Get Mystery Box with random crypto!

መልካም… '…ወያኔ ወደ ራያ አላማጣ እየመጣች ነው ሲባል ከወትሮው በተለየ መልኩ እግዚአብሔርን | Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

መልካም…

"…ወያኔ ወደ ራያ አላማጣ እየመጣች ነው ሲባል ከወትሮው በተለየ መልኩ እግዚአብሔርን የሚያመሰግን፣ ወደ ፔጄም ተንጋግቶ የሚገባ ብዙ ግሪሳ እያየሁ ነው። እግዚአብሔር ይመስገን።

"…አዲስ አበባን ፊንፊኔ በማለት የሚጠራት አዲሱ በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኤርቪን ጆሴ ማሲንጋ መጋቢት 16/2016 ዓ.ም የክልሉን ፕሬዘዳንት አቶ አረጋ ከበደን፣ በዐማራ ክልል የብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ሓላፊ ይርጋ ሲሳይና የዐማራ ክልል የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ መንገሻ ፈንታውን ጠርቶ ቪዛ እንዲሰጣቸው ከተደረገ በኋላ ህወሓት ራያን በደንብ እስክትይዝ ድረስ ወደ ኢትዮጵያ ድርሽ እንዳይሉ የኪስ ገንዘብ ዶላር ተሰጥቷቸው ወደ ላስቬጋስ አሜሪካ በሸነና እንዲሉ ተልከዋል። በዚያም አንድ ኤርትራዊ ባለ ሀብት እንዲያስተናግዳቸውም ተመድቧል።

"…ዐማራ ከባድ እና የዋንጫ ጨዋታ የሆነ በብዙ ግንባሮች ዐውደ ውጊያ ይጠብቀዋል። በሰሜን ጎንደር፣ በሰሜን ወሎ በራያና በዋግ ኽምራ፣ በደቡብ ወሎ። በጎጃም እና በሸዋ ውጊያ ይጠብቀዋል። የሞት ሽረት ውጊያ ነው። በአዲስ አበባና በዋና ዋና ከተሞች ደግሞ የዐማራና የትግሬ ተወላጆች በኦሮሙማው ይለቀማሉ፣ ይጠረጋሉ። ዐማራና ትግሬን አባልቶ በሸሻ አድርጎ ጊዜ ሳያጠፋ ደቡብን ለመሰልቀጥ ዝግጅቱን ጨርሷል። በቅርቡ ገረድ፣ ባርያ ሆነው ለአቢይ ሲሰግዱ የከረሙ ዐማሮች ለማኝ ይሆናሉ። ቱ…ዘመዴ አሁንስ አበዛኸው ሲሉኝ የነበሩ በሙሉ ደም እምባ ያለቅሳሉ። ከሃዲው አቢይ የብልጽግና አመራሮችን ቀርጥፎ ይበላቸዋል። አኝኮ ይተፋቸዋል። በጁንታው ጦርነት ጊዜ ወያኔ ላይ አፋቸውን የከፈቱ ሁሉ ይበላሉ። የሆነው ሆኖ ዋንጫው የዐማራው ነው።

"…ርዕሰ አንቀጽ ልጽፍ ነኝ። ለማንበብ ዝግጁ ናችሁ…?