Get Mystery Box with random crypto!

ይህ የኛ መሠረታዊ አጀንዳ ሊሆን አይችልም! አንድ ወዳጄ > የሚል መረጃ አድርሶኛል! ሲጀመር | ዘሪሁን ገሠሠ

ይህ የኛ መሠረታዊ አጀንዳ ሊሆን አይችልም!

አንድ ወዳጄ << የኦሮሚያ ልዩ ሀይል የምርጫ ፎርም ተዘጋጅቶለት እየሞላ ይገኛል፡፡ መቀላቀል የሚፈልጉትን ተቋማት ዝርዝር ከያዘው ከዚህ ቅፅ ውስጥ 'የአዲስአበባ ፖሊስ' የሚል ምርጫ መኖሩ ግርምትን ፈጥሮብኛል! ለሌሎቹም ልዩ ሀይሎች ነው ወይስ ለኦሮሚያ ልዩ ሀይል ብቻ? >> የሚል መረጃ አድርሶኛል!

ሲጀመር የኦሮሚያም ይሁን የሌሎች ክልሎች ልዩ ሀይሎች መፍረስ አለመፍረስ ጥያቄአችን አልነበረም፡፡ አይሆንምም፡፡ "የአማራ ልዩ ሀይል መፍረስ የለበትም !" ብለን ስንሞግትም ፥ አንድም የመርህና የአሰራር ቅደም ተከተሎችን ጠቅሰን ሁለትም የአማራ ህዝብ ያለበትን ነባራዊ ሁኔታና በሀገሪቱ አስቻይ ሁኔታዎች አለመኖራቸውን በተጨባጭ መረጃና ማስረጃ ይዘን ነው! ጥያቄአችን የጠራና ግልፅ አመክንዮ ያለው ነው!

ከዚያ ባሻገር የኦሮሚያ ልዩ ሀይል ፈረሰም አልፈረሰም ፥ የት ገባም የት ወጣም የእኛ መሠረታዊ አጀንዳ ሊሆን አይችልም !

ወዳጆች! መረጃውን ያጋራኃችሁ ፥ ምናልባት ይፋ ተደርጎ ስታውቁት "የተለየ አጀንዳ " እንዳታረጉት ከወዲሁ ለመጠቆም ያህል ነው!