"መሪ" መፍጠር ስለምን አልቻልንም? ምክንያት - 1- አብዛኛው "ኤሊት" ተብዬ መሪ ለመሆንና ዘውዱን በጉያው ይዞ ራሱን ለማንገስ ስለሚሻኮት ፥ መሪዎችን የመፍጠር ቢፈጠሩም ደግሞ የማክበር ባህላችን እየተሟጠጠ "መሪ አልባነትን" እጣፋንታችን ወደማድረግ እየተጓዝን ነው! መሪውን የሚያከብርና በስራው ብቻ የሚመዝን ተመሪ (የፖለቲካ ማህበረሰብ) ካልተፈጠረ ሁሉም ነገር "ውሃ ቢወቅጡት ...!" ነው! ምክንያት -2- ውስጣዊ የፖለቲካ ትምምን የተፈጠረበትና በጋራ ኮዙ ላይ የጋራ አመለካከት ያለው የፖለቲካ ማህበረሰብ መገንባት ያለመቻሉ! ምክንያት -3- አውራጃዊ (የጎጥ) አስተሳሰብ ከጋራ ጉዳያችን ከፍ ብሎ መስተጋባትና ይህን ውጥረት ለማርገብ መሪዎች በኮታ ድልድል እንጂ በብቃትና በእውቀት ተመስርተው መመረጥ አለመቻላቸው! ምክንያት - 4- መሪዎችን በቡድናዊ የጥቅም ሰንሰለትና በፖለቲካ ታማኝነት ላይ ብቻ ተመስርቶ የመሠየም የላሸቀ የፖለቲካ ልማድ ተጠናክሮ መቀጠሉ! ምክንያት -5- የመካድ ስነልቦናዊ ተፅእኖ ከዚህ ቀደም በተለያዩ መሪዎቻችን ያስተናገድናቸው ክህደቶችና እኩይ ተግባራት ሳቢያ ሁሉንም በአንድ ቅርጫት የመክተትና በጅምላ ተጠራጣሪ የመሆን ስነ-ልቦና እየገነገነ መምጣቱ! . . . . . . . . . . ግዙፉን አዕምሯዊ ፀጋ የተጎናፀፉ ምሁራን ይዘን ጠንካራና ብቁ የሆኑ መሪዎችን መፍጠር ላለመቻላችን ብዙ ብዙ ነጥቦች ማንሳት ቢቻልም ፥ እስኪ የእናንተንም ሀሳብና ምክንያቶች አክሉበትና እንወያይበት! የየድርሻችንንም እንውሰድ! ለሁለንተናዊ ውድቀቱም ሆነ ለስኬቱ እያንዳንዳችን በልካችን አበርክቶት አለን! 2.5K views15:57