Get Mystery Box with random crypto!

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

የሰርጥ አድራሻ: @zemedkunbekelez
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 412.24K
የሰርጥ መግለጫ

"ይህ የቴሌግራም ቻናሌ ግንቦት1/2011ዓም የተከፈተ ነው። የእኔን የስልክ ወጪ ጨምሮ አገልግሎቴን መደገፍ የምትፈቅዱ ጓደኞቼ በ
👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia እና
👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል ማገዝ ትችላላችሁ። በተረፈ ለቤተ ክርስቲያኔና ለኢትዮጵያ ሀገሬ የሚጠቅመውን ሁሉ አበረክት ዘንድ አብዝታችሁ ጸልዩልኝ።

Ratings & Reviews

4.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 6

2024-04-16 23:47:08
"…የነዳጅ ጉድጓዱ ከተገኘ፣ የባንኩ ፓስወርድ ተገኝቶ ለሕዝብ ሰደቃ ከሰጠ ወዲህ በኦሮሚያ ብር እንደ ቅጠል ነው አሉ። ርግፍ፣ ብትን ነው የሚልብህ አሉ። እንዲያውም ለአንድ ሴተኛ አዳሪ ለአንድ ቀን አዳር 2 ሚልዮን ብር በጨረታ የሚከፍሉ ወጣት የቄሮ ባለሀብቶች መፈጠራቸውን ስንሰማም እጅጉን ነው የተደመምነው።

"…አሁን በዚህም ይቀና ይሆናል እኮ…! ኢመቻቹ…
91.4K viewsedited  20:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-16 23:18:10
ይሄም ኦሮሚያ ነው…

"…በኦሮሚያ የትራንስፖርት እንቅስቃሴ እንዳይደረግ ቄሮ ያወጀውን ዐዋጅ ተላልፈው የተገኙ ናቸው የተባሉ ባጃጆች እና መኪኖች ዐዋጁን ባወጀው ቄሮ አቶ በቴ በተገደሉበት መቂ ከተማ በዚህ መልኩ ሲቃጠሉ፣ ሲነዱ አምሽተዋል።

"…ኦሮሚያ ግን እየለማች ነው። ሥልጣኔአቸውም በጣም፣ በጣም ይገርማል። የአቶ በቴ አሟሟት ግን ከምር ይዘገንናል። በስመ አብ ኦሮሚያ ያለው ጭካኔ ግን ያስደነግጣል።
89.8K views20:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-16 13:09:29
መልካም…

"…ወያኔ ወደ ራያ አላማጣ እየመጣች ነው ሲባል ከወትሮው በተለየ መልኩ እግዚአብሔርን የሚያመሰግን፣ ወደ ፔጄም ተንጋግቶ የሚገባ ብዙ ግሪሳ እያየሁ ነው። እግዚአብሔር ይመስገን።

"…አዲስ አበባን ፊንፊኔ በማለት የሚጠራት አዲሱ በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኤርቪን ጆሴ ማሲንጋ መጋቢት 16/2016 ዓ.ም የክልሉን ፕሬዘዳንት አቶ አረጋ ከበደን፣ በዐማራ ክልል የብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ሓላፊ ይርጋ ሲሳይና የዐማራ ክልል የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ መንገሻ ፈንታውን ጠርቶ ቪዛ እንዲሰጣቸው ከተደረገ በኋላ ህወሓት ራያን በደንብ እስክትይዝ ድረስ ወደ ኢትዮጵያ ድርሽ እንዳይሉ የኪስ ገንዘብ ዶላር ተሰጥቷቸው ወደ ላስቬጋስ አሜሪካ በሸነና እንዲሉ ተልከዋል። በዚያም አንድ ኤርትራዊ ባለ ሀብት እንዲያስተናግዳቸውም ተመድቧል።

"…ዐማራ ከባድ እና የዋንጫ ጨዋታ የሆነ በብዙ ግንባሮች ዐውደ ውጊያ ይጠብቀዋል። በሰሜን ጎንደር፣ በሰሜን ወሎ በራያና በዋግ ኽምራ፣ በደቡብ ወሎ። በጎጃም እና በሸዋ ውጊያ ይጠብቀዋል። የሞት ሽረት ውጊያ ነው። በአዲስ አበባና በዋና ዋና ከተሞች ደግሞ የዐማራና የትግሬ ተወላጆች በኦሮሙማው ይለቀማሉ፣ ይጠረጋሉ። ዐማራና ትግሬን አባልቶ በሸሻ አድርጎ ጊዜ ሳያጠፋ ደቡብን ለመሰልቀጥ ዝግጅቱን ጨርሷል። በቅርቡ ገረድ፣ ባርያ ሆነው ለአቢይ ሲሰግዱ የከረሙ ዐማሮች ለማኝ ይሆናሉ። ቱ…ዘመዴ አሁንስ አበዛኸው ሲሉኝ የነበሩ በሙሉ ደም እምባ ያለቅሳሉ። ከሃዲው አቢይ የብልጽግና አመራሮችን ቀርጥፎ ይበላቸዋል። አኝኮ ይተፋቸዋል። በጁንታው ጦርነት ጊዜ ወያኔ ላይ አፋቸውን የከፈቱ ሁሉ ይበላሉ። የሆነው ሆኖ ዋንጫው የዐማራው ነው።

"…ርዕሰ አንቀጽ ልጽፍ ነኝ። ለማንበብ ዝግጁ ናችሁ…?
19.1K views10:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-16 09:05:35
"…ከሰሜን ክፉ ነገርንና ጽኑ ጥፋትን አመጣለሁና ወደ ጽዮን ዓላማን አንሡ ሽሹ፥ አትዘግዩ። አንበሳ ከጭፍቅ ዱር ወጥቶአል፥ አሕዛብንም የሚዘርፍ ተነሥቶአል፤ ምድርሽን ባድማ ያደርግ ዘንድ ከስፍራው ወጥቶአል፥ ከተሞችሽም ሰው የሌለባቸው ፍርስራሾች ይሆናሉ። የእግዚአብሔር ጽኑ ቍጣ ከእኛ ዘንድ አልተመለሰምና ማቅ ልበሱ፥ አልቅሱም ዋይም በሉ። በዚያም ቀን፥ ይላል እግዚአብሔር፥ የንጉሡና የመኳንንቱ ልብ ይጠፋል፥ ካህናቱም ይደነቃሉ ነቢያቱም ይደነግጣሉ። ኤር 4፥ 6-9

"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?

"… መልሱ እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ
44.5K views06:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-16 00:10:58
እነሆ ዛሬም የማያልቅ ምክሬ ለዐማራው…

"…በፕሪቶሪያው ስምምነት መሠረት ዐማራ ከጨዋታው ከወጣ ቆየ። የወያኔ ጦር ትጥቅ አለመፍታት ብቻ ሳይሆን ተጨማሪ ትጥቅ ሁላቸውም አቅርበውለት እስከ አፍንጫው ድረስ በሚገባ ታጥቋል። የስንቁም ጉዳይ ክረምትን አሻግሮ እስከሚቀጥለው ዓመት የሚያሻግረው ዱቄትና ዘይት አግኝቷል። ለጁንታው በመቶ ቢልየን የሚቆጠር ብርና በዶላር ጭምር ከኢትዮጵያ ካዝና መስጠቱን አቢይ የትግሬን ወኪሎች አዲስ አበባ በጋበዛቸው ጊዜ ነግሮናል። በዚያ ላይ የጁላ ኦሮሙማ ጦር በዐማራ ፋኖ ስለተዋረደ ዐማራን ለመበቀል ሲል ስለሚረዳውም የሚመጣው የወያኔ ጦርም በሜካናይዝድ ተደራጅቶ ነው።

"…እናም እንደኔ እንደኔ ይሄንንም የወያኔ ጦር ልክ እንደብራኑ ጁላ ጦር በሽምቅ ውጊያ ከዚያም እንደ ሕዝብ በመግጠም፣ ማድቀቅ፣ መሰባበር ነው እንጂ ክላሽ በያዘ ሚኒሻ መመከት አይሞከረም። ዐማራው ማድረግ ያለበት ወያኔና አቢይ ልክ እንደራያው ሶዬ የሚያጸዱት እንዳለ ሆኖ እሱም ከሃዲ የብአዴን አመራሮችን እያጸዳ፣ ያለውን የሚኒሻና አድማ ብተና ኃይል ወደፋኖ ትግል በመቀላቀል እንደተለመደው ወደ ሽምቅ ውጊያ ዙረው ኪሳራ ላይ መጣል ነው። ዐማራን ልክ እንደ ትግሬ እንደ ሕዝብ ለማስነሣት የዐማራ ሥነ ልቦና ከባድ ቢሆንም ቆይቶ ጠኔና ስደት ውረደቱ እንዲባንን ያደረገዋል። መከራ ይመክረዋል።

"…ፋኖዎች መደማመጥ ከቻሉ። እንደ ጠላት በጣም ጨካኝ አረመኔ ከሆኑ፣ ነገ ወያኔ መጥታ የምትዘርፈውን ባንኩንም፣ የጦር መሣሪያውንም ከወዲሁ ከታጠቁ፣ የነበሩትን መሳሳቦች አርመው ከተናበቡ የራያ ሚኒሻ ብቻ ከፋኖ ጋር ተቀናጅቶ መታገል ከቻለ ሁለቱንም ደምስሶ ማሸነፍ ይቻላል። ለጊዜው ባለው ሴራ እነሂዊ አይደለም አላማጣ ወልዲያም ሊገቡ ይችላሉ። በዚህ መደናገጥ አይገባም። የዐማራ አክቲቪስቶችም እንደ ዐዋቂ ሁኑ።

• አመሰግናለሁ
62.6K viewsedited  21:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-15 21:45:35
ዜና ዘብጥያ…!

"…ዛሬ ከሰዓት ከምሳ በኋላ ቀውሲ በላይ መኮንን በV8 መኪናው የሞላቸውን አጃቢዎች ይዞ አፍሪካ ኅብረት ግቢ ውስጥ ወደሚገኘው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ያመራል። እንደ ደረሰም የምዕራብ ሸዋና የአሩሲ ቄሮ ናቸው የተባሉ አጃቢዎቹን መኪና ውስጥ አስቀርቶ ከገሚሶቹ ጋር ወደ ባንኩ ያመራል።

"…በአፍሪካ ኅብረት ግቢ ውስጥ የውጭ ሃገር ገንዘብ ማስቀመጥ ይቻላል። ቀሲስ በላይም በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከፓትርያርኩና ከአቡነ አብርሃም ቀጥሎ ዋና ባለ ሥልጣን ነውና ፍተሻም የለበት። እናም በሀገረ አሜሪካ በከፈተው የባንክ አካውንቱ ይተላለፍለት ዘንድ የተጻፈ ቼክ ይዞ ነበር የደረሰው። 5 ሚልዮን ዶላር። በ120 ብር ምቱት።

"…የባንኩ ሰዎች ፈሩ። ደነገጡም። ቀውሲ በላይ የጃዋር ጓደኛ ነው። የቄሮ አለቃ ነው። በዚያ ላይ የኦሮሞ ደኅንነቶችን አጃቢ ይዞ የመጣው። የባንኩ ሠራተኞች ጨነቃቸው። ቆይ አንዴ ይጠብቁን ፕሮሰስ እያደረግንሎት ነው አሉት። እሺ ብሎ ተዘፍዝፎ ተቀመጠ።

"…ቆይቶ የፌደራል ፖሊሶች እና የአፍሪካ ኅብረት የራሱ የፀጥታ ሠራተኞች በአካባቢው ፈሰሱ። ቀውሲ በላይንም በቁጥጥር ስር እንደዋሉት ነገረው ወደተዘጋጀው መኪና ይቀጥል ዘንድ አመለከቱት። ቀውሲ በላይም ከእንግሊዝኛ በቀር በኦሮሚኛም፣ በአማርኛም ቢፎክር፣ ቢያቅራራ፣ ቢቆጣ ማን ይስማው። ሰሞኑን በልማት ስም የቤተ ክርስቲያን ህንፃ ሲያስፈርስ የነበረው በላይ ውሎ ሳያድር ራሱ ፈረሰ። ለልጁ፣ ለራሱ፣ ለዘመዶቹ የቤተ ክርስቲያንን ሀብት የመዘበረው ሰው ሳይበላው ተያዘ።

"…የፌደራል መኪና፣ የአፍሪካ ኅብረትም የፀጥታ ሠራተኞች በመኪናቸው፣ ሌሎች ደግሞ የቀውሲ በላይን መኪናን አጅበው ወደ ማእከላዊ ወንጀል ምርመራ መሄዳቸው ነው የተነገረኝ። አንዴ ዐቢይ ጋር ልደውል አላለም…!

• ሥራው ያውጣው…!
70.5K views18:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-15 21:03:27
"…ለገሰ ቱሉ አሁን ብቅ ይልና…

"…በፕሪቶሪያው ስምምነት መሠረት ሕወሓት አፍርሺ የተባለችውን ጦር ሳታፈርስ ዳግሞ ጦሯን ወደ ዐማራ ክልል አስገብታለች። ይሄን ዓለም ሁሉ እየተመለከተው ነው። እነ ጌታቸው ረዳም ሆኑ እነ ደብረ ጽዮን ስምምነቱን ከሚያደፈርሱ ፀብ አጫሪ ድርጊቶች መቆጠብ አለባቸው።

"…ይህ ሁሉ በእንዲህ እያለ አስታዋዩ፣ አርቆ አሳቢው የሀገር መከላከያ ሰራዊታችንም በአካባቢው ተአማሪ ደም መፋሰስ እንዳይከሰት በማለት የዐማራ ብልጽግና ካድሬና መዋቅር፣ የዐማራ አድማ ብተናና የዐማራ ሚሊሻ ወደ ራያ ቆቦና ወደ ወልድያ ደጀን ወደ ሆነው ሕዝባችን አፈግፍገዋል።

"…ደግሞ እኮ ህወሓት ወረራ የፈጸመው የዐማራ ክልል ካቢኔ በርዕሰ መስተዳድሩ በአቶ አረጋ ከበደ የሚመራ ልኡክ ወደ አሜሪካዋ ምድራዊ ሲኦል ወደ ኃጢአት ከተማ ወደሆነችው ላስቬጋስ ለሥራ ጉብኝት መሄዳቸውን ተከትሎ እግራቸው ወጣ እንዳለ መሆኑ ነው ባይል ቱ… ምን አለ በሉኝ።

"…ወዳጄ ከ4 ኪሎ ላይ አይን አለማንሣት ነው።
70.7K views18:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-15 20:27:09
"…የሚገርመው እስከ አሁን ድረስ በንዴት ምግብ ያልበሉ፣ የደም ግፊታቸው ጨምሮ ሆስፒታል የገቡ ሁላ አሉ አሉኝ።

"…ማርያምን እነ ፋኖ ናሁሰናይን የመሳሰሉ ትንታግ ወጣትነታቸውን ለትውልድ ያለ ስስት የሚሰጡ ታማኝ ጀግኖችን እያየሁ ተስፋ ስለማልቆርጥ ፋኖ ምናምን እያልኩ የማላዝነው እንጂ ፒፕሉማ አስቂኝ ፕራንካም እና ቲክቶካም እኮ ነው።

"…ራብና ጠኔ እየቆላው አርሰናል ይባልልኛል። አርሰናልን ትበላው እንደሁ እናያለን። ደግሞ እኮ አርሰናልን እየደገፈ "እየመጡ ነው" ይባልልኛል አሉ። ምጣት ይምጣብህ አቦ አለ አሉ አጎቴ ሌኒን።
71.9K viewsedited  17:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-15 19:42:26
የትግሬ ነገር…!

"…እነ ዶር አምባቸውን ለመግደል ደመቀ መኮንንን አሜሪካ፣ ገዱ አንዳርጋቸውን ጀርመን ፍራንክፈርት ላከ አቢይ አህመድ። ከዚያ የሚገደሉት ተገድለው ሲያበቁ ይዟቸው በሄደው አውሮጵላን ሁለቱም ተመልሰው ቀበሯቸው። ዛሬም ህወሓትን ራያ ለለማስገባት መጀመሪያ እነ አረጋ ከበደንና የዐማራ ብልፅግና ብአዴኖችን አሜሪካ ቪዛ ሰጥታ ጠራቻቸው። እነርሱ ላስ ቬጋስ ከሴተኛ አዳሪ ጋር በሸነና ሲሉ ህወሓት ራያ አላማጣ ገባች። የሆነው ይኸው ነው።

"…ትግሬዎቹ ብልጦች ናቸው። ለዓላማቸው ቆራጦች፣ ታማኞችም ናቸው። ዐማራው የጦር ወታደር፣ የጦር መሪ ዋጋ ከፍሎ ከወኅኒ ቤት አስፈትቶ በወልድያ፣ በአላማጣ ተንከባክቦ መቀሌ ያስገባል። የጎጃም ፋኖ፣ እነ ማርሸት ይሄንን እንደታላቅ ጀብዱ፣ እነ አስረስ ዳምጤ ሲናገሩት ቅሽሽም አይላቸው። ይኸው እነ ማርሸት፣ የጎጃም ፋኖዎች የዐማራ ፋኖ ገብረው ያስፈቷቸው የትግሬ የጦር መሪዎች በቀጥታ የትግሬን ጦር እየመሩ፣ ከኦሮሙማው መከላከያ ጋር ተመሳጥረው አላማጣን አስወረሩ።

"…እነ ሂዊ እባብ ለመደ ተብሎ በኪስ አይያዝም ነገር ናቸው። የፈለገ ቢሆን ለዐማራው አይተኙለትም። ከምድር ላይ ያልቋታል እንጂ አይተኙለትም። ዐማራውን በአማርኛ ቋንቋ ሲያጃጅሉትና ሲያዝጉት ከቆዩት ተላላቆቹ ዓሣዎች መካከል ከእነ እስታሊን፣ ከእነ አሉላ ሰሎሞን እና ከነቴዲ ርዕዮት በቀር ሚጢጢ ቁጫጭ ውርጋጥ የኦነግ አሽከር የሆኑት የትግሬ አክቲቪስቶች በሙሉ ዛሬ ህወሓት አላማጣ ገባች በማለት ጮቤ ሲረግጡ ነው የዋሉት።

"…ሲነገረው ያልሰማን፣ ያልተዘጋጀውን ከብልፅግና ጋር አሽኮለሌ ሲል የከረመውን
ዐማራ አይደለም አላማጣ ለምን ደሴን አልፈው አዲስ አበባ ገብተው አይረግጡትም። ሁ ኬርስ አለ ሱሬ። ትግሬና ዐማራ ሲጨፋጨፍ ኦሮሙማ እረፍት ያገኛል። ዐማራም ብልጥ ከሆነ…

• አዙረኝ አታዙረኝ…
75.4K views16:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-15 16:56:45
"…መልካም

"…ከርዕሰ አንቀጹ ንባብ በኋላ የሚከተለው የእናንተ የበሰለ አስተያየት ነው። አስተያየት ለመጻፍ አቅምም፣ እውቀትም የሌላችሁ ግን አትገደዱም።  ለመሳደብ የሚመጣን ነውረኛ የወሬ ጠኔ ያለህ ብሎ እንዲቀር ነው የማደርገው። ከስድብ በቀር ተቃውሞም ቢሆን ሓሳብን በጨዋ ደንብ የመግለፅ መብት በእኔ ቤት በሽበሽ ነው። ቤቴ ለሓሳብ ነፃነት ክፍት ነው። የሰው ዓይን የሚያቆሽሽ ስድብ ብቻ ነው ክልክሉ።

"…በተለይ ፋኖን ይመጣል ብላችሁ በቲክቶከሮች ቀደዳ፣ በፕራንክ ሙድ ተከይፋችሁ… ደጅ ደጁን የምትጠብቁ አዲስ አበቤዎችም እስቲ ሓሳብ ስጡ። እንወያይ። ጀግኖቹን እናድንቅ። እናወድስ።

• አንድ… ክልኧተ… ሰዲ… ጀምሩ…!
77.5K views13:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ