Get Mystery Box with random crypto!

መንግሥት ከእስራኤል የገዛውን UFED የተሰኘ የስለላ ቴክኖሎጂ ለሰብዓዊ መብት ጥሰት እየተጠቀመበት | ዘሪሁን ገሠሠ

መንግሥት ከእስራኤል የገዛውን UFED የተሰኘ የስለላ ቴክኖሎጂ ለሰብዓዊ መብት ጥሰት እየተጠቀመበት ይገኛል!

የኢትዮጵያ መንግሥት እኤአ በ2021 NASDAQ ከተሰኘው Cellebrite የስለላ ቴክኖሎጂዎችን የሚያመርት ተቋም የገዛውና UFED የሚባል ቴክኖሎጂ ፥ በአሁኑ ሠአት በስፋት ጥቅም ላይ እየዋለ ይገኛል፡፡ የበርካታ አክቲቪስቶች ፥ ፖለቲከኞችና ተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች መረጃ እየተበረበረ መሆኑንም ከምንጮቻችን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ይህ UFED የተሰኘው የሴሌብራይት ቴክኖሎጂ ፥ በይለፍ ቃል የተጠበቁ ስልኮችን ለመጥለፍ ፥ የሚዲያ ፋይሎችን ፥ የጽሑፍ መልዕክቶችን ፣ የጥሪ ታሪኮችን ፣ የደወል ታሪኮችን እና ሌሎችንም ጨምሮ በመሳሪያው ላይ የተመዘገቡትን ግለሰቦች ሁሉንም መረጃዎች ዳውንሎድ አድርጎ ለመበርበር የሚያስችል ነው፡፡

አለምአቀፍ የሰብአዊ መብት ተቋማት እስራኤል ይህን ቴክኖሎጂ ለኢትዮጵያ መንግሥት በመስጠት ዜጎች ላይ አረመኔያዊ የሰብዓዊ መብት ጥሰት እንዲፈፀም ፥ መረጃዎቻቸው እንዲበረበሩ ብሎም ለእስርና ለግድያ እንዲዳረጉ ተባባሪ ሆናለች በማለት በተደጋጋሚ አቤቱታ ሲያቀርቡ እንደነበር የሚታወስ ነው፡፡