግር ይፈጥራሉ። በአማራው ላይ ችግር ሲፈጥሩ ግን ከሚሴ ያለውን አሸባሪ በክፉ ስሙን ማንሳት አይፈልጉም።
3.8K views12:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-16 15:10:41 አቶ ብርሀኑ ጁላ ፥ ረዘም ባለው ጥላቻ ፥ እብሪት ፣ ማንአለብኝ ባይነት ፣ ፍረጃና ስድብ ብቻ በተስተዋለበት የትናንቱ መግለጫቸው ፦

የአማራ ብልፅግናን << የተቀበሉና ያፈነገጡ >> ብለው ለሁለት ከፈሉ፡፡ ፋኖን <> ፅንፈኛና ፅንፈኛ ያልሆነ >> በማለት በተመሳሳይ በሁለት ጎራ መደቡ፡፡ ቀጠሉና " ልዩ ሀይሉ ለምን ተነካ !" ሲል ለክብሩ በይፋ ለትግል የተነሳውን ፋኖ ደግሞ << ፋኖ ልዩሀይሉን ጨፍጭፏል ፥ ዘርፏል …ወዘተርፈ >> ሲሉ በመፈረጅ ፤ አስነዋሪና ይሉኝታቢስነት በተንፀባረቀበት መልኩ ፦ የእርስበርስ መከፋፈልን ለመፍጠር ብሎም አንዱን በአንዱ ላይ ለማስነሳት ከፍተኛ ጥረት አድርገዋል፡፡

ታዲያ ይህን ሠው "ይሉኝታ ቢስ የሴራ ፖለቲከኛ" እንጂ የማዕረግ ስሙን አስቀድሞ "የኢትዮጵያ የጦር ሀይሎች ኤታማዦር ሹም " ብሎ መግለፅ ይቻላልን ?

በነገራችን ላይ ይሄ በነውር የተሞላው መግለጫ ፤ ቀጣዩን ሁኔታ ፍንትው አድርጎ የሚያሳይ የጥላቻ ፖለቲካውን የወደፊት አቅጣጫ አመላካች እንጂ በቀላሉ የሚታለፍ ጉዳይ አይሆንም!
4.2K viewsedited  12:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-15 23:35:44
በዛሬው እለት በሱዳን ጀነራል ዳጋሎ (ሄሜቲ) በሚመራው ጦር ፤ የተማረኩት የግብፅ ወታደሮች!
4.2K viewsedited  20:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-15 22:02:47
በዛሬው የሱዳን አየር ድብደባ ፥ የሳዑዲ ኤርባስ - A330-300 የመንገደኞች አውሮፕላን ተመትቷል!

ዛሬ በሱዳን ካርቱም አለምአቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በተፈፀመው የአየር ጥቃት ከወደሙት አውሮፕላኖች መካከል የሳኡዲ አረቢያ Airbus A330-300 (HZ-AQ30) እና የዩክሬናውያኑ ስካይአፕ አየር መንገድ  Boeing 737-800 (UR-SQH) ይገኙበታል፡፡

አውሮፕላናቹ የአየር ጥቃቱን ያስተናገዱት መንገደኞችን ለማሳፈር እየተዘጋጁ ባሉበት ሰአት ሲሆን ፥ ሳዑዲ ከጥቃቱ በኃላ  መንገደኞቹን ካርቱም በሚገኘው ኤምባሲዋ ገብተው ከለላ እንዲያገኙ አድርጋለች፡፡

ወደሱዳን የሚደረጉ በረራዎች ሙሉ በሙሉ ተቋርጠዋል!
1.2K views19:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-15 20:48:57 ግብፅ በይፋ ከአልቡርሃኒ ጦር ጎን በመሰለፍ ጦርነቱን መቀላቀሏን አምናለች!

CGTN AFRICA ከደቂቃዎች በፊት የግብፁን ወታደራዊ ቃል አቀባይ ኮሎኔል ጋህሪብ አብደል ሀፊዝን ጠቅሶ ፤ << Egypt’s military is coordinating with relevant Sudanese authorities to guarantee the safety of Egyptian forces. >> በማለት ፤ ግብፅ በሱዳን ላሉት ሀይሎቿ ስትል ከአልቡርሃኒ ጦር ጋር አብራ እንደምትሰራ መግለፇን ዘግቧል፡፡

በጀነራል ዳጋሎ (ሄሜቲ) የሚመራው ጦር ፤ በሱዳን የሚገኘውን የግብፅ ጦር ወታደራዊ ካምፕ ከ17 ሩሲያ ሰራሽ su25 ጀትና 179 ታንክ ጋር መማረኩን ይፋ ማድረጉ የሚታወስ ነው፡፡

ኢጋድ ከሰአታት በፊት ባወጣው መግለጫ << የሱዳን ጉዳይ ከሀገሪቱ አልፎ ለቀጠናው አደገኛ ሁኔታ የማፈጥር ነው! >> ሲል ማሳሰቡ ይታወቃል፡፡

በሱዳን ያለው ሁኔታ ምሽቱንም ተባብሶ ቀጥሏል፡፡ የተለያዩ የሱዳን ግዛቶች በከባባድ ተኩሶች እየተናጡ ይገኛሉ!
2.1K views17:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-15 19:16:40
የአልቡርሃን ማስጠንቀቂያና የግብፅ ወታደራዊ ኃይል መማረክ!

የዳጋሎ (ሄሜቲ) ሃይል ቤተ-መንግስቱን ጨምሮ ዋና ዋና ተቋማትን የተነጠቁት ፥ ጀነራል አልቡርሃን << የፈጥኖ ደራሽ ሃይሉ ከካርቱም ካልወጣ ተጨማሪ ጦር ከክልሎች እናስገባለን ! >> ሲሉ ማስጠንቀቂ መሠል መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

ጀነራል ሃምዳን ዳጋሎ በበኩላቸው “ቀድመን የተወጋነው እኛ ነን ፤ አልቡርሃንን ለፍትህ ሳናቀርብ ትግላችን አናቆምም!" ሲሉ በአር ኤስ ኤፍ የትዊተር ገጽ ላይ ገልፀዋል!
በጀነራል ዳጋሎ (ሄሜቲ) የሚመራው ጦር ፤ መቀመጫውን ሱዳን ያደረገው የግብፅ ጦር ወታደራዊ ካምፕ ከ17 ሩሲያ ሰራሽ su25 ጀትና 179 ታንክ ጋር መማረኩን ይፋ ካደረገ ሰአታት ተቆጥረዋል!

ግጭቱ በመላው ሱዳን በፍጥነት እየተዛመተ ሲሆን ኢጋድን ጨምሮ በርካታ የአለም ሀገራት ሁኔታው እንዳሳሰባቸው እየገለፁ ይገኛሉ!
2.7K views16:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-15 18:58:58 ይህ የኛ መሠረታዊ አጀንዳ ሊሆን አይችልም!

አንድ ወዳጄ << የኦሮሚያ ልዩ ሀይል የምርጫ ፎርም ተዘጋጅቶለት እየሞላ ይገኛል፡፡ መቀላቀል የሚፈልጉትን ተቋማት ዝርዝር ከያዘው ከዚህ ቅፅ ውስጥ 'የአዲስአበባ ፖሊስ' የሚል ምርጫ መኖሩ ግርምትን ፈጥሮብኛል! ለሌሎቹም ልዩ ሀይሎች ነው ወይስ ለኦሮሚያ ልዩ ሀይል ብቻ? >> የሚል መረጃ አድርሶኛል!

ሲጀመር የኦሮሚያም ይሁን የሌሎች ክልሎች ልዩ ሀይሎች መፍረስ አለመፍረስ ጥያቄአችን አልነበረም፡፡ አይሆንምም፡፡ "የአማራ ልዩ ሀይል መፍረስ የለበትም !" ብለን ስንሞግትም ፥ አንድም የመርህና የአሰራር ቅደም ተከተሎችን ጠቅሰን ሁለትም የአማራ ህዝብ ያለበትን ነባራዊ ሁኔታና በሀገሪቱ አስቻይ ሁኔታዎች አለመኖራቸውን በተጨባጭ መረጃና ማስረጃ ይዘን ነው! ጥያቄአችን የጠራና ግልፅ አመክንዮ ያለው ነው!

ከዚያ ባሻገር የኦሮሚያ ልዩ ሀይል ፈረሰም አልፈረሰም ፥ የት ገባም የት ወጣም የእኛ መሠረታዊ አጀንዳ ሊሆን አይችልም !

ወዳጆች! መረጃውን ያጋራኃችሁ ፥ ምናልባት ይፋ ተደርጎ ስታውቁት "የተለየ አጀንዳ " እንዳታረጉት ከወዲሁ ለመጠቆም ያህል ነው!
2.6K views15:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-15 17:29:44
2.8K views14:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-15 17:29:32 በኢትዮጵያ የዜጎች ፈተና ሆኖ የሚገኘው የዋጋ ግሽበት ፥ በቀጣይ ወራት አሁን ከሚገኝበት በ50% ሊያድግ ይችላል!

በነዳጅ ሀብቷ የበለፀገችውና የተሻለ የኢኮኖሚ አቅም ያላት ናይጄሪያ   ፥ ማዕከላዊ ባንኳ የሀገሪቱ የመገበያያ ገንዘብ የሆነውን  ናይራ/ naira የመግዛት አቅም የማዳከም እርምጃ ከወሰደበ በኃላ  ፥  የሀገሪቱ የዋጋ ግሽበት ባለፈው ወር ከነበረበት 21.91 በመቶ ወደ 22.04 በመቶ ማደጉን የስታስቲክስ ቢሮው ዛሬ ቅዳሜ  ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

በከፍተኛ የዋጋ ግሽበት ዜጎቿ እየተሰቃዩ የምትገኘው ኢትዮጵያ ፥ ከጊዜ ወደጊዜ እየተባባሰ ለመጣው ከፍተኛ የሆነ የዋጋ ግሽበት  ፥ የሀገሪቱ መንግሥት ካለፉት አመታት ጀምሮ የብርን የመግዛት አቅም በተከታታይ በማዳከሙና በየጊዜው እያተመ ወደኢኮኖሚው ስርአት የሚያስገባቸው ከፍተኛ ቁጥር ያለው የገንዘብ ኖት በመሠረታዊ ምክንያትነት ሲጠቀሱ ቆይተዋል፡፡

ሠሞኑን ኢትዮጵያ በታሪኳ በአንድ ጊዜ የጠየቀችውን የ2 ቢሊየን ዶላር ብድር ፥ ሂደት አስቻይ ሁኔታዎች ለመገምገም አዲስአበባ የሰነበቱት የአለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (IMF) እና የአለም ባንክ ከፍተኛ አመራሮች በሰጡት አስተያየት ፥ ሀገሪቱ ካለባት ያልተከፈለ ከፍተኛ ብድር  አንፃር አሁን የተጠየቀውን ብድር የሚፈቅዱት ከዚያ አኳያ ገምግመው መሆኑን ጠቅሰው  ፤ ነገርግን  ብድሩን ሙሉ በሙሉም ሆነ የተወሰነውን ቢፈቅዱ እንኳ በቅድሚያ የሀገሪቱ ብሔራዊ ባንክ የሀገሪቱን የመገበያያ ገንዘብ "ብር/birr " የመግዛት አቅም አሁን ካለበት በ50% ማዳከምን ጨምሮ ሌሎች ቅድመ ሁኔታዎችን ማሟላት እንደሚጠበቅባቸው ማስቀመጣቸው ታውቋል፡፡

እንግዲህ ይህ የአለም ባንክ ቅድመ ሁኔታ ከተተገበረ ፥ የ1 ዶላር ዋጋ አሁን በሀገሪቱ ባንኮች ከሚሸጥበት 54 ብር ገደማ በቀጥታ ወደ መቶ ብር ማደጉ ይጠበቃል፡፡ የሀገሪቱ የወጭ ንግድ ከውጭ ከምናስገባው አንፃር 1/3ኛ እንኳ የማይሸፍን ሆኖ ባለበት ሁኔታ ፥ የብርን የመግዛት አቅም በ50% ማዳከም ማለት አሁን ለህዝቡ ፈተና ሆኖ የሚገኘውን የዋጋ ግሽበትና የኑሮ ውድነት በአንድ ጊዜ በ50% መጨመር እና በቀጥታ ግሽበቱን ወደ Hyper Inflation ደረጃ ማሸጋገር መሆኑ ሳይታለም የተፈታ ነው፡፡

በቀላል ስሌት በዶላር የምንገዛው ነዳጅ አሁን ካለበት ዋጋ 50% ሲጨምር ፥ በሀገሪቱ የሸቀጦች ዋጋና መሠረታዊ ፍላጎቶች ላይ የሚያሳድረውን ተፅዕኖ መገመት የሚያዳግት አይሆንም፡፡

ከወር በፊት በወጭ ንግድ ላይ የተሰማሩ ባለሀብቶችና ድርጅቶች "ምርቶቻችንን ለአለም ገበያ በርካሽ ዋጋ እያቀረብን ከውጭ በውድ ገዝተን ከማስገባት  ይልቅ በሀገር ውስጥ ገበያ መሸጥ ያዋጣናል " ብለው ስራ ወደማቆም የገቡበትን አጨቃጫቂ ሁኔታ መዘገቤ ይታወሳል፡፡

እንደሚታወቀው ጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ ወደስልጣን በመጡ በወራት ውስጥ የብርን የመግዛት አቅም ያለበቂ ጥናት በተከታታይ የማዳከምና ከፍተኛ የሆነ የገንዘብ ኖት ፥ ከሀገሪቱ ብሄራዊ ባንክ በማይመለስ ብድር መልክ እየታተመ ወደኢኮኖሚ ስርአቱ እንዲገባ የማድረግ እርምጃ መውሰዳቸውን ተከትሎ ፥  በመላ ሀገሪቱ የዋጋ ግሽበት ለተከታታይ አመታት ፈታኝ እንደሆነ መቆየቱ የሚታወስ ነው፡፡

በአሁኑ ሠአት ሀገሪቱ ያላት የዶላር ክምችት ለ15 ቀን እንኳ የማይበቃ መሆኑና በከፍተኛ የኢኮኖሚ አጣብቂኝ ውስጥ እንደምትገኝ ከሰሞኑ የወጡ መረጃዎች አመላካች ናቸው፡፡

"በእንቅርት ላይ ጆሮገድፍ" ማለት ይኸው ነው!
2.9K views14:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-15 16:03:26 "ህውሓት ለኮረምና አላማጣ አካባቢዎች አመራር መድቦ የመከላከያ ሠራዊቱን መውጣት እየተጠባበቀ ይገኛል!" ስትል አዲስ ዘይቤ ዘግባለች!

የአዲስ ዘይቤን ሙሉ ዘገባ ሊንኩን ተጭነው ያንብቡ!

https://am.addiszeybe.com/featured/mekelle/current-affairs-am/It-is-known-that-the-TPLF-has-been-assigned-the-leadership-of-Korum-and-Alamata-areas
3.1K views13:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ