አቶ ብርሀኑ ጁላ ፥ ረዘም ባለው ጥላቻ ፥ እብሪት ፣ ማንአለብኝ ባይነት ፣ ፍረጃና ስድብ ብቻ በተስተዋለበት የትናንቱ መግለጫቸው ፦ የአማራ ብልፅግናን > ብለው ለሁለት ከፈሉ፡፡ ፋኖን ፅንፈኛና ፅንፈኛ ያልሆነ >> በማለት በተመሳሳይ በሁለት ጎራ መደቡ፡፡ ቀጠሉና " ልዩ ሀይሉ ለምን ተነካ !" ሲል ለክብሩ በይፋ ለትግል የተነሳውን ፋኖ ደግሞ > ሲሉ በመፈረጅ ፤ አስነዋሪና ይሉኝታቢስነት በተንፀባረቀበት መልኩ ፦ የእርስበርስ መከፋፈልን ለመፍጠር ብሎም አንዱን በአንዱ ላይ ለማስነሳት ከፍተኛ ጥረት አድርገዋል፡፡ ታዲያ ይህን ሠው "ይሉኝታ ቢስ የሴራ ፖለቲከኛ" እንጂ የማዕረግ ስሙን አስቀድሞ "የኢትዮጵያ የጦር ሀይሎች ኤታማዦር ሹም " ብሎ መግለፅ ይቻላልን ? በነገራችን ላይ ይሄ በነውር የተሞላው መግለጫ ፤ ቀጣዩን ሁኔታ ፍንትው አድርጎ የሚያሳይ የጥላቻ ፖለቲካውን የወደፊት አቅጣጫ አመላካች እንጂ በቀላሉ የሚታለፍ ጉዳይ አይሆንም! 4.2K viewsedited 12:10