Get Mystery Box with random crypto!

ግብፅ በይፋ ከአልቡርሃኒ ጦር ጎን በመሰለፍ ጦርነቱን መቀላቀሏን አምናለች! CGTN AFRICA | ዘሪሁን ገሠሠ

ግብፅ በይፋ ከአልቡርሃኒ ጦር ጎን በመሰለፍ ጦርነቱን መቀላቀሏን አምናለች!

CGTN AFRICA ከደቂቃዎች በፊት የግብፁን ወታደራዊ ቃል አቀባይ ኮሎኔል ጋህሪብ አብደል ሀፊዝን ጠቅሶ ፤ << Egypt’s military is coordinating with relevant Sudanese authorities to guarantee the safety of Egyptian forces. >> በማለት ፤ ግብፅ በሱዳን ላሉት ሀይሎቿ ስትል ከአልቡርሃኒ ጦር ጋር አብራ እንደምትሰራ መግለፇን ዘግቧል፡፡

በጀነራል ዳጋሎ (ሄሜቲ) የሚመራው ጦር ፤ በሱዳን የሚገኘውን የግብፅ ጦር ወታደራዊ ካምፕ ከ17 ሩሲያ ሰራሽ su25 ጀትና 179 ታንክ ጋር መማረኩን ይፋ ማድረጉ የሚታወስ ነው፡፡

ኢጋድ ከሰአታት በፊት ባወጣው መግለጫ << የሱዳን ጉዳይ ከሀገሪቱ አልፎ ለቀጠናው አደገኛ ሁኔታ የማፈጥር ነው! >> ሲል ማሳሰቡ ይታወቃል፡፡

በሱዳን ያለው ሁኔታ ምሽቱንም ተባብሶ ቀጥሏል፡፡ የተለያዩ የሱዳን ግዛቶች በከባባድ ተኩሶች እየተናጡ ይገኛሉ!