Get Mystery Box with random crypto!

ልድገመው ፦ በግሌ ስለፋኖም ሆነ ልዩ ሀይሉ የሚሠማኝ ይኸው ነው! በትግል ላይ የሰነበተውና አ | ዘሪሁን ገሠሠ

ልድገመው ፦

በግሌ ስለፋኖም ሆነ ልዩ ሀይሉ የሚሠማኝ ይኸው ነው!

በትግል ላይ የሰነበተውና አሁንም በግንባር ላይ ታጥቆ የሚገኘው ፋኖ ፥ እንደህዝብ ያለንበትን አሳሳቢ የህልውና አደጋ ከተረዳና ለመታገል ቁርጠኝነቱ ካለው ፥ ግራም ነፈሰ ቀኝ ያለው አማራጭ አንድና አንድ ነው!



የታጠቁ ሀይሎቹን ይዞ በቋሚነት ወደሚንቀሳቀስበት የትግል  መሬት መጓዝና መስፈር!  ደጋፊና አባላቶቹም መስመሩ በተለየ ግልፅ መንገድ ይደግፉት ፥ ይቀላቀሉት!

ከተማና መሀል አገር ሆኖ ግን ሁልጊዜ "ተከበበ" እያልን መኖራችን ይቀጥላል እንጂ ፥ መክበባቸውም ሆነ ትጥቅ ለማስፈታት መንቀሳቀሳቸው ፈፅሞ አይቀሬ ነው!

ያ ካልሆነ ግን የሁልጊዜ   አጀንዳችን ፥ "ህዝብን ከከበባ ይታደጋል" ተብሎ የታመነበትን ፋኖ "  ...ተከበበ ፥ ታሰረ ፥ ትጥቅ ተቀማ ፥  ...! " የሚል ብቻ ሆኖ ፥ ራሳችንን እያደከምን  መጓዛችን ይቀጥላል!

ይህ ከሚሆን ደግሞ በየቤቱ ሆኖ እንደህዝብ  የሚደረገው ትግል አካል ሆኖ የሚጠበቅበትን ቢወጣ የተሻለ ይሆናል!

ልዩ ሀይሉም መወሰን ያለበት ፥ ከዚህ ጋር ተቀራራቢ የሆነ ውሳኔ ነው ብዬ አምናለሁ!

ትጥቁን እንደያዘ ሚሊተሪውን አውልቆ ወደህዝቡና ቤተሰቡ ተቀላቅሎ ይታገል!  ዙሮ ዙሮ የተፈራውና የገመትነው ሁሉ እየተፈፀመ መሆኑ የተረጋገጠ ነውና በየአካባቢው ሆኖ ለቀጣይ የተቀናጀ ህዝባዊ ትግል ራሱን ያዘጋጅ!

ያ ካልሆነ ደግሞ የራሱን እዝና የአደረጃጀት ሰንሰለት ዘርግቶ ገዢ ቦታ ይዞ የሚታገልበትን አማራጭ ማበጀት አለበት!

አለበለዚያ ግን በሴራ የፖለቲካ አመራሮች ግራ እንደተጋባ ዩኒፎርም ለብሶ ከወዲያ ወዲህ   እንገፍ እንገፍ ማለቱን ከቀጠለ ፥  እጣፋንታው ተለቅሞ ማለቅና በጠላት እጅ መውደቅ ይሆናል!

አሁን ባለው መንገድና ነባራዊ ሁኔታ ፥ ሁለቱም ሀይሎች ለህዝቡ ተጨማሪ ጫና ከመፍጠር ውጪ ጫናውን ወደሚያቀል የትግል ስርአትም ሆነ ተደራዳሪ ኃይል ወደመፍጠር  ሊገቡ አይችሉም!

ሳጠቃልል ፦ እኩልነት ፣ ፍትህና ዴሞክራሲ የሰፈነባት ፥ አሳዳጅና ተሳዳጅ የሌለባት ብሎም አንዱን ልጅ ሌላውን የእንጀራ ልጅ የማታደርግ ሀገርና ስርአትን ለመፍጠር ፤ አንድም በሰላማዊ የሀሳብ ትግል ያለበለዚያ ደግሞ "በአፈሙዝ እታገላለሁ" የሚለው ሀይል ፥ በራሱ ላይ መቀለዱን ትቶ ወቅቱን ወደሚመጥን "መረር" ወዳለ ትግል መግባት ካልቻለ ፥ በተያዘው አካሄድ በራስ ላይ መከራን ከማክፋት የዘለለ ስንዝር መራመድ አይቻልም !

ይኸው ነው!