Get Mystery Box with random crypto!

በድጋሚ ለማስታወስ ያህል ፦ በትክክልም አላማና ግብ ያለው ሰላማዊ ትግል የምታደርግ ከሆነ ከእነ | ዘሪሁን ገሠሠ

በድጋሚ ለማስታወስ ያህል ፦

በትክክልም አላማና ግብ ያለው ሰላማዊ ትግል የምታደርግ ከሆነ ከእነዚህ 5 ነገሮች ተጠንቀቅ ፦

☞ የፖለቲካ ቡድንን (ባለስልጣንን) እንጂ በፍፁም ህዝብን እንደህዝብ አትፈርጅ ፥ አትስደብ ፥ አታጥላላ!

☞ ትችትና አስተያየትህ የግለሰቡን (የፖለቲካ ቡድኑን) እኩይ ተግባር መሠረት ያደረገ እንጂ ማንነቱን መገለጫ ከማድረግ ተቆጠብ

☞ በፍፁም ሀይማኖትና ፖለቲካን ከመቀላቀል ተቆጠብ!

☞ ትግልህ ፍትህና እኩልነት እንዲሰፍን ማድረግ እንጂ በአንተ ላይ የደረሰውን በሌሎች ላይ ለማድረስ አለመሆኑን አስረግጠህ እመን! በቀለኝነትንም አታንፀባርቅ!

☞ ተግባቦትህ ሁሉ ወዳጅ ማብዛት ላይ እንጂ ጠላትን በሚያበዛ መልኩ አይሁን!

በዚህ መልኩ ስትሄድ ሩቅ ትጓዛለህ ፤ የሚረዱህን ታበዛለህ ፥ አላማና ግብህ በሁሉም ይታወቃል ፤ እወክለዋለሁ ለምትለውም ህዝብ የተቀላጠፈ ለውጥ እንዲመጣ ማድረግ ትችላለህ!

መልካም አዳር!