Get Mystery Box with random crypto!

እነ ብርሃኑ ጁላ በክፉ የማያነሱት አሸባሪ! //በጋዜጠኛ - ጌታቸው ሽፈራው// በፎቶ የምትመለ | ዘሪሁን ገሠሠ

እነ ብርሃኑ ጁላ በክፉ የማያነሱት አሸባሪ!

//በጋዜጠኛ - ጌታቸው ሽፈራው//

በፎቶ የምትመለከቱት የከሚሴው "ሸኔ" ነው። የዚህ ቡድን መሪ ትህነግን ከሚሴ ላይ ተቀብሎ ሰራዊቱን የወጋ ነው። በድምፀ ወያነ ቲቪ ዜና የቀረበው የቡድኑ መሪ ከጦርነቱ ቀደም ብሎ በሰራው ወንጀል ደብረብርሃን ላይ ታስሮ ነበር። የኦሮሚያ ብልፅግና መንገድ በክልሉ ፖሊስ አዘግቶ ህዝብ ወደ አዲስ አበባ እንዳያልፍ አድርጎ ነው ያስፈታው።

ከዚህ በኋላ የኦሮሚያ ብልፅግና አጀንዳ ሲፈልግ ይህ ቡድን አጣዬንና አካባቢውን እንዲያጠቃ ያደርገዋል። ሰሞኑን ልዩ ኃይሎችንና ንፁሃንን ያጠቃው ይህ ቡድን ነው። ይህ ቡድን ትጥቅ አልፈታም። እንዲፈታም አይፈለግም። ህዝብና ሰራዊት ሲያጠቃም እነ ብርሃኑ ጁላ ስሙን አያነሱም። በሀሰት ፋኖ ልዩ ኃይል የመታ አስመስለው ሲያቀርቡ ይህ ቡድን በቀደሞ ከሚሴ ላይ የፈፀመውን ዘግናኝ ጥቃት ግን አይናገሩም። ምክንያቱም አጀንዳ ማስፈፀሚያቸው ነው።

በነገራችን ላይ ባለፈው እነ ምሬ ጋር ሰላም የተፈጠረው በአካባቢ ሽማግሌዎችና በቀጠናው ባሉ የሰራዊት መሪዎች እንጅ እነ ብርሃኑማ ችግሩ እንዲፈታ አይፈልጉም። በቀጣይም ሰበብ እየፈለጉ ችግር ይፈጥራሉ። በአማራው ላይ ችግር ሲፈጥሩ ግን ከሚሴ ያለውን አሸባሪ በክፉ ስሙን ማንሳት አይፈልጉም።