Get Mystery Box with random crypto!

ፍዝ ተመልካች ስትሆን ተመሳሳይ አክተሮች ይተውኑብሃል! ደበበ እሸቱ የሰላምም የጦርነትም ሌክቸር | ዘሪሁን ገሠሠ

ፍዝ ተመልካች ስትሆን ተመሳሳይ አክተሮች ይተውኑብሃል!

ደበበ እሸቱ የሰላምም የጦርነትም ሌክቸር እንዲሰጥህ ያደረከው ፥ ከመቶ ሚሊየን በላይ ሆነህ ፥ ሀገሪቱን መቶ የማይሞሉ ካንሰሮች በተመሳሳይ አዙሪት ውስጥ እየተሽከረከሩ እንዲፈነጩባት ምቹ ሁኔታ ፈጥረክ በመስጠትህ ነው!

በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የእያንዳንዳችን አስተዋጽኦ አለበት!

ብሮ ፦ አልሰማኸውም እንዴ ዛሬ << ስንዋጋም ከልብ ነው ፤ ስንታረቅም ከልብ ነው! >> ብሎ ሲሳለቅብህ?

አንተኑ አዋግቶ ፥ አጫርሶና አፋጅቶ በሀዘንና በሰቆቃህ ላይ " ከልብ ተራረቅን ይሉሃል!

እኛ ደግሞ ተላልቀን ፥ ተራርቀንና ተሸማቀን ፥ ዛሬም በብስቁልናና በመከራችን ላይ ፥ የመከራ ምንጮቻችንን እያፀደቅን ስንናከስ ቀጥለናል ...!

ህዝብ ለህዝብማ ከልብ እንዲተራረቅ ፥ እንዲቀራረብና እነሱ የዘሩትን የጥላቻ ትርክት ነቅሎ አብሮነቱን እንዲያስቀጥል ፈፅሞ አይፈልጉም !

ምክንያቱም መደበቂያ ዋሻቸው ነዋ!

"አብይ አህመድ አለምአቀፍ ወንጀለኛ ነው!" ስትል " ይህ የኦሮሞ ጥላቻ ነው!" ብሎ የሚደበቀው በምስኪኑ የኦሮሞ ህዝብ ነው፡፡

"ጌታቸው ረዳ የትግራይ ወጣቶችን አስፈጅቶ የህዝብ ስልጣን ላይ ያለ ወንጀለኛ ነው!" ብለህ ብትታገለው ፤ " ይህ የትግራዋይ ጥላቻ ያሰከራቸው የአሀዳውያን ዘመቻ ነው!" ብሎ ከለላ የሚያገኘው በዚሁ በሚያናክሰው መከረኛ ህዝብ ነዋ!

የሴራ ፖለቲከኞቹ በህዝብ ፍቅር የሚከስሩና የሚከስሙ ሲሆኑ የሚለመልሙት ደግሞ በሚዘሩት የጥላቻ ፍሬ ህዝብ ለህዝብ ተናክሶ ፥ የሴራ ወጥመዳቸው ሰለባ ሲሆን ብቻ ነው!

ሌላ ሌላውን ተወው "ድራማ" ነው!

ስር-ነቀል የአስተሳሰብ ለውጥና የትግል ጅማሮ ውስጥ መግባት ካልቻልን ፥ የኢትዮጵያና የህዝቦቿ እጣፋንታ ከዛሬው የነገው እጅግ ይከፋል!

ሠላም!