በትክክልም አላማና ግብ ያለው ሰላማዊ ትግል የምታደርግ ከሆነ ከእነዚህ 5 ነገሮች ተጠንቀቅ ፦ ☞ የፖለቲካ ቡድንን (ባለስልጣንን) እንጂ በፍፁም ህዝብን እንደህዝብ አትፈርጅ ፥ አትስደብ ፥ አታጥላላ! ☞ ትችትና አስተያየትህ የግለሰቡን (የፖለቲካ ቡድኑን) እኩይ ተግባር መሠረት ያደረገ እንጂ ማንነቱን መገለጫ ከማድረግ ተቆጠብ ☞ በፍፁም ሀይማኖትና ፖለቲካን ከመቀላቀል ተቆጠብ! ☞ ትግልህ ፍትህና እኩልነት እንዲሰፍን ማድረግ እንጂ በአንተ ላይ የደረሰውን በሌሎች ላይ ለማድረስ አለመሆኑን አስረግጠህ እመን! በቀለኝነትንም አታንፀባርቅ! ☞ ተግባቦትህ ሁሉ ወዳጅ ማብዛት ላይ እንጂ ጠላትን በሚያበዛ መልኩ አይሁን! በዚህ መልኩ ስትሄድ ሩቅ ትጓዛለህ ፤ የሚረዱህን ታበዛለህ ፥ አላማና ግብህ በሁሉም ይታወቃል ፤ እወክለዋለሁ ለምትለውም ህዝብ የተቀላጠፈ ለውጥ እንዲመጣ ማድረግ ትችላለህ! መልካም ቀን! 2.3K views12:15