Get Mystery Box with random crypto!

በነገራችን ላይ ባለፉት ቅርብ ጊዜያት ውስጥ በምስራቅ ወለጋ ብቻ ከመቶ በላይ የብልጽግና ፓርቲ አመ | ዘሪሁን ገሠሠ

በነገራችን ላይ ባለፉት ቅርብ ጊዜያት ውስጥ በምስራቅ ወለጋ ብቻ ከመቶ በላይ የብልጽግና ፓርቲ አመራሮችና የስራ ሀላፊዎች ተገድለዋል!

ጠቅላይ ሚኒስቴሩ ወደነቀምት ከመጓዛቸው አንድ ሳምንት ቀደም ብሎ እንኳ የነቀምት ብልፅግና ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ደሳለኝ ቦኮንጃ "ባልታወቁ ታጣቂዎች ተገደሉ!" ተብሎ መዘገቡ የሚታወስ ነው! ነቀምት ከተማ በኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ለሰአታት ሙሉ በሙሉ በቁጥጥር ስር ውላ ከ20 በላይ ባንኮች መዘረፋቸውና ከፍተኛ የሰብዓዊ ጉዳት መድረሱ አይዘነጋም!

በኦሮሚያ ክልል ከኢትዮጵያውያን አልፎ የውጭ ሀገር ዜጎችና በተለያዩ ኢንቨስትመንቶች የተሰማሩ ባለሀብቶች ጧት ማታ ይገደላሉ ፥ ይታገታሉ፡፡ አግቶ ገንዘብ መጠየቅ እንደስራ እድል ፈጠራ የተቆጠረ እስከሚመስል ድረስ ፥ እጅግ በርካቶች በወጡበት ደብዛቸው ጠፍቷል ፤ በሹፍርና ስራ የተሰማሩ በርካታ ወንድሞቻችን ኑሮን ለማሸነፍ ሲንከራተቱ ታግተው የተጠየቀው ገንዘብ ተከፍሎ እንኳ በህይወት ሳይለቀቁ ተገድለዋል ፡፡ የፋይናንስ ተቋማት ፥ ኢንቨስትመንቶች ፥ በየጊዜው ይዘረፋሉ ፥ ይወድማሉ፡፡ ይህ እንግዲህ በማንነታቸው ለአመታት ያለእረፍት የዘር ፍጅት ከሚፈፀምባቸው ፥ ሀብት ንብረታቸው ወድሞና ተዘርፎ ከሚሳደዱት ሚሊየኖች ውጭ ነው፡፡

አንዳንዴማ ክልሉን የሚመሩት ፥ እነሽመልስ አብዲሳ ምናልባት ዋና መቀመጫቸው አዲስአበባ ስለሆነ ፤ " ኦሮሚያ በንፁሐን ደም የምትታጠብ ምድራዊ ሲኦል" እስከምትባል ድረስ የእልቂት ማእከል መሆኗን ፥ አለምአቀፍ ተቋማትና ኤምባሲዎች ሳይቀር "ለጉዞ የማይመከር ቀጠና" ሲሉ የሚገልፇትን ክልል "ሽምጥጥ" አድርገው ምናባዊ ተረት ሲተርቱላት ሳይ ስለማያውቋት ክልል አስተያየት የሚሠጡ ሁሉ ይመስለኛል!

ሳጠቃልል ፦ ሁሉም የኦሮሞ የፖለቲካ ኃይሎች ፥ ሌሎችን "ፅንፈኛ" ብለው የመጥራት የሞራል ልእልናው የላቸውም !