Get Mystery Box with random crypto!

የመፍትሔ አካል ለመሆን ካሰብን ....! መደራደርም ሆነ መገዳደር የቻሉት ብሎም 'አሸናፊ ሆነናል | ዘሪሁን ገሠሠ

የመፍትሔ አካል ለመሆን ካሰብን ....!

መደራደርም ሆነ መገዳደር የቻሉት ብሎም "አሸናፊ ሆነናል!" ለማለት የበቁት የፖለቲካ ኃይሎች ፤ በጋራ ኮዛቸው ላይ ተግባብተው ፥ ውስጣዊ ችግሮቻቸውን አቻችለውና ፈትተው ፤ ከጀርባቸው ሀብትና ንብረቱን ፥ ጊዜና እውቀቱን እንዲሁም የራሱንና የልጆቹን ህይወት ሳይቀር ደስ እያለው የሚያዋጣ የፖለቲካ ማህበረሰብ ገንብተው ስላስከተሉ ብቻ ነው! ሌላ ሚስጥር የለውም!

"የፓርቲ አባል ሆነህ ታገል!" እንኳ ስትለው << አበል አለው ወይ ? ፤ ስንት ካሬ ቦታ ይሰጠኛል ? ፥ በጀት ከሌለው አልሰማህም ፤ ሹመትስ አገኛለሁ? " ወዘተረፈ እያለ ቅድመ ሁኔታ የሚደረድር ፥ ነፃነቱ ከሰማይ እንደሚወርድ መና በነፃ እንዲዘምብለት የሚሻ ፥ የሌሎችን ጥንካሬና ቁርጠኝነት በሂሳብ ዋጋና በጉርሻ ተመን የሚተምን ፤ "ተማርኩ" የሚልን ፥ እልፍና አዕላፍ አስመሳይ ደንቆሮ ሁሉ ፥ ጠፍጥፈህ ሳታስተካክልና ማህበረሰባዊ የአመለካከት ለውጥ ሳታመጣ ፥ ወደፊት ስንዝር መራመድ ቅዠት ነው!

እስኪ እያንዳንዳችን እጆቻችንን ለ5 ደቂቃ ከኪይቦርድ ላይ አንስተን "ለህዝባዊ ትግሉ ያለኝ ቁርጠኝነትና መስዋዕትነት እስከምን ድረስ ነው ? ምንስ ሚና አበረከትኩ ? ምንስ ደካማ ጎን አለኝ? >> ብለን እንጠይቅ!

በመቀጠልም ፦ ከምናገኘው የራሳችን ግምገማ ተነስተን ራሳችንን እናርም ፥ እናስተካክል!

ያኔ ለሁሉም ነገሮች አመቺና በቀላሉ የሚደራጅና ለትግል የሚዘጋጅ ትውልድ እንሆናለን!