Get Mystery Box with random crypto!

ዘሪሁን ገሠሠ

የቴሌግራም ቻናል አርማ zerihunkocha — ዘሪሁን ገሠሠ
የቴሌግራም ቻናል አርማ zerihunkocha — ዘሪሁን ገሠሠ
የሰርጥ አድራሻ: @zerihunkocha
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 13.77K
የሰርጥ መግለጫ

በመረጃ እንቀራረብ! በመረጃ እንተሳሰር!

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2023-06-07 20:45:27
ደራሲ እና የሰብዓዊ መብት ተሟጋች አሳዬ ደርቤ ፍርድ ቤት ቀርቧል!

ደራሲ፣ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች እንዲሁም የጠለስ ዩቱብ ሚዲያ መስራችና ባለቤት አሳዬ ደርቤ ግንቦት 30/2015 ዓ.ም በፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ ወንጀል ጉዳዮች ጊዜ ቀጠሮ ችሎት ቀርቦ ነበር።

የፌደራል ፖሊስ በሽብር እና ህግ-መንግስታዊ ሰርዓቱን በኃይል በመናድ ወንጀል ጠርጥሬ ምርመራ እያጣራሁኝ ነው በማለት የ14 ቀን የምርመራ ጊዜ ይፈቀድልኝ በማለት ጠይቋል።

በጠበቆች በኩልም የፖሊስ የጊዜ ቀጠሮ ጥያቄ ውድቅ ተደርጎ የደንበኛችን የዋስትና መብት ሊከበር ይገባል ሲሉ ሰፊ የህግ እና የፍሬ ነገር ክርክር ስለማቅረባቸው ከጠበቃ አዲሱ አልጋው መረጃ ማግኘቱን በመግለጽ ያጋራው ጋዜጠኛ አራጋው ሲሳይ ነው።

የግራ ቀኙን ክርክር ያዳመጠው ችሎቱም ፖሊስ ያቀረበው የጊዜ ቀጠሮ ጥያቄ ይፈቀድ ወይስ የደራሲ አሳዬ ደርቤ የዋስትና መብት ሊጠበቅ ይገባል በሚለው ጭብጥ ላይ ውሳኔ ለመሰጠት በአዳሪ ለሰኔ 1/2015 ዓ.ም ከጠዋቱ 3:00 ላይ ተለዋጭ ቀጠሮ ስለመያዙም ተገልጧል።

ደራሲ አሳዬ ደርቤ ግንቦት 28 ቀን 2015 ዓ.ም ከምሽቱ ሶስት ሰዓት ላይ አገዛዙ በላካቸው የፌደራል ፖሊስ አባላት ታፍኖ መወሰዱ አይዘነጋም።

ዘገባው የአሻራ ሚዲያ ነው።
4.8K views17:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-07 19:01:25
4.5K views16:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-07 19:01:18 ''አስመሳይ ህዝብ '' ራሱ የደገሰውን የመከራ ድግስ እየተቋደሰ ለመኖር ይገደዳል!

ብዙ ጊዜ ከአንዳንድ ጓዶች ጋር ተወያይተን በሀሳብ የምለይበት ''ህዝብ ድብን አድርጎ ይሳሳታል!'' በሚለው አቋሜ ፅኑ ነው። አቶ ልደቱ በዚህ ረገድ ከነአመክንዮዎቹ ባቀረበው ሀሳብ የምስማማውም ለዚያ ነው።

በሌላ መልኩ ህዝብን የሚፈጥረው ፈጣሪ ቢሆንም የህዝብን ማህበረሰባዊ ስነ-ልቦናና እሳቤ የሚቀርፀው ግን የፖለቲካ ኢሊቱ ነው ብዬም አምናለሁ። ከዚህ አኳያ በአሉታዊም ሆነ በአወንታዊ መልኩ የህዝብን ስነልቦናና አስተሳሰብ በመቅረፅ ረገድ የፖለቲካ ኤሊቱ ከፍተኛውን ሚና ይጫወታል ማለት ነው።

በመሆኑም ብልሹ የፖለቲካ ሀይል የተበላሸ የፖለቲካ ማህበረሰብና ባህል የመገንባት እድሉ ከፍተኛ ነው። በተለይ ይህ አይነቱ የፖለቲካ ኤሊት ስብስብ ለረዥም ጊዜ የህዝብን ስልጣን ይዞ የመቆየት እድል ካገኘ ፣ የራሱን መገለጫና ባህሪያት የፖለቲካ ማህበረሰቡ (የህዝቡ) ልማድ ወይም ባህል አድርጎ የማስረፅ ኃይል ያገኛል። በጥቅሉ የአፍሪካ ወረድ ስንል የኢትዮጵያችን ፖለቲካ ፣ በተመሳሳይ የብልሽትና ኃላቀር ፖለቲካዊ አዙሪት ውስጥ ተዘፍቆ ለዘመናት የሚሽከረከረውም ለዚያ ነው።

የፖለቲካ ቡድኖቹ ተራማጅና ለትውልድ የሚተርፍ በጎ የፖለቲካ አስተሳሰብ ይዘው ከመጓዝ ይልቅ ፣ የሚነሱት ከእነሱ በፊት የነበረውን ሀይል ሞዴል አድርገው ነው። ለአብነት ህወሓትን ሞዴል አድርጎ የተነሳው ''ብልፅግና'' የፈለገ ስሙንና ድስኩሩን ቢቀያይረውም ፤ በግብር ግን ሞዴል አድርጎ ከተነሳው (ከቀራፂው) ህወሓት በእጅጉ ልቆ የተገኘ ነው። በሀገራችን ፖለቲካ ትናንት ከነበረው ተሽሎ መገኘት ማለት ይህ ነው። ክፉ ከነበረው በጣም ክፉ ሆኖ መገኘት....

ወደዋናው ነጥቤ ስመለስ ፣ ከላይ እንዳልኩት ከሰላሳ አመት በላይ በህዝብ ስልጣን ላይ የመቆየት እድሉን ያገኘው ''ብአዴን'' አብዛሀኛዎቹ እኩይ መገለጫ ባህሪያቶቹን በህዝቡ (የፖለቲካ ማህበረሰቡ) ውስጥ ተክሏቸዋል። ነባር ህዝባዊ እሴቶችና ስነልቦናዊ ውቅሮችን በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ፣ በውድም ሆነ በግድ ሸርሽሯቸዋል። በአጭሩ ከሞላ ጎደል ፣ ''ህዝብ'' በሚባል ደረጃ ''ብአዴናዊ'' አስተሳሰብ ያለው የፖለቲካ ማህበረሰብ ተፈጥሯል።

<< ብአዴናዊነት ምንድን ነው? >> የሚለውን ጥያቄ አብዛኛው የሚያውቀው በመሆኑ በዚህ አጭር ፅሁፍ አላብራራውም። ነገርግን የተሻለ ነገን ለመፍጠር ፣ የትውልዱን መፃኢ እጣፋንታ ተራማጅና ስልጡን ፖለቲካዊ እሳቤ የተመላበት የማድረግ አላማን አንግቦ ፣ << በማንኛውም መልኩ ለህዝብ እታገላለሁ ! >> የሚል የፖለቲካ ኤሊት (ፓርቲ ወይም አደረጃጀት ) ፣ ከተጋባን የብልሽት ፖለቲካ አዙሪት ባሻገር መመልከትና አርአያና ሞዴሎቹንም የተሻለ ዴሞክራሲያዊ የፖለቲካ ባህል ከገነቡት አድርጎ በመውሰድ ፣ ለስር-ነቀል ለውጥ መታገል አለበት ባይ ነኝ!

ለመውጫ ግን ፦ ያኔ በሊቢያ በረሀ ኢትዮጵያውያን ሲታረዱ ፣ ድፍን ኢትዮጵያ ማቅ ለብሳለች ፣ ሀገር የብሄራዊ ሀዘን አውጃ አምብታለች ፣ ህዝብ ያለአንዳች ጎትጓች በመላ ሀገሪቱ ለሳምንታት የዘለቀ ተቃውሞና የሀዘን ሰልፎች አድርጓል።

ወዲህ መለስ ስል ፣ ያለፉትን አምስት አመታት አይኤስ ከፈፀመው በላይ የከፋ የዘር ፍጅትና እልቂት ኢትዮጵያውያን በኢትዮጵያውያን (በአብዛኛው በአማራ ህዝብ) ላይ ፈፅመዋል ፣ በመፈፀም ላይም ናቸው። ከሰሞኑ እንኳ በቪዲዮ ከማይቀረፀው ህልቆ መሳፍርት ፍጅት ባሻገር ፣ በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ልክ አይ ኤስ ሊቢያ ላይ እንዳደረገው ሁሉ ፣ የመንግስት ወታደሮች ንፁሀንን የፊጥኝ አስረውና አሰልፈው ሲረሸኑ በቪዲዮ ቀርፀው ልባችንን ደም እምባ እያስለቀሱት ይገኛሉ!

ታዲያ! ያ ሩህሩህና የኢትዮጵያውያን ሞት ያስቆጣው ህዝብ ወዴት ገባ ? የአምስት አመቱስ ይሁን ፥ የሌሎች ህዝቦችና ኢትዮጵያንም ከነመንግስቷ እርሷት ፣ ኧረ የአማራ ህዝብ አሁን እንኳ ከምን ገብቶ ይሆን ?

ስጀምር በመግቢያዬ <<አስመሳይ ህዝብ ራሱ የደገሰውን የመከራ ድግስ እየተቋደሰ ለመኖር ይገደዳል! >> ማለቴ ለዚያ ነው!
4.6K viewsedited  16:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-31 21:02:31
<< መስጂድና ቤተክርስቲያን ማቃጠል አክሳሪ በመሆኑ ....! >> አድምጡት!

'አንድ ሲቃጠል አስር ስለሚሰሩብን አያዋጣም !'' ብሎም ነበር!

ሠውዬውኮ የሚሰማው አጥቶ ነው እንጂ ሁሉንም ዘክዝኮ ይናገራል!
8.2K viewsedited  18:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-28 19:14:59
"ሰልፍ እና መፈክር ይቁም"

"ለምን በኦሮሚያ ብቻ ሰልፍ?"

"ንፁሀንን እየገደሉ እና ጦርነት ከዚህም ከዚያም እያሞቁ "መከላከያን እንወዳለን" ማለት አይቻልም።" አቶ ታዬ ደንደኣ

<<እስቲ እንነጋገር እውነት የሀገር መከላከያን እንወዳለን....? አዎን እንወዳለን ሁሉም ወንድሞቻችን እና ልጆቻችን ናቸው። በሰላም ወተን መግባታችን በነሱ ነው እና ልንጠላቸው አንችልም እናከብራቸዋላን። ነገር ግን የሀገር መከላከያን ትክክለኛ ትርጉም ማወቅ እንጅ ሰልፍ እና የመፈክር ጋጋታ አያስፈልግም።

የእውነት መከላከያችንን የምንወድ ከሆነ ያለባቸውን ሸክም ልናቀል ይገባል። ይሄ ደሞ የሚሆነው እውነተኛ ሰላም እና እርቅ በመፍጠር የህዝብን ሰላም ስናረጋግጥ ነው። ከዛ በተረፈ ንፁሀንን እየገደሉ እና ጦርነት ከዚም ከዛም እያሞቁ "መከላከያን እንወዳለን" ማለት አይቻልም።

እውነት መከላከያን እንወዳለን ከሆነ ህዝብን በሰልፍ ማድከም አስፈላጊ አይደለም። ሰላም እና እርቅ በማውረድ ላይ እናተኩር። ከህወሃት ጋር ያደረግነውን ንግግር ከኦነግ ጋርም እናድርግ። የቤት ውስጥ ፀብ እናቁም ከጎረቤት ጋርም አንጋጭ። መከላከያ በቴክኖሎጂ እናዘምን የተጎዱትን እንካስ።

እናም እንዲህ እንላላን መከላከያ የመላው ህዝብ ሆኖ ሳለ በኦሮሚያ ብቻ ሰልፍ የሚደረገው ለምንድነው.??? እውነት እላቹሀለው ይህ ለኦሮሞ ህዝብም ለመከላከየውም ጥሩ አይደለም። ሰላም ሰላም ሰላም ለሀገራችን!>> //አቶ ታዬ ደንደአ //
9.7K views16:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-28 17:21:09 የአማራ ህዝብ....!

የአማራ ህዝብ ፦ ለመከላከያ ሰራዊቱ ክብሩንና አጋርነቱን የገለፀው አብሮት በመዋደቅ ነው ፤ ደሙን አፍስሶ አጥንቱን ከስክሶ ከጎኑ በመቀበር ነው። ከጀርባው ሲወጋ እንደአራስ ነብር ተቆጥቶ ደጀንነቱን በተግባር በማስመስከር ነው። በየአውደ ውጊያው ምሽግ ድረስ እየዘለቀ በእጁ ፈትፍቶ እያጎረሰ ፣ ቀድቶ እያጠጣ ነው።

የአማራ ህዝብ ፦ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት የሀገር ዳር ድንበርና ሉአላዊነት ዘብ የሚሆን ፣ ከጥላቻ የጎሳ ፖለቲከኞች ምረዛና መጠቀሚያነት የፀዳ ፥ ራሷ ኢትዮጵያን የሚመስል ተቋም ሆኖ እንዲቀጥልም የሚመኝ ትልቅ ህዝብ ነው!

የአማራ ህዝብ ፦ በከሀዲዎች በገሀድ ለተጨፈጨፉት የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት አባላት ፣ ዛሬም ቢሆን ፍትህ እንዲያገኙ ፣ ለጉዳታቸው ተመጣጣኝ ካሳ እንዲከፈላቸው አበክሮ የሚጠይቅ ህዝብ ነው!

የአማራ ህዝብ የሀገርና የህዝብን ህልውና ለማስከበር ከትግራይ ወራሪ ሀይል ጋር ተዋግተው በሰሜን ኢትዮጵያ የጦር ግንባሮች ከሀገራቸው አፈር ጋር ተዋህደው ለቀሩ የኦሮሞ ፣ የደቡብ ፣ የሶማሌ ፣ የአፋር ፣ የጉራጌ ፣ የጋምቤላ ፣ .... ወዘተ ኢትዮጵያዊ ጀግኖች ክብርና አለኝታነቱን በተግባር የሚገልፅ ህዝብ ነው!

አዎ! ዛሬም ቢሆን የመከላከያ ሠራዊቱ ከጀርባው ተወግቶ ለተፈፀመበት እልቂት ፣ ለሀገርና ለህዝብ ህልውና መከበር ሲል ለከፈለው መስዋትነት ፍትህና ካሳ ሳያገኝ ብሎም ክህደት ፈፃሚ የሴራ ፖለቲከኞች የስልጣን ማፅኛና መቀራመቻ አድርገውት በሚገኝበት ሁኔታ ፣ ይህ አልበቃቸው ብሎ ይህን ሁሉ ግፍና መከራውን አብሮት ከተጋፈጠው ህዝብና የህዝቡ አርበኞች ጋር ፣ አፈሙዝ እንዲዟዟር ፣ ወንድም በወንድሙ ላይ እንዲተኩስ ለማድረግ እጃቸውን በሰራዊቱ ውስጥ የሰገሰጉ የሴራ ፖለቲካ ነጋዴዎችን ቆርጦ ሊጥልና በተሰጠው ክብር ልክ ፀንቶ ሊቆም ይገባል!

የመከላከያ ሰራዊቱ ክብሩን እንደያዘ ፣ ህዝባዊ አጋርነቱን እንደተጎናፀፈ ሊቆይ የሚችለውም ፥ ያጎረሱትን እጆች ሳይነክስ ፣ ለክብሩ አብረውት የተዋደቁ ጀግኖችን ውለታ ሳይዘነጋ ራሱን ከጎሳ ፖለቲከኞች ሴራ ጠብቆ ኢትዮጵያን መስሎ መጓዝ ሲችል ብቻ ነው!
8.3K views14:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-27 22:02:17
5.8K views19:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-27 22:02:10 ለቱለማ መሬት መቆርቆር... ለምን ? ለማን?

<< የቱለማን መሬት ሽጦ ለሴተኛ አዳሪ ተጫርቶ የከፈለውና ሚሊዮኖችን ቲፕ/ጉርሻ የሰጠው ማነው? >> //በታዬ ደንደአ//

//ትርጉም: ኢልመ-ቢያ በተለይ ለአዲስ ዘይቤ //

አሸብሽቦ አዳሪው፣ የሌባና የሴረኛ ተላላኪ፣ በቅርቡ በቱለማ መሬት ስም ይፎክር ይዟል። በቱለማ ላይ ስለተፈጸመው ዘረፋ ደጋግሞ አጀንዳ ያደርጋል። መስኪዶችና ሌሎች የእምነት ቤቶች የፈረሱት የቱለማን መሬት ለማዳን እንደሆነ ይናገራል። ይሄንና ይሄንን መሰሉ ነገር የፖለቲካ ቁማር ያሉትን ነገር ይመስላል። በቁማሩ ቱለማን አሲዞ ለማስበላት ይራወጣል። አስቀድሞ የቱለማን መሬት ሽጦ ይበላል፣ አሁን ደግሞ ቱለማን ለመስበላት ያሴራል ። ሌባውና ሴረኛው ቱለማን ከቀዬው የነቀለው ሳያንሰው ወደ ወንድሞቹ የተጠጋውን ሊያስበላ ይጋጋጣል። ይሄ በጭራሽ አይሳካም!

አዎን እውነት ነው! ቱለማ ከመሬቱ መፈናቀሉ ሐቅ ነው። ይህ ወንጀል መቆም ነበረበት። ይሁንና ማነው ቱለማን አፈናቅሎ ለማኝና ተፈናቃይ ያደረገው? ሌላ ኃይል ቢኖርም እንኳ በአብላጫው ቱለማን ከቀዬው ያፈናቀለው ሌባና ሴረኛው ነው። ባለፉት አምስት ዓመታት በአዲስ አበባ ዙሪያ ባሉ ከተሞች ውስጥ የሆነውን የማያውቅ የለም። በገበሬ ስም ማነው የአዲስ አበባን መሬት የተቀራመተው? የቱለማን መሬት ሽጦ ለሴተኛ አዳሪ ተጫርቶ የከፈለውና ሚሊዮኖችን ቲፕ/ጉርሻ የሰጠው ማነው? ሌባውና ሴረኛው ነው። ቀን ቀን የቱለማን ድኻ ያስለቅሳሉ፣ ማታ ውስኪ ቤት ይጨፍራሉ። ይቅርታ የማያሰጥ ወንጀል እየፈጸሙ ዛሬ ላይ እራሳቸውን የቱለማ ጠበቃ አድርገው ያቀርባሉ። ቱለማን ጭምብል በማድረግ ከወንጀላቸው ለመደበቅ ይጥራሉ። ይሁንና የሌባና የሴረኛ ተንኮል እራሱን ይበላው ይሆናል እንጂ ወንድማማቾችን አይነጣጥልም።

ቱለማ ለረጅም ዓመታት ተቸግሮ ኖሯል። ሲብስበት ደግሞ ወደ ወንድሞቹ ተሰድዷል። ዛሬ ላይ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ የቱለማ ልጆች በአርሲ፣ በጅማ፣ በባሌ፣ በሐረርጌ፣ በኢሉ እና በመሳሰሉት ይኖራሉ። በወንድሞቹ ቤት የሚፈጠር ችግርም መከራንም አብሮ ይካፈላል። በሚኖርበት ሁሉ ከሙስሊም ወንድሞቹ ጋር በፍቅርና በመከባበር ይኖራል። አሸብሽቦ አደሩ ግን ቱለማን ከሙስሊም ወንድሞቹ ጋር ሊያጣላ ይጋጋጣል። እስኪ "ለቱለማ ብለን ነው መስኪዶችን ያፈረስነው" ማለት ምን ማለት ነው? የመስኪዶችን መፍረስ የቱለማን መሬት በማገናኘት የህዝብን አንድነት ለማፍረስ ያለመ ነው። ኦሮሞን በመነጣጠል፣ ለየብቻው ለመሰልቀጥ የተሸረበ ሴራ ነው። በተለይ ደግሞ በቱለማ ልጆች ኪሳራ ሌቦችና ሴረኞች የፈጸሙትን ወንጀል መከለል ነው የተፈለገው። የቱለማ መሬት ስላላጠረቃው ቱለማን ለመብላት አንሰፍስፏል። ይህም እንጂ አይሳካም! ይሄ በመጀመሪያ ሙከራ ነው የከሸፈው።

ህግን ማክበርና ማስከበር ተገቢ ነው። የእምነት ሥፍራዎችን ጨምሮ ሁሉንም መገንባቱ በሥርዐትና በቅደም ተከተል መከናወን ይገባዋል። ነገር ግን ስርዓት ማስከበር በጠዋቱ ነው። ህገወጥ ግንባታን መከልከል ገንዘብ እና ጉልበት ሳይባክን በፊት ነበር። የእራሳቸውን መሬት ሽጠው፣ ቤት ሲሰራ ዝም ብለው፣ እራሳቸው መብራትና ውኃ ሲያስገቡ ከርመው ከፍተኛ የሀገር ኃብት መሬት ላይ ከፈሰሰ በኋላ በህግ ስም በድኾችን ቤቶችን፣ የእምነት ተቋማትን ማፍረስ ትርጉም አይሰጥም።

ስለሆነም የድኾች ቤቶችን እና የእምነት ተቋማት ማፍረሱ ቱለማን አይመለከተውም። ይሄንን አጀንዳ ከቱለማ ላይ አውርዱ። ሲጠቃለል የጉዳዩ ባለቤቶች በአምቻና በጋብቻ እንዲሁም በሚዜነት ስም የተደራጁት ሰዎች ይሆናል።

እኛ ሰላምን እንሻለን! እግዚአብሔር ሰላምን ይስጠን!

————————————————————————-

የአሮሚያ ብልፅግና አመራር እና የሰላም ሚኒስትር ሚኒስትር ዴኤታ የሆኑት አቶ ታየ ደንድአ በፌስቡክ ገፃቸው ያሰፈሩት ፅሁፍ ነው።
5.9K views19:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-25 16:19:52
ትናንት ፍርድ ቤት የቀረበችውና በግፍ ታስራ የምትገኘው ብርቱዋ ጋዜጠኛ - ገነት አስማማው ለችሎቱ ይህን አለች ፦

".... በማንነቴ ከደረሰብኝ ጥቃት በተጨማሪም በሴትነቴ ላይ የደረሰብኝ ጾታዊ ትንኮሳ እንዳለ ለፍርድ ቤቱ አቤቱታ ባቅርብም ፍ/ቤቱ ችላ ብሎ እያለፈብኝ ነው!”

የተቀበረች ፍትህ ቀባሪዎቿን ትቀብራለች!

ፍትህ በግፍ ታስረው ለሚገኙ በአስርት ሺዎች ለሚቆጠሩ የህሊና እስረኞች!
6.2K views13:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-24 20:49:27
የታሰሩበት ከታወቀው ይልቅ ታፍነው ደብዛቸው የጠፋው በርካቶች ናቸው !

ይህ ወጣት እንዳልካቸው እሸቱ እጅጉ ይባላል።

በሸገር ትራንስፓርት ውስጥ የስምሪት ክፍል ሀላፊና ምስጉን ሰራተኛ ነው። ሚያዚያ 30 ቀን 2015 ዓ.ም ስድስት ኪሎ አካባቢ ከሚገኘውና ተከራይቶ ከሚኖርበት መኖሪያ ቤቱ ፣ የፌደራል ፓሊስ ልብስ የለበሱና አምቡላንስ መኪና የያዙ የፀጥታ ሀይሎች አፍነውት መሰወራቸውን አከራዬቹና በአካባቢው ያዩ ግለሰቦች ተናግረዋል።

ከዚያን እለት ጀምሮ ወጣት እንዳልካቸው የት እንዳለ ለማወቅ አልተቻለም። ቤተሰቦቹም በየ ፀጥታ ተቋሙ ቢያመለክቱና ቢጠይቁም እስካሁን ‘’ አየን’’ የሚል መንግስታዊ አካል አልተገኘም። ወላጆቹ በከፍተኛ ጭንቀትና ህመም ላይ ናቸው።

የዜጎችን ሰላምና ደህንነት የማስጠበቅ ተቀዳሚ ሀላፊነት ባለበት ‘’መንግስት ነኝ ‘’ በሚለው አካል ይህን መሠል የጋንግስተር ተግባር እየተፈፀመ ወደማን አቤት ይባላል ?

በአዲስአበባና በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች በመንግሥት፣ የፀጥታ አካላት በተለመደው ሁኔታ ተይዘው ከሚታሰሩት አስርት ሺዎች ውጭ በድብቅ እየታፈኑ ለወራት አድራሻቸውና ያሉበት ሁኔታ የማይታወቅ ዜጎች ቁጥር እጅግ በጣም አሳሳቢ እየሆነ ነው!

አሳዛኝና በሀገራችን ለመኖር ዋስትና ባሳጣን ፋሽስታዊ ስርዓት ላይ ወድቀናል!

#ሼር በማድረግ በአንባገነኖች ታፍነው ደብዛቸው ለጠፋ ወገኖቻችን ድምፅ እንሁን !
7.8K views17:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ