Get Mystery Box with random crypto!

በቅርቡ የዶላር ዋጋ በመንግሥት ባንኮች ከመቶ ብር ሊያልፍ እንደሚችል ተገለፀ ! የአለም ባንክ ( | ዘሪሁን ገሠሠ

በቅርቡ የዶላር ዋጋ በመንግሥት ባንኮች ከመቶ ብር ሊያልፍ እንደሚችል ተገለፀ !

የአለም ባንክ ( WB) እና አለምአቀፉ የገንዘብ ድርጅት (IMF) ኢትዮጵያ የብርን የመግዛት አቅም አሁን ካለበት 50% እንድትቀንስ እንደሚፈልጉ መግለፃቸው ታውቋል! በዚህም መሠረት ተግባራዊ ከተደረገ አሁን በመንግሥት ባንኮች አንድ ዶላር ከሚሸጥበት 54 ብር በእጥፍ አድጎ ከመቶ ብር በላይ ሊሆን እንደሚችል እየተነገረ ነው!

በአሁኑ ሠአት ዶላር ከመቶ ብር በላይ የሚመነዘረው በብላክ ማርኬት ብቻ መሆኑ የሚታወስ ነው!

ሀገሪቱ አቶ አብይ አህመድ ወደስልጣን ከመጣበት ማግስት ጀምሮ ፥ በዋናነት ያለአንዳች ጥናትና የኢኮኖሚስቶች ምክረ ሀሳብ ፥ የብርን የመግዛት አቅም በተደጋጋሚ እንዲቀንስ በማድረጉና በየጊዜው እያሳተመ ወደኢኮኖሚክ ስርአቱ በሚያስገባው የገንዘብ ኖት ሳቢያ ፥ የሀገሪቱ ኢኮኖሚ ከጊዜ ወደጊዜ እየተዳቀቀና ይህን ተከትሎ ከፍተኛ የዋጋ ግሽበት በመፈጠሩ ፤ ለሀገሪቱ ህዝብ የኑሮ ውድነቱ እጅግ አሳሳቢና ለመቋቋም ከማይቻልበት ደረጃ እየደረሰ መሆኑ የሚታወቅ ነው፡፡

የመንግሥት ሠራተኛው ሆይ! ☞ ምናልባት ደመወዝህን በአዲሱ የዶላር ምንዛሬ ስትመታው በአለም ገበያው ላይ የምባይል ካርድ ሊገዛልህ ቢችል ነው !

ለማብራራት ☞ በአለም ገበያ ኢትዮጵያ ውስጥ የአንድ አማካኝ ደመወዝተኛ አመታዊ ክፍያ ከ1000 ዶላር በታች ይሆናል ማለት ነው፡፡ ይህ ማለት በወር በእጅህ ተጣርቶ የሚደርስህ 5 ሺ ብር በአለም ገበያ 50 ዶላር ሲሆን ፥ የ12 ወር አመታዊ ክፍያህ 600 ዶላር ይሆናል ማለት ነው፡፡

ስለገንዘብ የመግዛት አቅም መቀነስ ( devaluation ) ጥቅምና ጉዳት በተመለከተ ለማንበብ ከስር ያለውን ሊንክ ተጭነው ከወራት በፊት ለአንድ ካድሬ የሰጠሁትን መልስ ያንብቡ!

https://www.facebook.com/100077915236550/posts/168450745762099/?app=fbl

ኧረ አሁንስ ከፋ ጓዶች!