Get Mystery Box with random crypto!

ኢትዮጵያ ልትኖር የምትችለው ኢትዮጵያውያንን መምሰል ስትችል ብቻ ነው! በኦሪት ዘመን አስተሳሰብ | ዘሪሁን ገሠሠ

ኢትዮጵያ ልትኖር የምትችለው ኢትዮጵያውያንን መምሰል ስትችል ብቻ ነው!

በኦሪት ዘመን አስተሳሰብ ላይ የሚገኙት አብዛኛዎቹ የኦሮሞ ፖለቲከኞች ዘወትር በየመድረኩ << ... ምስራቅ አፍሪካን ማካለል ባንችል ፥ ኢትዮጵያን ኦሮሞን እንድትመስል አድርገን ጠፍጥፈን እንሰራታለን! >> የሚል ቅዠት ከአፋቸው አይጠፋም፡፡

እንዲህ አይነቱ የቅዠት ፖለቲካስ ወደፊት የሚያስጉዝ ይመስላችኃል? ይህ አይነቱ በህዝብ ጉያ ተወሽቆ በቅዠት አለም እያስጨበጨቡ ቡድናዊ ፍላጎትን ለማሳካት የመሮጥ አባዜ ለትልቁ የኦሮሞ ህዝብ ጠላት ከማብዛትና ጥቁር የሀፍረት ታሪክ ከማሸከም ውጪ የሚጠቅመው ነገር አለ ወይ ?

ጠዋት ማታ የትርክት ጡጦ ጠብቶ በጎለመሰው ስብእናችሁ "ነፍጠኛ ፥ ወራሪ ፥ አሀዳዊ ፣ ደፍጣጭ ፣ ..!" እያላችሁ የምታብጠለጥሉት የአማራ ህዝብኮ " እኩልነትና ፍትህ ይስፈን! ለሁላችንም እኩል የሆነች እናት ሀገር ትኑረን!" እንጂ " አማራን የምትመስል ኢትዮጵያ ትገንባ!" አላለም!

ለማንኛውም ፦ ኢትዮጵያ መምሰል ያለባት ኢትዮጵያውያንን ብቻ ነው፡፡ ሊሰፍንባት የሚገባውም ፍትህና ርትዕ ብቻ ነው፡፡ " ማንም የበላይ ማንም የበታች ያልሆነባትን ፍትሀዊና ዴሞክራሲያዊት ሀገር እንገነባለን!" በሚል አስተሳሰብ እስክትታነፅና እኩልነትን እስትቀበል ድረስ መዶሻው አያባራልህም!

ጠማማ ብረት እኩል ሆኖ የሚስተካከለው ፤ በእሳት አግለህ በመዶሻ ስትቀጠቅጠው ብቻ ነው!

ያ ካልሆነ ግን ፦ ለሁላችንም እኩል መሆን ያልቻለች ሀገር ደግሞ የማንኛችንም እንዳትሆን መደረጓ ሳይታለም የተፈታ ነው!