Get Mystery Box with random crypto!

አንድ ወዳጄ ያጋራኝን የአዛውንቱን ዝንጀሮ ታሪክ ላካፍላችሁ! እድሜ ጠገቡ ዝንጀሮ በሞት አፋፍ ላ | ዘሪሁን ገሠሠ

አንድ ወዳጄ ያጋራኝን የአዛውንቱን ዝንጀሮ ታሪክ ላካፍላችሁ!

እድሜ ጠገቡ ዝንጀሮ በሞት አፋፍ ላይ ሆኖ እያቃሰተ ነው፡፡ ልጆቹ ዙሪያውን ከብበውት የመጨረሻ የኑዛዜ ቃሉን መስማታቸውን ቀጥለዋል፡፡

በመሞቻው የመጨረሻ ሠአት ላይ የሚገኘው ዝንጀሮ እያቃሰተ ፦

<< እንግዲህ ልጆቼ አደራ ... መሞቴን እንዳረጋገጣችሁ በክብር የአቀባበር ስነ-ስርአት ቅበሩኝ ... ቀብሬን አክሱም ጽዮን አድርጉልኝ ... ፍትሐቴን ደግሞ ጎንደር ላይ ይሁንልኝ ... ተዝካሬን ደግሞ ላሊበላ እንዲወጣ አድርጉት ... ! >> በማለት ኑዛዜውን ቀጠለ ...

ኑዛዜውን የሚሠሙት ልጆች በአባታቸው ንግግር ተደናግጠው እርስበርስ ተያዩ፡፡

ነገር ግን አባታቸው በኑዛዜው መጨረሻ የተናገረው ዐረፍተ ነገር ሁሉንም ከድንጋጤአቸው አረጋጋቸው፡፡

<< ... ልጆቼ ይህንን የምናዘዘው ፥ ችላችሁ ታደርጉታላችሁ ብዬ ሳይሆን ... አያ ዝንጀሮ እንዲህ ብሎ ሞተ ተብሎ እንዲወራልኝ ፈልጌ ነው! >> ብሏቸው አረፈው!

ኧረ እነግርማ የሺጥላ ቢያንስ በ11ኛው ሰአታችሁ እንኳ ጥሩ ነገር ተናግራችሁ እለፉ!

ሻፓራካሻናታቂጦባራሲኮ!