Get Mystery Box with random crypto!

የምስራቅ እስቴ ወረዳ ሰለፍዮች ቻናል።

የቴሌግራም ቻናል አርማ selefiyya — የምስራቅ እስቴ ወረዳ ሰለፍዮች ቻናል።
የቴሌግራም ቻናል አርማ selefiyya — የምስራቅ እስቴ ወረዳ ሰለፍዮች ቻናል።
የሰርጥ አድራሻ: @selefiyya
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 85
የሰርጥ መግለጫ

ኑ እንማር، የተፈጠርንለትን አላማ እንወቅ!!!!
ይህ ግሩፕ በምስራቅ እስቴ ወረዳ ያሉ በማወቅም ይሁን በቸልተኝነት በሽርክና በቢድዓ የተዘፈቁ ወንድም እህቶችን ከሽርክና ከቢድዓ በማላቀቅ በአሏህ እገዛ ወደ ተውሂድ እና ሱና ለማምጣተ የተከፈተ ቻናል ነው።።
ቻናሉን ከወደዱት
ለአስተያየት ፣እርማትና ጥቆማ
👇👇👇👇👇
@discussbot

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2021-12-07 21:17:16 https://t.me/Sadik_Ibnu_Heyru?livestream
11 views::::::::::::::::::::‘:::::::'':'''''', 18:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-30 19:55:27 በማሕበረሰቡ ላይ የሙመይዓ አደገኝነት!!

خطر المميعة على الأمة
————— ክፍል_①
ሙመይዓ ማለት:- አቅላጭ ወይም የሚያሟሟ ማለት ነው። ይህ ማለት ለትክክለኛው ዲን ለሠለፊያ መንሀጅ ጠንካራ ወኔ እና ጉጉት የነበረውን ማህበረሰብ በተለያዩ ስልታዊ አካሄዶችና የተለያዩ ከሰለፎች የማይታወቁ መርሆዎችን እያበጁ የነበረውን ወኔና ጉጉት በሂደት እንዲሸረሸርና እንዲሟሟ የሚያደርግ አስተሳሰብ ማለት ነው።

ጠንካራና የተለያዩ ሸሪዓዊ መርሆዎችን በማሟሟት፣ በተለይ ሠለፊዩ ማህበረሰብ በቢድዓ ሰዎች ላይ ሊኖረው የሚገባውን ጠንካራ አቋምና ደጋግ ቀደምቶቹ በቢድዓ ሰዎች ላይ የሚወስዱትን ጠንካራ እርምጃና ደጋግ ቀደምቶቹ ያስቀመጧቸውን መርሆዎች እንዳይከተል የተለያዩ ዘዴዎችን በመጠቀምና ትክክለኛ ያልሆኑ የራሳቸውን አዳዲስ መርሆዎችን በማበጀት እንዲሟሟ ከፍተኛ ሚና ይጫወታሉ።

የዚህ አስተሳሰብ ስያሜ በሰለፊያው ማህበረሰብ ላይ ከሚያደርሰው አሎታዊ ተፅዕኖ አንፃር ትክክለኛውን ስያሜ ነው ያገኘው። በዋነኝነት ከአል-ኢኽዋኑል ሙስሊሚን የጥመት አንጃ ክንፍ ከሆነው "ሱሩሪያ" ጋር በተግባርም በአካሄድም የጠበቀ ግንኙነት አላቸው። የአል-ኢኽዋኑል ሙስሊሚን ክንፍ የሆነውን የሱሩሪያን መሰሪነትና የጥመት አካሄድ በትክክል ያወቀና የተገነዘበ ሰው ስለ ሙመይዓ በዝርዝር ሳይነገረው ይገበዋል ቢባል ማጋነን አይሆንም።

እንደሚታወቀው የአል-ኢኽዋኑል ሙስሊሚን የጥመት ቡድን በዋነኝነት ሶስት ክንፍ አለው። እነሱም:- 1, በናኢ፣ 2, ቁጥቢይና ሌላኛው ከሙመይዓ ጋር ግንኙነት ያለው ሙሀመድ ሱሩር ዘይነል ዓቢዲን የሚባለው አባላቸው የመሰረተው 3, ሱሩሪያ ነው። ሱሩሪያ ብዙዎች የሚሸነገሉበት አደገኛው አስተሳሰብና ሌላው አደገኛ የሆነው የአል-ኢኽዋኑል ሙስሊሚን ክንፍ ነው። በናኢ እና ቁጥቢያ የሚባሉት ክንፎች ማህበረሰቡ ብዙም ሳይቸገር ሊለያቸው የሚችሉ የአል-ኢኽዋኑል ሙስሊሚን ክንፎች ናቸው።

ሱሩሪያ የሚባለው ክንፍ ግን የተወሰነ የሰለፊያን ልብስ ለብሶ የመስበክ አቅም አለው። በአንፃሩ ከላይ የሚታይባቸው ገፅታቸውም ከሰለፊዩ ጋር የመመሳሳል እድሉ የሰፋ ነው። ይሁን እንጂ ግን በሰለፊዮች ላይ አደገኛ አካሄድ የሚሄዱት እነሱ ናቸው። በተለይ ሙስሊሙ ማህበረሰብ ልዩ ትኩረት የሚሰጠውን የዓቂዳ ትምህርት በማስተማር ስም የማህበረሰቡን ትኩረት ለመሳብ ይሞክራሉ።

በናኢይ ከሚባለው ክንፍ ቀብር አምላኪ፣ አሻዒራ ማቱሪዲያ፣ ሱፊይና የመሳሰሉ አደገኛ አስተሳሰቦችን ይዞ የሚራመድ አካል አለ። ቁጥቢይ የሚባለው ክንፍ ውስጥ ደግሞ እራሳቸውን በጂሃዲስት ስፍራ አስቀምጠው ሙስሊሙን የሚያከፍሩና ከተለያዩ አለማችን ውስጥ ከሚገኙ የሽብር ቡድኖች ጋር ሆነው የሚሰሩ አደገኛ አስተሳሰብ ይዘው የሚራመዱ አሉ። ይህ ከመሆኑም ጋር ግን ሶስቱንም ክንፎች የሚያስተሳስር አደገኛ የሆነ ሸሪዓዊ መርሆዎችን የሚጣረስ “በተስማማንበት ነገር ላይ ተስማምተን እንጓዝ፣ በማንስማማበት (በተከላለፍንበት) ነገር ደግሞ ዑዝር (ምክንያት) እንሰጣጥ” የሚል አደገኛ መርሆ አበጅተዋል።

ይህ ማለት ከመካከላቸው ሺርክ የሚሰራም ቢኖር አደገኛ ወደ ሺርክ የሚያደርሱ ቢድዐዎች ላይ የወደቀ አካልም ቢኖር… ሌሎች ሌሎችንም በሸሪዓ የተወገዙ ተግባሮችን የሚሰራ ቢኖር "ተው እንጂ ይህ አይፈቀደም!፣ ከዚህ ተግባርህ ተቆጠብ!፣ የማትቆጠብ ከሆነ አንተ ሸሪዓን እየጣስክ አብረን መቀጠል አንችልም!" መባባል የለም ማለት ነው። "የሆነ ምክንያት ይኖረዋል ዑዝር ስጠው" እየተባባሉ ተያይዘው ወደ ገደል ይጓዛሉ። ለዚያም ነው ሱሩሪዩ ከበናኢው ጋር በናኢው ከቁጥቢዩ ጋር በአንድነት የሚንቀሳቀሱት። ይህ መርሆዋቸው በዋነኝነት "በመልካም ማዘዝ፣ ከመጥፎ መከልከል" ከሚለው ሸሪዓዊ መርሆና "ሸሪዓን ከሚጋጩ ሰዎች እራስን ማግለል" ከሚባለው መርህ በእጅጉ ይጣረሳል። አምላካችን አላህ በተቀደሰው ቃሉ እንዲህ ብሏል:-

وَلْتَكُن مِّنكُمْ أُمَّةٌ يَدْعُونَ إِلَى الْخَيْرِ وَيَأْمُرُونَ بِالْمَعْرُوفِ وَيَنْهَوْنَ عَنِ الْمُنكَرِ ۚ وَأُولَٰئِكَ هُمُ الْمُفْلِحُونَ

«ከናንተም ወደ በጎ ነገር የሚጠሩ በመልካም ሥራም የሚያዙ ከክፉ ነገርም የሚከለክሉ ሕዝቦች ይኑሩ፡፡ እነዚያም እነሱ የሚድኑ ናቸው፡፡» አል-ዒምራን 104

እንዲህ ያሉ በርካታ የቁርኣን አንቀፆች አሉ። ይህ የአል-ኢኽዋኑል ሙስሊሚን የሚባለው የጥመት ቡድን በመካከላቸው የከፋና ለመለያየት የሚያበቃ ልዩነት እንዳይኖር ያበጀው መርህ ደግሞ እነዚያን የቁርኣን አንቀፆች ሁሉ የሚጣረስ አደገኛ መርህ ነው።

በዚህ አካሄዳቸው የተነሳ ከዚህ ቀደም በነበሩ ጊዜያት የተወሰኑ ሰዎች ወደ ሰለፊያ ተጠግተናል እያሉም በሱሩሪያ ሲሸነገሉ ይስተዋል ነበር። ይህን "ሱሩሪያ" የሚባለውን የአል-ኢኽዋኑል ሙስሊሚን ክንፍ አስተሳሰብ በሀገራችን ግንባር ቀደም ሆነው ሲያሰራጩት የቆዩና ይህን አስተሳሰብ ማስፋፋት አላማቸው አድርገው ከቀጠሉ ሰዎች መካከል በከፊል:- 1, ዶ/ር ጀይላን 2, ሙሀመድ ሃሚዲን 3, ባህሩ ዑመር 4, ሙሀመድ ፈረጅ 5, ሳዲቅ ሙሀመድ (አቡ ሀይደር) 6, ዐብዱሰላም አንዋር (ይህ 6ኛ ላይ የተጠቀሰው ግለሰብ ቀደም ሲል ወራቤ ይኖር የነበረ ሲሆን፣ በዚህ ጊዜ ደግሞ መኖሪያው አዲስ አበባ ቢሆንም ወራቤና አዲስ አበባ እያለ ከሙመይዓዎች ጋር ሆኖ በስልጤ ክልል የሰለፊያ ደዕዋን ለመበጥበጥ ያለ የሌለ ሀይሉን ተጠቅሞ እንደሚሯሯጥ ይታወቃል) ሲደክመውና ሲሰለቸው ይቆማል እንጂ ኢንሻ አላህ አይሳካለትም!። በሙመይዓዎች ጉያ ስር ተወሽቆ እንደ አዲስ መፍጨርጨር ጀመረ እንጂ በእርግጥም ከወራቤ ሲወጣ ተስፋ ቆርጦ ነበር። በየትኛውም አቅጣጫ ተቀያይሮ ብቅ ቢል አላህ ያጋልጠዋል!።

يُرِيدُونَ لِيُطْفِئُوا نُورَ اللَّهِ بِأَفْوَاهِهِمْ وَاللَّهُ مُتِمُّ نُورِهِ وَلَوْ كَرِهَ الْكَافِرُونَ

«የአላህን ብርሃን በአፎቻቸው ሊያጠፉ ይሻሉ፡፡ አላህም ከሓዲዎቹ ቢጠሉም እንኳ ብርሃኑን ገላጭ ነው፡፡» አስ-ሶፍ 8

የሙመይዓ አስተሳሰብ የተለያዩ በቢድዓና በቢድዓ ሰዎች ላይ ጠንካራ አቋም የነበራቸውን ጠንካራ ሰለፊዮችን በጊዜ ሂደት የተለያዩ መርሆዎችን እና "መስለሃና መፍሰዳ" ወይም "ጥቅምና ጉዳትን ማመዛዘን" የሚለውን መርህ ያለ ቦታው በመጠቀም ከጠንካራ አቋማቸው ተንሸራተው ጭራሽ እራሳቸውን "በቢድዐ ባለ ቤቶች ላይ ድንበር እንዳለፉ" አድርገው እንዲመለከቱና ከቢድዐ ባለ ቤቶች ጋርም በስመ ሰለፊይነት ከሚኖረው ልዩነት ባሻገር በተግባርና በአካል እንዲዋሀዱ አድርጓል። ሰለፊያው ማህበረሰብ ለቢድዐ ሰዎች ግዴለሽና ከቢድዐ ሰዎች ጋር تميز ልዩነትና መለያ ግርዶሽ እንዳይኖረው አድርጓል።

ይህን አስተሳሰብ ሠለፊያው ማህበረሰብ አደገኝነቱን በፍጥነት ተገንዝቦ ሊጠነቀቀው ይገባል!። ሰለፊይ መሻይኾችና ኡስታዞችም ይህን ግልፅ በማድረግ ረገድ ኀላፊነታቸውን ሊወጡ ይገባል!። ምክንያቱም ከሱሩሪያዎች በላቀ መልኩ የሰለፊያን ልብስ ለብሰው በማምታታት ብቃት የተካኑ ከመሆናቸውም ባሻገር በኢትዮጵያ ውስጥ እራሳቸውን የሰለፊያ መንሃጅ ባለ ውለታ እንደሆኑ አድርገው ለማህበረሰቡ ቀርፀዋል።
ኢብን ሽፋ: ረቢዐ ሳኒ 25/1443 ዓ. ሂ

የተለያዩ ት/ቶችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችን #join ያድርጉና ይቀላቀሉ
https://telegram.me/IbnShifa
https://telegram.me/IbnShifa
32 viewsአቡ ሐናን, 16:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-30 15:37:37
ጥያቄ፦ በምክንያትም ይሁን ያለ ምክንያት የጀናባን ትጥበት ማዝግየት ብይኑ ምንድነው?

መልስ፦ የሶላት ወቅት እስካልደረሰ ድረስ ችግር የለውም። የሶላት ወቅት ከደረሰ ታጥቦ ሶላቱን መፈፀም ግድ ይለዋል። ለምሳሌ ዙህርና 0ስርን ይመስል። ረፋድን በተመለከተ ግን ለምሳሌ ዙህር ላይ እስከሚታጠብ ድረስ ቢዘገይ (ችግር የለውም።) ሶሒሕ አልቡኻሪና ሙስሊም ላይ ሑዘይፋና አቡ ሁረይራ ባስተላለፉት ሐዲሥ እነሱ ነብዩን ﷺ ሲያገኙ ይሰውራሉ። ነብዩ ﷺ "ምንድነው ነገራችሁ?" ሲሏቸው "ጀናባ ላይ ነበርንና ጦሀራ ላይ ሳንሆን አብረንህ መቀመጥን ስለጠላን ነው" አሉ። በዚህን ጊዜ ነብዩ ﷺ "ሙስሊም አይነጀስም" አሉ። እና ያለ ጦሀራ መቆየታቸውን አልነቀፉም። አላህ ሆይ! በሳቸው ላይ ሶላትህን አውርድ።

ከሸይኽ ኢብኑ ባዝ ረሒመሁላህ ፈትዋ የተወሰደ
ምንጭ፦ https://binbaz.org.sa/fatwas/15618/%D9%85%D8%A7-%D8%AD%D9%83%D9%85-%D8%AA%D8%A7%D8%AE%D9%8A%D8%B1-%D8%BA%D8%B3%D9%84-%D8%A7%D9%84%D8%AC%D9%86%D8%A7%D8%A8%D8%A9

የቴሌግራም ቻናል
https://t.me/IbnuMunewor
29 viewsአቡ ሐናን, 12:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-28 11:04:59

37 viewsአቡ ሐናን, 08:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-28 07:05:52 ይህ ነው የኔ መንሀጂ
◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈
ወደድክም ጠላህም ባገሬ ኢትዮጲያ፡
እድገቱን ቀጥሏል ደምቋል ሰለፍያ፡
ገና ግልፅ ይሆናል ከዚህ በበለጠ፡
ቢድዐና ሽርክን እየገሸለጠ፡
◊◊◊◊◊◊◊◊◊◊◊◊◊◊◊◊◊◊◊◊◊
ተውሒድና ሱናን ለኛ እየገለፀ፡
በቀደምቶች ፈለግ እንደተቀረፀ፡
ደምቋል ሰለፍያ በምድረ ሀበሻ፡
ለሀቅ የሚሞቱ ፣
በመንሀጂ የፀኑ አፍርቷል ወጌሻ፡
ትግሉም ይቀጥላል…
በአላህ እገዛ እስከመጨረሻ፡
◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈
መንሀጁም ይደምቃል በሀበሻ ምድር፡
ሀቅን አያጠፋም ውሸት ቢተባበር፡
አንበሣን አያስርም በፍፁም ድር ቢያብር፡
በመንሀጀ ሰለፍ ይሰማናል ክብር፡
◉◉◉◉◉◉◉◉◉◉◉◉◉◉◉◉◉◉◉◉
አልሀምዱ ሊላሒ ደስተኛ ሆነናል፡
ጥርጥር የሌለው እምነት ተሰጥተናል፡
"ሰለፍይ"ተብለን ያው ተሰይመናል፡
ከቢድዐ ከሽርክ አምፀን ወጥተናል፡
በተውሒድ በሱና፣
በነብያት ፈለግ ረክተን ተብቃቅተናል፡
◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈
የማያልቅ ውለታው በጧትም በማታ፡
ይገባው ምስጋና የአለማት ጌታ፡
ዱንያ ላይ እያለን ሰለፍያን ሰጥቶ ከተንከባከበን፡
በዕዝነት በችሎታው ሀቅን ከደረበን፡
ነገም በችሎታው በጀነት ያስውበን፡
◉◉◉◉◉◉◉◉◉◉◉◉◉◉◉◉◉◉◉◉◉
የነብያት ፈለግ የሰው ልጂ መነሻ፡
የሀቀኝነት ጥግ የእምነት መጨረሻ፡
ከአወል እስከ አኺር እንከን የሌለበት፡
አመፅ የሚጠላ ሰላም የሞላበት፡
ጥርት ፍንትው ያለ እንደ ቀን ጠራራ፡
ይህ ነው የኔ መንሀጂ የሩስሎች አደራ
◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈
አልፈልግም ወሬ አመጣው ወሰደው፡
ጂብ ይገባል አሉ ውሻ በቀደደው፡
አያሻኝም ዳኛ አልፈልግም ፈራጂ፡
እጂግ ውብ የሆነው ይህ ነው የኔ መንሀጂ
➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴
https://t.me/abdulhalimibnushayk
30 viewsYunus omer, 04:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-27 16:12:47 ሙመይዓዎች አንድ ሰው "ሙብተዲዕ ነው" ተብሎ ብይን ሊሰጥበት (ኢጅማዕ) የዓሊሞች የጋራ ስምምነት መስፈርት ነው በማለታቸው ላይ የተሰጠ መልስ
–––––
ታላቁ ዓሊም ሸይኽ ረቢዕ ቢን ሓዲ ዑመይር አል-መድኸሊይ (ሀፊዘሁላህ) እንደሚከተለው ተጠየቁ:- የቢድዓ ባለቤትን በማነወር (ሙብተዲዕ ነው ብሎ ብይን በመስጠት) ላይ የዓሊሞች የጋራ አቋም መኖሩ መስፈርት ይደረጋልን? ወይስ የአንድ ዓሊም ንግግር በቂ ነው?

የሸይኽ ረቢዕ (ሀፊዘሁላህ) መልስ:- ይህች -ባረከላሁ ፊኩም- ቆሻሻ ከሆኑ የሙመይዓዎች መርሆ ነች። በየትኛው ዘመን ላይ ነው የዓሊሞች የጋራ አቋም መስፈርት የሆነው?? ለዚህ መስፈርት ማስረጃውስ ምንድነው?? ምክንያቱም የትኛውም በአላህ መፅሃፍ (ቁርኣን) ውስጥ የሌለ መስፈርት መቶ (100) መስፈርት ቢሆን እንኳን ውድቅ ነው።

አሕመድ ኢብኑ ሀንበል አለያም የህየ ኢብኑ መዒን አንድን ሙብተዲዕ ካነወሩ ዓለም ላይ ያሉ ሱኒዮች ተሰባስበው ይህ ሰው ሙብተዲዕ በመሆኑ ላይ የጋራ አቋም እስከሚይዙበት "አይሆንም" ልላቸው ነው?

ኢማሙ አሕመድ ኢብኑ ሐንበል (ረሂመሁላህ) አንድ ሰው ላይ "ይህ ሙብተዲዕ ነው" ካሉ ሁሉም ነገር አበቃ። ኢማሙ አህመድ ይህ ሙብተዲዕ ነው ካሉ ሰዎች ሁሉ ተቀብለው ከኋላቸው ይከተላሉ። ኢብን መዒን "ይህ ሰው ሙብተዲዕ ነው" ካለ አንድም የሚጨቃጨቀው አልነበረም።

የጋራ አቋም መስፈርትነትማ ግዴታ በሁሉም ሸሪዓዊ ህግጋት ላይ ሊሆን የማይችል ነገር ነው። ጥሩ፣ ለምሳሌ:- ሁለት ምስክሮች አንድ ሰው ላይ ሰው በመግደሉ ለመመስከር ቀረቡ፣ ግዴታ ሁሉም ሙስሊም ያ ሰው ገዳይ እንደሆነ መስማማቱን መስፈርት ሊደረግ ነው? አንድ ዳኛ የሆነ ሰው ገዳይ በሆነ ሰው ላይ የአላህን ህግ "ካሳ በማስከፈልም ሆነ የገደለን እንዲገደል" የአላህን ህግ እንደወረደ ተፈፃሚ በማድረግ ረገድ የሙስሊሙን ማህበረሰብ መስማማት (የጋራ አቋም) መያዝ ግዴታ ልናደርግበት ነው? ይህ ሙብተዲዕን ሙብተዲዕ ከማድረግ የከፋ ነውን?

እነዚያ እኮ (ኢጅማዕ መስፈርት ነው የሚሉት) የባጢል ባለ ቤት የሆኑ ሙመይዓዎች ናቸው። በደፈረሰ ውኃ ውስጥ የሚያድኑ የሸር ሰባኪያን ናቸው። እንዲህ ያሉ ውዳቂ ነገሮችን አትስሙ!።

አንድ እውቀት ያለው ሚዛናዊና ታማኝ ዓሊም አንድን ግለሰብ ካነወረ ይህን ያነወረበትን ነገር ወይም ማነወሩን መቀበል ግድ ነው። ይህ ዓሊም ያነወረውን ሌላ ሚዛናዊና ታማኝ የሆነ ዓሊም በተቃራኒው ከቀደሰው ይህን ጊዜ ሁለቱም በዚያ ግለሰብ ላይ የሚሉትን ነገር እናጠናለን፣ የዚህ ማነወርም በደንብ ይጠናል የሌላኛው መቀደስም በደንብ ይጠናል። ማነወሩ ግን የተብራራና ግልፅ የሆነ ከሆነ ከሚቀድሰው ይልቅ ምንም ያህል የቀዳሾች ቁጥር ቢበዛ እንኳ የዚህ ማነወር ይቀደማል (ከቀደሰው ዓሊም ይልቅ ያነወረው ዓሊም ተቀባይነት ይኖረዋል) ለምሳሌ:- አንድ ዓሊም በተብራራና ግልፅ በሆነ መልኩ አነወረ፣ ሌሎች 20 (ሀያ) እና 50 (አምሳ) የሚሆኑ ዓሊሞች በተነወረው ሰው ላይ ከመልካም ግምትና ግለሰቡ ከላይ ከሚያንፀባርቀው ነገር የዘለለ ማስረጃ ሳይኖራቸው ተቃርነውት ቢቀድሱት፣ ያ ዓሊም ደግሞ በማነወሩ ማስረጃ ካለው ይህ አነዋሪው አካል ማነወሩ ይቀደማል፣ ምክንያቱም በማነወሩ ላይ ማስረጃ አለው፣ ተቀዳሚው ማስረጃ ያለው አካል ነው። ምድርን የሚሞላ ፍጡር ሁሉ ቢቃረነው የሚቀደመው ማስረጃና ማስረጃ ያለው ነው።

ማስረጃው ከእርሱ የሆነ አካል ሐቁም ከእርሱ ነው። ጀመዓ ማለት ብቻውን ቢሆን እንኳን ሀቅ ላይ ያለ ነው። አንድ ሰው በሱና ላይ ቢሆንና የሁለት አለያም የሶስት ከተማዎች ባለ ቤት የሆኑ ሰዎች ሁሉ ቢቃረኑትና ሙብተዲዕ ቢሆኑ ሀቁ ብቻውን ከሆነው ሰው ጋር ነው። እርሱ ዘንድ ያለው እውነትና ማስረጃ ሌሎች ዘንድ ካለው ባጢል ይቀደማል። ሐቅን እና ግልፅ የሆነን ማስረጃ ማክበር ግዴታችን ነው።

قُلْ هَاتُوا بُرْهَانَكُمْ إِن كُنتُمْ صَادِقِينَ

«እውነተኞች እንደሆናችሁ ማስረጃችሁን አምጡ፣ በላቸው፡፡» አል-በቀረህ 111

وَإِن تُطِعْ أَكْثَرَ مَن فِي الْأَرْضِ يُضِلُّوكَ عَن سَبِيلِ اللَّهِ ۚ إِن يَتَّبِعُونَ إِلَّا الظَّنَّ وَإِنْ هُمْ إِلَّا يَخْرُصُونَ

«በምድርም ካሉት ሰዎች አብዛኞቹን ብትከተል ከአላህ መንገድ ያሳስቱሃል፡፡ ጥርጣሬን እንጅ ሌላን አይከተሉም፡፡ እነርሱም የሚዋሹ እንጂ ሌላ አይደሉም፡፡» አል-አንዓም 116

ጥቂት ሰዎች ቀርተው ምድር ላይ ያለው ሰው ሁሉ ያለ ማስረጃ ባጢል ላይ ቢስማማና በአንድ ነገር ላይ የጋራ አቋም ቢኖረው እንኳ ከማስረጃ የተራቆተች ብዛት ከሆነች ለብዛታቸውም ሆነ ለአቋማቸው ምንም አይነት ግምት የላትም!።

የባጢል ባለ ቤቶችን የሚቃረናቸውና በማስረጃ የሚሟገታቸው ሰው ብቸኛ ቢሆን አለያም ቁጥራቸው አናሳ ቢሆኑ እንኳን ግምት የሚሰጠው ማስረጃ ላላቸው የሀቅ ተከታዮች ነው እንጂ የባጢል ሰዎች ቁጥራቸው በዝቶ ምድርን ቢሞላም ግምት አይሰጣቸውም። አላህ! አላህ! ሀቅን በማወቅና በሀቅ ላይ በመጣበቅ አደራ! በተለይ ማስረጀ የሚደገፍለት ከሆነ ሐቁን በመከተል ላይ አደራ!። አላህ ሁሉንም ለመልካም ነገር ይግጠም!! [ሚን ሸሪጢ መንሀጅ አትተምይዕ ወቀዋዒዱሁ ሊ-ሸይኽ ረቢዕ]
ትርጉም:- ኢብን ሽፋ: ረቢዐ ሳኒ 22/1443 ዓ. ሂ
የተለያዩ ት/ቶችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችን #join ያድርጉና ይቀላቀሉ
https://telegram.me/IbnShifa
https://telegram.me/IbnShifa
30 viewsYunus omer, 13:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-25 16:01:26 እንዳትሆን ጠንቀቅ በል!
أَفَرَأَيْتَ مَنِ اتَّخَذَ إِلَهَهُ هَوَاهُ وَأَضَلَّهُ اللَّهُ عَلَى عِلْمٍ وَخَتَمَ عَلَى سَمْعِهِ وَقَلْبِهِ وَجَعَلَ عَلَى بَصَرِهِ غِشَاوَةً فَمَنْ يَهْدِيهِ مِنْ بَعْدِ اللَّهِ أَفَلَا تَذَكَّرُونَ
((ዝንባሌውን አምላኩ አድርጎ የያዘውን፣ አላህም ከእውቀት ጋር ያጠመመውን፣ በጆሮውና በልቡ ላይም ያተመበትን፣ በዐይኑም ላይ ሺፋን ያደረገበትን ሰው አየህን! ታዲያ ከአላህ በኋላ የሚያቀናው ማነው አትገሰፁምን)) (አልጃሢያህ፡ 23)
9. በኳስ ምክኒያት የራስህንም ሀላፊነት ያለብህን አካላትም ሐቅ እንዳትሸራርፍ፡፡ ሰርክ ኳስ እያሳደድክ በዚያ ሳቢያ ሀላፊነትህን ባግባቡ እየተወጣህ ካልሆነ አደጋ ላይ ነው ያለኸው፡፡ ነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም “ሁላችሁም እረኛ ናችሁ (ሀላፊነት አለባችሁ)፡፡ እያንዳንዳችሁም ስለእረኝነታችሁ (የተሸከማችሁት ሀላፊነት) ተጠያቂ ናችሁ) ይላሉ፡፡ መከታተሉ በጤናም ይሁን በትኛውም መልኩ እራስህንም የሚጎዳ መሆን የለበትም፡፡ አይደለም በቀልድና በዛዛታ ቀርቶ በዒባዳም እራስን መጎዳት አይፈቀድም፡፡ እስኪ ይህን ታሪክ አንዴ እንመልከት፡፡ ነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም መዲና ሲገቡ ሰልማኑልፋሪሲን እና አቡ ደርዳእን ረዲየላሁ ዐንሁማ ወንድማማች አድርገው አቆራኟቸው፡፡ ሰልማን አቡደርዳእን ሊጎበኝ ቤቱ ሲመጣ ሚስቱ ኡሙ ደርዳእ ረዲላሁ ዐንሃ እራሷን ጥላ አያት፡፡ “ምን ሆነሻል?” አላት፡፡ “አይ ወንድምህ አቡደርዳእ ለዱንያ ደንታ የለውም” ስትል እንዲያ የሆነችበትን ምክኒያት ነገረችው፡፡ ወዲያው አቡ ደርዳእ መጣ፡፡ ለሰልማን ምግብ አዘጋጀለትና “ብላ እኔ ፆመኛ ነኝ” አለው፡፡ ሰልማን ግን “አንተ ካልበላህ የምበላ አይደለሁም” አለው፡፡ ከዚያም (ፆሙን አፍርሶ) በላ…፡፡ ሌሊቱ ሲመጣ አቡ ደርዳእ ለሰላት ተነሳ፡፡ “ተኛ” አለው ሰልማን፡፡ ቆይቶም ተነሳ፡፡ “ተኛ” አለው አሁንም፡፡ የሌሊቱ መጨረሻ ሲደርስ ሰልማን እራሱ “ተነስ” አለውና አብረው ሰገዱ፡፡ ከዚያም ሰልማን እንዲህ አለው “ለጌታህ ባንተ ላይ ሐቅ አለ፡፡ ለራስህም ባንተ ላይ ሐቅ አለ፡፡ ለቤተሰብህም ባንተ ላይ ሐቅ አለ፡፡ እያንዳንዱን ባለሐቅ ሐቁን ስጥ!!” አቡ ደርዳእ ከነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ዘንድ ሄደና የሆነውን ነገራቸው፡፡ እሳቸውም “ሰልማን እውነት ተናገረ” አሉ፡፡ (ቡኻሪ የዘገቡት ነው) እንግዲህ አስተውል ሰሐባው በኳስ ሳይሆን በዒባዳ እንኳን እራሱን መጠበቅ እንዳለበት ተነግሮታል፡፡ አንተስ?
10. በኳስ ምክኒያት አጉል ወገንተኝነትና ዘረኝነት ውስጥ አትግባ!! ዘረኝነት የመሀይማን መገለጫ ነው!! ነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ((ተዋት! ምክኒያቱም እሷ (ዘረኝነት) ጥንብ ነችና!)) ይላሉ፡፡
11. በኳስ ምክኒያት አጉል ቁጣ ውስጥ አትግባ፡- ነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም “ምከረኝ” ያላቸውን ሰው (አትቆጣ!) ብለውታል፡፡ ደጋግሞ ሲጠይቃቸው ደጋግመው ((አትቆጣ!!) ብለውታል፡፡ “እከሌ ቡድን ተሸነፈ” ብሎ አጉል ብስጭት ውስጥ የሚገባን “ቂል” የሚለው ቃል በበቂ ሁኔታ ይገልፀው ይሆን?!! እኔ እንጃ!
12. አንዱን ቡድን ለመደገፍ በሚል ተልካሻ ሰበብ አታጨብጭብ! አትዝፈን! አትጨፍር፡፡ ዘፈን የተፈቀደው ውስን የሆኑ ክስተቶችን ምክኒያት በማድረግ ለሴቶች ብቻ ነው፡፡ ነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ይላሉ፡ (ሁለት ድምፆች የተረገሙ ናቸው!! የፀጋ ጊዜ መዝሙር እና የፈተና ጊዜ ዋይታ!!) “ወንድ ከዘፈነ ሴት ሆነ” ይላሉ ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያ እና ሸይኹል አልባኒ አላህ ይማራቸውና፡፡
13. ኧረ ከአቅል ሁን! ለመሆኑ ኳስ ሲከታተሉ ገደብ የለሽ ስሜት ውስጥ ስለገቡ ብቻ የሚሞቱ ሰዎች እንዳሉ ታውቅ ይሆን? ካላወቅክ በዚህ ላይ የተደረጉ ጥናቶችን አፈላልግ፡፡ “እከሌ ቡድን ተሸነፈ” ብለው እራሳቸውን የሚያጠፉ እንደሚያጋጥሙስ ይሰወርህ ይሆን? ብቻ ከኳስ ጋር በተያያዘ በየትኛውም ምክኒያት ህይወትህን ብታጣ ነገ አላህ ፊት መልስህ ምን እንደሚሆን ከወዲሁ አስብበት!! ጂሃድ ላይ አስደናቂ ጀብዱ ሲፈፅም ውሎ በደረሰበት ቁስለት ስቃዩን መቋቋም አቅቶት እራሱን የገደለውን ሰው ነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም “የእሳት ነው!” ማለታቸውን አትዘንጋ፡፡ አንተ ከሱ የተሻለ አሳማኝ ምክኒያት ካለህ ቀጥልበት!! አስተውል! ሞት አማክሮ አይመጣም፡፡
14. በኳስ ምክኒያት አንዱን በመደገፍ ሌላውን በመንቀፍ፣ ሌሎችን ለማናደድ፣ ወይም እንዲሁ በአጉል ብስጭት ፀያፍ ቃላትን አታውጣ! ዘወትር “ሐያእ” አይለይህ፡፡ ነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ምን እንደሚሉ አስተውል!
((الْبَذَاءُ مِنَ الْجَفَاءِ, وَالْجَفَاءُ فِي النَّارِ, وَالْحَيَاءُ مِنَ الْإِيمَانِ, وَالْإِيمَانُ فِي الجنة))
((ፀያፍ ቃላት መጠቀም ዋልጌነት ነው! ዋልጌነት ደግሞ ወደ እሳት ነው!! “ሐያእ” ከኢማን ነው፡፡ ኢማን ደግሞ ወደ ጀነት ነው!!)) ሸይኹል አልባኒ “ሰሒሕ” ብለውታል፡፡ (አስ-ሰሒሐህ፡ 495)
15. ኳስ ለመመልከት ብለህ ከአጅነቢ ሴት ጋር ተቀላቅለህ እንዳትቀመጥ፡፡ መቀላቀሉ ሌላው ቀርቶ ሰይጣናዊ ጉትጎታ ከሚቀንስበትም ቦታም አልተፈቀደም፡፡ ለሴቶች ከመስጂድ ይልቅ ቤታቸው እንዲሰግዱ መመረጡን ለመስገድ ከወጡም ሽቶ ሳይቀቡ፣ ሳይዋዋቡ መሆኑን አስተውል፡፡ ነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም “ከወንዶች የሰላት ሰፎች በላጩ የመጀመሪያው ነው፣ የከፋው ደግሞ የመጨረሻው (ለሴቶቹ የሚቀርበው) ነው፡፡ ከሴቶቹ የሰላት ሰፎች ደግሞ በላጩ የመጨረሻው (ከወንዶች የራቀው) ነው፡፡ የከፋው ደግሞ የመጀመሪያው (ለወንዶቹ የቀረበው) ነው” ማለታቸውን አስተውል፡፡ ሌላው ቀርቶ ነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ወንዶችና ሴቶች ከመስጂድ ውጭ ከሰላት ሲመለሱ ቢቀላቀሉ ሴቶቹን “ወደ ኋላ ሁኑ” ብለው ዳር ይዘው እንዲሄዱ ነው የነገሯቸው፡፡
16. ኳስ ለማየት ብለህ አስካሪ መጠጥ ከሚሸጥበት ወይም ከሚጠጣበት “ባር” እና “ካፍቴሪያ” ውስጥ ወይም ሌሎች ወንጀሎች ከሚፈፀሙባቸው አካባቢዎች ድርሽ እንዳትል፡፡ አላህን ፍራ! እምነትህንም እራስህን አክብር፡፡
ኢን ሻአላህ ከቻልኩ በዚህ ጉዳይ የኡለማዎችን ብይን አሰባስቤ ለመመለስ እሞክራለሁ፡፡
~----~~ ----
(ኢብኑ ሙነወር፣ ሃምሌ 03/2006)
የቴሌግራም ቻናል
https://t.me/IbnuMunewor
34 viewsአቡ ሐናን, 13:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-25 15:55:57 ጥቂት ምክር ለኳስ ጨዋታ ተመልካቾች
~ ~ ~~ ~~~~ ~~~
1. ኳስ እየተመለከትክ ወይም በኳስ ምክኒያት እንቅልፍህን አጥተህ ሰላት እንዳታሳልፍ!! ልብህ በህይወት ካለ ደወል እየተደወለ ነው፡፡ ስማ!!
فَخَلَفَ مِنْ بَعْدِهِمْ خَلْفٌ أَضَاعُوا الصَّلَاةَ وَاتَّبَعُوا الشَّهَوَاتِ فَسَوْفَ يَلْقَوْنَ غَيًّا
((ከእነርሱም (ከነቢያቱ) በኋላ ሰላትን ያጓደሉ፣ ከንቱ ፍላጎቶችንም የተከተሉ፣ መጥፎ ምትኮች ተተኩ! የጀሀነምንም ሸለቆ በእርግጥም ያገኛሉ!!)) (መርየም፡ 59) አስተውል! አይደለም ስንት አላስፈላጊ ኮተት አጭቆ በያዘው እግር ኳስ ምክኒያት ይቅርና አንድ ሰው በተራዊሕ ሰላት ምክኒያት ማምሸቱ የፈጅር ሰላትን በወቅቱ እንዳይሰግድ የሚያደርገው ከሆነ ተራዊሕ ሰላት መስገዱም አይፈቀድለትም፡፡ በኳስ ምክኒያት እያመሹ የፈጅር ሰላትን ማሳለፉስ ይቻል ይሆን? ብይኑን ለራስህ ትቼዋለሁ፡፡ እስኪ ህሊናህን አዳምጠው፡፡
2. ለኳስ ብለህ የወላጆችን ሐቅ አትጣስ! ቁርኣኑ “ ‘ኦፍ’ አትበሏቸው” ይላል ዛሬ ግን በጋጠ-ወጥ ልጃቸው ሰዐት እላፊ በራቸው ይደበደባል፣ ጎል ገባ ተብሎ ይጮህባቸዋል፡፡ የሚደግፈው ቡድን “ተሸነፈ” ብሎ እየተበሳጨ ይገባባቸዋል፡፡ ካሁን ካሁን ምን አግኝቶት ይሆን እያሉ በስጋት ይጨርሳቸዋል፡፡ … ኧረ ስንቱ! ጌታችን አላህ እንዲህ ይላል፡-
وَقَضَى رَبُّكَ أَلَّا تَعْبُدُوا إِلَّا إِيَّاهُ وَبِالْوَالِدَيْنِ إِحْسَانًا إِمَّا يَبْلُغَنَّ عِنْدَكَ الْكِبَرَ أَحَدُهُمَا أَوْ كِلَاهُمَا فَلَا تَقُلْ لَهُمَا أُفٍّ وَلَا تَنْهَرْهُمَا وَقُلْ لَهُمَا قَوْلًا كَرِيمًا (23) وَاخْفِضْ لَهُمَا جَنَاحَ الذُّلِّ مِنَ الرَّحْمَةِ وَقُلْ رَبِّ ارْحَمْهُمَا كَمَا رَبَّيَانِي صَغِيرًا (24)
((ጌታህም (እንዲህ ሲል) አዘዘ፡- “እርሱን እንጂ ሌላን አትገዙ፡፡ በወላጆቻችሁም መልካምን ስሩ፡፡ በአንተ ዘንድ ሆነው አንዳቸው ወይም ሁለታቸው እርጅናን ቢደርሱ “ኦፍ” አትበላቸው፡፡ አትገላምጣቸውም፡፡ ለእነርሱም መልካምን ቃል ተናገራቸው፡፡)) (አልኢስራእ፡ 23-24) ለመሆኑ ልባችን በህይወት አለ? ቁርኣን ሲነበብ የሚደነግጥ ይኖር ይሆን?
3. መሰረታዊ የእምነትህን ድንጋጌዎች ሳትለይ ነጋ ጠባ ኳስ ላይ የምታፈጥ ከሆነ አትጠራጠር ኪሳራ ላይ ነው ያለኸው!! እርግጥ ነው ሸሪዐችን ሐላል በሆኑ ነገር እራስን ዘና ማድረግን አይከለክልም፡፡ ነገር ግን ሐላል በሆነ ነገር ከዋጂብ መዘናጋትን አይፈቅድም፡፡ የእምነቱ ምሰሶ የሆነውን ተውሒድና ከአደጋው ሁሉ የከፋውን የሺርክ አደጋ በቅጡ ሳይለይ፣ ሰለሰላት፣ ሰለፆም፣… ስለሌሎችም መሰረታዊ የዲኑ ክፍሎች እዚህ ግባ የሚባል እውቀት የሌለው ሰው በኳስ ላይ ጊዜውን እንዲያጠፋ የሚፈቅድለት እምነቱ ይቅርና የትኛው ህሊና ነው?! ይሄ ችላ ካላሉት በቀር ብዙም ማሰብ አይጠይቅም፡፡ ማንም የሚደርስበት ግልፅ የሆነ ስሌት ነውና፡፡ “ነገ ከመመርመራችሁ በፊት ዛሬ እራሳችሁን መርምሩ” ይላል ዑመር ኢብኑልኸጣብ፡፡ ከአላህ ፊት ስላጠፋሃው ጊዜ፣ ገንዘብና ወጣትነትህ እንደምትጠየቅ አትርሳ፡፡ ነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ይላሉ፡-
لاَ تَزُولُ قَدَمَا عَبْدٍ يوم القيامة حَتَّى يُسْأَلَ عَنْ خمس، عَنْ عُمْرِهِ فِيمَا أَفْنَاهُ؟ وعن شبابه فيما أبلاه؟ وَمَالِهِ مِنْ أَيْنَ اكْتَسَبَهُ؟ وَفِيمَا أَنْفَقَهُ؟ وماذا عمل فيما علم؟
((የቂያማ እለት ከአምስት ነገሮች ሳይጠየቅ የአንድ ባሪያ እግሮች አይንቀሳቀሱም! እድሜውን በምን እንዳጠፋው፤ ወጣትነቱን በምን እንደጨረሰው፣ ገንዘቡን ከየት እንዳገኘው፤ እና በምን ላይ እንዳዋለው፤ በእውቀቱ ምን እንደሰራበት፤)) አልባኒ “ሰሒሕ ብለውታል፡፡ (አስ-ሰሒሐህ፡ 946)
4. ኳስ እመለከታለሁ ብለህ ከዐጅነቢ ሴቶች ላይ ጋር ተቀላቅለህ አትቀመጥ፣ ከአጅነቢም ላይ አታፍጥጥ!
قُلْ لِلْمُؤْمِنِينَ يَغُضُّوا مِنْ أَبْصَارِهِمْ وَيَحْفَظُوا فُرُوجَهُمْ ذَلِكَ أَزْكَى لَهُمْ إِنَّ اللَّهَ خَبِيرٌ بِمَا يَصْنَعُونَ
((ለአማኞችም ንገራቸው፡- ዐይኖቻችሁን (ያልተገባ ነገር ከማየት) ይስበሩ፣ ብልቶቻቸውንም ይጠብቁ፣ ይህ ለነሱ የተሻለ ነው፡፡ አላህ በሚሰሩት ሁሉ ውስጥ አዋቂ ነው፡፡)) (አን-ኑር፡ 30) ውድድሩ የሴቶች እግር ኳስ ከሆነ ግን አትጠራጠር በሐራም እየተጨማለቅክ ነው!! ሀፍረተ-ገላቸውን ያልሸፈኑ ሰዎችን እየተከታተልክ ከሆነም ስሜትህ ልቦናህን ሸፍኖት ካልሆነ በስተቀር ሐቁ አይሰወርህም፡፡ ባይሆን እኔ የወንድምነት ሃላፊነቴን አድርሻለሁ! “አላህን ፍራ!!” ብያለሁ፡፡
5. ላንቃህ እስኪበጠስ አትጩህ! ድምፅህን ዝቅ አድርግ፡፡ ወከባ ቀንስ፡፡ ጎረቤት አትረብሽ! ሀያሉ ጌታ አላህ ምን እንደሚል ረጋ ብለህ አስተውል!
وَاقْصِدْ فِي مَشْيِكَ وَاغْضُضْ مِنْ صَوْتِكَ إِنَّ أَنْكَرَ الْأَصْوَاتِ لَصَوْتُ الْحَمِيرِ
((በአካሄድህም መካከለኛ ሁን፡፡ ከድምፅህም ዝቅ አድርግ፡፡ ከድምፆች ሁሉ አስቀያሚው የአህዮች ድምፅ ነውና!!)) (ሉቅማን፡ 19) የቤት ስራ ሰጥቼሃለሁ፡፡ በጮህክ ቁጥር የአህዮችን አስቀያሚ ድምፅ አስታውስ፡፡ ጯሂዎችን አላህ በምን እንደመሰላቸውም በህሊናህ ያዝ፡፡
6. ተረጋጋ!! የምትደግፈው ቡድን ስላሸነፈ አትንቀባረር፡፡ አትጎረር፡፡ ስርኣት አልባ አትሁን! ሀያ ምናምን ወጠምሾች ከሆነ ሜዳ ውስጥ አንዲት ቅሪላ ተከትለው ከመሯሯጣቸው ውጭ ይህን ያክል ጮቤ የሚያስረግጥ ምንም ነገር የለም፡፡
وَلَا تُصَعِّرْ خَدَّكَ لِلنَّاسِ وَلَا تَمْشِ فِي الْأَرْضِ مَرَحًا إِنَّ اللَّهَ لَا يُحِبُّ كُلَّ مُخْتَالٍ فَخُورٍ
((ጉንጭህንም (በኩራት) ከሰዎች አታዙር፡፡ በምድርም ላይ ተንበጥርረህ አትሂድ፡፡ አላህ ተንበጣራሪን ጉረኛን ሁሉ አይወድምና!!) (ሉቅማን፡ 18)
7. ከቡድንና ከጨዋታ ጋር በተያያዘ ለቀልድና ለተረብ እያልክ አትዋሽ!! ውሸት አስቀያሚ ነቀርሳ ነው!! ሰሚ ጆሮ ካለህ ነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ይላሉ፡-
وَيْلٌ لِلَّذِي يُحَدِّثُ بِالْحَدِيثِ لِيُضْحِكَ بِهِ الْقَوْمَ فَيَكْذِبُ وَيْلٌ لَهُ وَيْلٌ لَهُ
((ሰዎችን ለማሳቅ ብሎ እየዋሸ ወሬን የሚያወራ ሰው ወዮለት! ወዮለት! ወዮለት!!)) አልባኒ “ሐሰን” ብለውታል፡፡
8. የኳስ ፍቅርህን ለከት አርግለት፡፡ ለኳስ ብለህ የምትጠላ፣ ለኳስ ብለህ የምትወድ፣ በኳስ ምክኒያት ሐራም ላይ የምትወድቅ፣ በኳስ ምክኒያት እምነታዊ ግዴታዎችን የማትፈፅም ከሆንክ አትጠራጠር ኳሱን ጣኦት አድርገህ ይዘኸዋል ማለት ነው፡፡ መልእክተኛው ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም “የዲናር ባሪያ ጠፋ! የዲርሃም ባሪያ ጠፋ! … ሲሰጡት ይወዳል! ካልሰጡት ይጠላል” ይላሉ፡፡ ዛሬ ኳስ ከገንዘብ ባልተናነሰ ምናልባትም በባሰ ሁኔታ ጣኦት ሆኖ በገሃድ እየታየ ነው፡፡ ይሄ ስሜትን አምላክ ማድረግ ካልሆነ ምን ሊሆን ነው! በሚከተለው አንቀፅ ከተገለፁት
32 viewsአቡ ሐናን, 12:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-22 23:48:38 ጥቂት ነጥቦች በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ
~ ~ ~ ~~~ ~~~~ ~~~~
1- ቁርኣናችን ማንም የማንንም ወንጀል እንደማይሸከም በግልፅ ያስቀምጣል። የትኛውም ሰው ቢበድለን በዘር ሰንሰለት እያገናኘን በጅምላ ሌሎች ላይ አንፍረድ። በሌሎች ጉዳትም አንደሰት።
2- አቅማችንን እንወቅ። ከአቅማችን በላይ በሆነ ጉዳይ ውስጥ እየገባን አናቡካ። አደብ ይኑረን። እውነት ለመናገር ብዙዎቻችን ሚሊዮኖችን ስለሚያነካካ ጦርነት ቀርቶ በአንፃራዊነት ቀላል ስለሚባሉ የፊቅህ ርእሶች እንኳ ለማውራት አቅም የለንም። ሁሉ ነገር ላይ ሃሳብ ካልሰነዘርን አንበል።
3- ከየብሄሩ የግጭት ተዋንያን ያልሆኑ፣ ግና በግጭቱ ሳቢያ ዘመድ፣ ቤተሰብ የተጎዳባቸው ብዙ ምስኪን ወገኖች እዚሁ ማህበራዊ ሚዲያ ውስጥ አሉ። የምንፅፈውን ያያሉ፣ የምንናገረውን ይሰማሉ። ኢንሻአላህ ይሄ ቀን ያልፋል። ለሚያልፍ ቀን የማያልፍ ቃል አንናገር። ያመጣልንን እያወራን በቁስላቸው ላይ እንጨት እየሰደድን እንዳንጎዳቸው፣ ቅስማቸውን እንዳንሰብር እንጠንቀቅ።
4- በያካባቢው ለፖለቲካ ባይተዋር የሆኑ ወገኖች መርጠው ባልተፈጠሩበት ብሄር የተነሳ ሲሳደዱ ማየት የተለመደ ሆኗል። ከፊሎች ወቅታዊ ፍተሻዎችንና ክትትሎችን ተከትሎ ያለ ወንጀላቸው ለቂም በቀል ጥቃትና ለስግብግብ ጅቦች ሲሳይ ሆነዋል። እነዚህን ወገኖች ብንችል ልናግዛቸው፣ አጥፊዎችን ልናወግዝ ይገባል። እሱ ቢቀር በሞራል እንኳ ከጎናቸው ልንቆም ይገባል። እንጂ ፈፅሞ ለበደል አጋዥ እንዳንሆን መጠንቀቅ አለብን።
5- ከሞቱ፣ ከንብረት ውድመቱ ባሻገር በተለያዩ የሃገራችን ክፍል እልፍ አእላፍ ከቀያቸው ተፈናቅለዋል። ሌሎች ደግሞ መሸሸም ቅንጦት ሆኖ አጣብቂኝ ውስጥ ገብተው ከዛሬ ነገ እልቂትን እየጠበቁ የሰቀቀን ህይወት እየገፉ ነው። 30ሺ እና 40ሺ የሚያወጡ ንብረቶቻቸውን 2ሺ እና 3ሺ እንኳ እንዳይሸጡ ታድሞባቸው እየተንከራተቱ ነው። እነዚህን ወገኖች የምናግዝበት አቅሙ ካለን እናግዛቸው። እሱ ቢቀር ቢያንስ በዱዐ አንርሳቸው።
6- አሰሰ ገሰሱን ሁሉ እየተከታተልን ለጅላጅል የዩቲዩብ ቃራሚዎች መጠቀሚያ አንሁን። ጥላቻን የሚዘሩ ስራዎችን ከማሰራጨት እንቆጠብ። የሴራ ፖለቲካ ከሚተነትኑ ከንቱዎች እንራቅ። ይልቁንም ትኩረታችን ለዱያንም ሆነ ለአኺራ በሚጠቅመን ላይ ይሁን። በዱዓ ላይ እንበርታ።

የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor
43 viewsአቡ ሐናን, 20:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-22 07:19:46 ኢስላምን ለልጆች ማስተማር፡፡
ክፍል 1
እድሜያቸው ከ3-6 አመት
ላሉ ታስቦ የተዘጋጀ
https://t.me/SadatKemalAbuMeryem/3851
44 viewsአቡ ሐናን, 04:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ