Get Mystery Box with random crypto!

በደቡብ ወሎ ሀይቅ ከተማ  አስተዳደር በርካታ ወጣቶች ለእስር መዳረጋቸው ተገለፀ! በዛሬው እለት | ዘሪሁን ገሠሠ

በደቡብ ወሎ ሀይቅ ከተማ  አስተዳደር በርካታ ወጣቶች ለእስር መዳረጋቸው ተገለፀ!

በዛሬው እለት ከያሉበት እየታደኑ ለጅምላ እስር ከተዳረጉት መካከል ፦

- አቶ ብርሃን አበራ ይመር
- መ/ር መሀመድ ይማም
- አቶ ዘርአይ እንድሪስና ሌሎች በርካቶች ይገኙበታል፡፡

ሌሎች ያልተያዙና በስም ዝርዝር ተይዘው እየተፈለጉ ያሉ ወጣቶች መኖራቸውንም ለማወቅ ተችሏል፡፡ ወጣቶቹ እስካሁን የታሰሩበት ምክንያት በውል ተለይቶ ባይታወቅም ፥ በተያዙበት ወቅት "ህዝብን ለአመፅ ቀስቅሳችኃል!" የሚል አመክንዮ እንደቀረበላቸው ከስፍራው ያገኘሁት መረጃ ያመለክታል፡፡

በተለያዩ አካባቢዎች የጅምላ እስርና አፈና ተባብሶ መቀጠሉንም መረጃዎች ያመለክታሉ!