Get Mystery Box with random crypto!

ቅዱሳት መካናት

የቴሌግራም ቻናል አርማ kidusat_mekanat — ቅዱሳት መካናት
የቴሌግራም ቻናል አርማ kidusat_mekanat — ቅዱሳት መካናት
የሰርጥ አድራሻ: @kidusat_mekanat
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.51K
የሰርጥ መግለጫ

ስለ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ገዳማትና አድባራት መረጃ መለዋወጫ ቻናላችንን ይቀላቀሉ ዘንድ የተዋህዶ ልጆችን ይጋብዙ
ለማንኛውም ጥያቄ
@betewali
@Zegedamat
💚👇❤ በፌስቡክ ያግኙን 💚👇❤
👉 https://www.facebook.com/abageorgis/
👉 https://m.facebook.com/zegedamat/

Ratings & Reviews

4.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-09-01 14:20:34 እንኳን ለታላቁ ጻድቅ ለአቡነ ሀብተ ማርያም ዓመታዊ በዓለ ክብር በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ!
ውድ የተዋህዶ ልጆች፦ ይህን ዘመንም በሰላም አስፈፅሞ ለቀጣይ አዲስ ዓመት ያድርሰንና በየዓመቱ መስከረም 21 ቀን የሚከበረውን የብዙኃን ማርያም ንግሥ በዓለ ክብር ምክንያት በማድረግ ከመስከረም 15 እስከ 26 ድረስ እንደተለመደው ወደ ግሸን ደብረ ከርቤ በማኅበረ ቅዱስ ፊልጶስ ወአቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ ልዩ ጉዞ የተዘጋጀ ሲሆን የጉዞ ተቀማጭ እና ምዝገባ ጀምረናል።
★ የጉዞ ዋጋ ማረፊያና መስተንግዶ ጨምሮ 5000 ብር
★ ለግሸን ነዳያን አስቤዛ ፤ አልባሳት እና ለገዳማት ዕጣን ፤ ዘቢብ ፤ ጧፍ ፤ ሻማ ፤ አልባሳት ፤ መጻሕፍት በአጠቃላይ ነዋየ ቅድሳት እንዲሁም ለአስኳላ ተማሪዎች ደብተር ፤ እስራስ ፤ እስክሪብቶ ፤ ቦርሳ ፤ ጫማ ለመርዳት እና ለመለገስ ቃል ገብታችሁ ገቢ ያላደረጋችሁ ከወዲሁ ገቢ እንድታደርጉ አደራ እያልን ነገር ግን ቃል ያልገባችሁ ደግሞ ቃል በመግባት እንድትለግሱ በእመቤታችን እንዲሁም በአምላከ ቅዱሳን ስም መልዕክታችንን እናስተላልፋለን።
★ በዚህ ጉዟችን፦
1ኛ) ደመራን መስቀልን በመስቀሉ ሥፍራ በግሸን ማርያም እናከብራለን።
2ኛ) ከእኛ ጋር ወደ ግሸን ሲጓዙ እንደተለመደው በርካታ ጥንታዊ ገዳማትና አድባራትን ይሳለማሉ።
• ደብረ ባሕርይ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ገዳም (ዋሻ)
• ጋስጫ አቡነ በጸሎተ ሚካኤል ገዳም (ዋሻ)
• «አባ ቅዱስ» በተሰኘው ፈዋሽ ጠበሉ የገባበትን እንጨት ሁሉ መቁጠራያ አድርጎ የሚሰጠው ተአምረኛው አቡነ ገብረ እንድርያስ ገዳም
• ደብረ ጽጌ አባ ጽጌ ድንግል ገዳም (ዋሻ)
• ተአምረኛው ደብረ መድኃኒት አቡነ መልከ ጼዴቅ ገዳም (ዋሻ)
• ጥንታዊው በልበሊት ኢየሱስ ገዳም
• ታሪካዊቷ ትርንጎ ማርያም
• ጥንታዊው ኤልሻማ መድኃኔዓለም ገዳም
• ታሪካዊው ተንታ ንጉሥ ሚካኤል
• ታሪካዊቷ ደብረ ጽጌ ማርያም ገዳም
• ጥንታዊው ደብረ ነጎድጓድ ሐይቅ እስጢፋኖስ ወቅ/ኪዳነ ምሕረት አንድነት ገዳም
• ጥንታዊው ሐይቅ ቅ/ጊዮርጊስ
• ተአምረኛው ግሸን ዋሻ ቅ/ጊዮርጊስ
• ጥንታዊቷ ወንዳንቺ ማርያም ገዳም
• ተአምረኛው ጠረግ ምችግ ኢየሱስ
• በመስቀለኛዋ ጥንታዊት ደብር በግሸን አምባ ላይ የሚገኙትን፦
→ አቡነ ከናፍረ ክርስቶስ የተባሉ ጻድቅ መነኮስ በ5ኛው መ/ክ/ዘ ታቦታቱን ከናግራን አምጥተው በሳር ጎጆ የመሠረቷቸው ጥንታዊዎቹ ግሸን እግዚአብሔር አብ እና ግሸን ማርያም፣
→ ቅዱስ ያሬድ በድጓው ቦታውን «ደብረ ሚካኤል» ብሎ ትንቢት ተናግሮለት በቀደሙ አበው የተመሠረተው ተአምረኛው ግሸን ሚካኤል፣
→ ግሸን ቅ/ገብርኤል እና ግሸን ቅ/ዑራኤል፣
• ታሪካዊው ደብረ ብርሃን ቅ/ሥላሴ
• ሳር አምባ ቅ/ኪዳነ ምሕረት ገዳም
• ተአምረኛው ሰንበቴ ቅ/ሚካኤል፣ እና ሌሎችንም ያካተተ ድንቅ ጉዞ ነው።
*** ጊዜያችንን በአግባቡ ከተጠቀምን አንድ ገዳም ሰርፕራይዝ ይደረጋል።

ለዚህ ልዩ የጉዞ መርሐ ግብር ምዝገባ የጀመርን ሲሆን እርሶም የመሄድ አሳብ ካለዎት ሳይሞላ በጊዜ ይመዝገቡ።

ይህንን የመንፈሳዊ ጉዞዎች መልእክት እንደደረሰዎ እርሶ በሚጠቀሙበት በማንኛውም ድህረ ገጽ ላይ ሼር በማድረግ ይተባበሩን አደራ።
ለበለጠ መረጃ፦
09111289877 / 0901070707
189 viewsዘዋልድባ 0901070707, edited  11:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-10 19:53:54 #አድርሺኝ
በጎንደር ከተማ በፍልሰታ ለማርያም ጾም ወቅት በካህናቱ፤ በሰንበት ትምህርት ቤት አባላትና በምእመናን አማካይነት በየዓመቱ የሚከናወን የተለመደ ሥርዓት አለ፡፡ ይህም ሥርዓት “አድርሺኝ” በመባል ይታወቃል፡፡

በጎንደር ከነገሡት ነገሥታት መካከል ከ1703-1708 ዓ.ም. ለአምስት አመታት በንግሥና የቆዩት ዐፄ ዮስጦስ የጎንደር መካነ ስብሐት ልደታ ለማርያም ቤተ ክርስቲያንን በመትከል የሚታወቁ ሲሆን፤ አድርሽኝ የተሠኘውንም ሥርዓት በእርሳቸው እንደተጀመረ ይነገራል፡፡

ስለ ሥርዓቱ አጀማመር አባቶች ሲናገሩ፣ ዐፄ ዮስጦስ ተቀናቃኞቻቸው የከፈቱባቸውን ጦርነት ለመመከት ወደ ጦርነት ሲዘምቱ “ልደታ ለማርያም ሳትለዪኝ በድል ብትመልሺኝ፤ ለዚህም ታላቅ ክብር ብታደርሺኝ በየዓመቱ በፍልሰታ ለማርያም ሱባኤ ካህናቱን፤ መኳንንቱንና ምእመናንን ሰብስቤ ግብዣ አደርጋለሁ” በማለት ብፅዐት ይገባሉ፡፡ እርሳቸውም ድል አድርገው በመመለሳቸው በቃላቸው መሠረት በጎንደር መካነ ስብሐት ልደታ ለማርያም ቤተ ክርስቲያን ደጀ ሰላም ሕዝቡን ሰብስበው ግብዣ ማድረጋቸውን ቀጠሉ፡፡ ሕዝበ ክርስቲያኑም እርሳቸውን ተከትሎ በየዓመቱ በጾመ ፍልሰታ ወቅት ይህንን ሥርዓት ይተገብሩት ጀመር፤ ስያሜውም “አድርሺኝ” ተባለ፡፡

አድርሺኝ በመላው ጎንደር በየአብያተ ክርስቲያናቱና በየአካባቢው በፍልሰታ ጾም ወቅት ይከናወናል፡፡ ምእመናን ከቅዳሴ መልስ ሱባኤው እስኪጠናቀቅ በመረጡት አንድ ቤት ውስጥ ተሰብስበው ቆሎና ጠላ አዘጋጅተው በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ስም ጽዋ ይጠጣሉ። በተለይም መነኮሳይያት እናቶች በሚታደሙበት ጽዋ ላይ “ኦ! ማርያም” የሚለውን የተማጽኖ መዝሙር ይዘምራሉ። ይህ መዝሙር በሚዘመርበት ጊዜ ያለ ምንም ጥርጥር እመቤታችን ፊት ለፊት ትቆማለች ተብሎ ስለሚታሰብ በፍጹም ተመሥጦና በመንበርከክ ያከናውኑታል።

የጎንደር መካነ ስብሐት ልደታ ለማርያም ቤተ-ኤስድሮስ ሰንበት ት/ቤት ወጥነት እንዲኖረው በማሰብ ይህንን የእናቶች የምሕላ ዝማሬ ለተተኪ ትውልድ ለማስተላለፍ እንዲቻል አሰባስቦ አዘጋጅቶታል፡-

ኦ! ማርያም
ኦ! ማርያም እለምንሻለሁ ባሪያሽ፤
እስኪ አንድ ጊዜ ስሚኝ ቀርበሽ፤ ከአጠገቤ ቆመሽ፤
ፅኑ ጉዳይ አለኝ ላንቺ የምነግርሽ፤
የዓለሙን መከራ ያየሽ፤
በእናትሽ በአባችሽ ሀገር፤
በምድረ ግብፅ ዞረሽ ውሃ የለመንሽ፡፡
ከሁሉ ሁሉ ጤፍ ታንሳለች፤
ከጭቃ ወድቃ ትነሳለች፤
ስትነሳ /2/ የአዳም ልጅ ሁሉ ሞትን ረሳ፤
የአዳም ልጅ ሁሉ ሰነፈና የኑሮ ቤቱን ረሳና፤
ተው አትርሳ /2/ ተሠርቶልሃል የእሳት ሳንቃ፡፡
ያን የእሳት ሳንቃ፤ የእሳት በር፤
እንደምን ብዬ ልሻገር፤
ተሻገሩት አሉ የሠሩ ምግባር፤
እኔ ባሪያሽ እንዴት ልሁን? ሰላም ሰጊድ /2/
በመሥቀሉ ሥር ያያትን ተሰናበታት እናቱን፤
እናትዬ ለምን ታለቅሻለሽ ተሰቅዬ፤
ይስቀሉኝ ሐሰት በቃሌ ሣይገኝ፡፡
ንፅሕት የወልደ እግዚአብሔር እናት፤
ንፅህት በፍቅሯ ወዳጆቿን ስትመራ፤
ንፅሕት በቀኝ ወዳጆቿን ስትጎበኝ፤
የእኛስ እመቤት ያች ሩኅሩኅ፤
ከለላችን ናት እንደ ጎጆ፤
እርሷን ብለው ጤዛ ልሰው ኖሩ ትቢያ ለብሰው /2/
ኪዳነ ምሕረት ሩኅሩኅ ተይ አታቁሚኝ ከበሩ፤
የገነሃም እሣት መራራ ነው አሉ፤
እኔ ባሪያሽ እንዴት ልሁን? ሰላም ሰጊድ /2/
ድንግል ማርያም ንፅሕት፤
የምክንያት ድኅነት መሠረት፤
እንለምንሻለን ወደ አንቺ አንጋጠን፤
ከፈጣሪ በይ አማልጅን ሰላም ሰጊድ /2/
ኃያል /2/ ቅዱስ ሚካኤል ኃያል፤
የለበሰው ልብሱ የወርቅ ሐመልማል፤
ይህም ተጽፏል በቅዱስ ቃል ሰላም ሰጊድ /2/
ጊዮርጊስ ስልህ ዘንዶ ሰገደ ከእግርህ፤
እፁብ ድንቅ ይላሉ ገድልህን የሰሙ፤
አንተ አማልደኝ ከሥልጣኑ ሰላም ሰጊድ /2/
አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ደግ አባት፤
መጥቼልሃለሁ ከደጋ፤
ስንቄንም አድርጌ አጋምና ቀጋ፤
አንተ አማልደኝ ከፈጣሪ ሰላም ሰጊድ /2/
ፃድቅስ ባያችሁ ተክለ ሃይማኖት፤
በአንድ እግር ቆመው ሰባት ዓመት፤
በተአምኖ ሰባት ባቄላ ምግብ ሆኖት /2/
ተክለ ሃይማኖት አባቴ፤
መሠላሌ ነህ ለሕይወቴ፤
የዓለሙን ኑሮ መጥፎነቱን፤
የፈጣሪያችን ቤዛነቱን፤
አስተውለኸው አጥንተኸው፤
ደብረ ሊባኖስ የተሰዋኸው፡፡
ክርስቶስ ሠምራ እናታችን፤
ከአምላካችን ፊት መቅረቢያችን፤
ሣጥናኤልን አሸንፈሽ፤
ከግዛቱ ውስጥ ነፍስን ማረክሽ፡፡
ክርስቶስ ሠምራ ቅድስቷ፤
ለጽድቅ ሕይወት አማላጇ፤
እንለምንሻለን ወደ አንቺ አንጋጠን፤
ከፈጣሪ በይ አማልጅን ሰላም ሰጊድ /2/
ኦ! አባቴ አንተ ረኃቤ ነህ ጥማቴ፤
የኔ መድኃኒት ኃያል ተመልከተን ዝቅ በል፤
የነገሩህን የማትረሳ፤
የለመኑህን የማትነሳ፤
አምላኬ አንተ ነህ አምባዬ፤
የሕይወት ብርሃን ጋሻዬ፡፡
ማርያም ስሚን ወደ ሕይወት መንገድ ምሪን፤
ከአጠገባችን ቁጭ ብለሽ አድምጭን፤
ይደረግልን ልመናሽ ስትመጪ /2/
አንቺ እናቴ ሆይ /2/ የሔድሽበትን ትቢያ ቅሜ፤
ያረፍሽበትን ተሳልሜ፤
በሞትኩኝ /2/ የኋላ ኋላ ላይቀር ሞት፡፡ /2/

በፍልሰታ ለማርያም ጾም ወቅት ዘወትር ከቀኑ 11፡00 ጀምሮ በቤተ-ኤስድሮስ ሰንበት ት/ቤት ካለፉት 30 ዓመታት ጀምሮ ጸሎት ዘዘወትር፣ ውዳሴ ማርያም፣ ይዌድስዋ መላእክት፣ መዝሙረ ዳዊት 50 እና 135፣ ጸሎተ ምናሴ፣ መሐረነ አብ ጸሎት በዜማ ከተጸለየ በኋላ ኦ! ማርያም የምሕላ መዝሙር ይዘመራል፡፡

ምንጭ፦ መካነ ስብሐት ልደታ ለማርያም ሰንበት ት/ቤት
1.6K viewsእልመስጦአግያ ዘሐዋርያት, 16:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-31 09:05:59
882 viewsፊልጶስ, 06:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-31 09:05:37
733 viewsፊልጶስ, 06:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-31 09:05:18 #ሐጊያ_ሶፊያ - #ቅድስት_ጥበብ (#Hagia_Sophia)
"ሐጊያ ሶፊያ" ወይም "ቅድስት ጥበብ" (Holy Wisdom) በሚለው የመድኃኔዓለም ስሙ የተሰየመው ይህ የእግዚአብሔር ወልድ ቤተ ክርስቲያን በቁስጥንጥንያ መንበር ታላቁ ሕንጻ ቤተ ክርስቲያን ሲሆን እጅግ አስደናቂ የሕንጻ ጥበብ የታየበትና የብዙ ቅዱሳን አጽም ያረፈት ታላቅ ካቴድራል ነበረ። ሀጊያ ሶፊያ ታላቁ ሊቅ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ወንበር ተክሎ ጉባዔ ዘርግቶ ያስተማረበትና በርካታ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን የፈሩበት ጥንታዊ ካቴድራል ነው። በኢትዮጵያ ገዳማዊ ሕይወትን ያስፋፉት ተሰዓቱ ቅዱሳንም በወቅቱ በሮም ግዛት ስር ከነበረቺው ቁስጥንጥንያ (የአሁኗ ኢስታንቡል) ከዚህ መንበር በተገኘ መንፈሳዊ እውቀት የከበሩ ደጋግ አበው ቅዱሳን ናቸው።

በኦርቶዶክሳዊያንና በዓለም የክርስትና ታሪክ ውስጥ ታላቅ ሥፍራ ያለውና በዩኔስኮ ከተመዘገቡ የዓለም ቅርሶች አንዱ የሆነው ይህ ካቴድራል በ1453 GC ቁስጥንጥንያ በኦቶማን ቱርክ እጅ ስትወድቅ በሱልጣን መሐመድ ዳግማዊ ትእዛዝ ወደ መስጊድነት ተቀይሯል። ከ1934 GC እስከ 2020 GC (ሐምሌ 3 ቀን 2012 ዓ.ም) ድረስ ለ86 ዓመታት ደግሞ ወደ ሙዝየምነት ተቀይሮ የቀደመ ታሪኩ ብቻ እየተነገረ ለጎብኚ ክፍት ሆኖ ቆይቷል። ከ10/07/2020 በኋላ ደግሞ ወደ መስጊድነት ቀይረውታል።

በታሪካዊው የቅድስት ሐጊያ ሶፍያ ካቴድራል ወደ መስጊድነት ከተቀየረ ከወር በሗላ በፈረንጆቹ ነሐሴ 15 ቀን 2020 (9/12/2012 ዓ.ም) በዕለተ ዐርብ በቦታው በማሰገድ ላይ የነበረው ኢማም በድንገት ወዲያውኑ ሕይወቱ ሊያልፍ ችሏል። በዚህም በተከታዮቹ ዘንድ ከፍተኛ መደናገጥ ተፈጥሯል።

አወዛጋቢው ሐጊያ ሶፊያ ቅርስ፦ «ዛሬ ለጁምዓ ጸሎት ክፍት ይሆናል!» የሚል ዜና በፈረንጆቹ አቆጣጠር ሐምሌ 10 ቀን 2020 ዓ.ም ሰምቶ ሕዝበ ክርስቲያኑ አዝኖ ሙስሊሙ ደግሞ ተደስቶ እንደነበር የሚታወስ ነው።

የሃገሪቱ ከፍተኛ ፍርድ ቤት መላው ዓለም የሚደምበትንና የ1500 ዓመታት ዕድሜ ያስቆጠረውን ጥንታዊውን የሐጊያ ሶፊያ ካቴድራል ሕንጻ በከፊል መስጊድ ሆኖ እንዲያገለግል የወሰነው በፕሬዝዳንቱ ኤርዶጋን ግፊትና ፊርማ ነው፡፡
በቱርክ ኢስታንቡል የሚገኘው ሀጊያ ሶፊያ ከዓለም ቅርሶች ልዩ ቦታ የሚሰጠው ነው። የኢስታንቡል ከንቲባ የርሊካያ አሊ በወቅቱ፦ “ሙስሊሞች በዜናው ተደስተዋል፤ ለጁምዓ ሁሉም ሰው እዚያ ለመገኘት ይፈልጋል።” ብለው ነበር፡፡

ቱርክ ታሪካዊውን ሙዚየም መስጊድ እንዲሆን ወሰነች። 1500 ዓመታት ያስቆጠረው ይህ በዩኔስኮ ልዩ ቦታ የሚሰጠው ታሪካዊ ሕንጻ ቤተክርስቲያን ወደ ሙዚየምነት የተቀየረው በፈረንጆቹ በ1934 ነበር፡፡ ከዚያ ቀደም ባሉት 3 ዓመታት ግን ዝግ ሆኖ ነበር።

ይህም የሆነው ቅርሱ በቢዛንታይን ጊዜ ሲገነባ የዓለም ትልቁ ቤተ ክርስቲያን የነበረ በመሆኑ ነው፡፡ በተጨማሪም ታላቁ ሊቅ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ያስተማረበት ነው።

ጥንታዊው ካቴድራል ወደ መስጊድነት ሲቀየር ለጁምዓ ስግደቱ ከተገኙት ምዕመናን መካከል የቱርኩ መሪ ጣይብ ኤርዶጋን አንዱ ሆኖ ቁርዓን ሲቀራ ታይቶ ነበር፡፡

ይህ ቅርስ መስጊድ ይሁን ወይስ ቅርስ ሆኖ ይቀጥል የሚለው ጉዳይ ላይ ለዓመታት የቱርክ ማኅበረሰብን ሲያነታረክ እንደነበር የሚታወስ ነው፡፡ ኤርዶጋን ይህ ቅርስ መስጊድ እንዲሆን መወሰኑን ሲያሳውቁ በርካቶች የተደሰቱትን ያህል በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ቅሬታዎችም ተስተናግደዋል፡፡ ለምሳሌ፦
የካቶሊኩ ጳጳስ ፖፕ ፍራንሲስ ውሳኔውን ተከትሎ፦ ‹‹ለኢስታንቡል እጸልያለሁ፤ ሳንታ ሶፊያን ባሰብኩ ቁጥር ሐዘኔ ይበረታል›› ብለው ነበር፡፡
የምሥራቅ ኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናትም በውሳኔው ሐዘናቸውን ገልጸው ነበር፡፡

☞ @gishenmaryam
☞ @Kidusat_Mekanat
744 viewsፊልጶስ, 06:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-20 16:52:40
#ይህን_ያውቁ_ኖሯል?
✥ ጦማሩን Forward & Pin በማድረግ ለወዳጆችዎ ያካፍሉት።

✞ በሥጋ ሞተው መቃብራቸው ያልተገኘ ቅዱሳን ✞
፩. ሊቀ ነቢያት ቅዱስ ሙሴ
፪. ጻድቁ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ
፫. አረጋዊው ጻድቅ ቅዱስ ዮሴፍ
፬. መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ
፭. የቅዱስ ዮሐንስ አባት(ካህኑ ዘካርያስ)
፮. ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስ

✞ እስካሁን በሕይወት በብሔረ ሕያዋን ያሉና ሞትን ያልቀመሱ ግን ወደፊት በዳግም ምጽዓት ጊዜ ለቅጽበት የሚሞቱ ተሰውረው ያሉ አበው ✞

፩. ርዕሰ አበው ሄኖክ (ሐምሌ 25 ቀን ተሰውሯል)
፪. ርዕሰ ነቢያት ኤልያስ (ጥር 6 ቀን ተሰውሯል)
፫. ነቢዩ እዝራ
፬. ዮሐንስ ወልደነጎድጓድ፤ ነባቤ መለኮት (ጥር 4 ቀን ተሰውሯል)
፭. ኢትዮጵያዊው ሊቅ ቅዱስ ያሬድ (ግንቦት 11 ቀን ተሰውሯል)
፮. አቡነ አረጋዊ (ዘሚካኤል) (ጥቅምት 14 ቀን ተሰውረዋል)
፯. ንጉሥ ነአኩቶ ለአብ (ሕዳር 3 ቀን ተሰውሯል)
፰. አቡነ ክፍለ ማርያም ዘትግራይ (የካቲት 20 ቀን ተሰውረዋል)
፱. አቡነ ገሪማ ይስሐቅ (ሰኔ 17 ቀን ተሰውረዋል)
፲. አቡነ አፍጼ (ግንቦት 29 ቀን ተሰውረዋል)
፲፩. አቡነ ሊቃኖስ (ሕዳር 28 ቀን ተሰውረዋል)
፲፪. የቅድስት ክርስቶስ ሰምራ ልጅ ዳግማዊ ቂርቆስ (ታኅሣሥ-12 ተሰውረዋል)
፲፫. አቡነ ምዕመነ ድንግል ዘጩጌ ማርያም
፲፬. አቡነ ሐዋርያ ክርስቶስ ዘተከዜ
፲፭. አቡነ እንድርያስ ዘደብረ ዘመዳ
፲፮. ጃንደረባው ባኮስ ዘራስ ደጀን
፲፯. አባ ገብረ ሕይወት (በአሰቦት ገዳም በ1945 ዓ.ም ተሰውረዋል)
፲፰. አባ በላይ ወ/ሚካኤል (በአሰቦት ገዳም ሐምሌ 7 ቀን በ1972 ዓ.ም ተሰውረዋል)

ከነዚህ በተጨማሪ ስማቸው ያልተጠቀሱ እናንተ የምታውቋቸው የተሰወሩ ቅዱሳን ካሉ በኮመንት ሥር ጻፉልን!
☞ @gishenmaryam
☞ @Kidusat_Mekanat
2.9K viewsፊልጶስ, edited  13:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-23 15:08:16 #ዕፀ_ገነት (#የገነት_ዛፍ) - #የአምላክ_እናት
በመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ
━━━━━━✦༒ ༒✦━━━━━━
✥ ጦማሩን ሌሎች እንዲያነቡትም Forward, React, Pin & Comment በማድረግ ለወዳጆችዎ ያካፍሉት።
☞ @gishenmaryam

☞ የሕይወት ፍሬ ክርስቶስን በድንግልና የወለደች ቅድስት ድንግል ማርያም በገነት ውስጥ ባሉት ዕፀዋት ኹሉ እንደምትመሰል በርካቶች ሊቃውንት በየድርሳናቸው ገልጸዋል፡፡ እነዚኽም በገነት ያሉ አዝርዕት፣ አትክልት፣ ዕፀዋት በዚኽ ዓለም ካሉት የተለዩ ናቸው፤ ቅጠላቸው ሰፋፊ ነው ዐሥራ ኹለት ክንድ ይኾናል፤ መዐዛቸው የመንፈቅ መንገድ ኼዶ ይሸታል፤ ፍሬያቸው የጋን መክደኛ ያኽላል፤ ጣዕማቸው ነፍስን ከሥጋ ይለያል፤ አላምጠው እስኪውጧቸው ድረስ ፍሬ ይተካሉ፤ ጥራታቸው እንደ መስታዮት ፊትን ያሳያል (ሕዝ ፵፯፥፲፪-፲፫፤ ራእይ ፳፪፥፪-፫)፡፡

☞ ሊቁ ኤጲፋንዮስ የሥነ ፍጥረትን ነገር በሚያሳውቀው መጽሐፉ የዕፅወ ገነትን ነገር ሲያስረዳ፡- “ወቈጽለ ዕፀዊሃኒ ለገነተ ንኡሳን በበ፲ቱ ወ፪ቱ እመት ወጽጹላን እሙንቱ ከመ ከዋክብት…” (በዚኽችም በገነት በውስጧ ያሉት አዝርዕት፣ አትክልት፣ ዕፀዋት ታናናሹ ቅጠላቸው ዐሥራ ኹለት ዐሥራ ኹለት ክንድ ይኾናል፤ ይኸውም እንደ ከዋክብት ያበራሉ፤ ፍሬያቸው እንደተመዘነ ብር ክብ ነው፤ ጣዕማቸው ከአፍ መዐዛቸው ከአፍንጫ ሳይለይ ሰባት ቀናት ይቆያል) በማለት ገልጧል፡፡

☞ ለነዚኽ ኹሉ ሊቃውንት መሠረት የኾናቸው ይኽ ታላቅ ምስጢር የተገለጠለት የአዳም ሰባተኛ ትውልድ የኾነው ሔኖክ ያየው እውነት ነው፡፡ ይኽ ሔኖክ ከሰው ተለይቶ ስድስት ዓመት በእግረ ገነት ወድቆ በሰባተኛው ተሰውሯል (ዘፍ ፭፥፳፬፤ ሔኖ ፬፥፩)፡፡ ይኽ አባት የቅድስት ድንግል ማርያም ምሳሌ ስለኾኑት ስለገነት ዛፎች ያየውን የተገለጠለትን ሲገልጥ “ወርኢኩ ፯ተ አድባረ ክቡራነ ወኲሉ ፩ዱ እምነ ፩ዱ ወየዐውድዎ ዕፀወ መዐዛ…” (የከበሩ ሰባት ተራራዎችን አየኊ፤ ኹሉም አንዱ ከአንዱ ልዩ ልዩ የኾኑ ዕንጨቶች ከበዋቸዋል፤ ከውስጣቸውም መቼም ቢኾን እንደ ርሱ አድርጐ የሸተተኝ ሌላ ዕፅ የሌለ ከሽቱ ኹሉ የበለጠ የሽቱ ዕንጨት አለ፤ ዛፉም ቅጠሉም አበባውም ለዘላለም አይጠወልግም፤ ፍሬውም ያማረ ነው፤ ያውም እንደ ዘንባባ ፍሬ ያለ ነው፤ ያን ጊዜ ይኽ ዕንጨት መልካም ነው፤ ቅጠሉም አበባውም ለዘላለም አይጠወልግም፤ ፍሬውም ያማረ ነው፤ ያውም እንደ ዘንባባ ፍሬ ያለ ነው፤ ያን ጊዜ ይኽ ዕንጨት መልካም ነው፤ ቅጠሉም ያማረ ነው፤ ፍሬውም ፊት ለፊት ለማየት እጅግ ያማረ ነው አልኊ) ሔኖ ፯፥፩-፲፩ በማለት በገነት ስላያቸው አዝርዕት፣ አትክልት፣ ዕፀዋት ምስጢር ተናግሯል፡፡

☞ ይኽቺውም የገነት ዛፍ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ምሳሌ ስትኾን፤ የማይጠወልገው ቅጠሏ ለዘላለም የማይለወጠው የድንግልናዋ፤ የዛፏ ፍሬ የልጇ የፍሬ ሕይወት የክርስቶስ ምሳሌ ነው፤ ያ ፍሬ ሲቈርጡት እየተካ እንደማያልቅ ኹሉ ለቤዛ ብዙኀን የተሰጠ የጌታ ቅዱስ ሥጋውና ክቡር ደሙ ዕለት ዕለት እየተሠዋ ሲሰጥ የመኖሩ ምሳሌ ነውና፤ ይኽነን ልዩ ምስጢር የተረዱ ሊቃውንት ይቺ ነቢዩ ሔኖክ ያያት በሱራፊ መልአክ የምትጠበቅ የገነት ዛፍ የድንግል ማርያም ምሳሌ መኾኗን መስክረዋል፡፡

☞ ኢትዮጵያዊው ሊቅ አባ ጊዮርጊስም በእንዚራ ስብሐት መጽሐፉ፡-
“ኦ እግዝእትየ ማርያም ደብረ ትንቢት ዘየዐውድዋ ዕፀወ መዐዛ
በውስተ መጽሐፉ ለሔኖክ እንተ ተጽሕፈ ዕዘዛ”
(እመቤቴ ማርያም ሆይ በሔኖክ መጽሐፍ ውስጥ ክብሯ የተጻፈ፤ የመዐዛ ዕፀዋት የሚከብቧት የትንቢት ተራራ ነሽ) በማለት በእውነት ምሳሌዋ መኾኑን አስተምሯል፡፡

☞ የማሕሌተ ጽጌ ደራሲያን ሊቃውንት አባ ገብረ ማርያም ዘደብረ ሐንታና አባ ጽጌ ድንግል በማሕሌተ ጽጌ መጽሐፋቸው፡-
“በኲናተ እሳት ዘይነድድ ዘየዐቅበኪ ሱራፊ
ወአጼነወ መዐዛኪ ሔኖክ ጸሐፊ
ጽጌ ዕፀ ገነት ማርያም ዘኢትትነገፊ”
(ሱራፊ መልአክ የእሳት ጦርን ይዞ የሚጠብቅሽ፤ መዐዛሽንም ጸሐፊ ሔኖክ ያሸተተልሽ የማትረግፊ የማትጠፊ የገነት ዛፍ ማርያም) በማለት ሔኖክ ያያቸው የገነት ዛፎች በእውነት የድንግል ማርያም ምሳሌ መኾናቸውን ተናግረዋል፡፡

☞ ዳግመኛም እነዚኹ ሊቃውንት የቅድስት ድንግልን የመዐዛ ንጽሕናዋን፣ የመዐዛ ቅድስናዋን፣ የመዐዛ ምግባሯን ድንቅነት በገነት ውስት ባሉት ልዩ ሽታን በሚሸቱ በገነት ዛፎች ሲመስሉ፡-
“እንዘ ይፀውረኪ በሐቂፍ ወይስዕመኪ በአፍ
አመ አፍለሰኪ ወልድ ውስተ የማኑ ለዐሪፍ
ጽጌ ዕፀ ገነት ማርያም ዘትጼንዊ ለአንፍ
እንዘ ይትጓድዑ አክናፈ በክንፍ
ለቀበላኪ ወረዱ አእላፍ”
(ለአፍንጫ መዐዛን የምትሰጪ የገነት ዛፍ ማርያም ሆይ፤ ልጅሽ በክንዱ ዐቅፎ በአፉ እየሳመ በቀኙ ሊያሳርፍሽ ባሳረገሽ ጊዜ፤ አንቺን ለመቀበል ክንፍ ለክንፍ እየተጋጩ እልፍ አእላፋት መላእክት ወረዱ) በማለት የመዐዛዋን ታላቅነት መስክረውላታል፡፡

☞ ኢትዮጵያዊዉ ቄርሎስ ዐምደ ሃይማኖት የተባለው ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫም ቅድስት ድንግል ማርያም አማናዊት ዕፀ ገነት መኾኗን በአርጋኖን መጽሐፉ፦ “ዕፀ ገገት ዘበጽጌሃ ንትሜዐዝ ወእምፍሬሃ ንሴሰይ ወታሕት አዕጹቂሃ ናጸልል… ኦ ድንግል ዖመ ገነት ዘተከላ የማነ እግዚአብሔር ወአጽገያ ኀይለ መንፈስ ወአፍረያ ጽላሎተ አብ - በአበባዋ የምንሻተትባት፤ ከፍሬዋም የምንመገባት፤ በሥሯም (በቅርንጫፎቿም) የምንጠለልባት የገነት ዕንጨት ናት… ድንግል ሆይ የእግዚአብሔር ቀኝ የተከላት፣ የመንፈስ ቅዱስ ኀይል እንድታብብ ያደረጋት፣ የአብ ጥላ እንድታፈራ ያደረጋት የገነት ዛፍ ነሽ።” በማለት በሥልጣነ እግዚአብሔር ተጠብቃ በሃይማኖት፣ በምግባር፣ በንጽሕና፣ በቅድስና ጸንታ በግብረ መንፈስ ቅዱስ አምላክን አፍርታ የተገኘች አማናዊት ዕፀ ገነት የመኾኗን ምስጢር አጒልቶ አሳይቷል። ሉቃ ፩፥ ፴፭- ፵፪

☞ በሕማማት ሰላምታው ላይም፡-
“ማርያም ገነቱ ለወልደ ያሬድ (ኢያራፕ) ወሬዛ
ዘተረክበ ብኪ ለድኂን ወቤዛ
ፍሬ ጽድቅ ምስለ መዐዛ ሰላም ለኪ፡፡”
(ከመልካም መዐዛ ጋራ የጽድቅ ፍሬ ለድኅነትና ለቤዛ የተገኘብሽ ጐልማሳ የሚኾን የያሬድ ልጅ የተክል ቦታ ማርያም ሰላምታ ላንቺ ይገባሻል፡፡)
በማለት ምስጢሩን አመስጥሯል፡፡

☞ የሕይወት ፍሬ ኢየሱስ ክርስቶስን ያስገኘሽልን የገነት ዛፍ ድንግል ማርያም ሆይ በረከትሽን በእኛ በልጆችሽ ላይ አትረፍርፊልን፡፡

ምንጭ፦ ነገረ ማርያም በብሉይ ኪዳን ክፍል ፩ እና መልክአ ሕማማት ንባቡና ትርጓሜው በመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ
☞ @gishenmaryam
•᳀͟͞ ͟͞ ̸͟͞ ͟͞ ͟͞ ͞ ͟͞ ̸ ͟͞ ͟͞᯼᳀᯼͟͞ ͟͞ ͟͞ ̸͟͞ ͟͞ †✙† ͟͞ ͟͞ ̸͞͝ ͟͞᯼᳀᯼͟͞ ͟͞ ͟͞ ̸͟͞ ͟͞ ͟͞ ͟͞ ̸͞͝ ͟͞᳀•

✥ በዚህ መንፈሳዊ ቻናል ላይ የሚተላለፉ መንፈሳዊ ጦማሮች ለእርስዎና ለወዳጆችዎ እንዲደርሱ ቻናሉን Join / Follow በማድረግ ሌሎችንም ወደ ግሩፓችን ይጋብዙ።

በቴሌግራም ወዳጅ እንሁን?
☞ @Kidusat_Mekanat
☞ @Kidusat_Mekanat
☞ @Kidusat_Mekanat

የዩቲዩብ ቻናላችንን « መኮሬታ Mekoreta Tube »ን በሚከተለው ሊንክ ከፍተው Subscribe & Join ያድርጉ።
https://m.youtube.com/channel/UCUBStsekCniQtATyZDdFqQQ
896 viewsአንተነህ ውብሸት, 12:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-27 09:53:21 እመቤታችን ዘወትር በ24 ሰዓት አንድ ጊዜ በአካል ተገኝታ የምትባርክበት ጥንታዊው ጣና ቂርቆስ የአባቶች ገዳም
→ ከተመሠረተ 2995 ዓመታትን ያስቆጠረ እጅግ ጥንታዊ ገዳም ነው።
→ ታቦተ ጽዮን ለ914 ዓመታት በመስዋእተ ኦሪት ስትገለገልበት የቆየችበት ታሪካዊ ገዳም ነው።
→ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ልጇ ወዳጇ መድኃኔዓለም ክርስቶስን ይዛ ከአረጋዊ ዮሴፍና ከቅድስት ሰሎሜ ጋር በተሰደዱ ጊዜ ለ100 ቀናት (3 ወር ከ10 ቀናት) የተቀመጡበት ቅዱስ ቦታ ነው።
→ ታቦተ ጽዮንን ወደ ኢትዮጵያ ይዞ የመጣው በጠቢቡ ሰሎሞን ጊዜ ሊቀ ካህናት የነበረው የሳዶቅ ልጅ ሊቀ ካህናት አዛርያስ ከታሪካዊው ጉዟቸው በኋላ በቦታው ላይ ድንቅ ተጋድሎውን ፈጽሞ በ፪ ድንጋዮች መካከል ቆሞ እየጸለየ በክብር ያረፈበት ድንቅ ቦታ ነው።
→ ዘጠኝ ስውር ቤተ መቅደሶች ከነምርፋቃቸው የሚገኝበት መካነ ኅቡዓን ነው።
→ እመቤታችን በየቀኑ አንድ ጊዜ በአካል ተገኝታ የምትባርክበትና ከመዓዛ ገነት በሚበልጠው ልዩ መዓዛዋም የሚታጠን ተአምረኛ ገዳም ነው።
→ በከበሩት አበው የቅዱሳን ከተማ እንደሆነ የሚነገርለት የጣና ሐይቅና ገዳማቱ በቀን ፫ ጊዜ በመዓዛ ገነት የሚታጠኑበት ቅዱስ ቦታ ነው።
→ እመቤታችን በስደቷ ወቅት በኪደተ እግሯ የባረከቻቸውን ቅዱሳት መካናት በረከት ለማግኘት ሲሉ ጉዞ የሚያደርጉ በርካታ ቅዱሳን ተጋድሎ የፈጸሙበት የቅዱሳን መካነ ጸሎት ነው።
→ ሊቁ ቅዱስ ያሬድ ለብዙ ጊዜያት የጸለየበትና ምልክት የሌለውን የመጀመሪያውን ድጓውን ቀለም በጥብጦ የጻፈበት ክቡር ገዳም ነው።
→ የኢትዮጵያ በመጀመሪያው ሊቀ ጳጳሳት አቡነ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን መስዋእት ያቀረበበትና ዘወትር ረዲኤተ እግዚአብሔር የረበበት ታሪካዊው መንበረ ሰላማ ነው።
→ ከቀዳማዊ ምኒልክ እስከ አጼ ኃይለ ሥላሴ ድረስ የነገሡ ደጋግ ነገሥታት ኃይለ እግዚአብሔር ከሚያገኙባቸው ከ፬ቱ መናብርተ ጽዮን አንዱ ነው።
→ በኢትዮጵያ ከሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ በአመሠራረት ታሪኩ ከአክሱም ጽዮን፣ ከተድባበ ማርያምና ከመርጡለ ማርያም ቀጥሎ ፬ኛ ነው።

የYouTube ቻናላችንን Subscribe በማድረግ የገዳሙን ታሪክና አሁናዊ ገጽታ ይመልከቱ
↓ «መኮሬታ Mekoreta Tube» ↓





«ንእምሮሙ አበዊነ ቅዱሳን ወመካኒሆሙ ይቄድሶ ለሰብእ!»
ቀጣይ ጉዞዎቻችን፦

፩) #ምጢራዊው_እመጓ_ደብረ_ቆጵሮስ_ቅዱስ_ዑራኤል
→ ይህ ጉዞ በዓለ ዕርገትን በእመጓ በዓለ መድኃኔዓለምን በአርብዓሐራ መድኃኔዓለም የምናከብርበትና በርካታ የመንዝ ገዳማትን ያካተተ ልዩ ጉዞ ነው።
* መነሻ፦ ግንቦት 24
* መመለሻ፦ ግንቦት 27
* የጉዞ ዋጋ፦ ቦታው ላይ ምግብና ማረፊያን ጨምሮ 1500 ብር
[በተጨማሪም በሰኔ ጾም ሐዋርያት ውስጥ ከሰኔ 3- 5፣ ከሰኔ 10- 12፣ ከሰኔ 17- 19፣ ከሰኔ 24- 26 ወደ ምሥጢራዊው እመጓ ዑራኤል ገዳም ጉዞ ይኖረናል።]

ጥንታዊው ጣና ቂርቆስ የአባቶች ገዳም Tana St.Kirkos Monastery @መኮሬታ Mekoreta Tube


1.2K viewsእልመስጦአግያ ዘሐዋርያት, edited  06:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-14 16:18:02 ###ታላቅ የመንፈሳዊ ጉባኤ ጥሪ ፦
እሑድ: ግንቦት 7 :2014 ዓ.ም ከቀኑ 7:00 ጀምሮ

አዘጋጅ:- በኢ/ኣ/ተ/ቤ/ክ/በሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት የደብረ ብሥራት አቡነ ዜና ማርቆስ አንድነት ገዳም።

ቦታ:-በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ሁለገብ አዳራሽ።

ስለ ገዳሙ አጭር መግለጫ
1)የቦታው ቃልኪዳን
* "ቦታህን የረገጠውን፣በአማላጅነትህ የተማፀነውን ኃጢአቱን በንሰሓ እስከሚያስወግድ ድረስ እድሜ ሰጥቼ እጠቡቀዋለሁ"
* "ከኢየሩሳሌም አምጥተህ በአዋሐድከው አፈርና ውኃ አምነው የተጠመቁትንና የተቀቡትን እየሩሳሌም እንደደረሱና በዮርዳኖስ ውኃ እንደ ተጠመቁ እቆጥርላቸዋለሁ።

2)አቡነ ዜና ማርቆስ ተጋድሏቸውን ፈጽመው በ14ዐ ዓመታቸው ታኅሣሥ 3ቀን በዚሁ ገዳም አርፈዋል።

3)አቡነ ተክለሃይማኖትን ተከትለው የሔዱ የደብረ ብሥራት ዛፎች፣እንጨቶችና ድንጊያዎች ከወንድሜ አባ ዜናማርቆስ ገዳም አትሔዱም የተባሉት እዛው በ ደብረ ብሥራት ይገኛሉ።

4)ማኀሌተ ጽጌ የተደረሰበት ቅዱስ ሥፍራ ነው።

5)የተሰነጠቀ ድንጋይ የአጣብቂኝ ዋሻ።

6)የገዳሙ በረከቶች
*ከሰማይ የወረደላቸው መስቀል።

*የዓመት ቡኮ(የ 464 ዓመት ቡኮ):- በግራኝ ወረራ ጊዜ ተሰደው የነበሩት የገዳሙ አባቶች ከ 27 ዓመት በኋላ በተመለሱ ጊዜ ያኔ ትተውት የሔዱት ሊጥ የእለት ሥንዴ ብኮ ሆኖ ሳይበላሽና ሳይኮመጥጥ አግኝተው ተመገቡት።ይህንንም እስከ ዛሬ ድረስ በመተላለፍ ለገዳሙ በረከት ሆኖ ይታደላል።

*የመቃብራቸው አፈር፦ብዙ ተአምራትን ያደረገና ሙት ያስነሳ በገዳሙ የሚታደል በረከት ነው።

*አጸደ ፂማቸው፤ ፈዋሹ ጸበላቸው፤እና ሌሎች ብዙ በረከቶች በገዳሙ ይገኛሉ።

እርሶም በዚህ ጻድቁን አቡነ ዜናማርቆስንእና ገዳማቸውን ደብረ ብሥራትን በሚያስተዋዉቅ ታላቅና ታሪካዊ መርሐግብር ላይ እንዲካፈሉ ተጋብዘዋል።

በጉባኤው ላይ የገዳሙ በረከቶች የሚታደሉ ይሆናል።

የጻድቁ አባታችን አቡነ ዜናማርቆስ ረድኤትና በረከታቸው ከሁላችን ጋር ይሁን።አሜን!!!

ለበለጠ መረጃ፦0921325839
0940852119
0911636177
1.1K viewsእልመስጦአግያ ዘሐዋርያት, 13:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-03 15:39:01 የሰባቱ ቅዱሳን አበው ጥንታዊ የዋሻ ገዳማትን የሚሳለሙበት ታላቅ መንፈሳዊ ጉዞ ወደ ጥንታዊቷና ታሪካዊቷ ርእሰ አድባራት ወገዳማት
#ተድባበ_ማርያም_ገዳም

በዚች ታላቅና ታሪካዊት ገዳም ግንቦት 1 ቀን 2014 ዓ.ም የሚከበረውን የእመቤታችንን በዓለ ልደት ምክንያት በማድረግ የንግሥ ጉዞ ተዘጋጅቷል። እርስዎም የጉዞው ተሳታፊ በመሆን የበረከቱ ተሳታፊ ይሁኑ። የእመቤታችን የቃል ኪዳን ልጆች ሁሉ በጉዞው ተሳታፊ ሆነው አኩሪ ታሪካቸውን ያውቁ ዘንድ ይህንን ጦማር ለወዳጅ ዘመድዎ ያካፍሉት፤ ቅንነት ለራስ ነውና!!!

→ በጉዞው ላይ የሚሳለሟቸው ጥንታዊያን አስደናቂ ገዳማት፦ ጋስጫ አቡነ በጸሎተ ሚካኤል፣ ተአምረኛው ደብረ ባህርይ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ፣ ደብረ ጽጌ ዋሻ ጻድቁ አባ ጽጌ ድንግል፣ መንክራዊው ወለቃ አቡነ ገብረ እንድርያስ፣ ሚዳ መራኛ አቡነ መልከ ጼዴቅ፣ ቀዳማይ ግሸን አቡነ ያዕቆብ ዋሻ፣ ገዛዛ ዋሻ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስን፣ ተአምረኛዋ ቅድስት ጸበለ ማርያም፣ ድማ ጊዮርጊስ፣ ጥንታዊቷ መርጡለ ማርያም፣ ገዳመ አስቄጥስ ቅ/አርሴማ፣ ደብረ ሊባኖስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት እና ሌሎችንም ሲሆን በአንድ የንግሥ ጉዞ የበርካታ ቅዱሳት መካናትን የቃልኪዳን በረከታቸውን የሚያፍሱበት ልዩ የዙር ጉዞ ነው።
* የጉዞው መነሻ ሚያዚያ 27 ከጠዋቱ 11:00- 12:00
* መመለሻ ግንቦት 3
* የጉዞ ዋጋ፦ ማረፊያን ጨምሮ 3000 ብር
✥ በማኅበሩ የጉዞ መርሐ ግብር መሳተፍ ከፈለጉ ሳያመነቱ ደውለው ይመዝገቡና አብረው ይጓዙ!!! ለበለጠ መረጃ፦
0901070707
0911289877
#ማኅበረ_ቅዱስ_ፊልጶስ_ወአቡነ_ሳሙኤል_ዘዋልድባ

መነሻ ቦታዎች፦ አራዳ ቅ/ጊዮርጊስ እና መስቀል አደባባይ ቅ/እስጢፋኖስ አብያተ ክርስቲያናት

✥ በዚህ መንፈሳዊ ቻናል ላይ የሚተላለፉ መንፈሳዊ ጦማሮች ለእርስዎም ለሌሎችም እንዲደርሱ ቻናሉንና ግሩፑን Follow / Subscribe / Join በማድረግ ሌሎችንም ወደ ፔጃችን ይጋብዙ።

"ገዳምህን የረገጠ" ብቻ ሳይሆን "ገዳምህን ለሌሎች ያሳዬ... እምርልሃለሁ!" ተብሎ ቃል የተገባላቸው ቅዱሳን እንዳሉን ገድለ አቡነ ዘርዓ ብሩክን ያስታውሱ!!!
☞ @gishenmaryam

✥✞✥ ጽሑፉን ሌሎች እንዲያነቡትም Like እና Share ያድርጉ፤ በዚህ መንፈሳዊ Page ላይ የሚተላለፉ መንፈሳዊ ጦማሮች ለእርስዎም ለሌሎችም እንዲደርሱ ፔጁን Like / Follow ሌሎችንም ወደ ፔጃችን ይጋብዙ።

በቴሌግራም ወዳጅ እንሁን?
☞ @Kidusat_Mekanat
☞ @Kidusat_Mekanat
☞ @Kidusat_Mekanat

የዩቲዩብ ቻናላችንን « መኮሬታ Mekoreta Tube »ን በሚከተለው ሊንክ ከፍተው Subscribe & Join ያድርጉ።
https://m.youtube.com/channel/UCUBStsekCniQtATyZDdFqQQ
1.1K viewsቤተ ዋሊ, edited  12:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ