Get Mystery Box with random crypto!

ከ80 የአለም ሀገራት ህዝብ ቁጥር የሚበልጥ ተፈናቃይ የተሸከመው የአማራ ክልል! የአማራ ክልል መ | ዘሪሁን ገሠሠ

ከ80 የአለም ሀገራት ህዝብ ቁጥር የሚበልጥ ተፈናቃይ የተሸከመው የአማራ ክልል!

የአማራ ክልል መንግሥት ባመነው ስታስቲክስና አሚኮ በዘገበው መረጃ ብቻ ተመስርተን ፥ ከመላ ሀገሪቱ በተለይም ከኦሮሚያ ክልል በሚፈፀምባቸው ማንነትን መሰረት ያደረገ ጥቃት ፥ ጭፍጨፋና ማፈናቀል ሳቢያ ህይወታቸውን ለማትረፍ ተሰደው ወደክልሉ የገቡና በተለያዩ የስደተኛ መጠለያዎች ብሎም በየጎዳናው የተበተኑ አማራዎች ቁጥር 2.4 ሚሊየን አልፏል፡፡

ይህ አሀዝ ላለፉት ወራት ከአዲስአበባና ከዙሪያዋ ካሉ ከተሞች ቤታቸው በላያቸው ላይ እየፈረሰ የተሰደዱትን በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን አያካትትም!

ከ120 ሚሊየን በላይ ህዝብ የያዘችው ኢትዮጵያ ከ224 የአለም ሀገራት ተርታ ፥ በህዝብ ቁጥር 12ኛ ደረጃ ላይ ስትገኝ ፥ አፍሪካዊቷ ቦትስዋና ደግሞ በ2,375,000 ህዝብ 145ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች፡፡

ታዲያ ይህ ባለፈው አሚኮ የዘገበውና መንግሥት ያመነው 2.4 ሚሊየን የተፈናቃዮች ቁጥር ብቻ ከአለም ሀገራት የ80ዎቹን ህዝብ ቁጥር የሚበልጥ ነው!

በሀገራችን ያሉ ክልሎችን እንኳ ብናነፃፅር የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልልን ሕዝብ ያህል ነው። የሌሎች በርከት ያሉ ክልሎችን ሕዝብ ይበልጣል። ሐረሪ ፣ ጋምቤላ ፣ አፋር ፥ ክልሎች ሕዝብ ድምር ይበልጣል፡፡

ወዳጄ! እንግዲህ ምንም ዝርዝር ሳያስፈልገው ፥ ይህ ምን ማለት እንደሆነ የማይገባው ለአፈናቃይ ብቻ ነው!

የአለም ሀገራቱን የህዝብ ቁጥር ደረጃ ለማረጋገጥ ከስር ያለውን ሊንክ ይጫኑ!

https://www.nationsonline.org/oneworld/population-by-country.htm