Get Mystery Box with random crypto!

የአማራ ህዝብ....! የአማራ ህዝብ ፦ ለመከላከያ ሰራዊቱ ክብሩንና አጋርነቱን የገለፀው አብሮት | ዘሪሁን ገሠሠ

የአማራ ህዝብ....!

የአማራ ህዝብ ፦ ለመከላከያ ሰራዊቱ ክብሩንና አጋርነቱን የገለፀው አብሮት በመዋደቅ ነው ፤ ደሙን አፍስሶ አጥንቱን ከስክሶ ከጎኑ በመቀበር ነው። ከጀርባው ሲወጋ እንደአራስ ነብር ተቆጥቶ ደጀንነቱን በተግባር በማስመስከር ነው። በየአውደ ውጊያው ምሽግ ድረስ እየዘለቀ በእጁ ፈትፍቶ እያጎረሰ ፣ ቀድቶ እያጠጣ ነው።

የአማራ ህዝብ ፦ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት የሀገር ዳር ድንበርና ሉአላዊነት ዘብ የሚሆን ፣ ከጥላቻ የጎሳ ፖለቲከኞች ምረዛና መጠቀሚያነት የፀዳ ፥ ራሷ ኢትዮጵያን የሚመስል ተቋም ሆኖ እንዲቀጥልም የሚመኝ ትልቅ ህዝብ ነው!

የአማራ ህዝብ ፦ በከሀዲዎች በገሀድ ለተጨፈጨፉት የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት አባላት ፣ ዛሬም ቢሆን ፍትህ እንዲያገኙ ፣ ለጉዳታቸው ተመጣጣኝ ካሳ እንዲከፈላቸው አበክሮ የሚጠይቅ ህዝብ ነው!

የአማራ ህዝብ የሀገርና የህዝብን ህልውና ለማስከበር ከትግራይ ወራሪ ሀይል ጋር ተዋግተው በሰሜን ኢትዮጵያ የጦር ግንባሮች ከሀገራቸው አፈር ጋር ተዋህደው ለቀሩ የኦሮሞ ፣ የደቡብ ፣ የሶማሌ ፣ የአፋር ፣ የጉራጌ ፣ የጋምቤላ ፣ .... ወዘተ ኢትዮጵያዊ ጀግኖች ክብርና አለኝታነቱን በተግባር የሚገልፅ ህዝብ ነው!

አዎ! ዛሬም ቢሆን የመከላከያ ሠራዊቱ ከጀርባው ተወግቶ ለተፈፀመበት እልቂት ፣ ለሀገርና ለህዝብ ህልውና መከበር ሲል ለከፈለው መስዋትነት ፍትህና ካሳ ሳያገኝ ብሎም ክህደት ፈፃሚ የሴራ ፖለቲከኞች የስልጣን ማፅኛና መቀራመቻ አድርገውት በሚገኝበት ሁኔታ ፣ ይህ አልበቃቸው ብሎ ይህን ሁሉ ግፍና መከራውን አብሮት ከተጋፈጠው ህዝብና የህዝቡ አርበኞች ጋር ፣ አፈሙዝ እንዲዟዟር ፣ ወንድም በወንድሙ ላይ እንዲተኩስ ለማድረግ እጃቸውን በሰራዊቱ ውስጥ የሰገሰጉ የሴራ ፖለቲካ ነጋዴዎችን ቆርጦ ሊጥልና በተሰጠው ክብር ልክ ፀንቶ ሊቆም ይገባል!

የመከላከያ ሰራዊቱ ክብሩን እንደያዘ ፣ ህዝባዊ አጋርነቱን እንደተጎናፀፈ ሊቆይ የሚችለውም ፥ ያጎረሱትን እጆች ሳይነክስ ፣ ለክብሩ አብረውት የተዋደቁ ጀግኖችን ውለታ ሳይዘነጋ ራሱን ከጎሳ ፖለቲከኞች ሴራ ጠብቆ ኢትዮጵያን መስሎ መጓዝ ሲችል ብቻ ነው!