Get Mystery Box with random crypto!

ዜና ዘብጥያ…! '…ዛሬ ከሰዓት ከምሳ በኋላ ቀውሲ በላይ መኮንን በV8 መኪናው የሞላቸውን አጃቢዎ | Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ዜና ዘብጥያ…!

"…ዛሬ ከሰዓት ከምሳ በኋላ ቀውሲ በላይ መኮንን በV8 መኪናው የሞላቸውን አጃቢዎች ይዞ አፍሪካ ኅብረት ግቢ ውስጥ ወደሚገኘው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ያመራል። እንደ ደረሰም የምዕራብ ሸዋና የአሩሲ ቄሮ ናቸው የተባሉ አጃቢዎቹን መኪና ውስጥ አስቀርቶ ከገሚሶቹ ጋር ወደ ባንኩ ያመራል።

"…በአፍሪካ ኅብረት ግቢ ውስጥ የውጭ ሃገር ገንዘብ ማስቀመጥ ይቻላል። ቀሲስ በላይም በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከፓትርያርኩና ከአቡነ አብርሃም ቀጥሎ ዋና ባለ ሥልጣን ነውና ፍተሻም የለበት። እናም በሀገረ አሜሪካ በከፈተው የባንክ አካውንቱ ይተላለፍለት ዘንድ የተጻፈ ቼክ ይዞ ነበር የደረሰው። 5 ሚልዮን ዶላር። በ120 ብር ምቱት።

"…የባንኩ ሰዎች ፈሩ። ደነገጡም። ቀውሲ በላይ የጃዋር ጓደኛ ነው። የቄሮ አለቃ ነው። በዚያ ላይ የኦሮሞ ደኅንነቶችን አጃቢ ይዞ የመጣው። የባንኩ ሠራተኞች ጨነቃቸው። ቆይ አንዴ ይጠብቁን ፕሮሰስ እያደረግንሎት ነው አሉት። እሺ ብሎ ተዘፍዝፎ ተቀመጠ።

"…ቆይቶ የፌደራል ፖሊሶች እና የአፍሪካ ኅብረት የራሱ የፀጥታ ሠራተኞች በአካባቢው ፈሰሱ። ቀውሲ በላይንም በቁጥጥር ስር እንደዋሉት ነገረው ወደተዘጋጀው መኪና ይቀጥል ዘንድ አመለከቱት። ቀውሲ በላይም ከእንግሊዝኛ በቀር በኦሮሚኛም፣ በአማርኛም ቢፎክር፣ ቢያቅራራ፣ ቢቆጣ ማን ይስማው። ሰሞኑን በልማት ስም የቤተ ክርስቲያን ህንፃ ሲያስፈርስ የነበረው በላይ ውሎ ሳያድር ራሱ ፈረሰ። ለልጁ፣ ለራሱ፣ ለዘመዶቹ የቤተ ክርስቲያንን ሀብት የመዘበረው ሰው ሳይበላው ተያዘ።

"…የፌደራል መኪና፣ የአፍሪካ ኅብረትም የፀጥታ ሠራተኞች በመኪናቸው፣ ሌሎች ደግሞ የቀውሲ በላይን መኪናን አጅበው ወደ ማእከላዊ ወንጀል ምርመራ መሄዳቸው ነው የተነገረኝ። አንዴ ዐቢይ ጋር ልደውል አላለም…!

• ሥራው ያውጣው…!