Get Mystery Box with random crypto!

'አምሐራነት ለሐገር የተከፈለ መስዋዕትነት' ወንድሜ ዶ/ር ቴዎድሮስ ኃ/ማሪያም ይህን 'አምሐራነት | ዘሪሁን ገሠሠ

"አምሐራነት ለሐገር የተከፈለ መስዋዕትነት"

ወንድሜ ዶ/ር ቴዎድሮስ ኃ/ማሪያም ይህን "አምሐራነት ለሐገር የተከፈለ መስዋዕትነት" በሚል ርዕስ የተሰናዳ መፅሐፍ ለህትመት ለማብቃት ሲባዝን በቅርቡ ነበርኩ፡፡ የአጋጣሚ ነገር ሆኖ በአንባገነኖች ግዞት ባለሁበት ሰአት ለህትመት በቅቷል፡፡

ዶ/ክ ብዙ የደከምክበት የልፋትህ ውጤት ወደ ፍሬ በመቀየሩ እጅግ በጣም ደስ ብልኛል!

መፅሐፉ እስካሁን በአዲስ አበባ ፣ ባህር ዳር ፣ ጎንደር ፣ ደብረ ብርሀን ፣ ደብረ ማርቆስ ፣ ደብረ ታቦር ከተሞች ተሰራጭቷል።

የመጀመሪያውን ምርቃትም ባህር ዳር ላይ በቅርቡ ለማከናወን እንደታቀደ መረጃውን አጋርቶኛል!

ይህን የታሪክ ዶሴ የሆነ ፥ በርካታ ቁምነገሮችን የሚያስጨብጥ መፅሐፍ በ400 ብር ብቻ በመግዛት ከቤታችን ልናኖር ይገባል!

ይህን መፅሐፍ በምስራቅ አማራ አካባቢ ባሉ ከተሞች በሙሉ በአጭር ቀን ውስጥ ተደራሽ ለማድረግ እናስተባብራለን!

ፍላጎታችሁን በአስተያየት መስጫው ላይ አስቀምጡልኝ!