Get Mystery Box with random crypto!

ዘሪሁን ገሠሠ

የቴሌግራም ቻናል አርማ zerihunkocha — ዘሪሁን ገሠሠ
የቴሌግራም ቻናል አርማ zerihunkocha — ዘሪሁን ገሠሠ
የሰርጥ አድራሻ: @zerihunkocha
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 13.77K
የሰርጥ መግለጫ

በመረጃ እንቀራረብ! በመረጃ እንተሳሰር!

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 5

2023-04-27 18:03:37
ጠመንጃ ካነሱትና ከጉልበተኞች ጋር ብቻ የሚደራደረው መንግስት!

<< መንግስት አሁን በያዘው መንገድ እያሳየ ያለው ጠመንጃ አንስታችሁ ታጥቃችሁ ካልታገላችሁኝ እውቅና አልሰጣችጉም ከእኔ ጋር የመደራደር መብት አልሰጣችሁም የሚል መልእክት ነው እያስተላለፈ ያለው ይሄ እጅግ አደገኛ እና ሀገሪቱን ወደ ከፋ ሁኔታ የሚወስድ ነው። >>

<< አንድ መንግስት መደራደር ያለበት የግድ አንድ ፖለቲካ ሀይል ተመንጃ ስላነሳ ጉልበታም ስለሆነ አይደለም የህዝብን ጥያቄ ካነሳ ማንኛውም ሀይል ጋራ ያለውን ችግር በሰላማዊ መንገድና በድርድር ለመፍታት መዘጋጀት አለበት። >>

// አንጋፋው ፖለቲከኛ - አቶ ልደቱ አያሌው የተናገረው //
5.1K viewsዘሪሁን ገሠሠ, 15:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-27 16:41:58
ገፀ-ባህሪያቶቹ...!

" ...ጁንታዎቹ ከፈለጉኮ ራሳቸው ያስቀመጡት ህግ አለ፡፡ በዚያ መሠረት ጥርግ ማለት ይችላሉ! " ያለችው " ..አዲስአበባ ላይ ፈቅደን ብናኖራቸው ፤ ... ሲጨፍሩብን ያድራሉ!" ስትል አዲስአበባን የግሏ ርስት አድርጋ በአደባባይ ስትውረገረግ የነበረችው ከንቲባ አዳነች አቤቤ ፥ መቀሌ መሄዷ ችግር አይደለም፡፡

የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ፥ " ..ጁንታው መሸበት..!" ሲሉ ኖረው ፥ "እንደምን አደርክ ጁንታው?" ለማለት ፥ ማልደው መቀሌ መገኘታቸውም ስህተት ላይሆን ይችላል፡፡

ጌታቸው ረዳም " ..ዳፍንታሞች!" ሲላቸው የከረሙትን ብአዴኖች መሪ ፥ እንደፋርማሲ እባብ አንገቱ ስር ጥምጥም ብሎ ሲተውን መመልከታችንም ፥ በአለም ላይ ያልተለመደ ነገር አይደለም፡፡

" ..ከህወሓት ጋር አብሮ መቀመጥ ሁሉ ሀፂያት ነው!" ሲል የከረመው ሽሜ አብዲሳ ፥ የጌታቸው ረዳን አንገት ላይ ተጠምጥሞ ሮማንቲክ አስተቃቀፍ ማሳየቱም የሚኮነን ላይሆን ይችላል፡፡

" ..ህወሓት የተበተነ ዱቄት ሆኗል ፥ የተበተነ ዱቄት ደግሞ ተሰብስቦ ተቦክቶ ሸገር ዳቦ አይሆንም! " ሲል የከረመው የፒፒ ካድሬ ፥ ህወሓትን ሊጠይቅ ዱቄት አስፈጭቶ "እንገፍ እንገፍ" ማለቱም ሊገርመን የማይገባ ጉዳይ ነው፡፡

ችግሩ ፦

ተጨባጭና ችግር ፈቺ ፖለቲካ በመስራት እንጂ ገፀባህሪያትን ተከፋፍለው እየተንሸራሸሩ ፥ ፖለቲካዊ ተውኔት በመተወናቸው "ዘላቂ ሰላም እናረጋግጣለን!" እያሉ የሚያቅራሩት ነገር ፥ ራሳቸውን ከማታለል በዘለለ አንዳች ፋይዳ የሌለው "እንዘጭ እንዘጭ" መሆኑ ነው!



አሁን የት ይገኛል 'ሰላም ሰላም' ቢሉት ደርሶ በለበጣ
ማስመሰል ድካም ነው ፥ የምሩ ሲመጣ!
5.1K viewsዘሪሁን ገሠሠ, edited  13:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-26 19:33:43
2.3K viewsNo War No Peace, 16:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-26 19:33:24 በትናትናው የአብን መግለጫ ዙሪያ የኔ የተለየ አስተያየት...!

ትናንት አብን ያወጣውን መግለጫ ተከትሎ እጅግ የተጋነኑ ተቃውሞዎችን አስተውያለሁ፡፡ ሁሉም ትችትና ተቃውሞዎች " ከዚያስ …?" ለሚለው ጥያቄ ምላሽ የሚሰጡ ሆነው አላገኘኃቸውም፡፡ በመሆኑም እኔ እንደግለሰብ ከተንሸራሸሩት ተቃውሞዎች የተለየ ሀሳብ ስላለኝ ፥ በአመክንዮ ልምግታችሁ ወድጃለሁ፡፡ ከተሳሳትኩ በጨዋ ደንብ በምክንያትና በውጤት የተደገፈ ሀሳብ በመሰንዘር ለምታርሙኝ በሩ ክፍት ነው፡፡

የአብንን መግለጫ አንድ ሰላማዊ የፖለቲካ ፓርቲ ማለት ካለበትና ከሚጠበቅበት የሀሳብ አበርክቶት ብሎም ከፖለቲካዊ ተግባቦት አኳያ በጥቅሉ ከገመገምነው ፥ የመግለጫው ሀሳብ ፈፅሞ ስህተት ነው ብዬ አላምንም፡፡

ነገርግን በግሌ ፥ " አብን ህዝቡን ሊያታግልም ሆነ ትግሉን ሊመራ የሚችለው በቅድሚያ ያሉበትን ድርጅታዊ ተግዳሮቶች ፈትቶ ፥ በፖለቲካ ምህዳሩ ላይ በሁለት እግሩ መቆም ሲችል በመሆኑ ፥ ትኩረትና ርብርቡ ግንቦት 6 ለማድረግ በወሰነው ጉባኤ ላይ መሆን ነበረበት" ብዬ ስለማምን ብሎም " የፖለቲካ ብልሽቱ የፈጠራቸው ተቋማት ላይ ያሉት የገነገኑ ችግሮች ፥ በተቋማቱ ላይ አስተማማኝ እምነት ለማሳደር የሚያስችሉ ባለመሆናቸው" ፤ ተቀዳሚ አስተያየቴ "አብን በዚህ ጉዳይ አስተያየት ሳይሰጥ ዝም ብሎ ቢያልፈው የተሻለ ነው!" የሚል ነው፡፡

ከዚያ ውጭ ሁሉም ክልሎች በተለይ ኦሮሚያ ፥ ከፍተኛ ርብርብ አድርገው አብዛኛዎቹ ልዩ ሀይሎች ፎርም ሞልተው ፥ ወደመከላከያ እንዲገቡ አድርገዋል፡፡ ነገ ከነገ ወዲያ ኦነግ ሸኔም ከድርድሩ በኃላ ወደመከላከያ ይግባ ይባላል፡፡ የአማራ ክልል ደግሞ ሰላሳ ፐርሰንቱን እንኳ በቅጡ አልተቆጣጠረውም፡፡

አብን እንደአንድ ሰላማዊ የፖለቲካ ድርጅት ፥ አስቀድሞ በምክንያት " ልዩ ሀይሉ መፍረስ የለበትም!" ብሎ ተከራከረ ፥ ታገለ ፤ አስጠነቀቀ፡፡ ነገርግን መንግሥት "አይቻልም!" ብሎ በውሳኔው ገፋበት፡፡ ህዝባችንም የህይወት መስዋዕትነት እስከመክፈል የደረሰ ትግል አድርጓል ፤ ነገርግን ልዩ ሀይሉ ከመበተን ውጪ ተቋማዊ ሆኖ እንደቀደመው የሚቀጥልበትን እድል መፍጠር ወይም መቀየር አልተቻለውም፡፡

በመሆኑም " ይህ ትጥቅ ይዞ የተበተነ ሀይል የት ይግባ ?" የሚለው መመለስ ያለበት ተቀዳሚ ጥያቄ ሆኖ አፍጥጦ መጣ፡፡ እኔ ከዚህ በፊት እንደግለሰብ "ልዩ ሀይሉ ግንባር ይዞና ተደራጅቶ ይታገል ፥ አለበለዚያ ('መንግሥት ትጥቅ ይዞ እንዲቀመጥ ይፈቅዳል አይፈቅድም) የሚለው ሌላ ጥያቄ ሆኖ ፤ በየቤቱ ገብቶ ይቀመጥና ከህዝብ ጋር ይታገል " ብያለሁ፡፡ አሁንም በግሌ ብጠይቁኝ ያንኑ ልደግም እችል ይሆናል፡፡

አብን እንደድርጅት ግን " ሌሎቹ እያደረጉ እንዳሉት የፌደራል ተቋማቱን ይቀላቀል!" ማለት እንጂ "አማፂ ቡድን ይሁን!" ብሎ ምክረ ሀሳብ እንዲይዝ መጠበቅ ምናልባትም የዋህነት ካልሆነ ምንም ሊሆን አይችልም፡፡ የመወሰንና የማስገደድ አቅምም የለውም፡፡

ቆይ እሺ ከመቶ ሺህ በላይ ልዩ ሀይል ውስጥ ሰላሳ ሺው እንኳ በክልሉ ሀንድል ካልተደረገ ፤ ወይ ገዢ ምድር ይዞ በሌላ እዝና ስያሜ የሚታገል ህዝባዊ ፎርስ ካልሆነ ፤ በየከተማው ትጥቅ ይዞ ተበትኖ በምን አግባብ ይኑር ? አይደለም ለአስር ሺዎች ለአስር ልዩ ሀይል ደመወዝ መክፈል የሚችል አደረጃጀትና ቁርጠኝነቱስ አለንን ? ሌላው ቀርቶ ይህ ሀይል ሲራብስ ....?

"መንግስት ነኝ" የሚለው አካልስ ፥ ይህን ተበትኖ ያለን የታጠቀ ሀይል በነፃነት እንዲንቀሳቀስ ይፈቅድለታልን ? ይህ ሀይል አሁን ባለበት ሁኔታ ለህዝባችን ሰላምና ደህንነት አስተዋፅኦ ማበርከት ይችላልስ ወይ ? ይህ ትጥቅ ይዞ የተበተነ ሀይል በዚህ መልኩ መጓዙ ለራሱ ደህንነትና ህልውና አያሰጋውም ወይ ?

በየአካባቢው ትናንትን ጨምሮ በተለያዩ ጊዜያት የተበታተኑት ልዩ ሀይል ወንድሞቻችን የጥቃት ተጋላጭ ሆነው በተናጠል እየሞቱ ነው፡፡ ይህ ለህዝቡም ሆነ ለእነሱ ይጠቅማቸዋልን ? ህዝባዊ መስዋትነትስ ነውን ?

እኚህን ጥያቄዎች ለራሳችን ከመለስን ፥ "የመከላከያ ሰራዊቱም ሆነ የፌዴራል ፖሊስ ተቋማት" የምናነሳባቸው ግድፈቶችን ባልቀረፉበትም ሁኔታ ቢሆን ፥ የሰው ሀይላቸውን እያጠናከሩ ወደፊት መቀጠላቸው እስካልቀረ ድረስ ፥ ይህ ተበትኖ የሚገኝ ሀይል ወደእነዚህ ተቋማት ቢገባ የተሻለ ህዝባዊና ሀገራዊ አስተዋጽኦ ማበርከት እንደሚችል ሳናመነታ እንረዳለን!

ተቋማዊ የሆነ አቋምም ፥ ሊሆን የሚችለው ይህኑ ነው፡፡ እንደግለሰብ ግን ሌላ አማራጭ ልናቀርብ እንችል ይሆናል! ተፈፃሚና የሚቻል ከሆነ...!

ያሰብነውና ያቀድነው ካልሆነ ግን ህዝባችን በየተቋማቱ ምንም ድርሽ እንዳይል አድርገን ከሁለት አንድ ያጣ ሆኖ ፥ በቀጣይ ምን እንደሚሆን አስባችሁታልን ?

ትችትና አስተያየታችን ሚዛን ይኑረው! ነባራዊ እውነታውን የተረዳ ይሁን! ሌላው ሆይ ሆይ ለህዝቡ ፈፅሞ አይጠቅመውም! ራሳሳችን ባቀበልነው አለንጋም እየተገረፍን መሆናችንን ማሰብ ያስፈልጋል፡፡

የምንታገለው ለህዝባችን ጥቅምና ፍላጎት ከሆነ " ከዚያስ…?" ብለን ራሳችንን በመጠየቅ ፥ አማራጭ መፍትሔ ማቅረብ በማንችልበት ጉዳይ ላይ በጭፍን ከመቃወም መቆጠብ ብሎም ከተለዋዋጩ የፖለቲካ ኡደት ጋር አብሮ የሚሄድ ፣ አቅምን ያገናዘበና የተተነተነ የፖለቲካ አስተሳሰብ ማራመድ ያስፈልጋል፡፡

በዚህ መልኩ የማይነገረውን ሁሉ ለማንሳት የወደድኩት ፥ የኛ የሳይበር ሰራዊት ሁሉ ነገር በአደባባይ ተሰጥቶ ቢነገርም ለመቀበል ስለማይፈቅድ ነው፡፡ ፖለቲካዊ ትምምን ቢኖርና ብንታደልኮ ፥ ትክክለኛ የተደራጀና በጋራ ኮዙ ላይ የተግባባ የፖለቲካ ማህበረሰብ ፥ የራሱ ፖለቲከኛ በአደባባይ ለፖለቲካል ኮሚዩኒኬሽን በተቃራኒ እንኳ ቢሆን በሚይዘው አቋምና ንግግር በጥቅሻ ተግባብቶ ፥ በውስጥ ግን የሚፈለገው ነገር በጋራ የሚፈፀምበትን አውድ መፍጠር የሚችል ነበር፡፡

በጥቅሉ የአማራ ህዝብ አሁናዊ የፖለቲካ ሁኔታ ፥ አይደለም ለሰው ለአምላክ እንኳ አሰልቺና አድካሚ ሆኗል ! ሁሉም የሚናገርበትና የሚፈርድበት ፥ በተናጠል የሚጮህበት ፥ ሁሉም በየእጁ አቅጣጫና መስመር የሚያመላክትበት ፥ መደማመጥ ፣ መተማመን ፣ መከባበርና መተባበር የራቀው የትርምስ ማዕከል ሆኗል ! ከዚህ መውጣት የምንችለው በቅድሚያ እያንዳንዳችን ራሳችንን መመልከትና ማረም ስንችል ነው ! መደማመጥ ፣ መከባበርና መተባበር መገለጫ ምግባራችን ሲሆን ብቻ ነው!

በግሌ ምናልባት ከእንግዲህ አልፎ አልፎ ካልሆነ በስተቀር ፤ በአማራም ሆነ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ምንም የምልበት አቅም እየተሟጠጠ በመምጣቱ ፥ ይህን ህዝብ " እሱ ይሁንህ !" ከማለት ባሻገር ብዙ ላልል እችላለሁ !

በሀሳብ ሊያርሙኝ ፥ ሊሞግቱኝ ለሚችሉ ወንድም እህቶች በሩ ክፍት ነው!

ትችትና አስተያየታችን ሚዛን ይኑረው!

ይኸው ነው!
2.3K viewsNo War No Peace, 16:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-25 22:42:41
የ35 የአማራ፣ 2 የአፋር ባለሃብቶችና ድርጅቶች የባንክ አካውንት ታገደ

የአማራ ሕዝብ ትግልን ሊደግፉ ይችላሉ በሚል አካውታቸው ታግዷል።  የፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት ዛሬ ለሁሉም ባንኮች በጻፈው ደብዳቤ የ35 የአማራ ባለሃብቶች እንዲሁም 2 የአፋር ባለሃብቶች በባንክ ያላቸው ገንዘብ እንዲታገድ ለሁሉም ባንኮች ተፅፏል። ደብዳቤውን ተመልከቱት።
የሞቱ ሰዎችም ጭምር በእገዳው ስማቸው ተጠቅሷል፡፡ ዘሀበሻ - ሚያዝያ 17/2015 ዓ.ም
4.3K viewsዘሪሁን ገሠሠ, 19:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-25 21:02:38 በነገራችን ላይ ፦

" መንግስት ነኝ" የሚለውን አካል ምንም እንበለው ምን ፥ ከሚቆጣጠረው የፀጥታ አካል ውጭ ታጥቆ ፥ በየከተሞቹ የሚንቀሳቀስን ኃይል ትጥቅ ማስፈታትና መቆጣጠር መደበኛ ስራው ነው!

ከተማ  መሀል በቡድንም ሆነ በተናጠል መሳሪያ ይዞ የሚንቀሳቀስ ፋኖ ሊኖር አይገባም ፥ አይችልምም! ፋኖ ወደቤቱ ሲመለስ ሰላማዊ ነዋሪ ነው፡፡ ወደቤቱ ካልተመለሰም የት መገኘት እንዳለበት ጠንቅቆ ያውቃል!

ትጥቅ ይዞ መንቀሳቀስ የሚቻልበትን ሁኔታ ማብራራት የሚያስፈልገው አይመስለኝም!

በመሆኑም  በየከተማው "ፋኖ እከሌ ተከበበ" የሚል ዜና ለህዝባችን አጀንዳ መሆን የለበትም !
4.2K viewsዘሪሁን ገሠሠ, 18:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-25 20:45:11 ምን ማለት እንደሚቻል አላውቅም ! ምንም አለማለትም አልተቻለም!

የክልሉ መንግሥት ለሌላ ችግር በመፍጠር ፥ ለችግሮች መፍትሔ ማምጣት እንደማይቻል የተረዳው አይመስለኝም !

ህግና ስርአት ለማስከበርምኮ ስሜትና ማንአለብኝነት ሳይሆን ስርአትና ስክነት ያስፈልጋል! አለበለዚያ እርስበርስ ከመጠፋፋትና ሌላ ችግር ከመውለድ ውጭ አንዳችም የሚመጣ ነገር የለም!

በመንዝ ቀያ ፥ በመንዝ ላሎ ምድር አካባቢ የተጀመረው አይነት ነገር ደስ አይለኝም! በአስቸኳይ መታረም ያለበት ጉዳይ ነው! መፍትሄን ከህዝቡ መፈለግ  ፥ ህዝቡንም የመፍትሔ አካል አድርጎ መንቀሳቀስ ያስፈልጋል!

"ሳይቃጠል በቅጠል "
4.1K viewsዘሪሁን ገሠሠ, 17:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-25 17:05:00 የመፍትሔ አካል ለመሆን ካሰብን ....!

መደራደርም ሆነ መገዳደር የቻሉት ብሎም "አሸናፊ ሆነናል!" ለማለት የበቁት የፖለቲካ ኃይሎች ፤ በጋራ ኮዛቸው ላይ ተግባብተው ፥ ውስጣዊ ችግሮቻቸውን አቻችለውና ፈትተው ፤ ከጀርባቸው ሀብትና ንብረቱን ፥ ጊዜና እውቀቱን እንዲሁም የራሱንና የልጆቹን ህይወት ሳይቀር ደስ እያለው የሚያዋጣ የፖለቲካ ማህበረሰብ ገንብተው ስላስከተሉ ብቻ ነው! ሌላ ሚስጥር የለውም!

"የፓርቲ አባል ሆነህ ታገል!" እንኳ ስትለው << አበል አለው ወይ ? ፤ ስንት ካሬ ቦታ ይሰጠኛል ? ፥ በጀት ከሌለው አልሰማህም ፤ ሹመትስ አገኛለሁ? " ወዘተረፈ እያለ ቅድመ ሁኔታ የሚደረድር ፥ ነፃነቱ ከሰማይ እንደሚወርድ መና በነፃ እንዲዘምብለት የሚሻ ፥ የሌሎችን ጥንካሬና ቁርጠኝነት በሂሳብ ዋጋና በጉርሻ ተመን የሚተምን ፤ "ተማርኩ" የሚልን ፥ እልፍና አዕላፍ አስመሳይ ደንቆሮ ሁሉ ፥ ጠፍጥፈህ ሳታስተካክልና ማህበረሰባዊ የአመለካከት ለውጥ ሳታመጣ ፥ ወደፊት ስንዝር መራመድ ቅዠት ነው!

እስኪ እያንዳንዳችን እጆቻችንን ለ5 ደቂቃ ከኪይቦርድ ላይ አንስተን "ለህዝባዊ ትግሉ ያለኝ ቁርጠኝነትና መስዋዕትነት እስከምን ድረስ ነው ? ምንስ ሚና አበረከትኩ ? ምንስ ደካማ ጎን አለኝ? >> ብለን እንጠይቅ!

በመቀጠልም ፦ ከምናገኘው የራሳችን ግምገማ ተነስተን ራሳችንን እናርም ፥ እናስተካክል!

ያኔ ለሁሉም ነገሮች አመቺና በቀላሉ የሚደራጅና ለትግል የሚዘጋጅ ትውልድ እንሆናለን!
4.2K views14:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-25 15:08:15 የደሀ ፖለቲካ ለምን ውሃ መውቀጥ ይሆንብናል ?

" አፍሪካውያን ለዘመናት ከድህነት መውጣት እንዴት ተሰሳናቸው ? " ብትለኝ ፥ መልሴ የሚሆነው << የህዝቡ ድህነት ለአንባገነን መሪዎቻቸው በስልጣን ላይ የመቆያ መሳሪያ ሆኖ ስለሚያገለግላቸው ነው ! >> እልሀለሁ፡፡


<< ደሀ (ድህነት) >> የሚለውን ቃል ከኢኮኖሚያዊ ድህነት ባሻገር ፥ በተለያዩ አውዶች ልንጠቀመውና ብያኔ ልንሰጠው እንችላለን፡፡ ሀብት ያላቸው ቢሊየነሮችም ፥ "ደሀ" የሚለውን ስም ሊጋሩ የሚችሉበትም በርካታ አጋጣሚዎች አሉ፡፡ " Money makes the world go round, but greed turns it upside down. " እንዲሉት ስግብግብ ባለፀጋም ደሀ ነው ፤ የአስተሳሰብ ደሀም አለ ፤ ጓደኛና ወዳጅ የሌለው የሰው ደሀ ፥ የእውቀት ደሀ ፣ ...ወዘተ እያልን ልንዘረዝር እንችላለን፡፡ እኔ ያነሳሁት ግን ስለኢኮኖሚያዊ ድህነት ነው፡፡


እንግዲህ በአለም ላይ ለሚደረጉ ጦርነቶችና የእርስበርስ ፍጅቶች በርካታ ምክንያቶችን መጥቀስ ቢቻልም ፥ ድህነትና ኢ-ፍትሃዊነት ( Poverty & Injustice ) ግን የመጀመሪያዎቹና አብዛኛዎቹ የጦርነትና የፍጅት መነሻዎች ናቸው፡፡


ደሀ ሰው ወይም ህዝብን ለመግለፅ ያህል ፥ ደሀ ህዝብ በፕሮግራም ወይም በጊዜ ሰሌዳ የሚመራ ህይወት የለውም፡፡ ሌላው ቀርቶ የሚመገበው ባገኘበት ሰአት በመሆኑ የተለየ የመመገቢያ ሰአት የለውም፡፡ ፕሮግራም "አለኝ!" ቢልም የሚመገበውን ካላገኘ ሊጠቀምበት አይችልም፡፡

" Where money talks, the poor have no voice. " እንደሚባለው ፥ ገንዘብ በሚናገርበት አለም ላይ ደሀ ድምፅ የለውም፡፡ ደሀ የመናገርና ሀሳብን የመግለጽ ነፃነቱን እንኳ ለመንግሥት ወይም ለናጠጡ ሀብታሞች አሳልፎ የሰጠ ነው፡፡ ደሀ በምኞትና በማይቀምሰው ፣ በማይዳስሰውና በማያጣጥመው ፍላጎት ውስጥ እየተበሳቆለ የሚኖር ህዝብ ነው፡፡ አለምን በሚታይ መልኩ ለሁለት የተለያዩ አለሞች የሰነጠቋትም ድህነትና ባለፀጋነት ናቸው፡፡

የደሀ ህዝብ ፖለቲካና ፖለቲከኞችም በአብዛኛው በአቢዮትና በጦርነት ካልሆነ በስተቀር ፥ ከማስመሰል ባሻገር ዴሞክራሲያዊ ሂደትን ለመለማመድም ሆነ በዴሞክራሲያዊ መልኩ የስልጣን ሽግግር ለማድረግ ፍላጎትና ዝግጅቱ የላቸውም፡፡ በተለይ በአብዛኛዎቹ የደሀ አፍሪካ ሀገራት አንባገነን መንግሥታት ድህነትን ከመዋጋት ይልቅ ደሀውን ህዝብና ድህነቱን ራሱ እንደመሳሪያ ተጠቅመው ፥ በተሻለ ሀሳብ የተገነባ ጠንካራ ትግል እንዳያደርግ ያሽመደምዱታል፡፡ በአፍሪካ ውስጥ በአብዛኛው ሀገራት የዴሞክራሲያዊ ትግልና የምርጫ ፖለቲካ ከይስሙላነት በዘለለ ፍሬ ሲያፈሩ ወይም ለውጥ ሲያመጡ የማይስተዋለውም ለዚህ ነው፡፡


አዲስና የተሻለ ሀሳብ በጥቂቱ እንኳ ወደፖለቲካ ጠረጴዛ ሊመጣ የሚችለው በአንባገነኖች ችሮታ እንጂ በህዝብ ድምፅ የመሆን እድሉ ዝቅተኛ ነው፡፡ ምክንያቱም ደሀ ህዝብ በድህነቱ ምክንያት ነፃነትና መብቱን ጭምር በቀላሉ በመንግሥታዊ አንባገነኖች ስለሚነጠቅ ነው፡፡ ነጮቹ " The poor man has sold his freedom of expression to the state. " ማለታቸውም ለዚያ ነው፡፡

ከደሀው ህዝብ አብራክ ወጥተው ፥ ደሀው ህዝባቸውን በድህነቱ ዙፋናቸውን ለማስጠበቅ የሚታትሩት እኚህ ጨካኝ አንባገነኖች ፥ እግሩን ለቆረጡት ህዝብ ዊልቸር ገዝተውለት እንዲያመሠግናቸው ይፈልጋሉ ፤ ለረሀብ ዳርገውት በኩርማን እንጀራ ወይም በጥቂት ፍርፋሪ የዜግነት ነፃነቱንና ሰዋዊ ክብሩን ሁሉ አሳልፎ እንዲሰጣቸው ይሞክራሉ ፥ ያደርጉታልም፡፡ የእለት የእለቱን ፥ የፊት የፊቱን የሚኖረው ደሀው ህዝብ ደግሞ ፥ መሻታቸውን እንዲቀበል ድህነቱ ጠፍንጎ ያስገድደዋል፡፡፡ ፖለቲካዊ ትግልም ስልጣን በያዙ አንባገነኖች በቀላሉ ይጨናገፋል ፣ ይከፋፈላል ፣ ይገዛል፡፡

ከዚያ አለፍ ሲልም ትልቅ አቅምና ሀሳብ ይዞ ፥ ምንም ማድረግ ወዳለመቻል መስመር ይጓዛል፡፡ ትግል በገንዘብ አቅም ሲደገፍ ግን ላለማድረግህ የምትደረድረው ሰበብ ይቀንሳል ፤ ለህዝብህ በአፈሙዝ መታገል ከፈለክ መሳሪያ ገዝተህ ፍላጎትህን ታሳካለህ እንጂ ትጥቅ " የሚሠጠኝ አጣሁ!" ብለህ ሀሳብ ብቻ ይዘህ አትቀመጥም፡፡ ከብሶት ይልቅ መፍትሄ በእጅህ ይሆናል፡፡ አቅደህ በሰአቱ ትፈፅማለህ፡፡ ትግልህ በፕሮግራምና በእቅድ ተሟልቶ ይመራል፡፡ ከወደረኞችህ ጋር መገዳደር ፣ ተፅዕኖ መፍጠርና ለውጥ ማምጣትንም ትችላለህ፡፡ በገንዘብ የምትገዛው እንጂ በድህነት የምታጣው ተፈላጊ ነገር አይኖርም፡፡ ከሌለህስ ? በቃ! የለህማ!

በደሀዋ ሀገራችን እንኳ በአንፃራዊነት ፥ መስኖ የሚያለሙ ፥ የተሻለ የሚያመርቱ ፥ ኢኮኖሚያቸው ከሌላው የሚሻል ዜጎች ባሉበት አካባቢ ፥ የተሻለ ማህበረሰባዊ ንቃት ፥ ብዙ ታጋይና አርበኞች ብሎም የነፃነት ትግል ጅማሮዎች ጎላ ብለው የመታየታቸውን ምስጢር ለማጤን ሞክራችኃልን ?

እናማ በደሀ ሀገራት ጦርነትና ሽኩቻ መለያና መገለጫ ሁነው ይቀጥላሉ፡፡ አምባገነኖችም በቀን አንድ ጊዜ መመገብ ያቃተው ሀህዝባቸውን ፥ ጥይት በዶላር ገዝተው ያዘንቡበታል ፥ አንገት አስደፍተውም ከፋፍለው ይገዙታል ፤ ተስፋም ያስቆርጡታል ፤ በድህነቱ የተሻለ ህልሙን እንዲረግም ያደርጉታል ፤ ድምፁን በቁራሽ ዳቦ ይለውጡታል፡፡

በመጨረሻም ተስፋ የቆረጠው ህዝብ ከሰለጠነ ዴሞክራሲያዊ የሀሳብ ፖለቲካ ይልቅ አቢዮት (አመፅን) ብቸኛ አማራጩ ያደርጋል፡፡ በአመፅና በአቢዎትም በሰአታት ወይም በጥቂት ቀናት ውስጥ አንባገነኖችን ጠራርጎ ያባርራል፡፡

የሚያሳዝነው ግን ከዚያ በኃላም የሚቀጥለው ተመሳሳይ አዙሪት መሆኑና በተመሳሳይ የጭካኔ ፖለቲካ ዲስኮርስ የታነፀ ስርአት የመሆን እድሉ ሠፊ መሆኑ ነው፡፡ አንባገነኖችና፡ በጥላቻ ትርክት የሰከሩ የፖለቲካ ሀይሎች የሚያበላሹብን ዛሬን ብቻ ሳይሆን ነጋችንንም የሚሆነው ለዚህ ነው፡፡

በመሆኑም አንድም ፥ በገዛ ህዝቡ ድህነትና ብስቁልና ዙፋኑን የሚያፀናው ጨካኝ የፖለቲካ ልሂቅ ዴሞክራሲያዊ የአስተሳሰብ ለውጥ አምጥቶ ፥ የህዝቡን ድህነት ታግሎ ማሸኘፍ ወደሚቻልበት መንገድ ካልመጣ ፤ ሁለትም ህዝቡ በብሶት የወለዳቸው ፥ የተሻለ አማራጭ ሀሳብ ያነገቡ መሪዎችን አምጦ በመውለድ የተደራጀ ሁለንተናዊ ትግል አድርጎ ስርነቀል ለውጥ ካላመጣ ፤ አቢዮትና አመፁም ቢሆን ፖለቲካዊ ግብ ተኮርና ዛሬውን የማይደግም እንዲሆን አድርጎ ማስኬድ ካልቻለ ፥ የደሀ የምርጫ ፖለቲካ በአንባገነኖች መዳፍ ስር የሚጥመሰመስ ፍሬአልባ ችግኝ ሆኖ ይቀጥላል፡፡ ህዝቡም በተመሳሳይ አዙሪት ውስጥ መከራና ግፉ እንደበረዶ እየዘነበበት መቀጠሉ ሳይታለም የተፈታ ነው፡፡

ሠላም!
4.2K views12:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-25 12:24:10 መረጃ!

ኦነግ ሸኔ በሰሜን ሸዋ በኤፍራታና ግድም ወረዳ ጥቃት እየሰነዘረ ይገኛል፡፡ እስካሁን ባለኝ መረጃ 7 ሰዎች ቆስለዋል፡፡ አርሷደሩ አካባቢውን ለቆ እየሄደ ነው፡፡ ለመከላከያ የድረሱልን ጥሪ ቢተላለፍም "ልንገባ ነው!" ከማለት ውጭ እስካሁን አልደረሰም!
4.4K views09:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ