Get Mystery Box with random crypto!

ዘሪሁን ገሠሠ

የቴሌግራም ቻናል አርማ zerihunkocha — ዘሪሁን ገሠሠ
የቴሌግራም ቻናል አርማ zerihunkocha — ዘሪሁን ገሠሠ
የሰርጥ አድራሻ: @zerihunkocha
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 13.77K
የሰርጥ መግለጫ

በመረጃ እንቀራረብ! በመረጃ እንተሳሰር!

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 4

2023-05-15 18:25:31
የረሐብ አድማ ላይ ናቸው!

"ሽብር፣ ሁከትና ብጥብጥ እንዲሁም ወቅታዊ እየተባለ የአማራ ምሁራንን ፣ የማኅበረሰብ ተወካዮችን ፣ ጋዜጠኞችን ወጣቶች እና የቀን ሠራተኞችን ማሰር ይቁም" በሚል እነ ረ/ፕ ሲሳይ አውግቸውን ጨምሮ 40 የሚሆኑ እስረኞች ከግንቦት 7/2015 ዓ.ም ጀምሮ የ3 ቀናት የረሃብ አድማ ላይ መሆናቸውን ጠበቃቸው አስታውቋል።

//ጋዜጠኛ በለጠ ካሳ//
3.8K views15:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-13 13:47:00
"አምሐራነት ለሐገር የተከፈለ መስዋዕትነት"

ወንድሜ ዶ/ር ቴዎድሮስ ኃ/ማሪያም ይህን "አምሐራነት ለሐገር የተከፈለ መስዋዕትነት" በሚል ርዕስ የተሰናዳ መፅሐፍ ለህትመት ለማብቃት ሲባዝን በቅርቡ ነበርኩ፡፡ የአጋጣሚ ነገር ሆኖ በአንባገነኖች ግዞት ባለሁበት ሰአት ለህትመት በቅቷል፡፡

ዶ/ክ ብዙ የደከምክበት የልፋትህ ውጤት ወደ ፍሬ በመቀየሩ እጅግ በጣም ደስ ብልኛል!

መፅሐፉ እስካሁን በአዲስ አበባ ፣ ባህር ዳር ፣ ጎንደር ፣ ደብረ ብርሀን ፣ ደብረ ማርቆስ ፣ ደብረ ታቦር ከተሞች ተሰራጭቷል።

የመጀመሪያውን ምርቃትም ባህር ዳር ላይ በቅርቡ ለማከናወን እንደታቀደ መረጃውን አጋርቶኛል!

ይህን የታሪክ ዶሴ የሆነ ፥ በርካታ ቁምነገሮችን የሚያስጨብጥ መፅሐፍ በ400 ብር ብቻ በመግዛት ከቤታችን ልናኖር ይገባል!

ይህን መፅሐፍ በምስራቅ አማራ አካባቢ ባሉ ከተሞች በሙሉ በአጭር ቀን ውስጥ ተደራሽ ለማድረግ እናስተባብራለን!

ፍላጎታችሁን በአስተያየት መስጫው ላይ አስቀምጡልኝ!
5.9K views10:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-29 23:33:45 በድጋሚ ለማስታወስ ያህል ፦

በትክክልም አላማና ግብ ያለው ሰላማዊ ትግል የምታደርግ ከሆነ ከእነዚህ 5 ነገሮች ተጠንቀቅ ፦

☞ የፖለቲካ ቡድንን (ባለስልጣንን) እንጂ በፍፁም ህዝብን እንደህዝብ አትፈርጅ ፥ አትስደብ ፥ አታጥላላ!

☞ ትችትና አስተያየትህ የግለሰቡን (የፖለቲካ ቡድኑን) እኩይ ተግባር መሠረት ያደረገ እንጂ ማንነቱን መገለጫ ከማድረግ ተቆጠብ

☞ በፍፁም ሀይማኖትና ፖለቲካን ከመቀላቀል ተቆጠብ!

☞ ትግልህ ፍትህና እኩልነት እንዲሰፍን ማድረግ እንጂ በአንተ ላይ የደረሰውን በሌሎች ላይ ለማድረስ አለመሆኑን አስረግጠህ እመን! በቀለኝነትንም አታንፀባርቅ!

☞ ተግባቦትህ ሁሉ ወዳጅ ማብዛት ላይ እንጂ ጠላትን በሚያበዛ መልኩ አይሁን!

በዚህ መልኩ ስትሄድ ሩቅ ትጓዛለህ ፤ የሚረዱህን ታበዛለህ ፥ አላማና ግብህ በሁሉም ይታወቃል ፤ እወክለዋለሁ ለምትለውም ህዝብ የተቀላጠፈ ለውጥ እንዲመጣ ማድረግ ትችላለህ!

መልካም አዳር!
10.4K views20:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-29 23:06:56 በደቡብ ወሎ ሀይቅ ከተማ  አስተዳደር በርካታ ወጣቶች ለእስር መዳረጋቸው ተገለፀ!

በዛሬው እለት ከያሉበት እየታደኑ ለጅምላ እስር ከተዳረጉት መካከል ፦

- አቶ ብርሃን አበራ ይመር
- መ/ር መሀመድ ይማም
- አቶ ዘርአይ እንድሪስና ሌሎች በርካቶች ይገኙበታል፡፡

ሌሎች ያልተያዙና በስም ዝርዝር ተይዘው እየተፈለጉ ያሉ ወጣቶች መኖራቸውንም ለማወቅ ተችሏል፡፡ ወጣቶቹ እስካሁን የታሰሩበት ምክንያት በውል ተለይቶ ባይታወቅም ፥ በተያዙበት ወቅት "ህዝብን ለአመፅ ቀስቅሳችኃል!" የሚል አመክንዮ እንደቀረበላቸው ከስፍራው ያገኘሁት መረጃ ያመለክታል፡፡

በተለያዩ አካባቢዎች የጅምላ እስርና አፈና ተባብሶ መቀጠሉንም መረጃዎች ያመለክታሉ!
11.8K viewsedited  20:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-29 17:26:01 በነገራችን ላይ ባለፉት ቅርብ ጊዜያት ውስጥ በምስራቅ ወለጋ ብቻ ከመቶ በላይ የብልጽግና ፓርቲ አመራሮችና የስራ ሀላፊዎች ተገድለዋል!

ጠቅላይ ሚኒስቴሩ ወደነቀምት ከመጓዛቸው አንድ ሳምንት ቀደም ብሎ እንኳ የነቀምት ብልፅግና ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ደሳለኝ ቦኮንጃ "ባልታወቁ ታጣቂዎች ተገደሉ!" ተብሎ መዘገቡ የሚታወስ ነው! ነቀምት ከተማ በኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ለሰአታት ሙሉ በሙሉ በቁጥጥር ስር ውላ ከ20 በላይ ባንኮች መዘረፋቸውና ከፍተኛ የሰብዓዊ ጉዳት መድረሱ አይዘነጋም!

በኦሮሚያ ክልል ከኢትዮጵያውያን አልፎ የውጭ ሀገር ዜጎችና በተለያዩ ኢንቨስትመንቶች የተሰማሩ ባለሀብቶች ጧት ማታ ይገደላሉ ፥ ይታገታሉ፡፡ አግቶ ገንዘብ መጠየቅ እንደስራ እድል ፈጠራ የተቆጠረ እስከሚመስል ድረስ ፥ እጅግ በርካቶች በወጡበት ደብዛቸው ጠፍቷል ፤ በሹፍርና ስራ የተሰማሩ በርካታ ወንድሞቻችን ኑሮን ለማሸነፍ ሲንከራተቱ ታግተው የተጠየቀው ገንዘብ ተከፍሎ እንኳ በህይወት ሳይለቀቁ ተገድለዋል ፡፡ የፋይናንስ ተቋማት ፥ ኢንቨስትመንቶች ፥ በየጊዜው ይዘረፋሉ ፥ ይወድማሉ፡፡ ይህ እንግዲህ በማንነታቸው ለአመታት ያለእረፍት የዘር ፍጅት ከሚፈፀምባቸው ፥ ሀብት ንብረታቸው ወድሞና ተዘርፎ ከሚሳደዱት ሚሊየኖች ውጭ ነው፡፡

አንዳንዴማ ክልሉን የሚመሩት ፥ እነሽመልስ አብዲሳ ምናልባት ዋና መቀመጫቸው አዲስአበባ ስለሆነ ፤ " ኦሮሚያ በንፁሐን ደም የምትታጠብ ምድራዊ ሲኦል" እስከምትባል ድረስ የእልቂት ማእከል መሆኗን ፥ አለምአቀፍ ተቋማትና ኤምባሲዎች ሳይቀር "ለጉዞ የማይመከር ቀጠና" ሲሉ የሚገልፇትን ክልል "ሽምጥጥ" አድርገው ምናባዊ ተረት ሲተርቱላት ሳይ ስለማያውቋት ክልል አስተያየት የሚሠጡ ሁሉ ይመስለኛል!

ሳጠቃልል ፦ ሁሉም የኦሮሞ የፖለቲካ ኃይሎች ፥ ሌሎችን "ፅንፈኛ" ብለው የመጥራት የሞራል ልእልናው የላቸውም !
2.2K views14:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-28 22:27:34 የአህያው ታሪክ….!

….ከእለታት አንድ ቀን ንጉስ አንበሳ ቀበሮን ይጠራውና << እጅግ በጣም እርቦኛል ፤ በአስቸኳይ የምበላው ካላመጣህልኝ ፥ አንተን ነው ቀረጣጥፌ የምበላህ! >> ይለዋል። ቀበሮም ተደናግጦ ለአንበሳው ምግብ ፍለጋ ሲሄድ ከአህያ ጋር ይገናኛል፡፡

ይሄኔ አህያን የጦስ ዶሮ ለማድረግ የማታለያ ሀሳብ የመጣለት ቀበሮ ፥ << አያ አህያ! ስፈልግህ አገኘሁህ፡፡ ንጉሳችን አንበሳ አንተን ንጉስ ሊያደርግህ ይፈልጋልና በአስቸኳይ እንሂድ ! >> ብሎ በማሳመን አስከትሎት ይሄዳል፡፡

የተራበው አንበሳ አህያው ከአጠገቡ ሲደርስ ፥ ጊዜ ሳያጠፋ ተንደርድሮ ጆሮውን ግሽልጥ አድርጎ ይበላዋል፡፡ ይሄኔ አህያ ደሙን እያዘራ ሲሮጥ ከቀበሮ ጋር ይገናኛሉ፡፡

<< አታለልከኝ አይደል ! ልታስበላኝ ነበር የጠራኸኝ ! >> ይለዋል፡፡

<< ኧረ በፍፁም አላታለልኩህም አያ አህያ ፤ ጆሮህን የበላህኮ ስትነግስ ዘውዱን ለመድፋት አንዳያስቸግርህ ብሎ ነው ! በል አሁን እንመለስ በቶሎ ..>> ይልና አሳምኖ ይመልሰዋል፡፡

ድጋሜ አህያው ከአንበሳው ፊት ሲደርስ ተንደርድሮ ጭራውን ቆርጦ ይበላዋል፡፡ አሁንም አህያው ደሙን እያዘራ ሲሄድ ከደላላው ቀበሮ ጋር ይገናኛሉ፡፡

<< አያ ቀበሮ ምን በድዬህ ነው ግን ፥ ያታለልከኝ ? አሁንም ጭራዬን በላኝኮ!>> ! >> ይለዋል፡፡

<< ኧረ በፍፁም አላታለልኩህም፡፡ ምነው አያ አህያ ? ለአንተው በደከምኩ ፤ አያ አንበሳ ጭራህን የቆረጠውኮ ፥ ከነገስክ በኃላ ዙፋኑ ላይ ስትቀመጥ እንዳያስቸግርህ አስቦ ነው፡፡ በል አሁን እንመለስ ..! >> ይልና በድጋሜ አሳምኖ ይወስደዋል፡፡

ይሄኔ አንበሳው አህያውን ደቋቁሶ ገደለው፡፡ ወደቀበሮውም ዘወር ብሎ << አህያውን አሳምነህ በማምጣትህ ጥሩ ሰርተሃል፡፡ በል አሁን ደግሞ አህያውን ገነጣጥለህ ቆዳውን ፥ ጭንቅላቱን ፣ ልቡን ፤ ሳንባውና ጉበቱን ብቻ ለይተህ አምጣልኝ! >> ሲል አዘዘው፡፡

ቀበሮ የታዘዘውን ፈፅሞ ለአንበሳው ይዞ ቀረበ፡፡ ነገርግን ይዞ ከመጣው ስጋ ውስጥ ጭንቅላቱን ስለበላው ሊገኝ አልቻለም፡፡ ይሄኔ አንበሳው በንዴት ጦፈ፡፡ << ጭንቅላቱን የት አባክ አስገብተኸው ነው ? >> ሲልም አፈጠጠበት፡፡

ቀበሮም የዋዛ አልነበረም << ጌታዬ! ጭንቅላት እኮ ቀድሞውኑ አልነበረውም፡፡ ጭንቅላት ቢኖረውማ ፥ ጆሮና ጅራቱን ከቆረጥከው በኃላ ዳግም ተመልሶ ወደአንተ ጋር ይመጣ ነበርን ? >> ብሎ በብልሃት በማሳመን ራሱን ከሞት አዳነ ይባላል፡፡

የሠው ልጅም ህይወት ለአንድና ለሁለት ጊዜ ሲሳሳት እንዲታረም ከሰጠችው እድል መማር ካልቻለ ፥ ከውድቀቱ በኃላ የመማር እድሉ ጠባብና ከባድ ዋጋ የሚያስከፍል ሊሆን ይችላል!
3.9K views19:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-28 19:34:41 መፍትሔው ግራ አለመጋባትና በአማራነትህ ፀንቶ መቆም ነው!

ልጅ እያለሁ ፤ በነጭ ወረቀት ላይ በስእል አሽሞንሙነው የገጠሟቸውን አጭሬ ግጥሞች ፥ ገበያ ላይ ወይም ሰው በሚበረክትበት ቦታ ይቀመጡና ፥ እያነበቡ በስሙኒ የሚሸጡ በርካታ ስራ ፈጣሪዎችን አስታውሳለሁ፡፡ ታዲያ ሻጩ በእጁ የያዛቸውን አጭሬ ግጥሞች እያነበበ ሲያስተዋውቅ ፥ ውስጥህ የገባውንና ስሜትህን የኮረኮረውን ግጥም "እሷን አምጣት!" ትልና በስሙኒ ሸምተህ ግድግዳህ ላይ ትለጥፋለህ፡፡

ታዲያ! በዚያ ዘመን ተገዝተው ከኛ ግድግዳ ላይ ከተለጠፉት አጭሬ ግጥሞች መካከል ፦

" ቢወፍሩ ዱባ ፤ ቢቀጥኑ ትንኝ"
"ቢያወሩ አፈኛ ፤ ዝም ቢሉም ሞኝ"
አምላክ ከዚህ ሁሉ አሟልተህ ስጠኝ!"
.
.
የምትልን ግራ የተጋባ ሰው እንደገጠማት የምታሳብቅ ግጥም ፈፅሞ እስካሁን አልረሳትም፡፡

ጓዶች! የአማራ ህዝብም ላለፉት ሰላሳ አመታት በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ፥ የገጠመው እንደዚህ ግራ የተጋባ ነገር ነውኮ!

የጥላቻ ትርክት ጡጦ ጠብተው ያደጉ ፅንፈኛ ብሄርተኞች ፥ በጠላትነት ፈርጀውትና የሀገረ-መንግስቱን ፖለቲካ ተቆጣጥረው ፍዳውን ሲያበሉት ፥ እንደህዝብ ማንነቱን ዋጋ ሰጥቶ ከመደራጀት ይልቅ "ዘር ለገበሬ ነው!" እያለ "ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ" በማለቱ " አሀዳዊ ፣ ደፍጣጭ ፥ ነፍጠኛ ፣ ትምክህተኛ ፣ ...ወዘተርፈ " የሚሉ ስሞች እየተሰጠው መከራውን ሲያይ ኖረ፡፡

በታሪክ አጋጣሚ ለ27 አመታት የሀገረ-መንግስቱን ስልጣን ይዘው የኖሩት የትግራይ ፅንፈኛ የብሄር ሀይሎች ፥ በህዝብ ትግል ከማዕከላዊ መንግሥት ስልጣን ተገፍተው ቢሰነብቱም ፥ "ፍጥጥ" ያሉት የከፉ ፅንፈኞች ተተክተው ፥ የፍረጃ ስያሜዎቹንም ለማጥቂያነት እየተጠቀሙ አባብሰው ቀጠሉ እንጂ የተለየ ነገር አልተፈጠረም!

ታዲያ! ከዚህ ሁሉ መከራ በኃላ የአማራ ህዝብ የተጋረጠበትንና ፥ ከጊዜ ወደጊዜ አሳሳቢ እየሆነ የመጣውን የህልውና አደጋ ለመቀልበስ ብሎም ጥቅምና ፍላጎቱን ለማስከበር " እንደህዝብ ተደራጅቼ የሀገረ-መንግስቱን የፖለቲካ አሰላለፍ ልመሳሰል!" በማለት " አማራ ነኝ!" ብሎ ሲነሳ ደግሞ ፤ የራሳቸውን ዘመን ተሻጋሪ የግብር መጠሪያ አውልቀው " የአማራ ፅንፈኞች" የሚል ካባ ደረቡለትና ፥ ይኸው ለጅምላ እልቂትና ሰቆቃ በይፋ መጠቀም ጀምረው አረፉት!

ገጣሚው "ቢወፍሩ ዱባ ፤ ቢቀጥኑ ትንኝ " ያለውም እንዲህ ግራ ቢገባው ነውኮ!

ለዚህ መፍትሔው " ትንኝም ፥ ዱባም ፥ ..!" ለሚሉት መስሚያህን "ጥጥ" አድርገህ ፥ ፍፁም ጠንካራ በሆነ ህዝባዊ አደረጃጀትና ትግል ፥ ለዘመናት የገነቡትን የትርክትና የጥላቻ ግንብ በመናድ ራስህን የአላፊ አግዳሚው መፈንጫ ከመሆን መዳን ብቻ ነው!

ይኸው ነው!
6.2K views16:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-27 23:14:15 የጠቅላዩ አጭር መግለጫ ፥ በወንጀሉ ላይ ምርመራ እንዳይደረግ የተሰጠ ትእዛዝ ይመስለኛል!

ጠሚው የአቦሰጥ ፍርድና ብይን ከሰጠ በኃላ ፥ " ፖሊስና የፍትህ ተቋማቱ የተፈፀመውን ወንጀል መርምረው ለህዝብ ይፋ ያድርጉ!" ማለት የዋህነት ካልሆነ ምንም ሊሆን አይችልም፡፡

ጠ/ሚኒስቴር አብይ አህመድን የመሠለ መስሚያው ጥጥ የሆነ ፍጡርኮ በአለም ላይ መኖሩን ሁሉ መጠራጠር ጀምሬአለሁ፡፡ እንደውም ቲክቶክ ላይ " እዋዋን ማንንም አልሰማም!" የሚለው ልጅ የሱን ገፀ-ባህሪ የተጫወው ይመስለኛል፡፡

ሀገሪቱ ላይ ስርአት አልበኝነትና የተቋማት ልፍስፍስነት ተባብሶ የቀጠለው በዋናነት በጠቅላይ ሚኒስቴሩ ማንአለብኝነትና እብሪት ነው፡፡

የሀገሪቱን ሁሉንም ተቋማት ተጠሪነታቸውን ለራሱ አድርጎ ፥ የሚመሩበትን ስርአትና የተሰጣቸውን ተልእኮ ሁሉ እውቀቱ ፣ ሙያው ፣ መብቱ ፣ ስርአታዊ ሀላፊነቱ ሳይኖረው እንዳሻው የሚረጋግጣቸው ራሱ ነው፡፡

አንድ ወንጀል ሲፈፀም መመርመር ፣ ማጣራትና ለህዝብ ይፋ ማድረግ የማን ሀላፊነት ነው ?

የሀገሪቱ ፖሊስና የፍትሕ አካላት ጠቅላይ ሚኒስቴሩ የተፈፀመው ወንጀል ያስከተለው ጉዳትና ሟቾች እንኳ በቅጡ ባልተለዩበት ሁኔታ ፥ በብርሃን ፍጥነት ሟችንም ፣ ገዳይንም ፥ የግድያ ምክንያትን ሳይቀር በይፋ በገለፁበት ሁኔታ ፥ ከነአካቴው በጉዳዩ ላይ ምርመራስ ያደርጋሉ ወይ ? ከጠቅላይ ሚኒስቴሩ የተለየስ የምርመራ ግኝት አገኘን እንዲሉ የሚጠብቅ የዋህ አለ ወይ ?

"ሙስና አትበሉ ፥ ሌብነት ነው!" እያለ አፉን ቀባብቶ ሲሰብክህ ይቆይና በፓርላማ ፊት ፥ " ...እኔ በግሌ ከወዳጆቼ ለምኜ የማመጣው ገንዘብ ነው!" ሲል ትንሽ እንኳ ፥ ተጠሪነቱ ለራሱ የሆነው "ፀረ-ሙስና" የሚባልን ተቋም ፥ እርባናቢስ እያደረገው እንደሆነ የማይረዳ "መስሚያው ጥጥ" የሆነ ጉደኛ ሰው ነው!

በሁሉም ዘርፍ ብትሄዱ የሀገሪቱን ተቋማት ግንባር ቀደም ሆኖ ህግጋትና ስርአታቸውን የሚጥሰው ፥ በህግ የተሰጠ ሀላፊነታቸውን የሚነጥቀው ይኸው " ስዩመ-እግዚያብሄር ነኝ!" የሚል ሠውዬ ነው!

አቶ ግርማን ጨምሮ በአሳዛኙ ጥቃት ህይወታቸውን ያጡ ወገኖቻችንን ነፍስ ይማር! ለወዳጅ ዘመዶቻቸው መፅናናትን እመኛለሁ!
7.6K views20:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-27 21:39:25
5.1K viewsNo War No Peace, 18:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-27 21:39:21 የሃዘን መግለጫ!

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) በብልጽግና ፓርቲ የአማራ ክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ እና የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ አባል በነበሩት አቶ ግርማ የሽጥላ ላይ የተፈጸመውን የግድያ ጥቃት በጽኑ ያወግዛል ፣ ጥልቅ ሃዘኑን ይገልጻል ፣ ለቤተሰቦቻቸው ፣ ለስራ ባልደረቦቻቸው እና ለመላው የሃገራችን ሕዝብ መጽናናትን ይመኛል።

የክልሉ መንግስት አመራሮች ላይ ተደጋግሞ እየተፈጸመ ያለው የግድያ ጥቃት ክልሉን የቀውስ ማዕከል የሚያደርግ ፣ የሃገራችንን ሰላም እና መረጋጋት አደጋ ላይ የሚጥል የዜሮ ድምር ፖለቲካዊ ሽብር ውጤት በመሆኑ ድርጅታችን አብን በጽኑ የሚያወግዘው ወንጀል ነው።

ፓርቲያችን አብን ከዚህ ቀደም በአማራ ክልል አመራሮች ላይ የተፈጸመው የግድያ ወንጀል ተሸፋፍኖ መቅረቱ እና ተጠያቂነት አለመስፈኑ ፣ በክልሉ አመራሮች ላይ የሚፈጸመው ጥቃት ተባብሶ እንዲቀጥል ምክንያት መሆኑን ያምናል። አሁንም ድርጊቱ አግባብ ባላቸው ተቋማት ሳይጣራ እና አጥቂዎቹ እና አጥፊዎቹ ተለይተው ሳይታወቁ ፣ ከጥቃቱ ፖለቲካዊ ትርፍ ለማግኝት ሲባል በአደባባይ የሚደረጉ ፍረጃዎችን እና መግለጫዎችን ድርጅታችን አብን በጽኑ የሚያወግዝ ሲሆን ፣ ግድያው አግባብ ባላቸው ተቋማት በልዩ ትኩረት እንዲጣራ ፣ በድርጊቱ የተሳተፉ ተዋንያን በሙሉ እንዲለዩ እና አጥቂዎቹ ለፍርድ እንዲቀርቡ ድርጅታችን አብን ጥሪውን ያስተላልፋል።

በመጨረሻም መላው የአማራ ሕዝብ እና ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን በሙሉ በተፈጠረው ጥቃት ሳትረበሹ ከመቸውም ጊዜ በበለጠ አንድነታችሁን እና ሰላማችሁን እንድትጠብቁ ድርጅታችን አብን ጥሪውን እያስተላለፈ ፣ በድጋሜ ለሟች አቶ ግርማ የሽጥላ ነብሳቸውን በአጸደ ገነት እንዲያኖርልን ፣ ለቤተሰቦቻቸው እና ለመላው የሃገራችን ሕዝብ መጽናናትን እንመኛለን።

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን)
አዲስ አበባ፣ ሸዋ፣ ኢትዮጵያ
ሚያዚያ 19 ቀን 2015 ዓ.ም.
5.0K viewsNo War No Peace, 18:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ