Get Mystery Box with random crypto!

ሁለት መንገዶች ብቻ አሉህ! ያለንበትን አሳሳቢ ሁኔታ በቅጡ ተረድተህ ፤ በአማራ ህዝብ ላይ የተደ | ዘሪሁን ገሠሠ

ሁለት መንገዶች ብቻ አሉህ!

ያለንበትን አሳሳቢ ሁኔታ በቅጡ ተረድተህ ፤ በአማራ ህዝብ ላይ የተደቀነው የህልውና አደጋ እንዲቀለበስ ፤ በሀገራችን ፍትህና እኩልነት ብሎም ሰው በሰውነቱ የሚከበርበት ሰዋዊ ስርአት እንዲዘረጋ በመሻት የመታገል ቁርጠኝነቱ ካለህ ፤ ሁለት የትግል አማራጮች አሉህ ፦

1ኛ. የጠብመንጃ (ትጥቅ) ትግል ፦ የሚፈለገው ለውጥ የሚመጣው  በአፈሙዝ ነው!" ብለህ የምታምን ከሆነ ፥ የመታገያ ቀጠናህን መርጠህ በመያዝ ፥ ስም ያለው የትግል ድርጅት በማቋቋም ተሰባሰብ ፥ የትግልና የድጋፍ ጥሪህን አቅርብ! ባስቀመጥከው ስትራቴጂና ስልት መሠረት ትግልህን አጠናክረህ ግፋ!

2ኛ. ፖለቲካዊና የሀሳብ ትግል - በተጣበበው የሀገሪቱ የመድብለ ፓርቲ ስርአት ውስጥም ቢሆን ፥ የጠራ ግብና አላማ ይዤ   ፥ እስከ ህዝባዊ እምቢተኝነት በዘለቀ የሰላማዊ ትግል ስልት በመጓዝ የታለመውን ሀገራዊ ለውጥ አመጣለሁ!" ብለህ ያመንክም ፥ ጥቃቅን ልዩነቶችህንና ውስጣዊ ሽኩቻህን ወደጎን ትተህ በአንድነት በመሰባሰብ ፤ እርስበርስህ ተከባብረህ ፥ ተደማምጠህ ፣ ተቻችለህና የማይናወጥ ቁርጠኝነትን የተላበሰ የፖለቲካ ማህበረሰብ በመገንባት ከጊዜው ጋር የሚመጥን ትግል ለማድረግ ሳታመነታ ተነሳ! በየዘርፉ የሚጠበቅብህን ሁሉ ሳትሰስት ለማበርከት መንገዱን አሁኑ "ሀ" ብለህ ጀምር!

በሁሉም ዘርፍ ለተነሳህበት አላማ መሳካት እስከህይወት መስዋትነት ለመክፈል ከራስህ ጋር ቃል ኪዳን የገባህና ፥ የግል መሻትህን ትተህ ራስህን ለአማራ ህዝብ ትግል አሳልፈህ የሰጠህ ሆነህ ተገኝ! በየመክሊትህና ማድረግ በምትችለው ልክ የሚጠበቅብህን ተወጣ!

3ኛው አማራጭህ ፥ አላፊ አግዳሚው እንደሠፌድ ቆሎ የሚዘግነው ፥ መከራና ግፉ እጣፋንታው የሆነ ብሎም አንገት ደፍቶ እየገበረ የሚኖር ማህበረሰብ መሆንህን አምነህ በባርነት መንገድ መጓዝ ብቻ ነው!

ፕ/ር ምንዳርአለው ዘውዴ "ለነፃነት የሰሰትካትን ነፍስ ፥ ተገደህ ለባርነት እንድትከፍላት ትገደዳለህ!"  እንዳሉት..!

ነፃነት ከሰማይ እንደሚወርድ መና ተቀምጦ መጠበቅ ፥ ሞኝነት ነው! ነፃነት ነፃ አይደለችም!

ይኸው ነው!