Get Mystery Box with random crypto!

የተሻለ ሀሳብ ዋጋ በማያወጣበት ሀገር ውስጥ ሁሉን ነገር ለማድረግ የሚያስችልህ ስልጣንና ገንዘብ ብ | ዘሪሁን ገሠሠ

የተሻለ ሀሳብ ዋጋ በማያወጣበት ሀገር ውስጥ ሁሉን ነገር ለማድረግ የሚያስችልህ ስልጣንና ገንዘብ ብቻ ነው!

ስልጣንና ገንዘብ ካለህ ፥ " ምሁር ፥ አዋቂና የሁሉ ነገር አድራጊ ፈጣሪ" ተደርገህ ትቆጠራለህ፡፡ የሚያስቅ ሳትናገር ይሳቅልሀል ፤ ለማይረባ ሀሳብህ ይጨበጨብልሀል ፥ አጀብህና ተከታይህ ብዙ ይሆናል፡፡

የተሻለ ሀሳብ ማራመድና ወደተሻለ ከፍታ መውጣት አይታሰብም፡፡ "ባለህበት እርገጥ ብቻ! በአንድ ክብ ዙሪያ መሽከርከር....!

በአስመሳይነት ፥ በአላዋቂነት ፥ በክፋትና በሴራ የተካኑት የትውልዱን ነገ ከጫማቸው ስር እየተረገጡ ሲጫወቱበት መመልከት ብቻ!

በዚህ አይነቱ አውድ "ብዬ ነበር...!" ማለት እጣፋንታህ ይሆናል!

ከዚህ አውድ ለመመንጠቅ ያለው ብቸኛ መንገድ ፤ ከተናጠል ለቅሶና ቁዘማ ወጥቶ ፤ በተደራጀ ሀሳብና አላማ ፤ በህብረትና በአንድነት መራራ ትግል ማድረግ ብቻ ነው!