Get Mystery Box with random crypto!

ትግላችን 3ተኛውን አማራጭ  ፖለቲካዊ መንገድ ለመክፈት መሆን አለበት! እርግጥ ነው ' ትህነግ/ህ | ዘሪሁን ገሠሠ

ትግላችን 3ተኛውን አማራጭ  ፖለቲካዊ መንገድ ለመክፈት መሆን አለበት!

እርግጥ ነው " ትህነግ/ህወሓት አሸባሪ ፥ ወንጀለኛና ለፍርድ መቅረብ ያለበት ድርጅት ነው"  ብዬ አምናለሁ፡፡ ነገርግን በአሁኑ ሠአት የዚች ሀገር የህልውና ስጋት "መንግስት ነኝ!" የሚለው የአብይ ስርአት እንጂ ህወሓት ነው ብዬ አላምንም! ይህን ስርአት በዚህ ደረጃ ያነቀዘው አንደኛው ምክንያትም   ፥ 5 አመታትን ሙሉ  24/7 "ህወሓት ፥ የህወሓት እጅ..!" ስንል መሰንበታችን ነው!

ኢትዮጵያ ምንአልባት የመዳን ተስፋ የሚኖራት የትግራይ እና የአማራ ህዝቦች ፖለቲከኞች ሶስተኛውን መንገድ መርጠው በጋራ ከተጓዙበት ብቻ ነው!

ይህ አሰላለፍ በዚሁ ከቀጠለና የዘይትና የውሃ አይነት ተፈጥሮ ያላቸው ሁለቱ ኃይሎች "በአማራ ጥላቻ ላይ ብቻ" ተስማምተው በሀገሪቱ ፖለቲካ ውስጥ የሚቀጥሉ ከሆነ የጊዜ ጉዳይ እንጂ ሊመሠረት የሚችለው ያ "አልሸሹም ዘወር አሉ" የሚሆነውና ያሳለፍነው የ27 አመቱ ስርአት ነው ፡፡ አለያም ደግሞ የፖለቲካ ብልሽቱ እዚያም ሳይደርስ ሀገሪቱን በማፍረስ ይጠናቀቃል!

ይህ አማራጭ ምርጫ የሚሆነው አሁን ያለው ፋሽስታዊ ስርአት ሌሎች አማራጮችን ሁሉ ለመስማትም ሆነ ለመከተል ፍፁም ፈቃደኛ ባለመሆኑ ነው!