Get Mystery Box with random crypto!

ቅዱሳት መካናት

የቴሌግራም ቻናል አርማ kidusat_mekanat — ቅዱሳት መካናት
የቴሌግራም ቻናል አርማ kidusat_mekanat — ቅዱሳት መካናት
የሰርጥ አድራሻ: @kidusat_mekanat
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.51K
የሰርጥ መግለጫ

ስለ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ገዳማትና አድባራት መረጃ መለዋወጫ ቻናላችንን ይቀላቀሉ ዘንድ የተዋህዶ ልጆችን ይጋብዙ
ለማንኛውም ጥያቄ
@betewali
@Zegedamat
💚👇❤ በፌስቡክ ያግኙን 💚👇❤
👉 https://www.facebook.com/abageorgis/
👉 https://m.facebook.com/zegedamat/

Ratings & Reviews

4.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-05-03 15:39:01 #በተድባበ_ማርያም_ብቻ_የሚገኙ_ቅርሶች፦
ወንጌላዊው ቅዱስ ሉቃስ ለእመቤታችን ከሳላቸውና ኢትዮጵያ ውስጥ ከሚገኙት ከ4ቱ ምስለ ፍቁር ወልዳ ስዕለ አድኅኖዎች ውስጥ አንዷ ስዕለ አድኅኖ ባለ 3 ተከፍች የገበታ ስዕልና ጥንታዊና ስነ ጥበባዊ ቅርሶች ይገኛሉ፡፡
የንጉሥ ዳዊት ወንበር፣
ሥዕርተ ሐና (የእመቤታችን እናት የእናታችን የቅድስት ሐና ፀጉር) በገዳሙ ይገኛል። ይህ ጸጉር የተቀመጠበት የሽክላ ገንቦ እጅግ ጥንታዊና በስነ ጥበባዊ ይዘቱ የሚያስገርም ትእይንት ይፈጥራል።
በ4ኛው መ/ክ/ዘመን ወንድማማቾቹ ቅዱሳን ነገሥታት አብርሃ ወአጽብሐ ያነጹት ስውር ቤተ መቅደስ፣
አዛዥ ጌራና አዘዥ ዘራጉኤል በእጃቸው ያመለከቱት ታላቁ ሊቅ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫም ያስተማሩበት ድጓ፣
የጥንታዊያን ነገሥታትና ጳጳሳት ከወርቅና ከብር የተሰሩ በወቅቱም ለገዳሟ የተበረከቱ የክብር አልባሳትና የነገሥታት ዘውድ እንድሁም አጼ ገላውዴዎስ ታቦተ ተድባበ ማርያምን ይዘው ዘምተው አላዊው ግራኝ አህመድን ሲያሸንፉት ከአላዊው ግራኝ የማረኳቸው አልባሳትና አንድ ሰው ተንገዳግዶ የሚያነሳው የግራኝ የበቅሎው ቃጪል
የበግ ምስልና የተቁለመለመ የበግ ቀንድ ያለበት መስቀል በዚያ ይገኛል፡፡ የዚህ መስቀል ብርሀን የሚያስገርምና ዓይንን የሚያንፀባርቅ ሲሆን ከምን አይነት ማዕድን እንደተሰራ አይታወቅም፡፡
ከጥንታዊያን ነገሥታትም መካከል ዐፄ ካሌብ ወደ ደቡብ አረቢያ የናግራንን ክርስቲያኖች ለመርዳት ሲዘምቱ ፓትርያርክ ዘሙሴ እሱም የኦየሩሳሌምን ገዳም ያቀናና በመጨረሻም በአባ ጴንጠሌዎን ገዳም ገብቶ ያረፈ አባት ጋር ዘምተው ድል አድርገው ሲመለሱ ይዘው የሄዱትን ጋሻ በስዕለት ለተድባባ ማርያም አስገብተውት በቦታው ይገኛል፡፡
የዕብራይስጥ ሲኖዶስና የአረማይክ ቅዳሴ እግዚእ በቦታው ላይ ይገኛል፡፡
በዚህ ገዳም ከ1000 ያላነሱ የብራና ጥንታዊያን መጻሕፍት ይገኛሉ፤ እነዚህም መጻህፍት ክፊሎቹ በጥንታዊት የአክሱም ዘመን መንግስት የተጻፉ ሲሆኑ ሌሎቹ ደግም በመካከለኛው ዘመን የተጻፉ ናቸው፡፡
በአረማክ ቋንቋ የተጻፉ የሰሌዳ መጻሕፍት፣
በዐረብኛና በግእዝ የተጻፉ በርካታ ጥንታዊያን መጻሕፍት፣
ወንጌል ዘወርቅ እየተባለ የሚጠራ ትልቅ የወርቅ ጉብጉብታ ያለበት የወንጌል መጽሐፍ ቅዱስ፣
ገድለ ጊዮርጊስ ወልደ አሚድ፣
ገድለ አዳም ከታላቅነቱ የተነሳ ሁለት ሰው ከቀኝ ከግራ ሆኖ የሚዘው ባለ ገበታ የብራና መጽሐፍ፣ እና ሌሎች በርካታ ጥንታዊያን መጻሕፍት በቅርስነት ተመዝግበው በተድባበ ማርያም የሚገኙ የመንፈሳዊ እሴት ማንጸባረቂያዎች ናቸው። በተጨማሪም ገዳሟ ሌሎችንም በርካታ ቅርሶችን በክብር ጠብቃ ይዛለች።

#መስቀል_በተድባበ_ማርያም፦
በርካታ ጥንታዊ የእጅና የመጾር መስቀል ይገኛሉ። ከእነዚህም መካከል፦
የመጀመሪያው የኢትዮጵያዊ ጳጳስ አቡነ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን የቀደሰበትና ለተድባበ ማርያም የሰጡት "ነዋ በግዑ" የእጅ መስቀል እና "ዘይቄድስ ኩሎ" የተባለ ቅብዓ ሜሮን፣
የመጥመቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ መስቀል፣
የእጨጌ ዮሐንስ በትረ ሆሣዕና እና የእጅ መስቀል፣
የአቡነ አኖሪዎስ የእጅ መስቀል፣
የአቡነ ቄርሎስ የእጅ መስቀልና ሌሎች ከወርቅ የተሰሩ ጥንታውያን መስቀሎች ናቸው፡፡

#በገዳሟ_ከሚገኙ_አጽመ_ቅዱሳን_መካከል፦
ሄሮድስ የጨፈጨፋቸው ሕጻናት ዓጽም በከፊል፣
የቅዱስ ጊዮርጊስ አውራ ጣት
በአጠቃላይ የ28 ሰማእታት ዓጽም የሚገኝ ሲሆን እንዲሁም በልዩ ስፍራ የሚገኘው መካነ መቃብር የዐፄ ገላውዴዎስን ጨምሮ የ6 ነገሥታትና የ4 እጨጌዎች ተሰብስቦ ይገኛል፡፡

ከ9ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ጀምሮ እሰከ 11ኛው ድረስ የጨለማው ዘመን በመባል ይታወቃል፡፡ ይህም የግእዝ ሥነ ጽሁፍ የተዳከመበት ዮዲት ከተከታዮቿ ጋር በመሆን ባደረሰችው ወረራ ሰነ ጽሁፍ የጠፉበት የትርጉም ስራዎች እንደቆሙ ተደረገበት ወቅት ነበር፡፡

ከ9-15ኛው ክፍለ ዘመን በዘጠነኛው መቶ ክፍለ ዘመን 40 ዓመታት መሉ ቤተ ክርስቲያንን ስታቃጥል መጸህፍትንና ሌሎችንም የቤተ ክርስትያን ንዋያተ ቅድሳት ሁሉ ተደምሰሱ፡፡ አያሌ የቤተክርስቲያን ሊቃውንት (ካህናት) አብረው ተቃጠሉ፡፡ በዚህም ጊዜ በኢትዮጵያ የስብከተ ወንጌል አገልግሎት በዕጅጉ ተዳክሞ ነበር። ነገር ግን በዚህች ጥንታዊት ገዳም ምንም አይነት ወረራ አልደረሰባትም።

በ15ኛው ክፍለ ዘመንም ግራኝ የተነሳበት በመሆኑ ቱርክ እየተላላከ ባስመጣው መሣሪያና በድብቅ ያስለጠነውን ወታደር አሳልፎ ኢትዮጵያን መውረር ሲጀምር 15 ዓመት ያህል ያለማቋረጥ በኢትዮጵያ ላይ የቱርክ ጥይት እንደ እሳት ሲነድ ከዮዲት ጉዲት ወራራ ተርፈው የቀሩና ከእርሷም በኋላ የተተኩት የቤተክርስቲያን ቅርሶች በግራኝ ወራራ ጨርሰው ሲወድሙ የግራኝ ወራራ በቤተክርስቲያንና በምዕመናን ሕይወት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ሲያስከትል አያሌ ገዳማትና አድባራት ሲቃጠሉና ሲመዘበሩ ይህቺ ታላቅ የታሪክና የቅርስ ባለቤት የሆነችው ርእሰ አድባራት ወገዳማት ተድባበ ማርያም ምንም አይነት ቃጠሎና የቅርስ ዝርፊያ አልደረሰባትም፡፡

ከዚህም አልፎ በአጼ ሱስንዮስ ዘመነ መንግስት ካቶሊካዊያን በየገዳማቱና በየአድባራቱ እንዲሁም በየቤቱና በየለቅሶው ቤት በየገበያው እየዘሩ የካቶሊክን ሃይማኖት ለማስፋፋት ሲጥሩ የኢትዮጵያ ቅዱሳን ዓጽም ካረፈበት እየወጣ መቃጠል ሲጀምር ብዙ ካህናትና መነኮሳት ሊቃውንትና ምእመናን ልጅ አዋቂ ሳይባል የተዋህዶ ሃይማኖት ልጆች የሆኑ ሁሉ ባሉበት እየታደኑ አሰቃቂ ድርጊት ሲፈጸምባቸው የርእሰ አድባራት ወገዳማት ተድባበ ማርያም ሊቃውንትና ካህናት መነኮሳት ግን እግዚአብሔርን አጋዥ በማድረግ በፆምና በፀሎት ፀንተው መከራውንና ችግሩን በመቋቋም ተዋህዶ ሃይማኖታቸውን አቅንተው እስከ አሁኗ ሰዓት ድረስ ታሪካቸውንና ቅርሳቸውን በመጠበቅ ይገኛሉ፡፡

ስለዚህ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ሊቃውንት እንዲሁም ምእመናንና ምእመናት ሁላችሁም ይህንን አስደናቂ የሆነውን የርእሰ አድባራት ወገዳማት ተድባበ ማርያም ታሪክ አንብቦ (ሰምቶ) በመረዳት ልዑልና ቅዱስ እግዚአብሔር ፍቅዶላቸሁ ከያላችሁበት ወደ ቦታዋ ድረስ በመሄድ በረከት እንድታገኙ አደራችን የፀና ነው፡፡
☞ @gishenmaryam
715 viewsቤተ ዋሊ, edited  12:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-03 15:39:01 ከታቦር ቀጥሎ ሳይንትን ጨርሶ ወደ ቦረና መግቢያ ላይ ሊባኖስ፣ ደማስቆ፣ አርሞንኤም፣ ደብር ፋራን፣ በስተ ሰሜን በኩል ኮሬብ፣ ቃዴስ፣ ደብረ ፋጌ፣ ቂሣርያ፣ ቢታኒያ፣ ጋዛ፣ ጎልጎታ፣ ፌልስጥኤም ወዘተ ተብለው ተሰይመዋል፡፡ ይኸውም መታሰቢያነቱ ለ12ቱ ነገደ እስራኤል እንደሆነ ይነገራል፡፡

ተድባበ ማርያም ከአክሱም ቀጥላ ሁለተኛዋ መናብርተ ጽዮን ናት፡፡ ስለዚህም በሥርዓቱ መሰረት የአክሱም ጽዮን አስተዳደሪ ንቡር ዕድ፣ የተደባበ ማርያም አሰተዳደሪ ፓትርያርክ፣ የመርጡለ ማርያም አስተዳደሪ ርእሰ ርኡሳን እና የጣና ቂርቆስ አስተዳደሪ ሊቀ ካህናት በመባል ይጠራሉ፡፡ ከቀዳሚዊ ምኒልክ ጀምሮ በየዘመኑም ለሚነግሡት ነገሥታት ቅብዐ መንግስቱን በመቀባት ሁሉም የየራሳቸው ድርሻ ነበራቸው።

ይህም፦
1ኛ) የአክሱም ንቡረ ዕድ ከቀዳሚ ምኒልክ ጀምሮ በተያያዘው መሠረት ማንኛውም ንጉሥ ሲነግሥ ከሥርዓተ ንግሥ በኋላ ዘውዱን በክብር ከራሱ ላይ ያቀዳጃል፡፡
2ኛ) የተድባበ ማርያም ፓትርያርክ ‹ቅንት ሰይፈከ ኃያል ውስተ ሐገርከ በሥንከ ወበላሕይከ አርትዕ ተሰራህ ወንገሥ በትረ ጽድቅ ወበትረ መንግስትከ" ብሎ ሰይፈ መንግስቱን ለንጉሥ ያስታጥቀዋል፡፡ በትረ መንግስቱን ህለተ ወርቁን ጠላትህን በእጅህ ጭብጥ በእግርህ እርግጥ አድርገህ ግዛ ብሎ በቀኝ እጅ ያሲይዘዋል፡፡ በዚህ እውነተኛ ፍርድ ፍረድበት የእግዚአብሔርን ሕግ ጠብቅበት የተበላሸውን አድስበት የታደሰውን አጽናበት አመፀኞችን ቅጣበት ፍቃዶኞችን ሹምበት በዚህ ሁሉ አምላካችንን አገልግልበት ብሎ ይሾመዋል፡፡
3ኛ የመርጡለ ማርያም ርእስ ርኡሳን ልብስ መንግሥቱን ያለብሰዋል፡፡
4ኛ የጣና ቂርቆስ ሊቀ ካህናት ቅብዐ መንግሥቱን ይቀባዋል።

ይህ ሁሉ ሥርዓት የሚደርሰው 40 ቀን ለሥርዓተ ንግሥ የተወሰነው ከብሉይና ከሐዲስ ኪዳን የተውጣጣው ጸሎትና መሥዋዕት ካረገ በኋላ ነው፡፡ በእነዚህ አራት መናብርተ ጽዮን ያልነገሠ ንጉሥ ጠላት አጥፍቶ፣ አገር አስፍቶ እና በሃይማኖት ፀንቶ ሊኖር አይችልም፡፡ እነዚህ ባሉበት ከነገሠ ግን ሀገር ለመጠበቅና ሁሉን ነገር ለማድረግ ይቻለዋል፡፡ ይኸውም ከቀዳማዊ ምኒልክ ሲያያዝ መጥቶ እስከ ግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ድረስ በነዚህ 4 መናብርተ ጽዮን ግርማዊነታቸው ነግሠው 43 ዘመን ያለምንም እንከን ገዝተዋል፡፡ ግርማዊነታቸው ሲነግሡ የነበሩት የርእሰ አድባራት ወገዳማት አሰተዳደሪ ለግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ሰይፈ መንግሥትና ሕለተ ወርቅ ያስጨበጡና ያስታጠቁ ፓትርያርክ አፈወርቅ ይባሉ ነበር፡፡

ከላይ በርእሱ ለመግለጽ እንደተሞከረው ዘመነ ኦሪት አልፎ በክርስቶስ ልደት ዘመን ሐዲስ እንደተተካ በ337 ዓ.ም በቅዱሳን ነገሥታት አብረሃ ወአጽበሃ ዘመን ተድባበ ጽዮን የሚለው የምሳሌ ስም አልፎ በአማናዊነት ድንግል ስም ተድባበ ማርያም ተባለች፡፡ ነገሥታቱ አብርሃ ወአጽብሃም የኦሪታዊት ተድባበ ማርያምን ክብር ከፍ በማድርግ ለሥርዓተ ቁርባንና ለሐዲስ ኪዳን ለተዋህዶ ሃይማኖት መሰረት ትሆናቸው ዘንድ 318 መዘመራን ካህናትና ዲያቆናት ከካህናተ ኦሪቱ ጋር ያለውን ሐዲስ ኪዳን የሚያስተምሩ መምህራን ተክለው ከቀዳሚው ምኒልክ ዘመን በሚልጥ ክብር አክብረው እንበረምን ህዝበ ቀደስ አሰኝተው በፍሬምናጦስ አባ ሰላማ ከሳቴ ብርሃን ሥልጣን አጽንተው የተደባበ ማርያም ክብር እስከ አሁን ድረስ የቆየውን ማዕረግ የመሰረቱ እነሱ ናቸው፡፡ በአብረሃ ወአጽብሃ ዘመን መንግሥት የነበረው ፓትርያርክ መርሐ ጽዮን ሲሆን በአጼ ካሌብ ዘመን የነበርው ፓትርያርክ ደግሞ ፓትርያርክ ዘሙሴ ይባላል። እንዲህ ሆኖ ሲያያዝ ታሪክ መጣና ከአጼ ገላውዴዎስ ዘመነ መንግስት ሲደርስ የግራኝ ወረራ ተነስቶ አድባራቱን ሁሉ ሲያጠፋ የተድባበ ማርያም ደብር ክብር ምንም አልተደፈረም፡፡

አንዳንድ ፀሐፊዎች ግን እርግጠኛ ካልሆነ ታሪክ በመነሳት ገና በይሆናል "ግራኝ ተድባበ ማርያምን አቃጥሏታል" በማለት ጽፈዋል፡፡ እንዲያውም በዘመኑ የነበረው ፓትርያርክ አባ ዮሐንስ የተድባበ ማርያምን ጽላት ይዞ ዘምቶ አጼ ገላውዴዎስ ጋር ግራኝን ድል ነስቷል፡፡ በዚህም ጦርነት ጊዜ በበጌ ምድር አፈረዋናት ያለው የመካነ ሰማዕት ገላውዴዎስ ጽላትም ግራኝን ድል በማድረግ ተመስርቷል፡፡ ከዚህ በኋላ አጼ ጋላውዴዎስ አብርሃ ወአጽብሃ በተደባበ ማርያም በሰጡት ክብር ልዕልና ጨምሮ ከአባይና ከበሽሎ ከጎንደር በር አንስቶ በጠቅላላ በወሎ ምድር እስከ አዳል ነጭ ሣር ድረስ ለገዳሟ መተዳደሪያ ሲሶ መንግሰት ሰጥቷል፡፡

#ሥርዓተ_በዓላት_በተድባበ_ማርያም
በዘመነ ኦሪት የቂጣ በዓልና የአይሁድ ፋሲካ ይከበር ነበር፡፡ ወደ ኢትዮጵያ ታቦተ ጽዮንን ተከትለው ከመጡት 12,000 ነገደ እስራኤል 2,500ዎቹ ተድባበ ማርያም እንደገቡ ይነገራል፡፡ በዘመነ ክርስትና አብረሃ ወአጽብሃ ተድባበ ማርያምን አንጽው ካበቁ በኋላ ጥር 21 ቀን በዓሏን ለማክበር ደንግገው ነበር፡፡ ይህም የበዓል አከባበር እስከ ዐፄ ገላውዴዎስ ከቆየ በኋላ ዐፄ ገላውዴዎስ ግራኝ አህመድን ድል አድርጎ ሲመለስ ግንቦት 1 ቀን ተድባበ ማርያም በመግባቱ «የገባሁት በልደቷ ዕለት ስለሆነ በዚህ ቦታ በደማቅ የንግሥ በዓል የእመቤታችን ልደቷ መከበር አለበት!» በማለት የልደታን ጽላት አሰገብቶ የተድባበ ማርያምን በዓል ግንቦት ፩ ቀን እንዲሆን አዋጅ አስነገረ፡፡ ከዚያ በኋላ እስከ አሁን ድረስ ግንቦት ፩ ቀን በደማቅ ሁኔታ ይከበራል፡፡ በማግስቱ ግንቦት ፪ የገላውዴዎስ ልደት በመሆኑ ተከብሮ ይውላል፡፡

ዋዜማው ከጧቱ 3:00 ሰዓት ተጀምሮ ከቀኑ 10:00 ሰዓት ያልቃል፤ ማሕሌቱ ማታ 2:00 ሰአት ተጀምሮ እስከ ቅዳሴ መግቢያ ይቀጥላል፡፡ በማሕሌት ሰርዓቱ ላይ የሚቆመው እንደሌላ ቦታ መልክዓ ማርያም ሳይሆን የራሷ ሊቃውንት የደረሱት መልከዓ ልደታ ነው፡፡ ለአብነት ያህል፦
"ሰላም ለህንብርትኪ ዘአርያሁ ሰሌዳ ወለ ማሕጸንኪ ቤቴል ማሕደረ ክርስቶስ እንግዳ በእንቲአኪ ይብሉ ማርያም ሠራዊተ ንጉሥ ይሁዳ ዳዊት ዘመዳ ኢያቄም ወለዳ ኢያቄም ወለዳ ዳዊት ዘመዳ፡፡" እያሉ የራሷን ድርሰት ይቆማሉ፡፡ ይህም በሌላ ቦታ አይባልም፡፡

ከክብረ በዓሏ በተጨማሪ ከዓመት እስከ ዓመት ስብሐተ ነግሕና ሠዓታት ቅዳሴና መዓልት ሰዓታት አይቋረጥባትም፡፡ ወደ ሌሎች አንዳንድ አድባራት ስንሄድ "ዓመት እስከ ዓመት ይቀደስበት ነበር፤ ስብሐተ ነግሕ ይቆምበት ነበር" ተብሎ ይነገርበታል እንጅ ሲሆን አይታይም። በተድባበ ማርያም ግን እስከ አሁን ድረስ ቅዳሴና ስብሐተ ነግሕ የሌሊት ሰዓታትና የመዓልት ሰዓታት ዓመት እስከ ዓመት አይቋረጥም፡፡ እንዲያውም የቃለ እግዚአብሔር የቀለሙ ፋብሪካ ናት ቢባል ማጋነን አይሆንም፤ መላ የኢትዮጵያ ሊቃውንት ያውቁታልና፡፡

በታቦር ተራራ የምትገኘዋ ታሪካዊቷ ርእሰ አድባራት ወገዳማት ተድባበ ማርያም የሐዲስ ኪዳን የሥርዓት መነሻ፣ የቅኔ ምንጭ፣ የድጓ ምልክት ነቅ፣ ድጓ ከጠፋ በኋላ በጎ ነገርን በሚያሳስብና በበጎ ሰዎች እያደረም መልካም የሆነውን ሁሉ እንደፈቃዱ የጠፋውን መልሶ የተሰወረውንም ገልጦ በሚያሰራ በእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ፈቃድና አነሳሺነት እንደገና የድጓን ምልክት በመድረስ ለትወልድ ያሰተላልፉ አዛዢ ጌራንና አዛዢ ዘራጉኤልን ያፈራች፣ ዙሪያዋን በታላላቅ ገዳማት እና አድባራት የተከበበች፣ የአማርኛ ቋንቋ የተፈጠረባት፣ የጎንደር የጎጃም የሸዋና የወሎ መገናኛ ማዕከል፣ ለስነ ልሳን ተመራማሪዎች ትልቅ የቅርስ ስፍራ፣ ሰማንያ ጋሻ መሬት የሸፈነ የደንቆሮ ጫካ (ቦረና ሳይንት ብሔራዊ ፓርክ) የሚገኝባት ስትሆን ለኢትዮጵያ ታላቅ የታሪክ ማሕደር ናት፡፡
520 viewsቤተ ዋሊ, edited  12:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-03 15:39:01 አስደናቂዋ የታሪክ ማኅደር መካነ ቅዱሳን ወመካነ ነገሥት
#ርእሰ_አድባራት_ወገዳማት #ተድባበ_ማርያም
★ ከክርስቶስ ልደት በፊት በ982 ዓ.ዓ በሊቀካህናት አዛርያስ ተመሥርታ 2996 ዓመታትን ያስቆጠረቺው ድንቅ ገዳም፤ በቀደሙት አበው ብሒልም፦ "...በተለይም ሴት ልጅ ዕረፍተ ሞት ሳይገታት ትሳለማት!" ተብሎ የተነገረላት መካነ አብርሃ ወአፅብሃ ጥንታዊቷ ርዕሰ አድባራት ወገዳማት ተድባበ ማርያም ታሪክ ባጭሩ፡፡

#Forward_Pin_React_Comment በማድረግ ይህችን ድንቅ ቦታ ለተዋህዶ ልጆች ሁሉ ማስተዋወቅ ትልቅ በረከት ነው።
☞ @gishenmaryam

“ጥበበ ንነግሮሙ ለጠቢባን ወአኮ ጥበበ ዝዓለም ወኢጥበበ መላእክተ ዝንቱ ዓለም ዘሀለዎሙ ይሰዐሩ ዘንነግሮሙ። ዘእንበለ ጥበበ እግዚአብሔር ዘንነግር ዘኅቡእ ወክቡት ዘአቅደመ እግዚአብሔር ሐድሶቶ ወአጽንዖቶ እምቅድመ ይትፈጠር ዓለም ዘሠርዐ እግዚአብሔር ለክብረ ዚአነ።”
«በበሰሉት መካከል (ለአዋቂዎች) ግን ጥበብን እንናገራለን፥ ነገር ግን የዚችን ዓለም ጥበብ አይደለም የሚሻሩትንም የዚችን ዓለም ገዦች ጥበብ አይደለም፤ ነገር ግን እግዚአብሔር አስቀድሞ ከዘመናት በፊት ለክብራችን የወሰነውን፥ ተሰውሮም የነበረውን የእግዚአብሔርን ጥበብ በምሥጢር እንናገራለን።» ፩ኛ ቆሮ ፪፥ ፮- ፯

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በደቡብ ወሎ ሀገረ ስብከት በአምሐራ ሳይንት ወረዳ ውስጥ የምትገኘው ጥንታዊቷ የታሪክ ማሕደር ርእሰ አድባራት ወገዳማት ተደባበ ማርያም የተመሰረተችው በዘመነ ብሉይ ኪዳን በፈቃደ እግዚአብሔር በቃዳማዊ ምኒልክ ዘመነ መንግስት 982 ዓመተ ዓለም ነው፡፡ ይህቺ ገዳም 2993 ዓመታትን ስላስቆጠረችና ከአክሱም ጽዮን ቀጥላ ስለተተከለች ከ4ቱ መናብርተ ጽዮን 2ኛ የሆነች እጅግ በጣም ጥንታዊትና ታሪካዊት ገዳም ናት። ለ1000 ዓመታት ያህል መስዋዕተ ኦሪት ተሰውቶባታል፤ ከዚያ እስካሁን ደግሞ መስዋዕተ ወንጌል እየተሰዋባት ነው። በዘመነ ኦሪት በሊቀ ካህናት፣ በዘመነ ሐዲስ ደግሞ በፓትርያርክ ትመራ ነበር። በ1951 ዓ.ም ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ፓትርያርክነቷን ነጥቀው ይህ ስልጣኗ ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ርእሰ ሥልጣናት ተደረገ።

በ40 ዓመቱ በዮዲት ጉዲት ዘመነ ፅልመት፣ በ15 ዓመቱ በግራኝ አህመድ የመከራ ዘመንና በ5 ዓመቱ የፋሺስት ጣሊያን ወረራ ጊዜ ቃጠሎም ውድመትም አልደረሰባትም።
በገዳሟ ዘወትር የ7 ቀን ምሕላ፣ ስብሐተ ነግሕና ጸሎተ ቅዳሴ ዓመቱን ሙሉ አይሰታጎልም።
ሁልጊዜ የሚቀድሱት 7 ልዑካን ሲሆኑ አመራረጣቸውም 20 ዓመት ያልሞላቸው 4 ሕፃናት ዲያቆናትና 3 አበው መነኮሳት ሆነው ነው።
ገዳሟ ውስጥ 2 የንባብ፣ 2 የቅኔ፣ 4 የድጓ፣ 2 የአቋቋም፣ የዝማሬ መዋስዕትና የቅዳሴ ጉባዔያት አሏት።
በኢትዮጵያ 2ኛ በአምሐራ ክልል 1ኛ ባለ ብዙ ቅርስ፣ የታሪክ የባህልና የእምነት ባለ አደራ ናት።

አመሠራረቷም በመፅሐፈ ሱባኤ ዘአማኑኤል ካልእ ላይ እንደተጻፈው ሌዋዊያን ካህናት ከእስራኤል በአዛሪያስ መሪነት የጁን አልፈው ከዛሪዋ አምሐራ ሳይንት ደረሱ፡፡ 12 በሮች ባለው ተራራ ላይ ለእግዚብሔር ቤተ መቅደስ ከሰሩ በኋላ ግማሾቹ "ደብር ደባብ" እንበላት አሉ አዛርያስ እና የዳዊት የወንድም ልጆች ሳቤቅ ይህቺማ የኢየሩሳሌም የዳዊት መታሰቢያ ከተማ ትሆን ዘንድ ተድባበ ጽዮን እንበላት ብለው እንደሰየሟት ይነገራል፡፡

#አስራ_ሁለቱ_የተድባበ_ማርያም_መግቢያ_በሮች፦
፩) ፊት በር
፪) የጌላት በር
፫) የታንኳ በር
፬) አምጣ ፈረሴን በር
፭) ግራዢ በር
፮) ገተም በር
፯) አቅቻ በር
፰) ፈረስ መጣያ በር
፱) ቦካ በር
፲) ጨረር በር
፲፩) የጎድ በር
፲፪) መርገጫ በር ይባላሉ።

በዘመነ ሐዲስ ክርስትና ሲስፋፋ አምሐራዎች ተድባበ ጽዮን የሚለውን ስያሜ እንዲቀይሩ የአክሱም ነገሥታት አሰገደዷቸው ነገስታቱም አብረሃ ወአጽበሃ ተድባብ ጽዮንን ተድባበ ማርያም ብለው ሰየሙ፡፡ ትርጓሜውም ለእግዚአብሔር የተመረጠ ከፍተኛ ቦታ ማለት ነው፡፡

ርእሰ አድባራት ወገዳማት ተድባበ ማርያም በብሉይ ኪዳን ስለመመስረቷ ምስክር የሚሆኑ አንዳንድ የኦሪት ሥርዓቶች ሲከናወኑ ይስተዋላሉ። ታቦታቱ በበሚነግሡበት ወቅት በምስራቅ ያሉ ምዕመናን ንዋያተ ቅዱሳቱን ይዘው በምዕራብ ካህናት ተሰልፈው በሰሜን ያሉ ምዕመናን መጋረጃን ይዘው በደቡብ ያሉ ምዕመናን ጎራዴውንና ካሰማውን ይዘው መንቀሳቀሳቸው በኦሪት ዘኁልቁ ፪፣፫-፬ ያለውን የኦሪት ሥርዓት ያመለክታል፡፡

በሐዲስ ኪዳንም ቢሆን ክርስትና በ34 ዓ.ም በኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ከተሰበከ በኋላ እና ሚስጢራተ ቤተክርስቲያን የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ልደት ማክበር ጥምቀትንና መሰዋዕተ ወንጌል መፈፀም የጀመሩት ወንድምማማቾቹ ደጋግ ነገሥታት አብረሃ ወአጽብሃ በ330 ዓ.ም አካባቢ ነው፡፡ በዚህም ተድባበ ማርያም እነዚህን የሐዲስ ኪዳን ሥርዓቶች በመፈፀም ቀዳሚዋ ናት፡፡ በብሉይ ዘመን መስዋዕተ ኦሪት ከተሰዋባቸው መካከል አክሱም ጽዮን፣ ተድባበ ጽዮን የዛሬዋ ተድባበ ማርያም፣ መርጡለ ጽዮን የዛሬዋ መርጡለ ማርያም እና ጣና ቂርቆስ ይጠቀሳሉ፡፡

ቀዳማዊ ምኒልክ ከአባቱ ከንጉሡ ከሰሎሞን መንግስት ተቀብሎ ከኢየሩሳሌም ወደ ኢትዮጵያ ሲመጣ 4 መናብርተ ጽዮን ይዞ መጥቶ ነበር፡፡
1. የአክሱም ጽዮን ንቡረ ዕድ
2. የተድባበ ማርያም ፓትርያርክ
3. የመርጡለ ማርያም ርእሰ ርኡሳን
4. የጣና ቂርቆስ ሊቀ ካህናት ናቸው፡፡

ሦስቱ በእመቤታችን ምሳሌ በጽዮን ስም አራተኛው የሊቀ ካህናቱ ታቦት ቅዱስ ሚካኤል ነው፡፡ ከእነዚህ ጋር ቀዳማዊ ምኒልክን ተከትለው ወደ ኢትዮጵያ የመጡ 12,000 መሣፍንትና መኳንንት ወይዛዝርት 1,500 በተግባረ ዕድ የሰለጠኑ የወርቅና የብር፣ የብረትና የመዳብ፣ እንዲሁም የነሐስ አንጥረኞች አዋቂዎች ጠቢባን ፀበርተ ዕፀውና ወቀርተ አዕባን ናቸው፡፡

እነዚህ ኢትዮጵያ ገብተው በየክፍለ ሀገሩ ሥራቸውን ሲጀምሩ አክሱም ጽዮን ትግራይ ላይ ከመሠረቱ በኋላ የዳዊት የወንድም ልጅ ሳቤቅ የሰሎሞን አጎት ከመጀመሪያው ፓትርያርክ አዛሪያስ ጋር ተከዜን ተሻግሮ አምሐራ ሳይንት ደረሰ፡፡ የአሁኗ ተድባበ ማርያም ካለችበት አምባ ላይ ሲደርስ ቤተ እግዚአብሔር መሥራት ጀመረ፡፡ ቦታዋንም በሀገሩ ስም ገሊላ ብሎ ጠራት፡፡ ፓትርያርክ አዛሪያስ ደስ አለውና ስሙን በቡራኬ አፀደቀለት፡፡ ለዚህችውም ተድባበ ጽዮን ቤተ መቅደሱን ሰርቶ ሲጨርስ ከሌዋውያኑም ከካህናቱም ከፍሎ መስዋተ ኦሪት የሚሰው ካህናትና ሌዋውያንንም ሾመ፡፡ መስፍኑ ሳቤቅ ቤተልሄማዊም በገፀ ንጉሥ በወርቅ ወንበር የሚቀመጥ ነበር፡፡

ከዚህ ላይ ገሊላ ብሎ ከሰየመ በኋላ አገሮቹን አሻግሮ እያየ በሀገሩ ምሳሌ ይሰይማቸው ጀመር፡፡ ደብረ ዘይት፣ ኬብሮን አሁን ከቀን ብዛት የተነሳ ህዝቡ ኬብሮንን "ከሚኖር" ይለዋል ይኽውም ከተድባበ ማርያም አባ በር ወደ ምስራቅ ያለውን መግቢያ ነው፡፡ ወደ ቀኝ በኩል ተመልከተና ኢያሪኮ ትባል አለ ከቀን ብዛት ግን ሕዝቡ ኢያሪኮን "አራሆ" ይሏታል። ቀጥሎ ኢየሩሳሌም ቀጥሎ ሎዛ ከዚህ ከሎዛ በላይ ታቦር አለው ይኸውም በአፄ በዕደ ማርያም ዘመን መንግሥት የተነሱት የቅኔ ፈጣሪዎች እነ ዮሐንስ ገብላአዊ፣ እነ ሠምራ አብ፣ እነ ወልደ ገብርኤል እነ ደቅ እስጢፋኖስ የነበሩበት ነው፡፡
589 viewsቤተ ዋሊ, edited  12:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-24 08:14:53 የበዙቱ የቀደመ መነሻውን ከግሪኩ ተውሰው ሰላምታውንም በሰጣዊ ተሰጣዊ (ሰጪና ተቀባይ) ቃል ልውውጥ ይከውኑታል እንዲህ ሲሉ

#ሰጣዊ ☞ ክሪስቶስ አኔስቲ Χριστός ἀνέστη! Christ is Risen! ✧ ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን

#ተሰጣዊ ☜ አሊቶስ አኔስቲ "Ἀληθῶς ἀνέστη! " - "Truly He is Risen!" or "He Has Risen Indeed!" ✧ (አሜን) በአማን ተንሥአ

በአረማይኩ ግን ጥቂት የተሰጣዊ ምላሽ ልዩነት ያለው ሆኖ ይነገራል

☞ ክሪስቶስ ሃሪያቭ ኢ ሜሬሎዝ Քրիստոս հարյա՜վ ի մեռելոց: Christ is risen! ክርስቶስ ተንስሥኣ እሙታን

☜ ኦርኺያል ኤ ኻሮውቲዮን ክሪስቶስ Օրհնյա՜լ է Հարությունը Քրիստոսի: Blessed is the resurrection of Christ!" ቡሩክ ትንሣኤሁ ለክርስቶስ

በሀገርኛ ልሣናት አገባቡ እንዲህ ሊገለጥ ይችላል

⇝ በአማርኛ (☞ ክርስቶስ ተነስቷል፣ ☜ በእርግጥ ተነስቷል!)

⇝ ኦሮሚፋ /Oromiffa (☞ Kiristoos du'aa ka'eera ፣ ☜ Dhugumaan ka'eera)

⇝ በትግሪኛ (☞ ክርስቶስ ተንሢኡ፣ ☜ በኻቂ ተንሲኡ)

⇝ በጉራጊኛ (☞ ክርስቶስ ተረሳም፣ ☜ በውረም ተረሳም)
.
.
.
⇨☞ (በሌሎችም ሀገርኛ ልሳናት የቻላችሁትን ጨምሩበት)
☞ @gishenmaryam

✥ በዚህ መንፈሳዊ ቻናል ላይ የሚተላለፉ መንፈሳዊ ጦማሮች ለእርስዎም ለሌሎችም እንዲደርሱ ቻናሉንና ግሩፑን Follow / Subscribe / Join በማድረግ ሌሎችንም ወደ ፔጃችን ይጋብዙ።

በቴሌግራም ወዳጅ እንሁን?
☞ @Kidusat_Mekanat
☞ @Kidusat_Mekanat
☞ @Kidusat_Mekanat

የዩቲዩብ ቻናላችንን « መኮሬታ Mekoreta Tube »ን በሚከተለው ሊንክ ከፍተው Subscribe & Join ያድርጉ።
https://m.youtube.com/channel/UCUBStsekCniQtATyZDdFqQQ
807 viewsቤተ ዋሊ, edited  05:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-24 08:14:52 #የፋሲካ_አመላለስና_ሠላምታ - ምሕዛል ወቃለ ባሕ ዘትንሣኤ [Paschal troparion & Greeting]
በመጋቤ ሃይማኖት ዶክተር ቴዎድሮስ በለጠ
•᳀‌ ‌ ‌ ‌ ‌ ‌ ‌ ‌ ‌ ‌᯼᳀᯼‌ ‌ ‌ ‌ ‌ †✙† ‌ ‌ ‌ ‌᯼᳀᯼‌ ‌ ‌ ‌ ‌ ‌ ‌ ‌ ‌᳀•

✥ ጦማሩን ሌሎች እንዲያነቡትም Forward, Pin, React & Comment በማድረግ ለወዳጆችዎ ያካፍሉት።
☞ @gishenmaryam

(ለትንሣኤ የተቆነጠረ ሐሳብ)

ሀገርኛው የዘውትር ሰላምታችን ሰላም ላንተ ይኹን ጠላትኽን ያውድቅ ቢሰኛኽን ያርቅ! በሚል መነሻ ስብሐተ እግዚአብሔር የሚታከልበት ምኞት መግለጫና ምስጋና ማቅረቢያ ነው!

የሰላምታው መንገድ ደግሞ በሦስት ሂደት (በቃል በእጅና በአንገት) የሚከወን ነው።


መጨባበጥ (ተራክቦተ እድ ፣ ፅብጠት፣ ተጻብሖ) ☞ በእጅ የሚፈጸም ፦ በመጨባበጥ [handshake] በመተቃቀፍ [hugging] አልያም በጉንጭ በመሳሳም [cheek kissing] ይፈጸም የነበረውን በቀደሙቱ ዘንድ “አምኃ ቅድሳት” [holy kiss & kiss of peace ⇨ ἐν ἁγίω φιλήματι, και φιλί της ειρήνης ] እየተባለ የሚጠራው መንገድ ነው!

በዚኽ አጋጣሚ በወቅቱ ጉዳይ መጨባበጥ መተቃቀፍና መሳሳም ለወረርሽቹ በፍጥነት መዛመት ምክንያት መሆናቸውን አውቀን #አካላዊ_ፈቀቅታ|ን በመጠበቅ በበሽታው የምናልፍ ሳንሆን በሽታውን የምናሳልፍ ነገንም የምናይ እንድንሆን በተከታዮቹ መንገዶች ሰላምታ የምንለዋወጥ ይሁን!


"እጅ መነሳሳት" (እማኄ) ☞ ባንገት፣ በወገብና በጕልበት የሚፈጸም ነው።


የሰላምታ ቃል መለዋወጥ (በቃለ ተአምኆ) ሰላምታ በንግግር በመለዋወጥ የሚፈጸም ዋናዎቹ ናቸው!

ወደተቆነጠረው ሐሳብ እንለፍ ተዝካረ ትንሣኤው በሚታሰብበት ዐባይ ፋሲካ ፶ ዕለት በቤተክርስቲያናችን የሚፈጸም የተለየ ሰላምታና የዜማ ድጋም አመላለስ አለ።

የጌታችን ተዝካረ ትንሣኤ በቤተክርስቲያናችን ሰፊ ቦታና ትርጉም ያለው በመሆኑ የዓመት ሢሦው (⅓) ነገረ ፋሲካን የሚያስታውስ ነው (የፋሲካ ጾም ⁵⁵ እና ዘመነ ትንሣኤ⁵⁰)

በቅዳሴው መግቢያ መስዋእቱ ከቤተልሔም ወደ ቤተ መቅደስ ሲመጣ ከትንሳኤው እስከ በዓለ ፶ ጊዜው የተለየ መሆኑን ለማሳወቅ "እመቦ ብእሲ… " በሚለው መግቢያ ፈንታ "ሃሌ ሉያ ዮሴፍ ወኒቆዲሞስ ገነዝዎ ለኢየሱስ በሰንዱናት ለዘተንሥአ እሙታን በመንክር ኪነ ⇨ ሃሌ ሉያ ዮሴፍና ኒቆዲሞስ ድንቅ በሚሆን ጥበብ ከሙታን ተለይቶ የተነሣ ኢየሱስን በበፍታ ገነዙት፡፡" የሚል መልእክት በዜማ ይደርሳል!

ከዚኽ ውጪ ምሕዛል ዘትንሣኤ ወይም «የፋሲካ አመላለስ» ያልነው [Paschal troparion] እና ቃለ ባሕ ዘትንሣኤ «የፋሲካ ሰላምታ» ያልነው [Paschal Greeting] ከወትሮው በተለየ መንገድ ይፈጸማል። ሁለቱም በልሳነ ጽርእ (ግሪክ) #ክሪስቶስ_አኔስቲ / Χριστὸς ἀνέστη እየተባለ ይጠራል።

① #ምሕዛል_ዘትንሣኤ [Paschal troparion] የፋሲካ አመላለስ

በእርግጥ ምሕዛል አልያም ምስትሕዛል የሚባለው በድጓው ሊቃውንቱ የሚያስተዛዝሉት ዜማ ድጋም ሲሆን መነሻውን ድጓ ያደረገው በቅዳሴው ክፍል የምናገኘው ይኽ የተዝካረ ትንሣኤ ምስትሕዛል
«ህየንተ ዝውእቱ ጊዜ ባርኮት እምትንሣኤ እስከ በዓለ ፶ » በሚል የገባ ሦስት ጊዜ ደጋግመን በመቀባበል የምናደርሰው " ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን ሞተ ወኬዶ ለሞት ለእለ ውስተ መቃብር ወሀበ ሕይወተ ዘለዓለም ዕረፍተ ⇝ ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ ተነሣ ሞቶ ሞትን አጠፋው በመቃብር ላሉ የዘላለም ዕረፍት የሚሆን ሕይወትን ሰጠ "

በሌሎች ምሥራቃውያን (Eastern ) እና ጽባሓውያን (Orientals) ዘንድም በእጅጉ የተለመደ ነው!

በግሪክ ፓስካል ትሮፓርዮን አልያም [χριστος ανεστη] የሚባል በዜማ የሚደርስና የዘመነ ሐዋርያት ጭምር ጥንታዊ መገለጫ አለው ተብሎ የሚታመን ነው።

Χριστὸς ἀνέστη ἐκ νεκρῶν,

θανάτῳ θάνατον πατήσας,

καὶ τοῖς ἐν τοῖς μνήμασι,

ζωὴν χαρισάμενος!

የንባባዊ ፍቺው አማርኛ ትየባ (transliteration) ደግሞ ይኽን ይመስላል!

ክርስቶስ አኔስቲ ኤክ ኔክሮኒ ፣ ታናቶ ታናቶን ፓቲሳስ፣ ኬቲስ ኤን ቲስ ሚ’መሲ፣ ዞይን ካሪዛሜኖስ

በትርጉሙም የእኛው " ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን ሞተ ወኬዶ ለሞት ለእለ ውስተ መቃብር ወሀበ ሕይወተ ዘለዓለም ዕረፍተ ⇝ ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ ተነሣ ሞቶ ሞትን አጠፋው በመቃብር ላሉ የዘላለም ዕረፍት የሚሆን ሕይወትን ሰጠ " ካለው ጋር አቻ ፍቺ አለው።

Christ is risen from the dead, Trampling down death by death, And upon those in the tombs, Bestowing life!

② #ቃለ_ባሕ_ዘትንሣኤ [Paschal Greeting] «የፋሲካ ሰላምታ»

በሓ ወይም ባሕ የሚባለው የሰላምታ የቡራኬ ቃል ፍሥሓ ሰላም የሚለውን የሚገልጥ ነው!

በቤተክርስቲያናችን አበው መምህራንም ቅድመ ቃለ እግዚአብሔር ፣ ድኅረ ቃለ ቡራኬ ለ፶ው ዕለት ከምእመናን ጋር የሚለዋወጡት ሰላምታ ነው! ከዚያም አልፎ ምእመናንም ከምእመናን ጋር የትንሳኤውን የምሥራች ለማብሰርና መልካም ምኞት ለመግለጥ ያውሉታል።

አቀራረቡ በአመላለስ አገባብ የሚከወን ሲሆን ሰላምታ ሰጪና ሰላምታ ተቀባይ ይኽን ይለዋወጣሉ፤

በኢትዮጵያዊቷ የተዋህዶ ቅድስት ቤተክርስቲያናችም ከ6ኛው ምዕተ ዓመት አንስቶ አገልግሎት ላይ መዋሉን መረጃዎች ይገልጣሉ። በቅዱስ ያሬድ ምዕራፍ (ዘመወድስ) ውስጥ በፍታሕ ሊተ ሥር በመሪና ተመሪ የሚቀርብ ዛሬ ለፋሲካ ሰላምታ የምንገለገልበት የትንሣኤው ምስክርነት ቃል አለ። እንዲህ ይላል ፦

☞ ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን ••• በዓቢይ ኃይል ወሥልጣን፤
አሠሮ ለሰይጣን ••• አግዓዞ ለአዳም፤
ሰላም ••• እምይእዜሰ፣
ኮነ ••• ፍስሐ ወሰላም!
[ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ ተነሣ ••• በታላቅ ኃይልና ሥልጣን፤ ሰይጣንን አሠረው ••• አዳምን ነጻ አወጣው፤ ሰላም ••• ከዛሬ ጀምሮ፤ ሆነ (ይሁን) ••• ደስታና ሰላም!]

በመቀባበል እንዲህ ተጽፏል

☞ Christ is risen from the dead!
☜ By the highest power and authority!
☞ He chained Satan!
☜ Freed Adam!
☞ Peace!
☜ Henceforth!
☞ Is!
☜ Joy and Peace!

☞ ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን!
☜ በዐቢይ ኃይል ወሥልጣን!
☞ አሰሮ ለሰይጣን!
☜ አግዐዞ ለአዳም!
☞ ሰላም!
☜ እምይእዜሰ!
☞ ኮነ!
☜ ፍስሐ ወሰላም!

ክርስቶስ በታላቅ ኃይልና ሥልጣን ከሙታን ተለይቶ ተነሣ ዲያብሎስን አሰረው አዳምን ነጻ አወጣው፤ሠላም ከዛሬ ጀምሮ ሰላም ሆነ!

በውጪው ግን ሰጥቶ መቀበል እንጂ አመላለስ የሌለው ባለ አጭር ይዘት ሆኖ በተለያየ ስያሜ የሚጠራ ነው The Paschal Greeting / the Easter Acclamation / The Paschal troparion / Christos anesti…
☞ @gishenmaryam
692 viewsቤተ ዋሊ, edited  05:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-09 16:31:24
#የቤተክርስቲያን_መከራ_በኦሮሚያ_ምድር
የእውነት ቤተክርስቲያን ከዚህ በላይ ትገፋለች ወይ??

የኦነግ ወታደር በኦሮሚያ ምድር አዳአ በርጋ ወረዳ እንዲህ ምዕመናን ገድሎ ቀሪዎቹን አሰድዶ ቤተክርስቲያን ውስጥ በመግባት ልብሰ ተክኖ በመልበስ እንዲህ እየተሳለቁ ይገኛሉ፡፡፡
1.0K viewsቤተ ዋሊ, 13:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-06 09:39:56 የእመቤታችንን በዓለ ልደት ለማክበር ወደ ጥንታዊቷ
#ርእሰ_አድባራት_ወገዳማት_ተድባበ_ማርያም
ኑ አብረን እንጓዝ! አብረን እናክብር! አብረን እንባረክ!
* መነሻ ሚያዚያ 27 እና 29
* መመለሻ ግንቦት 3

ስለ ታሪካዊቷ ተድባበ ማርያም ምን ያክል ያውቃሉ?
→ ከተመሰረተች 2996 ዓመታት አስቆጥራለች።
→ በአመሰራረቷ ከአክሱም ጽዮን ቀጥሎ በኢትዮጵያ ፪ኛ ናት።
→ ከቀዳማዊ ምኒልክ እስከ አፄ ኃይለ ሥላሴ ድረስ በቅብዓ ነገሥት ከብረው ለነገሡ ደጋግ ነገሥታት ኃይለ እግዚአብሔር የሚያገኙባቸው ጥንታዊያን ቅዱሳት መካናት ከሆኑት ከ፬ቱ ጥንታዊያን መናብርተ ጽዮን መካከል አንዷ ናት።
→ ዐቃቤ ቅርስ ከሆኑት ገዳማቶቻችን በኢትዮጵያ ፪ኛ በአማራ ክልል ፩ኛ ናት።
→ ደገኛው ንጉሥ አጼ ገላውዴዎስ የቤተክርስቲያንና የሃገር ጠላት የሆነውን ግራኝ አህመድን ያሸነፈው የተድባበዋን ታቦተ ልደታ ለማርያም ይዞ ዘምቶ ነው።
→ በትውፊተ አበው “...በተለይም ሴት ልጅ ዕረፍተ ሞት ሳይገታት ትሳለማት!” ተብሎ የተነገረላት የጥንታዊቷ ተድባበን የጊቢዋን አፈር የያዘ አማኝ ክርስቲያን ከመከራ ሥጋ ከመከራ ነፍስ ይድናል።
→ እንደ ገነት ፲፪ መግቢያና መውጫ በሮች ያሏት ሲሆን እነርሱም፦ ፊት በር፣ የጌላት በር፣ የታንኳ በር፣ አምጣ ፈረሴን በር፣ ግራዢ በር፣ ገተም በር፣ አቅቻ በር፣ ፈረስ መጣያ በር፣ ቦካ በር፣ ጨረር በር፣ የጎድ በር እና መርገጫ በር ይባላሉ። የአካባቢው ሕዝበ ክርስቲያንም በሚደንቅ መተባበር በነዚህ በሮቿ ሁሉ በየተራ ታጥቆ በንቃት የሚጠብቃት አስገራሚ ገዳም ናት።
→ ሄሮድስ ካስፈጃቸው ፩፻፵፬ ሺህ ሕፃናት ከፊሉ አጽም፣ የእመቤታችን እናት የቅድስት ሀና የራሷ ፀጉር፣ የ፳፰ ሰማእታትና የ፮ እጨጌዎች ዐጽማቸው በክብር ያረፈባት ቅድስት ቦታ ናት።
→ እመቤታችን ለቀደሙ አበው እንደገለጠቺው በየዓመቱ ለአስተርእዮ ማርያም የምትገለጥባት ንጽሕት ገዳም ናት።
→ በ340ዓ.ም በጻድቃን ነገሥታት በአብርሃ ወአጽብሃ ታንጾ በየዘመኑ እየታደሰ በግራኝ ወረራ ጊዜ የተሰወረ ግሩም መቅደስ ያላት ናት።
→ በግእዝ፣ በአረማይክና በአረብኛ ቋንቋዎች የተጻፉ በወርቅና በብር የተለበጡ እጅግ በርካታ ጥንታዊ ቅዱሳት መጻሕፍትን ለዘመናት ጠብቃ ያቆየች መካነ ቅርስ ናት።
- የአቡነ ሰላማ ከሳቴ ብርሃን፣ የአቡነ ፊልሞና እና የሌሎችንም ቅዱሳን የእጅ መስቀሎች፤ በብር በወርቅና በአልማዝ ፈርጥ የተሰሩ የቀደሙ አበው ካባዎችንና ዘውዶችን የያዘ ቤተ መዘክር ያላት አስደናቂ የታሪክ ማሕደር ናት።
→ የብፁእ አቡነ ጌርሎስ መንበር፣ የአንጋፋዎቹ የድጓ ሊቃውንት የአዛዥ ጌራና የአዛዥ ዘራጉኤል፣ የዋድላ ቅኔ መስራች ሊቅ የዮሐንስ ገብላዊ መፍለቂያ ናት።
→ በአላውያንና መናፍቃን ነገሥታት ዮዲት ጉዲት፣ ግራኝ አህመድ፣ አፄ ሱስንዮስ፣ በፋሺስት ጣሊያን ወረራ ወቅት ሁሉ የእሳት ቃጠሎም ሆነ ውድመት ሳያገኛት አልፋ ከነሙሉ ክብሯ ያለች እና በርካታ ቅርሶችንም ከወረራው አትርፋ ከጠላት ጠብቃ ያቆየች የታሪክም የእምነትም የባህልም ባለአደራ ናት።
→ ወንጌላዊው ቅ/ሉቃስ የሳላት ባለ፫ ተከፋች የገበታ ሥዕለ አድኅኖ ያለችበት የጥንታዊያት ስነጥበባዊ ቅርሶች መገኛ ናት።
→ ታቦተ ጽዮን ወደ ኢትዮጵያ ስትመጣ ከቀዳማዊ ምኒልክ ጋር ከመጡት 300 ሌዋውያንና 12000 በኩራት መካከል በሊቀካህናቱ አዛርያስ ፈቃድ ከ፲፪ቱም ነገድ ተውጣጥተው በቦታዋ ላይ ሰፍረው በኖሩት 2500 እስራኤላውያን በዕብራይስጥ ቋንቋ የተሰየሙና የቦታዋን ታሪክ ምጡቅነት የአገራችንንም ልዕልናና ምስጢራዊነት የሚገልጹ ከ፲፰ በላይ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ቦታዎች በተድባበና አካባቢዋ ያሏት ናት።
→ በ485 ዓ.ም ታቦተ መድኃኔዓለምን ይዘው በአብረንታንት ዋልድባ ለተሰወሩት የቡልጋ ቅዱሳን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በወጣት መልክ በአካል የተገለጠባት በኪደተ እግሩም የባረካት እጅግ የከበረች ቅድስት ቦታ ናት።
→ የደጋጎቹ አበው ነገሥታትና ቅዱሳን ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን በተለይም ጻድቁ አቡነ ተክለሃይማኖት፣ አቡነ ሰላማ ከሳቴ ብርሃን፣ አቡነ ፊልሞና፣ አቡነ እጨጌ ዮሐንስ፣ አቡነ ዜና ማርቆስ፣ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ፣ አባ ጽጌ ድንግል፣ ፱ቱ ቅዱሳን፣ በአቡነ ኢየሱስ ሞዓ ቡራኬ ከተላኩት 800ው ንቡራነ እድ ቁጥራቸውና ስማቸው ያልተገለጠ በርካታ ቅዱሳን ያገለገሉባት ጥንታዊት መካነ ጸሎት ናት።

→ ይህ ልዩ የንግሥ ጉዞ የሰባቱ ታላላቅ ቅዱሳን አበው ጥንታዊ የዋሻ ገዳማት፦ ጋስጫ አቡነ በጸሎተ ሚካኤል፣ ተአምረኛው ደብረ ባህርይ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ፣ ደብረ ጽጌ ዋሻ ጻድቁ አባ ጽጌ ድንግል፣ መንክራዊው ወለቃ አቡነ ገብረ እንድርያስ፣ ሚዳ መራኛ አቡነ መልከ ጼዴቅ፣ ቀዳማይ ግሸን አቡነ ያዕቆብ ዋሻ፣ ገዛዛ ዋሻ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስን፣ ተአምረኛዋ ቅድስት ጸበለ ማርያም፣ ድማ ጊዮርጊስ፣ ጥንታዊቷ መርጡለ ማርያም፣ ገዳመ አስቄጥስ ቅ/አርሴማ፣ ደብረ ሊባኖስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ጨምሮ በርካታ ገዳማትን ያካተተ የቃልኪዳን በረከታቸውን የምናፍስበት ልዩ ጉዞ ነው።

* መነሻ ሚያዚያ 27 እና በ29
* መመለሻ ግንቦት 3
* የጉዞ ዋጋ 3000 ብር

√ በዚህ ልዩ የንግሥ ጉዞ መርሐ ግብር ላይ መሳተፍ ከፈለጉ ሳያመነቱ ይደውሉልንና አብረን እንጓዝ!!! ለበለጠ መረጃ በሚከተሉት የስልክ አድራሻዎች በመደወል ፈጥነው ይመዝገቡ!
0901070707
0911289877
#ማኅበረ_ቅዱስ_ፊልጶስ_ወአቡነ_ሳሙኤል_ዘዋልድባ

✥✞✥ ጽሑፉን ሌሎች እንዲያነቡትም Forward እና Pin ያድርጉ፤ በዚህ መንፈሳዊ ቻናል ላይ የሚተላለፉ መንፈሳዊ ጦማሮች ለእርስዎም ለሌሎችም እንዲደርሱ ቻናሉን Subscribe / Follow / Join ያድርጉ ሌሎችንም ወደ ፔጃችን ይጋብዙ።

"ገዳምህን የረገጠ" ብቻ ሳይሆን "ገዳምህን ለሌሎች ያሳዬ ...እምርልሃለሁ!" ተብሎ ቃል የተገባላቸው ቅዱሳን እንዳሉን ገድለ አቡነ ዘርዓ ብሩክን ያስታውሱ!!!

በቴሌግራም ወዳጅ እንሁን?
☞ @gishenmaryam
☞ @gishenmaryam
☞ @Kidusat_Mekanat
☞ @Kidusat_Mekanat

የዩቲዩብ ቻናላችንን « መኮሬታ Mekoreta Tube »ን በሚከተለው ሊንክ ከፍተው Subscribe & Join ያድርጉ።
https://m.youtube.com/channel/UCUBStsekCniQtATyZDdFqQQ
968 viewsአንተነህ ውብሸት, edited  06:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-05 14:28:08
"እንደ ተሰቀለ ሆኖ ተሥሎ ነበር" ገላ ፫፥ ፩
+++
ስቅለትህን እንስለው ዘንድ ተገብትቶን ሳይሆን በደምህና ወዝህ የሳልክብን ፍቅር ልባችንን ፈንቅሎት ነው፡፡
✿✿✿፥፥፥፥፥✞ ✞፥፥፥፥፥✿✿✿
አቤቱ ቀለማት ከገለጡህ በላይ በስቅለትህ የተገለጠልን ፍቅር ቢበልጥብን የአለማትን ሠዓሊ እንሥልህ ዘንድ ተነሳን ፡፡
""""""""""""""""""""""
እኛም እንለምንሀለን በስቅለትህ የሠቀልካቸውን ክፋ ምግባራት የምንተውበትን በጎ ሃሳብ በውስጣችን ሳልብን፡፡
777 viewsቤተ ዋሊ, 11:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-04 11:09:36 ✥ ልዩ ጉዞ መስዋእተ ኦሪት ወደተሰዋባት የደቡቧ ኮከብ ✥
#ጥንታዊቷ_ጽዮን_ሰማያዊት_ብርብር_ማርያም_ገዳም
* መነሻ ሚያዚያ 1
* መመለሻ ሚያዚያ 9
#Share_Tag_Like_Comment በማድረግ ገዳሙን ለተዋህዶ ልጆች እናስተዋውቅ
☞ @negeretewahido

→ በዚህ ጉዟችን እስከ ኬኒያ ጠረፍ ድረስ ተጉዘን በርካታ ጥንታዊ ገዳማትና አድባራትን እንሳለማለን። ለምሳሌ፦
#በአርባ_ምንጭ_ከተማና_በአቅራቢያው፦ መንክራዊው ዝጊቲ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ፣ ተአምረኛዋ ደብረ ጽዮን ማርያም፣ አርባ ምንጭ መድኃኔዓለም፣ ቅ/ገብርኤል እና ሌሎችንም... #በደቡብ_ኦሞ፦ ወላይታ ሶዶ ደብረ መንክራት አቡነ ተክለ ሃይማኖት፣ ዋጅፎ ኪዳነ ምሕረት፣ ቦረዳ ድንቅ ዋሻ ቅ/ሚካኤል፣ ምዕራብ ዓባይ ቅ/ገብርኤል፣ ላንቴ ቅ/ሚካኤል፣ ሻራ ቅ/ሥላሴ እና ሌሎችንም... #በብርብር_አካባቢ፦ ጥንታዊቷ የደቡብ ኮከብ ጽዮን ሰማያዊት ብርብር ማርያም፣ ጥንታዊው ኤሉ ቅ/ገብርኤል፣ ዶርዜ ቅ/ጊዮርጊስ እና ሌሎችንም... #በጨንቻ_አካባቢ፦ ጨንቻ መድኃኔዓለም እና ኤልዞ ቅ/ሚካኤል እና ሌሎችንም... ሐመር ቡስካ ማርያም ወአቡነ ሙሴ ጸሊም ገዳም፣ ኤልቦሬ ቅድስት ኪዳነምሕረት፣ በሻዴ ዮሐንስ፣ ሻንቆ ጊዮርጊስ፣ ኬንያ ጠረፍ ኦሞራቴ ኪዳነ ምሕረትን እና ሌሎችንም ቅዱሳት መካናት በመሳለም የቃልኪዳን በረከታቸውን አፍሠን የአቢያተ ጉባዔያት ጸሎትና ቡራኬ ተቀብለን በደቡብ ክልል የሚገኙ የተለያዩ ማኅበረሰባዊ አኗኗርና ባሕሎችን ጎብኝተን እንመለሳለን።

በተጨማሪም በዓለ ሆሣዕናን በዝዋይ ስለምናከብር በዝዋይ ሐይቅ ደሴቶች ላይ የሚገኙ ጥንታዊ ገዳማትን፦ ደብረ ገሊላ ፳፬ቱ ካህናተ ሰማይና አቡነ ተክለ ሃይማኖት፣ ደብረ ሲና ቅድስት ማርያም፣ ታላቋ ደብረ ጽዮን ቅድስት ድንግል ማርያም ገዳም፣ ፋማት / ፋንዱሮ ጌቴሴማኒ አርባዕቱ እንስሳ፣ አይሱት / ጠዴቻ ደብረ አብርሃም እና ዝዋይ ሐመረ ብርሃን ቅዱስ ገብርኤል ገዳምን እንሳለማለን።
* መነሻ ሚያዚያ 1
* መመለሻ ሚያዚያ 9
* የጉዞ ዋጋ ማረፊያን ጨምሮ 3000 ብር
✥ ውስን ወንበሮች ብቻ ስለቀሩን ይህንን ቅዱስ ቦታ ለመሳለም የምትሹ የኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ልጆች ሁሉ ደውሉልንና አብረን እንጓዝ!!!

#ልዩ_ማሳሰቢያ፦ በደቡብ ኦሞ ሀገረስብከት ከፍተኛ ቁጥር ያለው አርብቶ አደር ወደ ክርስትና እየመጣ የሚገኝበት ሀገረስብከት ነው። ይህን ከፍተኛ ፍሠት ያለው የቅድስት ሥላሴ ልጆች በቅጥረ ቤተክርስቲያን ይጸኑ ዘንድ የአገልግሎት መዋቅር ያስፈልጋል።

ስለዚህም በዚህ ልዩ ጉዟችን ለበርካታ አዲስ አማኒያን [የአንገት መስቀል፣ ማዕተብ፣ ነጠላና የሰንበት ትምህርት ቤት አልባሳት]፣ በቤተ መቅደሱ ለሚከናወነው ሥርዓተ ጸሎት ማለትም ለማሕሌት ለጸሎተ ኪዳንና ለቅዳሴ (አኮቴተ ቁርባን) አገልግሎት የሚሆን መብዓ [ጧፍ፣ እጣን፣ ዘቢብ፣ ሻማ፣ ...ወዘተ]፣ ለአዳዲስ አቢያተ ክርስቲያናት አገልግሎት የሚውሉ ንዋያተ ቅዱሳት [ከበሮ፣ መቋሚያ፣ ጸናጽል፣ ልብሰ ተክህኖ፣ መጎናጸፊያ ከነቀጸላው፣ ጽንሓሕ፣ ኩስኩስት፣ ጻሕል፣ መጋረጃ፣ ቃጭል፣ ደወል እና ሌሎችንም] በቻልነው መጠን ይዘን ለመሄድ አስበናል።

በረከቱን መሳተፍ የምትፈልጉ ኦርቶዶክሳዊያን ሁሉ ከተጠቀሱት ውስጥ ልባችሁ የሻተውንና አቅማችሁ የፈቀደውን ገዝታችሁ በመላክ እና ፈቃደ እግዚአብሔር ከሆነላችሁ ደግሞ አስፈላጊውን ነገር ሁሉ ይዛችሁ አብራችሁን በመጓዝ ራሳችሁ በእጃችሁ ሰጥታችሁ ጸሎት ተቀብላችሁ በምድራዊ ነገር የማይገመት ብዙ በረከት እንድታፍሱ ጥሪ እናቀርባለን።
☞ @negeretewahido

#መነሻ_ቦታዎች፦ ቀጨኔ መድኃኔዓለም፣ አራዳ ቅ/ጊዮርጊስ፣ መስቀል አደባባይ ቅ/እስጢፋኖስ እና መገናኛ

#የምዝገባ_ቦታዎች፦
1) ቀጨኔ መድኃኔዓለም አካባቢ፦፦
ማትያስ የመኪና ዕቃ መሸጫ፣
ማርሶሊ ፎቶ ቤት፣

2) አራዳ ጊዮርጊስ አካባቢ
ገኒ የወንዶች ፀጉር ቤት
መሲ ሕትመትና ማስታወቂያ

3) ባላችሁበት አካባቢ ለመመዝገብ (ትኬት ለመቁረጥ)
በኢትዮጵያ ንግድ ባንክና በአዋሽ ባንክ ሁሉም ቅርንጫፎች በካሽ ወይም በሞባይል ባንኪንግ በሚከተሉት የመምህር አንተነህ ውብሸት አካውንቶች አስገብታችሁ ደረሰኙን የጉዞው ቀን ይዞ መምጣት ወይንም Screenshot አድርጋችሁ በቴሌግራም ልትልኩልን ትችላላችሁ።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1000099794899
አቢሲኒያ ባንክ 73439825
አዋሽ ባንክ 01320104564900

#ለመንፈሳዊ_ጉዞዎቹ_የሚያስፈልጉ_ነገሮች፦ የቀበሌ መታወቂያ (ፓስፖርት)፣ ለብርድ የሚሆን ወፍራም ጃኬት፣ ለእግር መንገድ የሚሆኑና ተቀያሪ ጫማዎች፣ ሌሊት የሚለበስ ስሊፒንግ ባግ / ወፍራም ጋቢ/ ወፍራም ወይባ/ ፎጣ/ ቀለል ያለ ብርድ ልብስ/፣ ክርስቲያናዊ አለባበስ፣ ጃንጥላ፣ የእጅ ባትሪ፣ ሰዓት አክባሪነት፣ ታጋሽነት፣ የወጡበትን መንፈሳዊ ዓለማ ለማሳካት በጋራ መትጋት...

✥ በማኅበራችን የጉዞ መርሐ ግብራት መሳተፍ ከፈለጉ ሳያመነቱ ይደውሉልንና አብረን እንጓዝ!!! ለበለጠ መረጃ በሚከተሉት የስልክ አድራሻዎች በመደወል ፈጥነው ይመዝገቡ!
0901070707
0911289877
0941960723
#ማኅበረ_ቅዱስ_ፊልጶስ_ወአቡነ_ሳሙኤል_ዘዋልድባ
☞ @negeretewahido

✥✞✥ ጽሑፉን ሌሎች እንዲያነቡትም Forward እና Pin ያድርጉ፤ በዚህ መንፈሳዊ ቻናል ላይ የሚተላለፉ መንፈሳዊ ጦማሮች ለእርስዎም ለሌሎችም እንዲደርሱ ቻናሉን Join / Follow / Subscribe ያድርጉ፤ ሌሎችንም ወደ ፔጃችን ይጋብዙ።

"ገዳምህን የረገጠ" ብቻ ሳይሆን "ገዳምህን ለሌሎች ያሳዬ... እምርልሃለሁ!" ተብሎ ቃል የተገባላቸው ቅዱሳን እንዳሉን ገድለ አቡነ ዘርዓ ብሩክን ያስታውሱ!!!

በቴሌግራም ይቀላቀሉን
☞ @waldiba
☞ @waldiba
☞ @waldiba

የዩቲዩብ ቻናላችንን « መኮሬታ Mekoreta Tube »ን በሚከተለው ሊንክ ከፍተው Subscribe & Join ያድርጉ።
https://m.youtube.com/channel/UCUBStsekCniQtATyZDdFqQQ
532 viewsእልመስጦአግያ ዘሐዋርያት, 08:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-25 07:30:16 ፬) #ምሥጢራዊው_ደብረ_ሐዊ_ቅዱስ_ያሬድ_ገዳም
→ እምነቱ በቅዱሳን መላእክት ከገነት የሚመጣበት ድንቅ ቦታ፤
→ ትምህርት ለማይገባው ሁሉ በኃይለ እግዚአብሔር በቅዱስ ያሬድ ቃልኪዳን አእምሮውን ለብዎውን ባርኮ አስተዋይና ጠቢብ የሚያደርግ ፈዋሽ ጠበሉን ተጠምቀውና ጠጥተው የሚመለሱበት፤
→ ጃንደረባው ባኮስ፣ ሊቁ ቅዱስ ያሬድና ሌሎች በርካታ ቅዱሳን በተሰወሩበት ደብረ ሐዊ ገዳም የቃልኪዳናቸውን በረከት የሚያፍሱበት፤
→ እጅግ በርካታ ገዳማትን የሚሳለሙበት የጉዞ መርሐ ግብር ነው።
→ መነሻ ግንቦት 6 መመለሻ ግንቦት 18
→ የጉዞ ዋጋ፦ ማረፊያን ጨምሮ 4000 ብር

፭)#ምጢራዊው_እመጓ_ደብረ_ቆጵሮስ_ቅዱስ_ዑራኤል
→ ይህ ጉዞ በዓለ ዕርገትን በእመጓ በዓለ መድኃኔዓለምን በአርብዓሐራ መድኃኔዓለም የምናከብርበትና በርካታ የመንዝ ገዳማትን ያካተተ ልዩ ጉዞ ነው።
→ መነሻ፦ ግንቦት 24 መመለሻ፦ ግንቦት 27
→ የጉዞ ዋጋ፦ ቦታው ላይ ምግብና ማረፊያን ጨምሮ 1500 ብር
[በተጨማሪም በሰኔ ጾም ሐዋርያት ውስጥ ከሰኔ 3- 5፣ ከሰኔ 10- 12፣ ከሰኔ 17- 19፣ ከሰኔ 24- 26 ወደ ምሥጢራዊው እመጓ ዑራኤል ገዳም ጉዞ ይኖረናል።]

፮) #ማኅበረ_ሥላሴ_ገዳም_እና_የጣና_ገዳማት
→ ከባህርዳር እስከ ጎርጎራ የሚገኙ የጣና ገዳማትን ጨምሮ በርካታ ጥንታዊ ገዳማትና አድባራትን የምንሳለምበት እና ታሪካዊ ቦታዎችን የምንጎበኝበት የ9 ቀናት ልዩ የንግሥ ጉዞ ነው።
→ በጉዟችን በቀን 3 ጊዜ በመዓዛ ገነት የሚታጠነውንና እመቤታችን በየቀኑ በጣና ቂርቆስ ገዳም እየተገለጸች የምትባርከውን ባለ ልብ ቅርጹን የጣና ሐይቅን ከባህርዳር እስከ ጎርጎራ በዘመናዊ ጀልባ እየቀዘፍን በቅዱሱ ሐይቅ ላይ የሚገኙ በርካታ ቅዱሳት መካናትን እንሳለማለን።
* መነሻ፦ ሐምሌ 4 ጠዋት 11:30
* መመለሻ፦ ሐምሌ 12

፯) #ቁሉቢ_ቅዱስ_ገብርኤል_ገዳም
→ መካነ ሰማእታት ጅጅጋ ኪዳነ ምሕረትን፣ ታሪካዊውን ጅጅጋ ቅ/ሚካኤልን፣ ጥንታዊውን ጀጎል መድኃኔዓለምን እና ሐረር ሥላሴን እንሳለማለን።
* መነሻ፦ ሐምሌ 16
* መመለሻ፦ ሐምሌ 20
☞ @gishenmaryam

#መነሻ_ቦታዎች፦ ቀጨኔ መድኃኔዓለም፣ አራዳ ቅ/ጊዮርጊስ፣ መስቀል አደባባይ ቅ/እስጢፋኖስ እና መገናኛ

#የምዝገባ_ቦታዎች፦
1) ቀጨኔ መድኃኔዓለም አካባቢ፦፦
ማትያስ የመኪና ዕቃ መሸጫ፣
ማርሶሊ ፎቶ ቤት፣

2) አራዳ ጊዮርጊስ አካባቢ
ገኒ የወንዶች ፀጉር ቤት
መሲ ሕትመትና ማስታወቂያ

3) ባላችሁበት አካባቢ ለመመዝገብ (ትኬት ለመቁረጥ)
በኢትዮጵያ ንግድ ባንክና በአዋሽ ባንክ ሁሉም ቅርንጫፎች በካሽ ወይም በሞባይል ባንኪንግ በሚከተሉት የመምህር አንተነህ ውብሸት አካውንቶች አስገብታችሁ ደረሰኙን የጉዞው ቀን ይዞ መምጣት ወይንም Screenshot አድርጋችሁ በቴሌግራም ልትልኩልን ትችላላችሁ።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1000099794899
አቢሲኒያ ባንክ 73439825
አዋሽ ባንክ 01320104564900

#ለመንፈሳዊ_ጉዞዎቹ_የሚያስፈልጉ_ነገሮች፦ የቀበሌ መታወቂያ (ፓስፖርት)፣ ለብርድ የሚሆን ወፍራም ጃኬት፣ ለእግር መንገድ የሚሆኑና ተቀያሪ ጫማዎች፣ ሌሊት የሚለበስ ስሊፒንግ ባግ / ወፍራም ጋቢ/ ወፍራም ወይባ/ ፎጣ/ ቀለል ያለ ብርድ ልብስ/፣ ክርስቲያናዊ አለባበስ፣ ጃንጥላ፣ የእጅ ባትሪ፣ ሰዓት አክባሪነት፣ ታጋሽነት፣ የወጡበትን መንፈሳዊ ዓለማ ለማሳካት በጋራ መትጋት...

✥ በማኅበራችን የጉዞ መርሐ ግብራት መሳተፍ ከፈለጉ ሳያመነቱ ይደውሉልንና አብረን እንጓዝ!!! ለበለጠ መረጃ በሚከተሉት የስልክ አድራሻዎች በመደወል ፈጥነው ይመዝገቡ!
0901070707
0911289877
0941960723
#ማኅበረ_ቅዱስ_ፊልጶስ_ወአቡነ_ሳሙኤል_ዘዋልድባ
☞ @gishenmaryam

✥✞✥ ጽሑፉን ሌሎች እንዲያነቡትም Forward እና Pin ያድርጉ፤ በዚህ መንፈሳዊ ቻናል ላይ የሚተላለፉ መንፈሳዊ ጦማሮች ለእርስዎም ለሌሎችም እንዲደርሱ ቻናሉን Subscribe / Follow / Join ያድርጉ ሌሎችንም ወደ ፔጃችን ይጋብዙ።

"ገዳምህን የረገጠ" ብቻ ሳይሆን "ገዳምህን ለሌሎች ያሳዬ ...እምርልሃለሁ!" ተብሎ ቃል የተገባላቸው ቅዱሳን እንዳሉን ገድለ አቡነ ዘርዓ ብሩክን ያስታውሱ!!!

በቴሌግራም ወዳጅ እንሁን?
☞ @Kidusat_Mekanat
☞ @Kidusat_Mekanat
☞ @Kidusat_Mekanat

የዩቲዩብ ቻናላችንን « መኮሬታ Mekoreta Tube »ን በሚከተለው ሊንክ ከፍተው Subscribe & Join ያድርጉ።
https://m.youtube.com/channel/UCUBStsekCniQtATyZDdFqQQ
1.5K viewsቤተ ዋሊ, edited  04:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ