Get Mystery Box with random crypto!

እነሆ ዛሬም የማያልቅ ምክሬ ለዐማራው… '…በፕሪቶሪያው ስምምነት መሠረት ዐማራ ከጨዋታው ከወጣ ቆ | Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

እነሆ ዛሬም የማያልቅ ምክሬ ለዐማራው…

"…በፕሪቶሪያው ስምምነት መሠረት ዐማራ ከጨዋታው ከወጣ ቆየ። የወያኔ ጦር ትጥቅ አለመፍታት ብቻ ሳይሆን ተጨማሪ ትጥቅ ሁላቸውም አቅርበውለት እስከ አፍንጫው ድረስ በሚገባ ታጥቋል። የስንቁም ጉዳይ ክረምትን አሻግሮ እስከሚቀጥለው ዓመት የሚያሻግረው ዱቄትና ዘይት አግኝቷል። ለጁንታው በመቶ ቢልየን የሚቆጠር ብርና በዶላር ጭምር ከኢትዮጵያ ካዝና መስጠቱን አቢይ የትግሬን ወኪሎች አዲስ አበባ በጋበዛቸው ጊዜ ነግሮናል። በዚያ ላይ የጁላ ኦሮሙማ ጦር በዐማራ ፋኖ ስለተዋረደ ዐማራን ለመበቀል ሲል ስለሚረዳውም የሚመጣው የወያኔ ጦርም በሜካናይዝድ ተደራጅቶ ነው።

"…እናም እንደኔ እንደኔ ይሄንንም የወያኔ ጦር ልክ እንደብራኑ ጁላ ጦር በሽምቅ ውጊያ ከዚያም እንደ ሕዝብ በመግጠም፣ ማድቀቅ፣ መሰባበር ነው እንጂ ክላሽ በያዘ ሚኒሻ መመከት አይሞከረም። ዐማራው ማድረግ ያለበት ወያኔና አቢይ ልክ እንደራያው ሶዬ የሚያጸዱት እንዳለ ሆኖ እሱም ከሃዲ የብአዴን አመራሮችን እያጸዳ፣ ያለውን የሚኒሻና አድማ ብተና ኃይል ወደፋኖ ትግል በመቀላቀል እንደተለመደው ወደ ሽምቅ ውጊያ ዙረው ኪሳራ ላይ መጣል ነው። ዐማራን ልክ እንደ ትግሬ እንደ ሕዝብ ለማስነሣት የዐማራ ሥነ ልቦና ከባድ ቢሆንም ቆይቶ ጠኔና ስደት ውረደቱ እንዲባንን ያደረገዋል። መከራ ይመክረዋል።

"…ፋኖዎች መደማመጥ ከቻሉ። እንደ ጠላት በጣም ጨካኝ አረመኔ ከሆኑ፣ ነገ ወያኔ መጥታ የምትዘርፈውን ባንኩንም፣ የጦር መሣሪያውንም ከወዲሁ ከታጠቁ፣ የነበሩትን መሳሳቦች አርመው ከተናበቡ የራያ ሚኒሻ ብቻ ከፋኖ ጋር ተቀናጅቶ መታገል ከቻለ ሁለቱንም ደምስሶ ማሸነፍ ይቻላል። ለጊዜው ባለው ሴራ እነሂዊ አይደለም አላማጣ ወልዲያም ሊገቡ ይችላሉ። በዚህ መደናገጥ አይገባም። የዐማራ አክቲቪስቶችም እንደ ዐዋቂ ሁኑ።

• አመሰግናለሁ