Get Mystery Box with random crypto!

ዘሪሁን ገሠሠ

የቴሌግራም ቻናል አርማ zerihunkocha — ዘሪሁን ገሠሠ
የቴሌግራም ቻናል አርማ zerihunkocha — ዘሪሁን ገሠሠ
የሰርጥ አድራሻ: @zerihunkocha
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 13.77K
የሰርጥ መግለጫ

በመረጃ እንቀራረብ! በመረጃ እንተሳሰር!

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 7

2023-04-21 15:15:44 በትክክልም አላማና ግብ ያለው ሰላማዊ ትግል የምታደርግ ከሆነ ከእነዚህ 5 ነገሮች ተጠንቀቅ ፦

☞ የፖለቲካ ቡድንን (ባለስልጣንን) እንጂ በፍፁም ህዝብን እንደህዝብ አትፈርጅ ፥ አትስደብ ፥ አታጥላላ!

☞ ትችትና አስተያየትህ የግለሰቡን (የፖለቲካ ቡድኑን) እኩይ ተግባር መሠረት ያደረገ እንጂ ማንነቱን መገለጫ ከማድረግ ተቆጠብ

☞ በፍፁም ሀይማኖትና ፖለቲካን ከመቀላቀል ተቆጠብ!

☞ ትግልህ ፍትህና እኩልነት እንዲሰፍን ማድረግ እንጂ በአንተ ላይ የደረሰውን በሌሎች ላይ ለማድረስ አለመሆኑን አስረግጠህ እመን! በቀለኝነትንም አታንፀባርቅ!

☞ ተግባቦትህ ሁሉ ወዳጅ ማብዛት ላይ እንጂ ጠላትን በሚያበዛ መልኩ አይሁን!

በዚህ መልኩ ስትሄድ ሩቅ ትጓዛለህ ፤ የሚረዱህን ታበዛለህ ፥ አላማና ግብህ በሁሉም ይታወቃል ፤ እወክለዋለሁ ለምትለውም ህዝብ የተቀላጠፈ ለውጥ እንዲመጣ ማድረግ ትችላለህ!

መልካም ቀን!
2.3K views12:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-20 23:00:26
መንግሥት ከእስራኤል የገዛውን UFED የተሰኘ የስለላ ቴክኖሎጂ ለሰብዓዊ መብት ጥሰት እየተጠቀመበት ይገኛል!

የኢትዮጵያ መንግሥት እኤአ በ2021 NASDAQ ከተሰኘው Cellebrite የስለላ ቴክኖሎጂዎችን የሚያመርት ተቋም የገዛውና UFED የሚባል ቴክኖሎጂ ፥ በአሁኑ ሠአት በስፋት ጥቅም ላይ እየዋለ ይገኛል፡፡ የበርካታ አክቲቪስቶች ፥ ፖለቲከኞችና ተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች መረጃ እየተበረበረ መሆኑንም ከምንጮቻችን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ይህ UFED የተሰኘው የሴሌብራይት ቴክኖሎጂ ፥ በይለፍ ቃል የተጠበቁ ስልኮችን ለመጥለፍ ፥ የሚዲያ ፋይሎችን ፥ የጽሑፍ መልዕክቶችን ፣ የጥሪ ታሪኮችን ፣ የደወል ታሪኮችን እና ሌሎችንም ጨምሮ በመሳሪያው ላይ የተመዘገቡትን ግለሰቦች ሁሉንም መረጃዎች ዳውንሎድ አድርጎ ለመበርበር የሚያስችል ነው፡፡

አለምአቀፍ የሰብአዊ መብት ተቋማት እስራኤል ይህን ቴክኖሎጂ ለኢትዮጵያ መንግሥት በመስጠት ዜጎች ላይ አረመኔያዊ የሰብዓዊ መብት ጥሰት እንዲፈፀም ፥ መረጃዎቻቸው እንዲበረበሩ ብሎም ለእስርና ለግድያ እንዲዳረጉ ተባባሪ ሆናለች በማለት በተደጋጋሚ አቤቱታ ሲያቀርቡ እንደነበር የሚታወስ ነው፡፡
4.3K views20:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-20 19:45:47
በመላው ሀገራችን ለምትገኙ የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ1444ኛው የኢድ አል-ፈጥር በዓል በሠላም አደረሳችሁ  ፤ አደረሰን!

Hordoftoonni Amantaa Musliimaa Naannoofi Biyya keenyaa hundi baga Ayyaana Iid Al Faxir waggaa 1444ffaa Nagaan Geessan Baga Geenye!

ሰዓብቲ እስልምና ኣብ መላእ ሃገርና ንመበል 1444 ዒድ ኣልፈጥር እንኳዕ አብፀሀኩም ፥ አብፀኸና!

Dhamaan umada islaamka meelkasta oo ay joogaan waxaan ku salaamayaa ciidul fidriga 1444-ka.

ዒድ ሙባረክ!
Ciid mubaarak!
EID MUBARAK!
4.9K views16:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-19 14:09:45 ትግላችን 3ተኛውን አማራጭ  ፖለቲካዊ መንገድ ለመክፈት መሆን አለበት!

እርግጥ ነው " ትህነግ/ህወሓት አሸባሪ ፥ ወንጀለኛና ለፍርድ መቅረብ ያለበት ድርጅት ነው"  ብዬ አምናለሁ፡፡ ነገርግን በአሁኑ ሠአት የዚች ሀገር የህልውና ስጋት "መንግስት ነኝ!" የሚለው የአብይ ስርአት እንጂ ህወሓት ነው ብዬ አላምንም! ይህን ስርአት በዚህ ደረጃ ያነቀዘው አንደኛው ምክንያትም   ፥ 5 አመታትን ሙሉ  24/7 "ህወሓት ፥ የህወሓት እጅ..!" ስንል መሰንበታችን ነው!

ኢትዮጵያ ምንአልባት የመዳን ተስፋ የሚኖራት የትግራይ እና የአማራ ህዝቦች ፖለቲከኞች ሶስተኛውን መንገድ መርጠው በጋራ ከተጓዙበት ብቻ ነው!

ይህ አሰላለፍ በዚሁ ከቀጠለና የዘይትና የውሃ አይነት ተፈጥሮ ያላቸው ሁለቱ ኃይሎች "በአማራ ጥላቻ ላይ ብቻ" ተስማምተው በሀገሪቱ ፖለቲካ ውስጥ የሚቀጥሉ ከሆነ የጊዜ ጉዳይ እንጂ ሊመሠረት የሚችለው ያ "አልሸሹም ዘወር አሉ" የሚሆነውና ያሳለፍነው የ27 አመቱ ስርአት ነው ፡፡ አለያም ደግሞ የፖለቲካ ብልሽቱ እዚያም ሳይደርስ ሀገሪቱን በማፍረስ ይጠናቀቃል!

ይህ አማራጭ ምርጫ የሚሆነው አሁን ያለው ፋሽስታዊ ስርአት ሌሎች አማራጮችን ሁሉ ለመስማትም ሆነ ለመከተል ፍፁም ፈቃደኛ ባለመሆኑ ነው!
3.3K views11:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-18 20:48:33 በአዲስአበባ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ላይ ማንነትን መሠረት ባደረገ መልኩ የሚደረገው እስርና እንግልት ተባብሶ መቀጠሉን ተማሪዎች ገልፀዋል ፡፡ ባለፉት ቀናት ቁጥራቸው በውል ተለይቶ ያልታወቀ ተማሪዎች መታሰራቸውም ታውቋል!

ከ6 ኪሎ ካምፓስ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት በስልክ ያነጋገርኩት አንድ ተማሪ " እስካሁን 6 ጓደኞቼ ታስረዋል፡፡ እኔም ፈርቼ ወደቤተሰብ ለመሄድ ተገድጃለሁ !" ሲል የሁኔታውን አሳሳቢነት አረጋግጦልኛል !
2.6K views17:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-18 16:33:50
ተከታዩ ንግግር ኦቦ ብርሃኑ ጁላ በደብረ ዘይት ከተማ በተደረገ የኦሮሞ ፖለቲከኞች መድረክ ላይ ከተናገረው ነው ፦

<< እኔ ወታደር ነኝ። ጄኔራል ነኝ። መለዮን ጥየ ሲብል ልብስ ለብሼ ነው የመጣሁ። ለምንድን ነው? እንደ አንድ የኦሮሞ ልጅ መሳተፍ ሥለምፈልግ ነው። እኛ እየሰራን ያለነው ለኦሮሞ ጥቅም እና ክብር ነው። ጠቅላይ ሚኒስቴር ዶ/ር አብይም የሚሰራው ለኦሮሞ ክብር እና ጥቅም ነው። የሚቻል ከሆነ በምሥራቅ አፍሪካ በወታደራዊ አደረጃጀት ፣ በኢኮኖሚ ፣ በዲፕሎማሲ እና በፖለቲካው የታፈረች እና የተከበረች ታላቋን ኦሮምያ ሀገር ለመመሥረት ነው የምንሠራው። ይህንን ካልቻልን ግን በኦሮሞ ፍላጎት ብቻ የምትተዳደር ኢትዮጵያን እንመሠረታለን። ሁላችሁም የኦሮሞ ልጆች አግዙን! >> ኦቦ ብርሃኑ ጁላ

ኢትዮጵያ ወደአስከፊው የዝቅጠት ደረጃ መውረዷ በጉልህ የተረጋገጠው ፤ እንዲህ አይነቱ በዘረኝነትና በጥላቻ የተገነባ ተራ ሰው ፥ በብሄር ኮታ ገብቶ ያለግብሩ በአለም ላይ በጣት ከሚቆጠሩ ሀገራት ውጪ የማይሰጥ የማዕረግ ስም አውጥተው ጭነውበት " የኢፌዲሪ የጦር ኃይሎች ኤታማዦር ሹም " ተብሎ የተጠራ ጊዜ ነው !
4.2K views13:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-18 16:33:19 "በቃ!" ብለን ፤ መሸቀጫ ሱቆቻቸውንና መደበቂያ ዋሻዎቻቸውን ልንዘጋባቸው ይገባል!

በስንፍናቸውና ሀገር መምራት ባለመቻላቸው ትችት ሲሰነዘርባቸው " የኦሮሞ ጥላቻ ነው!" እያሉ ፥ ሲያሻቸው የኃይማኖት ካባ ደርበው " ጠቅላይ ሚኒስቴሩን መተቸት ፕሮቴስታንት ጠልነት ነው!" የሚል ለክ/ዘመኑ የማይመጥን ኃላቀር መከራከሪያ እያቀረቡ ፥ ሌላው ቀርቶ " የሚሰነዘርብን ተቃውሞ የአህመድ ልጅ አይመራንም የሚል ነው!" የሚል አስነዋሪና የድንቁርና ማሳያ የሆነ ብሎም በብዘሀ ማንነት ፣ ሀይማኖትና ባህል የተገነባችውን ኢትዮጵያ ወደእልቂት የሚያመራ አመክንዮ እያቀረቡ ደሀውን ህዝብ ከፋፍለው መደበቂያ ዋሻ በማድረግ በቅጥፈት እያደናገሩ ዛሬም የህዝብን ስልጣን ተቆናጠው በቁልቁለት መንገዱ እየተጓዙ ይገኛሉ !

ከእንግዲህ ግን ይህ ህዝብ ፥ የተሻለ ነገውን ፣ ሰላምና አብሮነቱን ብሎም ፍትህና ርትእ የሰፈነባትን ኢትዮጵያ የሚሻ ከሆነ " በቃ!" የሚልበት ጊዜው አሁን ነው! ከዚህ በላይ የምንሸከመው መከራና ግፍ ሊኖር አይገባም !

ታላቁ የኦሮሞ ህዝብ በስሙ ለሚነግዱ ፤ በተግባር ከራሳቸው የዘረፋ ኔትወርክ ውጭ አንዳችም ለማይፈይዱለት ብሎም የአብሮነት እሴቱን ሸርሽረው ከሌሎች ኢትዮጵያውያን ወንድም ህዝቦች ጋር ለሚያቃቅሩት ዘረኞች ፣ ሰነፎችና ዘራፊዎች መደበቂያ ዋሻ ሊሆን አይገባም!

ኃይማኖቶችም የግል አምልኮና የዘላለማዊው ህይወት መጠጊያ ቤቶች እንጂ የዘረኛ የፖለቲካ ቡድኖች መሸቀጫ ሱቅ እንዲሁም መደበቂያ ዋሻ መሆናቸው ሊያከትም ይገባል !
3.5K views13:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-17 20:11:41 ጋዜጠኛ መሳይ መኮንን - ሉሲፈር አብይ በቅርቡ እየተገለፀለት ስለሆነ መሠለኝ ፥ የዛሬ 3 አመት የተናገረውን ተከታዩን ንግግር ገና ዛሬ አድምጦት ኖሯልና ስሜታዊ አርጎታል!

ጠሚው በባሌ የተናገረው ንግግር በአጭሩ እንዲህ ይላል ፦

<< ... ትናንት ያዋረደንን አዋርደነዋል ፤ ትናንት የሠበረንን ሠብረነዋል ፤ ትናንትና አትወጡም አትገቡም ብሎ አጥር ያጠረብን ከእኛ ፈቃድ ውጪ ዛሬ መጥቶ መግባት አይችልም፡፡ ...... ብልፅግና ፓርቲ የኦሮሞ ህዝብ ነው!!! >>

ይህ ንግግር ጠ/ሚ አብይ አህመድ (ዶ/ር) ጥር 26 ቀን 2012 ዓ.ም ፥ በባሌ በተደረገው ፥ የወልመል ግድብ ምረቃ ላይ በኦሮምኛ ከተናገረው ንግግር በትንሹ የተቀነጨበ ነው! ይህን ንግግር በተደጋጋሚ ፅፌው አውቃለሁ!

ከዚያ በኃላማ በፓርላማ የቀጥታ ስርጭት የዘር ፍጅት ቅስቀሳ ሁሉ ሲቀሰቅስ ሰንብቶ የለምን ?

ለማንኛውም እንኳንም አወቃችሁት ፥ እንኳንም የተገለፀላችሁ!

አሁን የሚጠበቅብን ተባብረንና ተረባርበን በመታገል ፤ የዚህን አስከፊ ስርአት ፍፃሜውን ማወጅ ብቻ ነው!
3.3K views17:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-17 17:07:28 "መንግስት ነኝ!" የሚለው አካል ፥ በጥድፊያ በልዩሀይሉ ላይ የወሰደው እርምጃን ትንሽ ዘወር አድርገህ ካሰብከው ፥ ለአፍራሹ " ባሌን ጎዳሁ ብላ ፥ …!" እንዲሉት ብሂል አይነት ውጤት ያለው ሲሆን ፥ "የህልውና አደጋ ላይ ነኝ ፥ ፍትህና እኩልነት የሰፈነበት ስርአት እንዲፈጠር እታገላለሁ !" ለሚለው ኃይል ደግሞ ፥ አመራር መስጠትና አቀናጅቶ መጠቀም ከቻለ እጁ ላይ የወደቀ መልካም እድል ነው!

ለክፋት የተሰነዘረን ለመልካም አላማ ማዋል ይቻላል!
355 views14:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-16 17:16:14 ሁለት መንገዶች ብቻ አሉህ!

ያለንበትን አሳሳቢ ሁኔታ በቅጡ ተረድተህ ፤ በአማራ ህዝብ ላይ የተደቀነው የህልውና አደጋ እንዲቀለበስ ፤ በሀገራችን ፍትህና እኩልነት ብሎም ሰው በሰውነቱ የሚከበርበት ሰዋዊ ስርአት እንዲዘረጋ በመሻት የመታገል ቁርጠኝነቱ ካለህ ፤ ሁለት የትግል አማራጮች አሉህ ፦

1ኛ. የጠብመንጃ (ትጥቅ) ትግል ፦ የሚፈለገው ለውጥ የሚመጣው  በአፈሙዝ ነው!" ብለህ የምታምን ከሆነ ፥ የመታገያ ቀጠናህን መርጠህ በመያዝ ፥ ስም ያለው የትግል ድርጅት በማቋቋም ተሰባሰብ ፥ የትግልና የድጋፍ ጥሪህን አቅርብ! ባስቀመጥከው ስትራቴጂና ስልት መሠረት ትግልህን አጠናክረህ ግፋ!

2ኛ. ፖለቲካዊና የሀሳብ ትግል - በተጣበበው የሀገሪቱ የመድብለ ፓርቲ ስርአት ውስጥም ቢሆን ፥ የጠራ ግብና አላማ ይዤ   ፥ እስከ ህዝባዊ እምቢተኝነት በዘለቀ የሰላማዊ ትግል ስልት በመጓዝ የታለመውን ሀገራዊ ለውጥ አመጣለሁ!" ብለህ ያመንክም ፥ ጥቃቅን ልዩነቶችህንና ውስጣዊ ሽኩቻህን ወደጎን ትተህ በአንድነት በመሰባሰብ ፤ እርስበርስህ ተከባብረህ ፥ ተደማምጠህ ፣ ተቻችለህና የማይናወጥ ቁርጠኝነትን የተላበሰ የፖለቲካ ማህበረሰብ በመገንባት ከጊዜው ጋር የሚመጥን ትግል ለማድረግ ሳታመነታ ተነሳ! በየዘርፉ የሚጠበቅብህን ሁሉ ሳትሰስት ለማበርከት መንገዱን አሁኑ "ሀ" ብለህ ጀምር!

በሁሉም ዘርፍ ለተነሳህበት አላማ መሳካት እስከህይወት መስዋትነት ለመክፈል ከራስህ ጋር ቃል ኪዳን የገባህና ፥ የግል መሻትህን ትተህ ራስህን ለአማራ ህዝብ ትግል አሳልፈህ የሰጠህ ሆነህ ተገኝ! በየመክሊትህና ማድረግ በምትችለው ልክ የሚጠበቅብህን ተወጣ!

3ኛው አማራጭህ ፥ አላፊ አግዳሚው እንደሠፌድ ቆሎ የሚዘግነው ፥ መከራና ግፉ እጣፋንታው የሆነ ብሎም አንገት ደፍቶ እየገበረ የሚኖር ማህበረሰብ መሆንህን አምነህ በባርነት መንገድ መጓዝ ብቻ ነው!

ፕ/ር ምንዳርአለው ዘውዴ "ለነፃነት የሰሰትካትን ነፍስ ፥ ተገደህ ለባርነት እንድትከፍላት ትገደዳለህ!"  እንዳሉት..!

ነፃነት ከሰማይ እንደሚወርድ መና ተቀምጦ መጠበቅ ፥ ሞኝነት ነው! ነፃነት ነፃ አይደለችም!

ይኸው ነው!
3.6K viewsedited  14:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ