Get Mystery Box with random crypto!

ደራሲ እና የሰብዓዊ መብት ተሟጋች አሳዬ ደርቤ ፍርድ ቤት ቀርቧል! ደራሲ፣ የሰብዓዊ መብት ተሟጋ | ዘሪሁን ገሠሠ

ደራሲ እና የሰብዓዊ መብት ተሟጋች አሳዬ ደርቤ ፍርድ ቤት ቀርቧል!

ደራሲ፣ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች እንዲሁም የጠለስ ዩቱብ ሚዲያ መስራችና ባለቤት አሳዬ ደርቤ ግንቦት 30/2015 ዓ.ም በፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ ወንጀል ጉዳዮች ጊዜ ቀጠሮ ችሎት ቀርቦ ነበር።

የፌደራል ፖሊስ በሽብር እና ህግ-መንግስታዊ ሰርዓቱን በኃይል በመናድ ወንጀል ጠርጥሬ ምርመራ እያጣራሁኝ ነው በማለት የ14 ቀን የምርመራ ጊዜ ይፈቀድልኝ በማለት ጠይቋል።

በጠበቆች በኩልም የፖሊስ የጊዜ ቀጠሮ ጥያቄ ውድቅ ተደርጎ የደንበኛችን የዋስትና መብት ሊከበር ይገባል ሲሉ ሰፊ የህግ እና የፍሬ ነገር ክርክር ስለማቅረባቸው ከጠበቃ አዲሱ አልጋው መረጃ ማግኘቱን በመግለጽ ያጋራው ጋዜጠኛ አራጋው ሲሳይ ነው።

የግራ ቀኙን ክርክር ያዳመጠው ችሎቱም ፖሊስ ያቀረበው የጊዜ ቀጠሮ ጥያቄ ይፈቀድ ወይስ የደራሲ አሳዬ ደርቤ የዋስትና መብት ሊጠበቅ ይገባል በሚለው ጭብጥ ላይ ውሳኔ ለመሰጠት በአዳሪ ለሰኔ 1/2015 ዓ.ም ከጠዋቱ 3:00 ላይ ተለዋጭ ቀጠሮ ስለመያዙም ተገልጧል።

ደራሲ አሳዬ ደርቤ ግንቦት 28 ቀን 2015 ዓ.ም ከምሽቱ ሶስት ሰዓት ላይ አገዛዙ በላካቸው የፌደራል ፖሊስ አባላት ታፍኖ መወሰዱ አይዘነጋም።

ዘገባው የአሻራ ሚዲያ ነው።