Get Mystery Box with random crypto!

ገፀ-ባህሪያቶቹ...! ' ...ጁንታዎቹ ከፈለጉኮ ራሳቸው ያስቀመጡት ህግ አለ፡፡ በዚያ መሠረት ጥ | ዘሪሁን ገሠሠ

ገፀ-ባህሪያቶቹ...!

" ...ጁንታዎቹ ከፈለጉኮ ራሳቸው ያስቀመጡት ህግ አለ፡፡ በዚያ መሠረት ጥርግ ማለት ይችላሉ! " ያለችው " ..አዲስአበባ ላይ ፈቅደን ብናኖራቸው ፤ ... ሲጨፍሩብን ያድራሉ!" ስትል አዲስአበባን የግሏ ርስት አድርጋ በአደባባይ ስትውረገረግ የነበረችው ከንቲባ አዳነች አቤቤ ፥ መቀሌ መሄዷ ችግር አይደለም፡፡

የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ፥ " ..ጁንታው መሸበት..!" ሲሉ ኖረው ፥ "እንደምን አደርክ ጁንታው?" ለማለት ፥ ማልደው መቀሌ መገኘታቸውም ስህተት ላይሆን ይችላል፡፡

ጌታቸው ረዳም " ..ዳፍንታሞች!" ሲላቸው የከረሙትን ብአዴኖች መሪ ፥ እንደፋርማሲ እባብ አንገቱ ስር ጥምጥም ብሎ ሲተውን መመልከታችንም ፥ በአለም ላይ ያልተለመደ ነገር አይደለም፡፡

" ..ከህወሓት ጋር አብሮ መቀመጥ ሁሉ ሀፂያት ነው!" ሲል የከረመው ሽሜ አብዲሳ ፥ የጌታቸው ረዳን አንገት ላይ ተጠምጥሞ ሮማንቲክ አስተቃቀፍ ማሳየቱም የሚኮነን ላይሆን ይችላል፡፡

" ..ህወሓት የተበተነ ዱቄት ሆኗል ፥ የተበተነ ዱቄት ደግሞ ተሰብስቦ ተቦክቶ ሸገር ዳቦ አይሆንም! " ሲል የከረመው የፒፒ ካድሬ ፥ ህወሓትን ሊጠይቅ ዱቄት አስፈጭቶ "እንገፍ እንገፍ" ማለቱም ሊገርመን የማይገባ ጉዳይ ነው፡፡

ችግሩ ፦

ተጨባጭና ችግር ፈቺ ፖለቲካ በመስራት እንጂ ገፀባህሪያትን ተከፋፍለው እየተንሸራሸሩ ፥ ፖለቲካዊ ተውኔት በመተወናቸው "ዘላቂ ሰላም እናረጋግጣለን!" እያሉ የሚያቅራሩት ነገር ፥ ራሳቸውን ከማታለል በዘለለ አንዳች ፋይዳ የሌለው "እንዘጭ እንዘጭ" መሆኑ ነው!



አሁን የት ይገኛል 'ሰላም ሰላም' ቢሉት ደርሶ በለበጣ
ማስመሰል ድካም ነው ፥ የምሩ ሲመጣ!