Get Mystery Box with random crypto!

ለቱለማ መሬት መቆርቆር... ለምን ? ለማን? > //በታዬ ደንደአ// //ትርጉም: ኢልመ-ቢያ በ | ዘሪሁን ገሠሠ

ለቱለማ መሬት መቆርቆር... ለምን ? ለማን?

<< የቱለማን መሬት ሽጦ ለሴተኛ አዳሪ ተጫርቶ የከፈለውና ሚሊዮኖችን ቲፕ/ጉርሻ የሰጠው ማነው? >> //በታዬ ደንደአ//

//ትርጉም: ኢልመ-ቢያ በተለይ ለአዲስ ዘይቤ //

አሸብሽቦ አዳሪው፣ የሌባና የሴረኛ ተላላኪ፣ በቅርቡ በቱለማ መሬት ስም ይፎክር ይዟል። በቱለማ ላይ ስለተፈጸመው ዘረፋ ደጋግሞ አጀንዳ ያደርጋል። መስኪዶችና ሌሎች የእምነት ቤቶች የፈረሱት የቱለማን መሬት ለማዳን እንደሆነ ይናገራል። ይሄንና ይሄንን መሰሉ ነገር የፖለቲካ ቁማር ያሉትን ነገር ይመስላል። በቁማሩ ቱለማን አሲዞ ለማስበላት ይራወጣል። አስቀድሞ የቱለማን መሬት ሽጦ ይበላል፣ አሁን ደግሞ ቱለማን ለመስበላት ያሴራል ። ሌባውና ሴረኛው ቱለማን ከቀዬው የነቀለው ሳያንሰው ወደ ወንድሞቹ የተጠጋውን ሊያስበላ ይጋጋጣል። ይሄ በጭራሽ አይሳካም!

አዎን እውነት ነው! ቱለማ ከመሬቱ መፈናቀሉ ሐቅ ነው። ይህ ወንጀል መቆም ነበረበት። ይሁንና ማነው ቱለማን አፈናቅሎ ለማኝና ተፈናቃይ ያደረገው? ሌላ ኃይል ቢኖርም እንኳ በአብላጫው ቱለማን ከቀዬው ያፈናቀለው ሌባና ሴረኛው ነው። ባለፉት አምስት ዓመታት በአዲስ አበባ ዙሪያ ባሉ ከተሞች ውስጥ የሆነውን የማያውቅ የለም። በገበሬ ስም ማነው የአዲስ አበባን መሬት የተቀራመተው? የቱለማን መሬት ሽጦ ለሴተኛ አዳሪ ተጫርቶ የከፈለውና ሚሊዮኖችን ቲፕ/ጉርሻ የሰጠው ማነው? ሌባውና ሴረኛው ነው። ቀን ቀን የቱለማን ድኻ ያስለቅሳሉ፣ ማታ ውስኪ ቤት ይጨፍራሉ። ይቅርታ የማያሰጥ ወንጀል እየፈጸሙ ዛሬ ላይ እራሳቸውን የቱለማ ጠበቃ አድርገው ያቀርባሉ። ቱለማን ጭምብል በማድረግ ከወንጀላቸው ለመደበቅ ይጥራሉ። ይሁንና የሌባና የሴረኛ ተንኮል እራሱን ይበላው ይሆናል እንጂ ወንድማማቾችን አይነጣጥልም።

ቱለማ ለረጅም ዓመታት ተቸግሮ ኖሯል። ሲብስበት ደግሞ ወደ ወንድሞቹ ተሰድዷል። ዛሬ ላይ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ የቱለማ ልጆች በአርሲ፣ በጅማ፣ በባሌ፣ በሐረርጌ፣ በኢሉ እና በመሳሰሉት ይኖራሉ። በወንድሞቹ ቤት የሚፈጠር ችግርም መከራንም አብሮ ይካፈላል። በሚኖርበት ሁሉ ከሙስሊም ወንድሞቹ ጋር በፍቅርና በመከባበር ይኖራል። አሸብሽቦ አደሩ ግን ቱለማን ከሙስሊም ወንድሞቹ ጋር ሊያጣላ ይጋጋጣል። እስኪ "ለቱለማ ብለን ነው መስኪዶችን ያፈረስነው" ማለት ምን ማለት ነው? የመስኪዶችን መፍረስ የቱለማን መሬት በማገናኘት የህዝብን አንድነት ለማፍረስ ያለመ ነው። ኦሮሞን በመነጣጠል፣ ለየብቻው ለመሰልቀጥ የተሸረበ ሴራ ነው። በተለይ ደግሞ በቱለማ ልጆች ኪሳራ ሌቦችና ሴረኞች የፈጸሙትን ወንጀል መከለል ነው የተፈለገው። የቱለማ መሬት ስላላጠረቃው ቱለማን ለመብላት አንሰፍስፏል። ይህም እንጂ አይሳካም! ይሄ በመጀመሪያ ሙከራ ነው የከሸፈው።

ህግን ማክበርና ማስከበር ተገቢ ነው። የእምነት ሥፍራዎችን ጨምሮ ሁሉንም መገንባቱ በሥርዐትና በቅደም ተከተል መከናወን ይገባዋል። ነገር ግን ስርዓት ማስከበር በጠዋቱ ነው። ህገወጥ ግንባታን መከልከል ገንዘብ እና ጉልበት ሳይባክን በፊት ነበር። የእራሳቸውን መሬት ሽጠው፣ ቤት ሲሰራ ዝም ብለው፣ እራሳቸው መብራትና ውኃ ሲያስገቡ ከርመው ከፍተኛ የሀገር ኃብት መሬት ላይ ከፈሰሰ በኋላ በህግ ስም በድኾችን ቤቶችን፣ የእምነት ተቋማትን ማፍረስ ትርጉም አይሰጥም።

ስለሆነም የድኾች ቤቶችን እና የእምነት ተቋማት ማፍረሱ ቱለማን አይመለከተውም። ይሄንን አጀንዳ ከቱለማ ላይ አውርዱ። ሲጠቃለል የጉዳዩ ባለቤቶች በአምቻና በጋብቻ እንዲሁም በሚዜነት ስም የተደራጁት ሰዎች ይሆናል።

እኛ ሰላምን እንሻለን! እግዚአብሔር ሰላምን ይስጠን!

————————————————————————-

የአሮሚያ ብልፅግና አመራር እና የሰላም ሚኒስትር ሚኒስትር ዴኤታ የሆኑት አቶ ታየ ደንድአ በፌስቡክ ገፃቸው ያሰፈሩት ፅሁፍ ነው።