Get Mystery Box with random crypto!

የአልቡርሃን ማስጠንቀቂያና የግብፅ ወታደራዊ ኃይል መማረክ! የዳጋሎ (ሄሜቲ) ሃይል ቤተ-መንግስቱ | ዘሪሁን ገሠሠ

የአልቡርሃን ማስጠንቀቂያና የግብፅ ወታደራዊ ኃይል መማረክ!

የዳጋሎ (ሄሜቲ) ሃይል ቤተ-መንግስቱን ጨምሮ ዋና ዋና ተቋማትን የተነጠቁት ፥ ጀነራል አልቡርሃን << የፈጥኖ ደራሽ ሃይሉ ከካርቱም ካልወጣ ተጨማሪ ጦር ከክልሎች እናስገባለን ! >> ሲሉ ማስጠንቀቂ መሠል መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

ጀነራል ሃምዳን ዳጋሎ በበኩላቸው “ቀድመን የተወጋነው እኛ ነን ፤ አልቡርሃንን ለፍትህ ሳናቀርብ ትግላችን አናቆምም!" ሲሉ በአር ኤስ ኤፍ የትዊተር ገጽ ላይ ገልፀዋል!
በጀነራል ዳጋሎ (ሄሜቲ) የሚመራው ጦር ፤ መቀመጫውን ሱዳን ያደረገው የግብፅ ጦር ወታደራዊ ካምፕ ከ17 ሩሲያ ሰራሽ su25 ጀትና 179 ታንክ ጋር መማረኩን ይፋ ካደረገ ሰአታት ተቆጥረዋል!

ግጭቱ በመላው ሱዳን በፍጥነት እየተዛመተ ሲሆን ኢጋድን ጨምሮ በርካታ የአለም ሀገራት ሁኔታው እንዳሳሰባቸው እየገለፁ ይገኛሉ!