Get Mystery Box with random crypto!

'በቃ!' ብለን ፤ መሸቀጫ ሱቆቻቸውንና መደበቂያ ዋሻዎቻቸውን ልንዘጋባቸው ይገባል! በስንፍናቸ | ዘሪሁን ገሠሠ

"በቃ!" ብለን ፤ መሸቀጫ ሱቆቻቸውንና መደበቂያ ዋሻዎቻቸውን ልንዘጋባቸው ይገባል!

በስንፍናቸውና ሀገር መምራት ባለመቻላቸው ትችት ሲሰነዘርባቸው " የኦሮሞ ጥላቻ ነው!" እያሉ ፥ ሲያሻቸው የኃይማኖት ካባ ደርበው " ጠቅላይ ሚኒስቴሩን መተቸት ፕሮቴስታንት ጠልነት ነው!" የሚል ለክ/ዘመኑ የማይመጥን ኃላቀር መከራከሪያ እያቀረቡ ፥ ሌላው ቀርቶ " የሚሰነዘርብን ተቃውሞ የአህመድ ልጅ አይመራንም የሚል ነው!" የሚል አስነዋሪና የድንቁርና ማሳያ የሆነ ብሎም በብዘሀ ማንነት ፣ ሀይማኖትና ባህል የተገነባችውን ኢትዮጵያ ወደእልቂት የሚያመራ አመክንዮ እያቀረቡ ደሀውን ህዝብ ከፋፍለው መደበቂያ ዋሻ በማድረግ በቅጥፈት እያደናገሩ ዛሬም የህዝብን ስልጣን ተቆናጠው በቁልቁለት መንገዱ እየተጓዙ ይገኛሉ !

ከእንግዲህ ግን ይህ ህዝብ ፥ የተሻለ ነገውን ፣ ሰላምና አብሮነቱን ብሎም ፍትህና ርትእ የሰፈነባትን ኢትዮጵያ የሚሻ ከሆነ " በቃ!" የሚልበት ጊዜው አሁን ነው! ከዚህ በላይ የምንሸከመው መከራና ግፍ ሊኖር አይገባም !

ታላቁ የኦሮሞ ህዝብ በስሙ ለሚነግዱ ፤ በተግባር ከራሳቸው የዘረፋ ኔትወርክ ውጭ አንዳችም ለማይፈይዱለት ብሎም የአብሮነት እሴቱን ሸርሽረው ከሌሎች ኢትዮጵያውያን ወንድም ህዝቦች ጋር ለሚያቃቅሩት ዘረኞች ፣ ሰነፎችና ዘራፊዎች መደበቂያ ዋሻ ሊሆን አይገባም!

ኃይማኖቶችም የግል አምልኮና የዘላለማዊው ህይወት መጠጊያ ቤቶች እንጂ የዘረኛ የፖለቲካ ቡድኖች መሸቀጫ ሱቅ እንዲሁም መደበቂያ ዋሻ መሆናቸው ሊያከትም ይገባል !