Get Mystery Box with random crypto!

#ሐጊያ_ሶፊያ - #ቅድስት_ጥበብ (#Hagia_Sophia) 'ሐጊያ ሶፊያ' ወይም 'ቅድስት ጥበብ' | ቅዱሳት መካናት

#ሐጊያ_ሶፊያ - #ቅድስት_ጥበብ (#Hagia_Sophia)
"ሐጊያ ሶፊያ" ወይም "ቅድስት ጥበብ" (Holy Wisdom) በሚለው የመድኃኔዓለም ስሙ የተሰየመው ይህ የእግዚአብሔር ወልድ ቤተ ክርስቲያን በቁስጥንጥንያ መንበር ታላቁ ሕንጻ ቤተ ክርስቲያን ሲሆን እጅግ አስደናቂ የሕንጻ ጥበብ የታየበትና የብዙ ቅዱሳን አጽም ያረፈት ታላቅ ካቴድራል ነበረ። ሀጊያ ሶፊያ ታላቁ ሊቅ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ወንበር ተክሎ ጉባዔ ዘርግቶ ያስተማረበትና በርካታ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን የፈሩበት ጥንታዊ ካቴድራል ነው። በኢትዮጵያ ገዳማዊ ሕይወትን ያስፋፉት ተሰዓቱ ቅዱሳንም በወቅቱ በሮም ግዛት ስር ከነበረቺው ቁስጥንጥንያ (የአሁኗ ኢስታንቡል) ከዚህ መንበር በተገኘ መንፈሳዊ እውቀት የከበሩ ደጋግ አበው ቅዱሳን ናቸው።

በኦርቶዶክሳዊያንና በዓለም የክርስትና ታሪክ ውስጥ ታላቅ ሥፍራ ያለውና በዩኔስኮ ከተመዘገቡ የዓለም ቅርሶች አንዱ የሆነው ይህ ካቴድራል በ1453 GC ቁስጥንጥንያ በኦቶማን ቱርክ እጅ ስትወድቅ በሱልጣን መሐመድ ዳግማዊ ትእዛዝ ወደ መስጊድነት ተቀይሯል። ከ1934 GC እስከ 2020 GC (ሐምሌ 3 ቀን 2012 ዓ.ም) ድረስ ለ86 ዓመታት ደግሞ ወደ ሙዝየምነት ተቀይሮ የቀደመ ታሪኩ ብቻ እየተነገረ ለጎብኚ ክፍት ሆኖ ቆይቷል። ከ10/07/2020 በኋላ ደግሞ ወደ መስጊድነት ቀይረውታል።

በታሪካዊው የቅድስት ሐጊያ ሶፍያ ካቴድራል ወደ መስጊድነት ከተቀየረ ከወር በሗላ በፈረንጆቹ ነሐሴ 15 ቀን 2020 (9/12/2012 ዓ.ም) በዕለተ ዐርብ በቦታው በማሰገድ ላይ የነበረው ኢማም በድንገት ወዲያውኑ ሕይወቱ ሊያልፍ ችሏል። በዚህም በተከታዮቹ ዘንድ ከፍተኛ መደናገጥ ተፈጥሯል።

አወዛጋቢው ሐጊያ ሶፊያ ቅርስ፦ «ዛሬ ለጁምዓ ጸሎት ክፍት ይሆናል!» የሚል ዜና በፈረንጆቹ አቆጣጠር ሐምሌ 10 ቀን 2020 ዓ.ም ሰምቶ ሕዝበ ክርስቲያኑ አዝኖ ሙስሊሙ ደግሞ ተደስቶ እንደነበር የሚታወስ ነው።

የሃገሪቱ ከፍተኛ ፍርድ ቤት መላው ዓለም የሚደምበትንና የ1500 ዓመታት ዕድሜ ያስቆጠረውን ጥንታዊውን የሐጊያ ሶፊያ ካቴድራል ሕንጻ በከፊል መስጊድ ሆኖ እንዲያገለግል የወሰነው በፕሬዝዳንቱ ኤርዶጋን ግፊትና ፊርማ ነው፡፡
በቱርክ ኢስታንቡል የሚገኘው ሀጊያ ሶፊያ ከዓለም ቅርሶች ልዩ ቦታ የሚሰጠው ነው። የኢስታንቡል ከንቲባ የርሊካያ አሊ በወቅቱ፦ “ሙስሊሞች በዜናው ተደስተዋል፤ ለጁምዓ ሁሉም ሰው እዚያ ለመገኘት ይፈልጋል።” ብለው ነበር፡፡

ቱርክ ታሪካዊውን ሙዚየም መስጊድ እንዲሆን ወሰነች። 1500 ዓመታት ያስቆጠረው ይህ በዩኔስኮ ልዩ ቦታ የሚሰጠው ታሪካዊ ሕንጻ ቤተክርስቲያን ወደ ሙዚየምነት የተቀየረው በፈረንጆቹ በ1934 ነበር፡፡ ከዚያ ቀደም ባሉት 3 ዓመታት ግን ዝግ ሆኖ ነበር።

ይህም የሆነው ቅርሱ በቢዛንታይን ጊዜ ሲገነባ የዓለም ትልቁ ቤተ ክርስቲያን የነበረ በመሆኑ ነው፡፡ በተጨማሪም ታላቁ ሊቅ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ያስተማረበት ነው።

ጥንታዊው ካቴድራል ወደ መስጊድነት ሲቀየር ለጁምዓ ስግደቱ ከተገኙት ምዕመናን መካከል የቱርኩ መሪ ጣይብ ኤርዶጋን አንዱ ሆኖ ቁርዓን ሲቀራ ታይቶ ነበር፡፡

ይህ ቅርስ መስጊድ ይሁን ወይስ ቅርስ ሆኖ ይቀጥል የሚለው ጉዳይ ላይ ለዓመታት የቱርክ ማኅበረሰብን ሲያነታረክ እንደነበር የሚታወስ ነው፡፡ ኤርዶጋን ይህ ቅርስ መስጊድ እንዲሆን መወሰኑን ሲያሳውቁ በርካቶች የተደሰቱትን ያህል በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ቅሬታዎችም ተስተናግደዋል፡፡ ለምሳሌ፦
የካቶሊኩ ጳጳስ ፖፕ ፍራንሲስ ውሳኔውን ተከትሎ፦ ‹‹ለኢስታንቡል እጸልያለሁ፤ ሳንታ ሶፊያን ባሰብኩ ቁጥር ሐዘኔ ይበረታል›› ብለው ነበር፡፡
የምሥራቅ ኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናትም በውሳኔው ሐዘናቸውን ገልጸው ነበር፡፡

☞ @gishenmaryam
☞ @Kidusat_Mekanat