Get Mystery Box with random crypto!

'…የሚያሳዝነው እንዲህ ዓይነቱ የኦቦ በቴ ኡርጌሳ አሟሟት ነው። በገዛ ቀበቶ ታስረህ፣ ካረፍክበት | Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…የሚያሳዝነው እንዲህ ዓይነቱ የኦቦ በቴ ኡርጌሳ አሟሟት ነው። በገዛ ቀበቶ ታስረህ፣ ካረፍክበት ሆቴል ተጠርተህ ወጥተህ፣ ከሌሊቱ በ6 ሰዓት፣ በ6 ፖሊሶች ታጅበህ፣ በ6 ጥይት በትውልድ መንደርህ፣ በቆሻሻ መጠያ ስፍራ ጭንቅላትህ ተበረቃቅሶ በኦሮሞ ምድር በኦሮሚያ ፖሊሶች ከመሞት በላይ የሚሰቀጥጥ ምን አለ።

"…ማዘንስ ለእንዲህ ዓይነቱ ምስኪን ነው…! ማዘንስ ለቄሮ ነው። ማዘንስ ለምስኪኑ ኦሮሞ ነው። እንጂማ ለአፄ ቴዎድሮስ ልጅ ለዐማራው ፋኖ ለናሁሰናይማ የምን ልቅሶ፣ የምን ኀዘን ነው? እልልታ፣ ከበሮ፣ ጭፈራ፣ ዝማሬ፣ መዝሙር ነው እንጂ እንዴት የምን ለቅሶ? የማይደረገውን።

"…እኔ ዘመዴም ብሆን አሁን ወንድ እባላለሁ…? የወንድ አልጫ እንጂ…!