Get Mystery Box with random crypto!

ዘሪሁን ገሠሠ

የቴሌግራም ቻናል አርማ zerihunkocha — ዘሪሁን ገሠሠ
የቴሌግራም ቻናል አርማ zerihunkocha — ዘሪሁን ገሠሠ
የሰርጥ አድራሻ: @zerihunkocha
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 13.77K
የሰርጥ መግለጫ

በመረጃ እንቀራረብ! በመረጃ እንተሳሰር!

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 11

2023-04-12 01:50:02
ለህዝባዊ እንቢተኝነት ተዘጋጁ

አክቲቪስትና አርቲስት ታማኝ በየነ

"ከህወሓት የኮረጃችሁት በበላይነት ደፍጥጦ መግዛት የሚባል አስተሳሰብ አያዋጣም። ቤንሻንጉል፣ ጋምቤላ፣ ሶማሊ፣ ሲዳማ፣ አማራ ጋር መሬት አለን እያላችሁ ከእያንዳንዱ ክልል ጋር የመሬት ጥያቄ እያነሳችሁ በጉልበት ሁሉንም እንገዛለን  የሚባል አስተሳሰብ አያዋጣም። ከህወሓት ተማሩ። የተወሰነ ጊዜ በስካር መንፈስ ልታደርጉት ትትላላችሁ። ነገ ለሁላችንም ልጆች የማትሆን ኢትዮጵያ ነው በትናችሁ የምትሄዱት።

ኢትዮጵያውያን  እንቢይ በሉ። አብሩ።ተነጋገሩ። መብታችሁን ለማስከበር አንድ ላይ ቁሙ። ለህዝባዊ እንቢተኝነት ተዘጋጁ።

መንግስት ውሳኔውን ቀልብሶ፣ ሁኔታዎችን በሰላማዊ መንገድ ነገሩ እንዲፈታ ካላደረገ የሚመጣው ጦስ በታሪክ የሚያስጠይቀው ነው።"
3.2K views22:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-11 20:49:05
የመከላከያ ሠራዊቱ ዛሬ በኮምቦልቻ ባልታጠቁ ሰላማዊ ሰልፈኞች ላይ በከፈተው ጥቃት በከፍተኛ ሁኔታ ከቆሰሉት መካከል ይህ ወንድማችን ይገኝበታል!
4.1K views17:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-11 19:22:00 መረጃ!

በአንቶኖቭና በተሽከርካሪዎች በመታገዝ የተጓጓዘው   ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሰራዊት ኮምቦልቻ ደርሷል !
4.4K views16:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-11 17:58:04
4.7K views14:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-11 17:57:37 4) የመከላከያ ሰራዊት አባላት በሕዝባቸውና የቁርጥ ቀን ባለውለታቸው በሆነው ልዩ ኃይል ላይ የሚወስዱትን እርምጃ እንዲያቆሙና ወደ ካምፓቸው እንዲመለሱ፤ በተለይም የአማራ ልዩ ኃይል አባላት የአገር አንድነት የመጨረሻ ምሽግ ከሆነው የመከላከያ ኃይል ጋር ወደ ግጭት የሚያስገቡ ጉዳዮችን በማስወገድ ተረጋግተውና አንድነታቸውን ጠብቀው በካምፓቸው እንዲሰበሰቡ፤ የአማራ ሕዝብ ለልዩ ኃይሉ ተገቢውን ድጋፍ ሁሉ እንዲያደርግ፤ መላው ኢትዮጵያውያንም የብልጽግና ፓርቲ የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴን ኢሕገመንግስታዊ አገር አፍራሽ እርምጃ በአንድነት እንድታወግዙ ጥሪያቸንን እናቀርባለን።

5) የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ልኂቃን፣ ሚዲያዎችና የማኅበረሰብ አንቂዎች ግጭት አባባሽ ከሆኑ ጉዳዮች በመታቀብ የገዥውን ፓርቲ ፋሽስታዊ እርምጃዎች በመርሕና ሕግ በመመርኮዝ በጽናት ትታገሉ ዘንድ ከአደራ ጭምር ጥሪያችንን እናቀርባለን።

6) የዓለምአቀፍና የዲፕሎማቲክ ማኅበረሰቡ የብልጽግና ፓርቲ ከገባበት አገርን የማፍረስ እኩይ ተልእኮው በመታቀብ ሕግ አክብሮ እንዲንቀሳቀስ፤ በየጊዜው ግጭቶችን እየጠመቀ በንፁኃን ላይ የሚያደርሰውን የዘር ፍጅትና ማንነት ተኮር ጅምላ ጭፍጨፋዎች እንዲያቆም፤ የሰብአዊ መብቶችን አክብሮ የመንቀሳቀስ ዓለምአቀፋዊ መርሆ እንዲያከብር አስፈላጊ እርምጃዎችን ሁሉ በመውሰድ ታሪካዊ ኃላፊነታችሁን ትወጡ ዘንድ ጥሪ እናቀርባለን። ይህ የማይሆን ከሆነ ግን ዓለምአቀፍ ማኅበረሰቡ በሩዋንዳ የዘር ፍጅት የፈፀመውን ታሪካዊ ስህተት እንደሚደግም ማስጠንቀቅ እንፈልጋለን።

ሚያዝያ 03፣2015 ዓ/ም
አዲስ አበባ፥ ሸዋ፣ ኢትዮጵያ
4.5K views14:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-11 17:57:37 የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ የክልል ልዩ ኃይሎች እንዲፈርሱ ያሳለፈውን ውሳኔ በፌዴራል መንግስት ስምና በመከላከያ ሰራዊት የኃይል እርምጃ ለማስፈፀም የሚያደርገውን ፋሽስታዊ እርምጃ ሊያቆም ይገባል፤
*
ኢትዮጵያና ሕዝቦቿ ባለፉት አስርት ዓመታት በተለይም ባለፉት አምስት ዓመታተ እጅግ አስከፊ በሆነ ርሀብና ጠኔ፣ ስደትና መፈናቀል፣ ማንነት ተኮር ጅምላ ግድያዎችና የዘር ፍጅቶች እንዲሁም በማያባሩ ግጭቶችና የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ውስጥ ይገኛሉ። ሕዝባዊ የፍትኅ፣ የእኩልነት፣ የነፃነትና የዴሞክራሲ ጥያቄዎች ሲበረቱበት የኢሕአዴግ አገዛዝ የሄደባቸውን የጥፋትና አገር የማፍረስ እኩይ ስምሪቶች የመንፈስ ግብር ወራሹ የሆነው ገዥው የብልጽግና ፓርቲም ዓይነትና መጠናቸውን አሳድጎ ቀጥሎባቸዋል። ፓርቲውና የፓርቲው አመራሮች በአመራር ስልታቸውና ብቃታቸው ላይ እንደአካልና ግለሰብ የሚቀርቡባቸውን ጥያቄዎችና ትቺቶች የብሔርና ኃይማኖት ቅርጽ በመስጠት ነቀፌታዎቹ የሆነ ብሔርና ኃይማኖት ላይ የቀረቡ በማስመሰል ወደለየለት ሕዝብን በሕዝብ ላይ የሚያነሳሳ የዘር ፍጅት ቅስቀሳ ገብቷል። አገዛዙ ግጭትን እንደኅልውና ማስቀጠያ መሣሪያ እየተጠቀመበት ይገኛል።

ለአብነትም የብልጽግና ፓርቲ የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ በመጋቢት፣2015 ዓ/ም የክልል ልዩ ኃይል አደረጃጀትን በተመለከተ ያሳለፈውን ውሳኔ ተከትሎ አገራችን ከነበረችበት አንፃራዊ መረጋጋት፣ ሰላምና ተስፋ መፈንጠቅ ወደ ትርምስ፣ ስጋትና የመበተን አደጋ ገብታለች። ይህንንም ተከትሎ ለኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን በጎ እሳቤ ያላቸው ወገኖች ሁሉ ገዥው ፓርቲ የወሰነውን አስተውሎት የጎደለው ውሳኔ እንዲያጤነው ደጋግመው ቢወተውቱም ካፈርሁ አይመልሰኝ በሚመስል ጎረምሳዊ ግብር ውሳኔውን የተቹ ንቁ ዜጎችን የመንግስት የፀጥታ መዋቅሮችን በመጠቀም ወደ ማፈን ተሸጋግሯል፤ የአገር መከላከያ ሰራዊቱንም ከሕግና ሕገመንግስታዊ መርሆዎች ባፈነገጠ መልኩ በፓርቲ ጥርነፋ በማስገባት በሕዝብና የክልል መንግስት መዋቅሮች ላይ በይፋ በማዝመት በንፁኃን ላይ ግድያና አፈናዎችን በመፈፀም ላይ ይገኛል።

በዚህም በ6ኛው ዙር ምርጫ የሕዝብ ተወካዮች ምክርቤት አባል ሆነን በእንደራሴነት የተመረጥን እኛ፦
1) የተከበሩ ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ
2) የተከበሩ ክርስቲያን ታደለ
3) የተከበሩ ሙሉቀን አሰፋ
4) የተከበሩ አበባው ደሳለው እና
5) የተከበሩ ዘመነ ኃይሉ

የብልጽግና ፓርቲ፤ በመረጠን ሕዝባችን ላይ እየፈፀመ ያለውን ፋሽዝም በጽኑ እያወገዝን፤የተፈፀሙ ሕገመንግስታዊ ጥሰቶቸንና መደረግ ያለባቸውን ምክረሐሳቦች እንደሚከተለው እናቀርባለን።

1) ብልጽግና ፓርቲ እንደሌሎች የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች ሁሉ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ተመዝግቦ የሚንቀሳቀስ ሆኖ ሳለ፤ በሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴው የክልል ልዩ ኃይሎችን በተመለከተ ያስተላለፈው ውሳኔ በየትኛውም የአገሪቱ ሕግ ለፓርቲው በሥልጣንነት ያልተፈቀደ ሆኖ አግኝተነዋል። የብልጽግና ፓርቲ የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ውሳኔ ፓርቲው ሕገመንግስታዊ የመንግስትና ሕዝብ ተቋማትን እንደፓርቲው አደረጃጀት የቆጠረ፤ ለብቻው በፓርቲ ደረጃ በሕዝብና መንግስት ተቋማት ላይ አዛዥ ናዛዥ እንደሆነ አድርጎ ያቀረበ በመሆኑ ከሕግ፣ ሞራልና አሰራር አንፃር ተቀባይነት የሌለው ከመሆኑም ባሻገር በሰላማዊና ሕጋዊ መንገድ ተመዝግበው የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች የታጠቀ ኃይል ማንቀሳቀስ የማይችሉ መሆናቸውን የሚደነግገውን የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ስነምግባር የተመለከተውን አዋጅ ቁጥር 1162/2011 የተላለፈ ነው። በመሆኑም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ይኸንኑ የብልጽግና ፓርቲ የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ሕግ የጣሰ ውሳኔ በመርመር በፓርቲው ላይ ተገቢውን የሕግ እርምጃ እንዲወስድ እንጠይቃለን።

2) በኢፌዴሪ ሕገመንግስት የክልሎችን ሥልጣን በሚደነግገው አንቀጽ 52/2/ሰ ሥር «የክልሉን ፖሊስ ኃይል ያደራጃል፤ ይመራል፤ የክልሉን ሰላምና ፀጥታ ያስጠብቃል» በማለት ክልሎች የየራሳቸውን የፖሊስ ኃይል የማደራጀት ሕገመንግስታዊ መብት እንዳላቸውና አደረጃጀቱና አመራሩም በራሳቸው የሚወሰን መሆኑን በማያሻማ መልኩ ያስቀምጣል። የክልል ልዩ ኃይሎች በክልል መንግስታት ምክርቤቶች በኩል በአዋጅ የተቋቋመው የፖሊስ ኃይል አካል ሲሆኑ ተጠሪነታቸውም ለየክልሎቹ ፖሊስ ኮሚሽኖች ነው። ሰይጣን ላመሉ ከመጽሐፍ ያጣቅሳል እንዲሉ የብልጽግና ፓርቲ ክልሎች የመደበኛ ፖሊስ ብቻ ነው የተፈቀደላቸው የሚል የዓይናችሁን ጨፍኑ ላሞኛችሁ ሙግት ቢያቀርብም ቅሉ፤ እንደኃይማኖታዊ ቅዱስ መጽሐፍ በሚያመልከው የኢፌዴሪ ሕገመንግስት ውስጥ አንድም ቦታ መደበኛ ፖሊስ ብቻ ስለመፈቀዱ የሚያትት የሕግ ድንጋጌ የለውም። ይልቁንም በዚሁ ሕገመንግስት አንቀጽ 52/1 ላይ «ለፌዴራል መንግስት በተለይ ወይም ለፌዴራሉ መንግስትና ለክልሎች በጋራ በግልጽ ያልተሰጠ ሥልጣን የክልል ሥልጣን ይሆናል» የሚለው ድንጋጌ «የልዩ ኃይል ፖሊሰ» ማቋቋምን የክልሎች ልዩ መብት አድርጎ የሚያስቀምጥ ነው። የክልሎች የልዩ ኃይል አደረጃጀት ሕገመንግስታዊ አይደለም ቢባል እንኳን በአንድ ፓርቲ የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ውሳኔ ሳይሆን ባቋቋሟቸው የክልል መንግስታት በኩል የማቋቋሚያ አዋጆቻቸው ማስተካከያ እንዲደረግበት ተደርጎ የሕግ ክፍተቱ የሚታረም ሆኖ መሰል መብቶች ለክልሎች የተተው መሆናቸው ተጠየቅ የሚቀርብባቸው አይሆኑም።

3) የፌዴራል መንግስቱና የአገር መከላከያ ሰራዊት የአንድ ፓርቲ የግል ንብረቶች አለመሆናቸው እየታወቀ በተለይም በኢፌዴሪ ሕገመንግስት አንቀጽ 87 ስለመከላከያ መርሆዎች በሚያትተው ንዑስ አንቀጽ 5 «የመከላከያ ሰራዊቱ ተግባሩን ከፖለቲካ ድርጅቶች ወገናዊነት ነፃ በሆነ አኳኋን ያከናውናል» የሚለውን ድንጋጌ በመጣስ እንዲሁም የአገር መከላከያ ሰራዊት በፖሊስ ሰራዊት በተለይም በክልሎች የፖሊስ አደረጃጀት ላይ ውሳኔ ለመስጠትና ማስተካከያ ለማድረግ የሕግ ሥልጣን ሳይኖረው በመረጠን ሕዝብና በራሱ በጀት በሚያስተዳድራቸው ሕዝባዊ ተቋማቱ ላይ የታወጀው ጦርነት የለየለት ፋሽስታዊ ተግባር ሆኖ አግኝተነዋል። ጣልቃገብነቶችም በኢፌዴሪ ሕገመንግስት አንቀጽ 51/14፣ 55/16 እና 62/9 መሰረት የተከናወኑ ባለመሆናቸው ግልጽ ሕገመንግስታዊ ጥሰቶችና አገር አፍራሽ ተልእኮዎች ናቸው። የፌዴራል መንግስቱ በክልሎች ላይ በተለይም በአማራ ክልል እያደረገ ያለው ጣልቃገብነት የብልጽግና ፓርቲ በመቃብሬ ካልሆነ አልደራደርባቸውም የሚልላቸውን ፌዴራሊዝምና የኢፌዴሪ ሕገመንግስት ጭምር ገደል የከተተ ነው። በተለይም ሰራዊቱ በማናቸውም ጊዜ ለሕገመንግስቱ ተገዥ መሆን እንዳለበት የሚደነግገውን አንቀጽ 87/4 የሻረ ነው።

በብልጽግና ፓርቲ የተፈፀሙ መሰል የአገር አፍራሽነት ሕገመንግስታዊ ጥሰቶችን የሕዝብ ተወካዮች ምክርቤት፣ የፌዴሬሽን ምክርቤትና መላው ኢትዮጵያውያን በጽኑ እንድታወግዙት ጥሪያችንን እናቀርባለን። በተለይ ሕገመንግስታዊ ሥርዓትን የመጠበቅና የማስጠበቅ የሕግ ግዴታ ያለባችሁ ተቋማት አስፈላጊውን እርምጃ ሁሉ በመውሰድ የብልጽግና ፓርቲን አገር የማፍረስ እኩይ ተልእኮ ታስቆሙ ዘንድ በአጽንዖት እናሳስባለን።
4.1K views14:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-11 17:45:25 መረጃ

በግልፅ ወረራ ከፈፀሙበት ክልል ውጪ ከተራ ነዋሪ እስከ ተቋማት አመራርና ሰራተኞች በማንነታቸው እየለዩ ወደእስር ቤት የማጋዙ ዘመቻ ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡ በአዲስአበባና በዙሪያዋ ባሉ ከተሞች እስር ቤቶች ሞልተዋል፡፡

አሁን በዚህ ሠአት ደግሞ ከአየር ሀይል ውስጥ "ተፅዕኖ ይፈጥራሉ!" ያሏቸውን በማንነታቸው በመለየት ወደእስር ቤት እየወሰዷቸው ነው፡፡ ከደብረዘይት አየር ሀይል ውስጥ የተያዙት አየር ወለዶችና ኮማንዶዎች ወደሚዛን ቴፔ ጫካ ውስጥ ለማሰር እያንቀሳቀሷቸው መሆኑን ከውስጥ አዋቂ ምንጮች ለማረጋገጥ ችያለሁ፡፡

በሌላ መልኩ በርካታ ቁጥር ያለው ሰራዊት በአዋሽ ዞሮ በባቲ አድርጎ ወደወሎ እየገሰገሰ መሆኑንም ለማወቅ ተችሏል!

ይቺን ሀገር ወደምን አይነት የቀውስ አዙሪት ሊከቷት እንደደፈለጉ አላውቅም !
6.0K viewsedited  14:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-11 16:24:41
አንድም እክል ለመፍጠር የሞከረ የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር አመራርም ሆነ የፀጥታ አካል የለም!

ማለዳ የጀመረው ህዝባዊ ተቃውሞን ለመታዘብ እንደሞከርኩት ፥ ከመነሻው ጀምሮ በስርዓት እየተጓዘ ነበር፡፡ ከመሀል ከተማ እስከ ኮስፒ ድረስ ግራና ቀኝ ፀጥታ እያስከበሩ የሚታዩት የልዩ ሀይል ፣ የሚሊሻና ህዝባዊ ፖሊሶች ብቻ ነበሩ፡፡

የተቃውሞ ሰልፈኞቹ ኮስፒ ከደረሱ በኃላ ግን ከያፒ መርከዚ ካምፕ የወጡ የመከላከያ ሰራዊት አባላት በሰልፈኛው ላይ በቀጥታ እሩምታ ከፈቱ፡፡ በዚህም በርካቶች ተጎድተው በህክምና ላይ ሲሆኑ ሁለት ሰዎችም እንደሞቱ ታውቋል፡፡

ሂደቱን ወዳልተፈለገ አቅጣጫና ትርምስ የቀየረው ፥ በህዝቡ ላይ ተኩስ የከፈተው የመከላከያ ሰራዊት ብቻ ነው!

አሁንም ቢሆን ህዝቡ ጦርነትና ትርምስ ሰልችቶታል፡፡ ተጀምሮ እስኪጨረስ በመላ ሀገሪቱ ግጭትን ጠንስሶ የሚመራውና ህዝባችንን ረፍት አልባ ያደረገው ፥ "መንግስት ነኝ" የሚለው አካል ብቻ ነው፡፡ ህዝቡ ፍፁም ሀላፊነት የሚሰማውና በሰላም ወጥቶ መግባትን የሚፈልግ ነው፡፡

በየከተሞቹ ገብቶ የመሸገው የመከላከያ ሰራዊት ጊዜ ሳያጠፋ ለቆ መውጣት አለበት! ይህን አለማድረግ ነገሮችን ወደውስብስብነትና አስቸጋሪ ደረጃዎች መቀየሩ ሳይታለም የተፈታ ነው!
4.3K viewsedited  13:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-11 15:54:22
እኛም ያልነው ይህኑ ነው ፤ ደጀን ከሆንነውና አብረነው ከተሰለፍነው የመከላከያ ሰራዊት የምንጠብቀውም ይህንን እንዲል ነው!

የምዕራብ ዕዝ ዋና አዛዥ #ሌተናል_ጀኔራል_መሰለ_መሰረት (ሲዳማ) እና የ6ኛ ዕዝ ዋና አዛዥ #ሜጀር_ጀኔራል_ተስፋየ_ወልደማርያምን (ሃድያ) መጋቢት 29, 2015 ዓ.ም የሰጡት አስተያየት ፦

<< ‘የአማራ ልዩ ኃይል እንዴት ትጥቁን እንቀማው!’ በሚል የአብይ አህመድ ቡድን ባዘጋጀው ውይይት ላይ ይህ ልዩ ኃይል የሰራዊታችን ክንድ ሆኖ ታሪክ የሰራ ኃይልን በዚህ መልኩ ክብሩን በሚነካ መንገድ ትጥቅህን ፍታ ማለት ለእኔ እጅግ ይከብደኛል:: መንግስት የሰጠኝን ግዳጅ ተቀብየ በጎንደር በኩል ሰራዊት ይዥ ስዘምት ይህ ኃይል ባይኖር ኖሩ አሁን ላይ የምናየው ነገር በፍፁም አይኖርም ነበር:: ይህንን ኃይል ትጥቅ መፍታት ወይም መልሶ መደራጀት ካስፈለገ ጊዜ ወስድን ከህዝቡና ከሰራዊቱ ጋር ተመካክሮ መሆን አለበት:: ትልቅ ስህተን እንዳንሰራ ስጋት አለኝ፡፡ >> // የምዕራብ ዕዝ ዋና አዛዥ ሌተናል_ጀኔራል_መሰለ_መሰረት//

<< መንግስት የጦር ሜዳ ጀብዱ የሽለመኝ የአማራ ፋኖና ልዩ ኃይል በጋራ በሰራነው ስራ ነው:: ይህንን ልዩ ኃይል በዚህ መንገድ ትጥቅህን ፍታ ማለት ለወደፊቱ ጀግናን ማምከን ነው የሚሆነው:: እኔ ዕዜን #በድሬ_ሮቃ ግንባር ይዠ ስዋጋ የአማራ ፋኖና ልዩ ኃይል የሰራውን የውጊያ ታሪክ እኔም: ሰራዊቱም ያውቃል:: መንግስት እኛንም ባያደክመን: አሁን ላይ እየትሄደበት ያለው ትጥቅ የማስፈታት መንግድ እጅግ አደገኛ ነው: መንግስት ይህንን ጉዳይ ቢያጤንበት መልካም ነው! >>// ሜጀር ጀኔራል ተሰፋየ ወልደማርያም//

እናመሠግናለን!
4.4K viewsedited  12:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-11 14:36:06 ደሴ!

ደሴ ዛሬ ከእንቅስቃሴዎች ተገተትታ ብትውልም ፥ መከላከያ ግን መሀል ከተማ ገብቶ ህዝቡን በተኩስ እያሸበረ ይገኛል! በአሁኑ ሰአት ዞን መስተዳድር አካባቢ ከፍተኛ ተኩስ አለ!

ትናንት እንዳጋራሁት መከላከያ አዳሩን በባቲ በኩል ገብቶ በየስፍራው መሽጎ ነበር ያረፈደው!

ግልፅ ስላደረጉት "የመከላከያ አላማው ምንድን ነው?" ብሎ መወዛገብ አያስፈልግም !
4.5K viewsedited  11:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ