Get Mystery Box with random crypto!

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

የሰርጥ አድራሻ: @zemedkunbekelez
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 412.24K
የሰርጥ መግለጫ

"ይህ የቴሌግራም ቻናሌ ግንቦት1/2011ዓም የተከፈተ ነው። የእኔን የስልክ ወጪ ጨምሮ አገልግሎቴን መደገፍ የምትፈቅዱ ጓደኞቼ በ
👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia እና
👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል ማገዝ ትችላላችሁ። በተረፈ ለቤተ ክርስቲያኔና ለኢትዮጵያ ሀገሬ የሚጠቅመውን ሁሉ አበረክት ዘንድ አብዝታችሁ ጸልዩልኝ።

Ratings & Reviews

4.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 5

2024-04-18 10:49:20
“…ጠላትነቱን በተንኰል የሚሸሽግ፥ ክፋቱ በጉባኤ መካከል ይገለጣል።” ምሳ 26፥26 … “…ቅንዓትና አድመኛነት ባሉበት ስፍራ በዚያ ሁከትና ክፉ ስራ ሁሉ አሉና።” ያዕ 3፥16

"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?

"… መልሱ እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ
63.7K views07:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-17 20:33:35
መልካም…

"…መቼም ያን ሊማሊሞ፣ አርበረከቴ ግራካሱ የመሰለ እኝኝብላ የሆነ የዛሬውን ርዕሰ አንቀጼን እንዳነበባችሁ በላይክ አድራጊው ብዛት ገምቻለሁ። አይናችሁን እስትራፖ ሳላስየዘው አልቀርም። የሆነው ሆኖ የጻፍኩት ጊዜ አግኝተው የማንበብ ፍላጎት ላላቸው የቲጂ መንደር ጓደኞቼ ነው። ያው በል በል ሲለኝ፣ ግራ ትከሻዬንም ቀኝ ትከሻዬንም ሲሸክከኝ እና ሲያመኝ ጤና የለኝም አይደል? ለዚያ ነው ያስረዘምኩባችሁ። እስከ ነገ ድረስ ሌላ ነገር አልጽፍባችሁም። በመሃል ካልሸከከኝ በቀር ቃሌን እጠብቃለሁ ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ። ብጽፍስ ደግሞ ምን አለበት? ምን ክፋት አለው? አይደል…?

"…ለማንኛውም በሥራ ምክንያት ትናንት ያልገባንበት የቲክቶክ መንደራችንን ለመጎብኘት ገባ ብዬ ወጣ ለማለት ወደዚያው እየሄድኩ ነው። እስከዚያው በርዕሰ አንቀጹ ላይ ያላችሁን የራሳችሁን አስተያየት ለማንበብ ዝግጁ መሆኔን ስገልፅ ከፍ ባለ አክብሮት እና ትህትና ነው። (ወይ ትህትና እቴ)

• እየጻፋችሁ…እየሄዳችሁ…!
80.8K views17:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-17 18:36:25 ከላይኛው የቀጠለ… …ማወዛገብም ሊሆን ይችላል! የቼሪ እና አስረስ ጨዋታ ማለቴ ነው! የሆነው ሆኖ. . .ምክንያቱ ከላይ ከተጠቀሱት አንዱ ይሁን ወይም ሌላ ፍፃሜው ግን አጓጊ ነው! ይልና ይሄንኑ የታደሰ ወረደን መግለጫ መነሻ በማድረግ የፌደራል መንግሥቱ እና የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ከስምምነት መድረሳቸውን በማተት ሌላ ትንተና ይሰጣል። አደገኛውንና በከባዱ የተመከረበትን ምክርም የሚያሳይ ምልክትም ይሰጣል።

"…ታዲያ የፌደራል መንግሥቱ እና የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር በትግራይ ክልል ፖሊስ፣ የዐማራ ፋኖን ከመሬቱ በማንፃት የራሱንን አስተዳደራዊ መዋቅር እንዲገነባ ከፈቀደ ይህም በምዕራብ ትግራይ ይቀጥላል ማለት ነው። ይህ ሆነ ማለት ደሞ የፕሪቶሪያው ስምምነት ተተግብሯል ማለት ነው!! በዚህም የፋኖ ኃይል ላይ ከፍተኛ ስጋት የሚፈጥር አጋርነት ሲሆን ለፌደራሉ መንግስሥት ደግሞ የዓለም መንግሥታት የሚለቁትን የዶላር ገንዘብ ይለቀቅለታል ማለት ነው።

"…ነገር ግን የሻብዕያ ልጅ የሆነው ፋኖን ይላል "ነገር ግን የሻብዕያ ልጅ የሆነው ፋኖን የፌደራሉ እና የትግራይ ኃይል በጋራ ጥምረት የሚመቱት ከሆነ እና የምዕራብ ትግራይ ጉዳይም እንደ ደቡብ ትግራይ በትግራይ ሠራዊት የሚፈታ ከሆነ የኤርትራ እና የኢትዮጵያ ቀጠናዊ ቆርሾ ከፍ ይላል ማለት ነው። ይህ ከሆነ ደግሞ የዓለም መንግሥታት በአፍሪካ ቀንድ በዚህ ሰዓት ውጥረት ለማስተናገድ ፍቃደኛ ስለማይሆኑ አንዱ ኃይል በዓለም መንግሥታት ይመታል ማለት ነው።

"…የኢትዮጵያ መንግሥት የዓለም መንግስታትን ፍላጎት በፕሪቶሪያው ስምምነት የሚያስፈፅም ከሆነ የኤርትራ ጉዳይ ከኢትዮጵያ ጋር ሳይሆን ከዓለም መንግሥታት ጋር ስለሚሆን ጨዋታው በትግራይ መንግሥት እና በፌደራል መንግሥቱ ስምምነት ወቅት ተጠናቅቋል በማለት በጓዳ ተመክሮ የወሰኑበትን ጉዳይ ይዘረግፈዋል። ዐማራ ከትግሬ ጋር ፍቅር ይኖረኛል ብለህ መጃጃሉን ትተህ በእነሱው የጭካኔ መስመር ሄደህ መብትህን እንድታስከብር እመክርህሃለሁ። ሲያዩት የሚከብድ የሚመስል ቢሆንም ዓረቡም ሆነ እነ አሜሪካ ተደርበው ቢገቡ ሱማሌና አፍጋኒስታን ድል የነሱትን ኃይል የዐማራ ፋኖ ያቅተዋል ተብሎ አይታሰብም። ስለዚህ ከዚህ የትግሬዎቹ ትንተና ተነሥተን ትግሬም አቢይም የሚፈልጉትን ፍላጎት ለሟሟላት ዐማራውን ተጠቃቅሰው ጭዳ ለያያደርጉት መጨረሳቸውን ዐወቆ በዚያው ልክ መዘጋጀት ያስፈልጋል።

• ድል ከዐማራው ፋኖ…!
• ድል ለተገፋው ለዐማራው ሕዝብ…!

• ድርጅቱ ዘመዴ ነኝ አሸበርቲው ከራየን ወንዝ ማዶ…!
80.1K views15:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-17 15:44:03 ከላይኛው የቀጠለ… ቦለጢቃ የሚጠመቁት።

"…ሰሞኑን በየከተማው በሰሜኑ ጦርነት አሳብበው ዐማራንም ትግሬንም ያፍሳሉ። ከምላሴ ጠጉር ይነቀል። ዐማራ ከፌደራል መሥሪያ ቤቶች በሙሉ ተለቅሞ ይወጣል። የኦሮሙማው ኃይል የአዲስ አበባን ባለቤትነት ለማረጋገጥ የሚቻለኝ በአዲስ አበባ የተከማቸውን የዐማራ ሕዝብ ቁጥር ማጥፋት መቀነስ ስችል ነው በማለት በጀመረው መንገድ የዐማራን ርስቱን፣ ታሪካዊ አሻራውን በሙሉ ይንዳል። ያፈርሳል። ያፈናቅለዋልም። ከሥራ ገበታውም ጠልዞ ያባርረዋል። የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን ጨምሮ የፌደራል መሥሪያ ቤቶች በሙሉ በፌደራል ፖሊስ የታዘዘ ነው በሚል ሁሉም የፌደራል መሥሪያ ቤቶች "ብሔራቸውን" እንዲሞሉ የተላከላቸውን ፎርም ደርሶኝ አይቼዋለሁ። እናም ዘጸአት የሆነ መፈናቀል በኦሮሙማው በኩል ዝግጁ ሆኖ ይጠባበቃል።

"…ሁሉም ክልል ሊበላ የተዘጋጀ እንደሆነ በማወቅ መከላከያው ውስጥ የሚገኙ ወታደሮች ጭምር አሁንም አልረፈደም ወደ ፋኖ ትግል በመቀላቀል ሀገሩንም ማዳን ራሳቸውንም ማትረፍ ይችላሉ። ያ ሲሆን ህወሓት በዚያው ትቆማለች። አቢይም ዐማራን ቀርጥፎ በልቶ ትግሬ ላይ መልሶ የማጣሪያ እኘካ በመፈጸም ወደ ሌላ ክልል በሻሻ ወደ ማድረጉ አይሄድም። ስልጤም ህወሓት ወደ ውጊያው ከገባች የወሎና የጎጃም፣ የጎንደር ዐማሮችን በሃይማኖት ስም መርዝ እየጋተ በገንዘብ እየረዳ ዐማራ ላይ ማዝመቱን ያቆማል። ብዙም ኃይል አይኖረውም። አቢይ አሕመድ ፋኖ ሊውጠው ሲደርስ የፋኖን ቀጣይ ዕቅድ በነመሳይ መኮንን በኩል እያስጠና፣ የፋኖ ቀጣይ ዕቅድም ምስጢር ስለማያውቅ ሃላል ስለሆነ ህወሓትን አላማጣን ከማሲያዙ በፊት የኦነጉን በቴን ገድሎ ኦሮሞ በራሱ አጀንዳ ተወጥሮ፣ ራሱን በቀበቶ አስሮ ፌስቡክ ላይ እየተንደባለለ እንዲያለቅስ አድርጎ ቁማሩን በሚገባ በጥንቃቄ ያስኬደዋል።

"…ዐማራ ከትግሬ፣ ትግሬ ከዐማራ፣ ኦሮሞ ከዐማራ እንዲናቆሩ ሒሳቡን ሠርቶታል። ኦሮሞ ወሎን የራሱ ለማድረግ ወሎ ከትግሬ ጋር መዋጋት አለበት። ትግሬ ለጊዜው በራያ ላይ ለሀጩን ቢጥልም በዐማራ ጥላቻ የታወረው ትግሬ የኦሮሚያ ካርታ ራያንም አጠቃልሎ እንደተዘጋጀ ማወቅም፣ ማየትም አይፈልግም። ኦሮሞ አቢይን እንዲያግዝ አውራ ጎዳናን ወደ ኦሮሚያ ክልል አጠቃልሎ አስገብቶለታል። ደብረ ብርሃን፣ ደብረ ሲናና ሸዋሮቢት ሲቀር ሌላው ለኦሮሚያ ለማካለል የሰሜን ሸዋን ሕዝብ የማያባራ ጦርነት ውስጥ አስገብቶታል። ቤቱ፣ ንብረቱ፣ እርሻው ወድሞ፣ ከብቱን እየነዳ በግፍ ወስዶበታል። ዘመቻ ወሎን የኦሮሞ ቲክቶከሮች ሳይቀሩ ዋይዋይ የሚሉበት ነው። ኦሮሞ አዲስ በመጣለት የመሬት ደስታ ምክንያት አቢይን በፋይናንስም ህውሓትን በፕሮፓጋንዳ በማሞካሸትም እየደከመ ነው። የኦሮሞ አክቲቪስት አሁን ተጋሩ ጀግና! ደቡብ እና እኛ አንድ ነን! አገው እና ቅማንት ኩሽ ናቸው! የሚሉት ለመብላት ሲያዘናጓቸው ነው። የፖለቲካው ቅማንትም፣ የፖለቲካው አገው ሸንጎም ሁለቱም ጥገኞች በራሳቸው ምንም ማረግ የማይችሉ መሆናቸውን ስለሚያውቁ እንደ እስስት እየተቀያየሩ ያጃጅሏቸዋል። ቆይቶ አይሸነፍም እንጂ ዐማራ ቢሸነፍ በግሬደር ሰብስቦ በአንድ ጉድጓድ ነው የሚቀብሯቸው።

"…ስለዚህ ኦሮሙማው ሓሳብ ነው የፈጠረው። ይሄን ሓሳቡን ደግሞ ተግባራዊ ለማድረግ፣ ደቡቡም፣ አፋሩም ልቡ ወደ ፋኖ ከሆነ አቢይ ኦሮሞን ብቻ ይዞ ምንም ማድረግ አይችልም። ትግሬም የጎጃም ፋኖ የወታደራዊ አዛዦቹን ከፈታላቸው በኋላ ፋኖ ፋኖ ማለት መጀመሯ አደጋ ስለፈጠረበት ነው አሁን በቶሎ ራያን ያዙ፣ ግን ከዐማራ ፋኖ ጋር አታብሩ ብሎ ያዘዘው። የአባዲ ዘሙ ልጅ በፌስቡክ ገጹ ህወሓት ለዐማራ ፋኖ መሳሪያ እያቀረበች ነው ብሎ ከለጠፈ በኋላ ለገሰ ቱሉ ወጥቶ ህወሓት እየረበሸች ነው። የዐማራ ክልል ሰላም እንዳይሆን እየረበሸች ነው ብሎም መግለጫ እስከመስጠት ደርሶ ነበር። ሲገመገም ሕወሓት የምትፈልገውን ሰጥተን ከዐማራ ጋር መቆሟን እንድታቆም ማድረግ አለብን፣ ሁሉንም ከምናጣ አንዱን እንጣ ነው ነገሩ። ትናንት እንዳልኩትም መከላከያ ተብዬው ራያ አላማጣን አስተዳዳሪ ገድሎ ህወሓት እንድትገባ ካደረገ በኋላ ለገሰ ቱሉ ወደ ሚዲያ ወጥቶ ህወሓት የፕሪቶሪያውን ስምምነት ጥሳለች ብሎ ዋይ ዋይ እያለ አዛኝ ቅቤ አንጓች ሆኖ ይተውናል ባልኩት መሠረት ይኸው ዛሬ ወደ ሚዲያ ወጥቶ "ህወሓት የፕሪቶሪያን ስምምነት ጥሷል" እያለ ይፎግራል። ማፈሪያ።

"…ብልፅግና ስር እደሌለው ዛፍ ነው። ተቦርቦሮም ያለቀ ነው። ማድያት ፊቱን ወርሮት በሜካፕ ሸፍኖ የሚዘንጥ ነው ብልጽግና። ውኃ ሲነካው የሚለቅ ቡራቡሬ ነው ብልጽግና። ምስጥ በልቶት ሊወድቅ የደረሰ፣ ነገር ግን በቀለም ያማረ፣ በመብራት ያሸበረቀን ቤት ነው የሚመስለው። ብልጽግና እስስት ነው። መናፍቅ ከሃዲ ነው። ብልጽግና አራጅ ነው። የአውሬ ገባሪ ነው። ብልፅግና ውሸት ሀሰትም አይደለም። ራሱ የሀሰት ፈጣሪዋ ነው። በብልፅግና ሴራ መታለል፣ መሸወድ አይገባም። እያንዳንዱ የብልጽግና ሴራ ለዐማራ ፋኖ እንደ መልካም እድል መጠቀም ያስፈልጋል። ሁሉም ዐማራ ዓይኑን ከ4ኪሎ ላይ ማንሣት አይገባውም። ለወያኔ የራያን ፋኖ ብቻ ይዞ መግጠም ይቻላል። የብልፅግና ሴራ በፈጠጠ ቁጥር ዐማራው ይነቃል። በሰው ኃይል ሁላ ይደራጃል። ብአዴን ይፈርሳል።

"…በመጨረሻም ይህቺን ከትግሬ ቦለጢቀኞች ቤት የተገኘች የፖለቲካ ትንተና እና ግምት፣ ትንቢትም በሉት ደጋግማችሁ ታነቡት ዘንድ በመጋበዝ ርዕሰ አንቀጼን ልቋጭ።

"…የወዲ ወረደ የትላንቱ መግለጫ፣ የጌታቸው አጭር የፌስቡክ ጽሑፍ እና የዛሬው የዐማራ ክልል መግለጫ

"…የትግራይ ክልል መንግሥት ከብአዴን ጋር የተፈራረመው ምንም ዓይነት ውል የሌለ በመሆኑ የክልሉ መንግሥት በዐማራ ክልል መንግሥት መግለጫ ላይ ምላሽ ይሰጣል ብዬ ባላምንም. . .ይህንን በሚመለከት ግን በቅርቡ የፌደራል መንግሥቱ የሚሰጠው መግለጫ ምላሽ ሁሉን ነገር ግልፅ ያረገዋል የሚል እምነት አለኝ…!

"…የሆነው ሆኖ የብአዴን እና የወጣት ሊጉ አብን ከቀናት በፊት የሰጠው መግለጫ መመሳሰል የሚነግረን ነገር ቢኖር

1. የክልሉ መንግሥት በዚህ አጋጣሚ ድጋፍ ለማግኘት እና ወልቃይት እና ራያ ከጦርነቱ በፊት ወደ ነበሩበት ሲመለሱ እኔ የለሁበትም ወረራ ሰጠ! ወረራ ነሳ በማለት ከደሙ ንፁህ ነኝ ለማለት!

2 በብአዴን እና በፌደራል መንግሥቱ መሃል ምናልባትም የፕሪቶሪያ ስምምነቱ አፈፃፀም ላይ አለመግባባት መኖሩን

3.ወይም በክተት ሰበብ ተበትኖ በየቀበሌው በደፈጣ ያስቸገረውን የፋኖ አደረጃጀትን ወልቃይት እና ራያ ላይ ለመሰብሰብ እና በመደበኛ ውጊያ ለመደምሰስ

4. የትግራይ ክልል መንግሥት ልክ የዛሬ ዓመት ጌታቸው ረዳ አሜሪካ ከትግራይ የዲያስፖራው ማኅበረሰብ ጋር በነበረው ውይይት እንዳለው. . ''.የፌደራል መንግሥቱ በወረራ የተያዘብንን ግዛት በጉልበት እንድናስመልስ በተደጋጋሚ ጥያቄ ቢያቀርብልንም. . ይህ ሃላፊነት የፌደራል መንግሥቱ በመሆኑ እና ከአቅሙ በላይ ይሆናል የሚል እምነት ስለሌለን አልተቀበልነውም! ነገር ግን ከአቅሙ በላይ ሆኗል ብለን ካመንን እና ጥያቄ ከቀረበልን ሕገ መንግሥታዊ ግዛታችንን ለማስመለስ አስፈላጊውን ትብብር ማድረጋችን አይቀርም'' እንዳለው በፌደራል መንግሥት ይሁንታ በወረራ የተያዙ ግዛቶችን በጉልበት የማስመለስ ሂደት ላይ መኮኑን መደምደም ይቻላል!

5. የመጨረሻው እና የመሆን ውስን አጋጣሚ ያለው ግምቴ ደግሞ የፌደራል መንግሥቱ በብአዴን በኩል ለዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ ማስተላለፍ እና ሁኔታው… ከታች ይቀጥላል
80.2K viewsedited  12:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-17 15:42:40 ከላይኛው የቀጠለ… …መንግሥት ያከበረው፣ የወደደው ሁላ ነው የሚመስለው። የአሜሪካ ጳጳሳትና ካህናት ዋነኛ ችግራቸው ይሄ ነው። ኤምባሲ ለእነርሱ የመንግሥተ ሰማያት ያህል ነው። እንቅልፍ ሁላ አይወስዳቸውም። ጥግረራዋ እየዋለች ኤምባሲ ራት የምትጠራ አንዲት ሴት ዐውቅ ነበር። በእነ ዶር አምባቸው ሞት በተለይ አሜሪካ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ዋነኛ አጋፋሪ ሆና የምትታይ። የብልፅግና ደጋፊ። ከእሷ ብሶ እኔኑ ትሰድበኝ ነበር። የኖ ሞር ዋነኛም ነበረች። አቤት ስትጠላኝ ለጉድ ነበር። አሁን ምኗን ብልፅግና እንደቀነደሸባት አላውቅም ውኃ ገብታ የወጣች አይጥ መስላ… 

"…በዳያስጰራ የሚገኘው አክቲቪስት፣ ጋዜጠኛ እና ሚዲያም መገምገም ነው ያለበት። የዐማራ ጠላቱ ሁላ የዐማራ ስም ይዞ ሚድያ በዐማራ ስም ነው የሚያንቀሳቅሰው። መጥራት አለበት። ጋዜጠኞቹና ሚዲያዎቹ ፕሮፌሽናል ሥራ ለመሥራት አልታደሉም። ጋዜጠኛው የፖለቲካ ፍላጎቱን ይዞ ነው የሚመጣው። ከሙያዊ ትንተናና መረጃ ከመስጠት ይልቅ ለዐማራ ፋኖ ማኒፌስቶ ሁላ የሚያዘጋጁ አይቻለሁ። እገሌ የሚባለውን ፋኖ ካልተቀላቀላችሁ ገንዘብ አንሰጥም የሚል ጋዜጠኛ እንዴት የዐማራን ትግል በፕሮፓጋንዳ ፈቅ ሊያደርገው ይችላል ተብሎ ይገመታል። የመንደራቸውን ፋኖዎች ብቻ ሲያወድሱ፣ ፋኖው ሲጣላና ሲከፈል ለአንዱ ወገን አድልተው ሌላውን የሚወቅጡ እያሉ ከባድ ነው ነገሩ። የሆነው ሆኖ ፖለቲከኞቹም፣ ጋዜጠኛና አክቲቪስቱም ሂስ ግለሂስ አውርዶ አንድ ከመሆን በቀር አማራጭ የላቸውም። ሺ ተከታይ ያላቸው የዐማራ ቲክቶከሮች የከፋፋይነት ትንተና መሬት ላይ ችግር አይፈጥርም ባይባልም የከፋ አደጋ ግን የለውም። ሞጣ ብሪጅ ስቶንሁላ… የለንደን ፋኖን ተመልከት።

"…የዐማራ አንድነት ለዐማራ ማሸነፍ ወሳኝ ነው። የሚደንቀው ምን መሰላችሁ ይሄን ሁሉ ግሪሳ የዐማራ ጠላት ኃይል የሚገጥመው የዐማራ ፈኖ በሎጀስቲክ በኩል ተተኳሽ ጥይት የሚያቀርብለት ሀገርም ሆነ ድርጅት የለም። ከላይ ከሰማይ ፈጣሪ፣ ከምድር ሕዝቡና ነፍጡ ብቻ ነው የፋኖ መተማመኛው። ተተኳሽ የሚያገኘው ከኦሮሞና ከትግሬ ሠራዊት ነው። በተቃራኒው ግን ለትግሬው ኃይል የርዳታው መጠን ተቆጥሮም፣ ተለክቶም አያልቅም። ምዕራባውያን በርዳታ ስም ቀለብም ተተኳሽም ያቀርቡለታል። አሜሪካ እንደ ስለት ልጅ ነው ዋይዋይ የምትልለት። የተባበሩት መንግሥታት በቀን 10 ጊዜ ስብሰባ ሊቀመጥለት ሁላ ይችላል። እንግሊዝን ጨምሮ የአውሮጳ ኅብረት መቀሌ ድረስ ተመላልሰው እነ ደጺን ጉንጫቸውን እያሻሹ "ኡሙንዱኖ ኢሹ" አይዞኝ ኤሊፖፕ እናመጣላችኋለን ሁሉ ሊሏቸው ይችላሉ። የምዕራባውያን የዜና ማሰራጫዎች በሙሉ ለጣሊያን የሚደግፉ እስኪመስሉ ድረስ ነው የሚጮሁላቸው። ቴዎድሮስ አድሃኖም ስለ ኮቪድ መግለጫ እየሰጠ በመሃል ቆሞ ስለትግራይ ሊያለቅስ ሁላ ይችላል። ይሄ አልበቃ ብሎም አረቦቹ ለኦሮሙማው ኃይል ከድሮን እስከ ሮኬት ድረስ ያስታጥቁታል። አቢይ በአሁኑ ረመዳን ቤተ መንግሥት ለጠራቸው መጅሊሶች "ኢንሻ አላህ ዱአ አድርጉልኝ፣ ሰአውዲ አረቢያ በገንዘብ ከረዳችኝ ኢትዮጵያን የአረብ ሊግ አደርጋታለሁ፣ በሽሪአ ሕግም ትተዳደራለች። ትግሉን ግፉበት" ሲል የተደመጠው የኦሮሙማው አገዛዝ ቁንጮ አቢይ በቢልዮን የሚቆጠር በጀት ከዐረብ ተቀብሎ ለትግሬ ይለቃል። ተተኳሽና የአየር ሽፋን በመስጠትም ያግዛል። የትግሬና የብልጽግና አክቲቪስቶች፣ ጋዜጠኞችና ፖለቲከኞችም ግንባር ፈጥረው ዐማራው ላይ የፕሮፓጋንዳ ዘመቻቸውን ይከፍታሉ። የመጨረሻው የዋንጫ ጨዋታ ስለሆነም ግርግሩ ይበዛል፣ ይከብዳልም። ዐማራው ግን ጆሮ ዳባ ልበስ ብሎ ፅዳቱ ላይ መበርታት ነው ያለበት። ትኩረቱን ከ4 ኪሎ አለመንቀል። ሁሉንም እንደ አመጣጡ መመለስ። ብአዴን የተባለ በሙሉ እረፍት ማሳጣት። የወልድያው አቶ መስፍን ላይ የተፈጸመው ለዚህ ምስክር ነው። በጥፋቴ ቤተሰቤን አስፈጅቼ ነበር። በጣም ይቅርታ እስኪል ያደረሰው የቦንቡ ውርጅብኝ ነው። የዐማራ ብልጽግና፣ የብአዴን ሰዎች እረፍት ካጡ ነገሩ ሁሉ ይቀለላል። አሸወይና ነው የሚሆነው።

"…በራያ ላይ የነበረው የብልፅግና አመራር ገሚሱ ወደኋላ ወደ ወልድያ ይሰደዳል። ገሚሱ ደግሞ በወያኔም፣ በመከላከያም፣ በፋኖም ይገደላል። የዐማራ ብልጽግናን አምኖ አብሮ ማዘጥዘጥ መጨረሻው ሞት ነው። ዕድል የቀናው ነው ስደት እንኳ የመውጣት ዕድል የሚያገኘው እንጂ በቀረ አቢይ አሕመድን አምኖ ኦሮሙማውን እና ወያኔን የሚያገለግሉ፣ ሕዝባቸውንም ዘላለም ባሪያ አድርገው እንዲገዛ ያስደረጉ የሚያስደርጉ ብአዴኖች በሙሉ የሰቡቱ ፍሪዳዎች ናቸውና ይበላሉ። ብልፅግና አሁን በራያ ተጀመረውን የራሱን ገረዶች አርዶ መብላት ካልነቁና በጊዜ ካልባነኑ፣ ወደ ሕዝብ ማዕቀፍ ካልገቡ ይኸው መበላት በወልቃይትም ይቀጥላል። ብልፅግናን ደግፎ እንጀፍ እንጀፍ ሲል የከረመው ሁላ አይኑ እያየ፣ ጆሮው እየሰማ ይበላል። ስም አጠራሩም ይጠፋል። ቢሰደድ እንኳ በተሰደደበት ሀገር ቀና ብሎ ለመሄድ እጁና ግንባሩ በሰው ደም የጨቀየ ስለሆነ ይሸታል፣ ይጠነባል፣ ይከረፋል። ከሰው መቅረብ አይችልም። እንደ ጎበጠ፣ በብቸኝነትም እንደማቀቀ፣ ከሰው ሳይቀላቀል እንደ መርገም ጨርቅ እንደተቆጠረ ይኖራል። በዚያው ይሞታል።

"…አሁን ሸዋ የሸዋ ፋኖ ወደ አንድ እየመጣ ነው። ጨርሷል። የጎንደር ፋኖንም ከብዙ ድካም በኋላ ወደ አንድ ለማምጣት እንቅልፍ አጥተን በስተመጨረሻ በትናንትናው እለት ለማቀራረብ ተሳክቶልናል። ዐዋጅ ማወጅ ነው የሚቀራቸው። ከምር ሆኗል። ወደ አንድነቱ ያልመጡ በጎጃም ያሉ ጦሮችም አሁን ልዩነታቸውን አጥበው፣ አስወግደውም የግድ ወደ አንድ ቢጠቃለሉ ሸጋ ነው የሚሆነው። በጎጃም ከአንድነቱ ያልገቡ ስላሉ፣ ስለየሚቀሩም ይሄን የምለው። በጎጃም አንድነት ላይ የደከማችሁ ሰዎች አሁንም ግዙፍ ጦር ያላቸውን የፋኖ አደረጃጀቶችን ጊዜ ወስዳችሁ ወደ አንድ ብታመጧቸው መልካም ነው። ጎጃም በተለይ ዳሞት ስለ ተጋድሎው አይነገርም። አይወራምም። ጎጃም ጥሩ ላይ ነው ያለው። ከአደባባይ ፉከራ ባሻገር በዓይን የሚታይ ተጋድሎ በማድረግ ግንባር ቀደም ሆኖ በታሪክ ተመዝግቧል። ጎንደር፣ ወሎ፣ ሸዋም እንደዚያው። አሁን ግን የጦር ግንባሩ በዛ ያለ ስለሆነ ከምን ጊዜውም በላይ አንድነት ወሳኝ ነው። በውጭ ያለውም ዐማራ አንድ ላይ ከመቆም በቀር ሌላ አማራጭ የለውም። በመሬት ላይ ያለው ዐማራም አላማጣ ሲያዝ ወደ ቆቦ፣ ቆቦ ሲያዝ ወደ ደሴ መሸሹን ትተህ ወስነህ እንደ ትግሬ እንደ ሕዝብ ተነሥ። ከአቢይ ጋር ተስማምቶ ሊወጋህ የመጣን ከሃዲ የትግሬ ሠራዊት ከወያኔ ትግሬ ጋር አንድ ላይ ሆነን ሠርተን አቢይን እናወርደዋለን ብለህ አትጃጃል። ህወሓት ሳትኖር የትግሬ ሕዝብ የሚመራው ፖለቲካም ቢሆን እንኳ እሺ ይሁን ይታሰብበት፣ ይመከርበትም ይባል ነበር። አሁን ግን በጭራሽ አይታሰብም። አትጃጃል።

"…አቢይ ዐማራ እና ትግሬን እያጫረሰ በዚህ መሀል ግዙፍ ጦር ያዘጋጃል። ትግሬና ዐማራን በልቶ በሻሻ ካረገ በኋላ ከዚያ የቀሩትን እነ አፋርን፣ ሱማሌን፣ ደቡብን ወዘተ በአስተማማኝ መልኩ በሻሻ ያደርጋል። ከዚያ የነጻነት ሃውልቱን አምቦ ላይ ያቆማል። ይሄ ነው ቃሉ። ስለዚህ አሁን እነ አቢይ ጉዞ ወደ ደቡብ አድርገው ሟች ወታደር ይመለምላሉ። ለኦሮሞ አሁን ታማኝ ኃይሉ የደቡብ ጴንጤው ነው። በአዲስ አበባ በቀን ሥራ ላይ፣  በህዳሴ ግድብ የጉልበት ሥራ ላይ ጭምር እንዲሠሩ የሥራ ዕድል ሳይቀር የተመቻቸላቸው የደቡብ ጴንጤዎች ናቸው። የደቡብ ጴንጤው በየቸርቹ ነው በፓስተሮቹ የብልጽግና ወንጌል … ከታች ይቀጥላል
74.0K viewsedited  12:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-17 15:42:09 ከላይኛው የቀጠለ… …ኃይል ስለመኖሩም ግን አላውቅም። የሰማሁት ነገርም የለም። (ጥርት ብሎ እንዲገለጽልኝ ግን ጸልዩልኝ ወይም የገባችሁ አስረዱኝ) በግሌ ግን እኔ በበኩሌ ከነ ጥርጣሬዬም ቢሆን የማርሸት የግሉ አድናቂ ነኝ። ንግግሩ፣ የቃላት አሰዳደሩ፣ ፍጥነቱ ሁሉ አፍ የማያስከድን ነው። አንደበተ ርቱዕም ነው። (በዐማራ ላይ ጄኖሳይድ አልተፈጸመም) የሚለው ሙግቱን ደጋግሜ ስሰማው ነገርየው ሊገባኝ ባይችልም ብቻ የጠራ ነገር የለኝም። ኦሮሙማው በጎጃም ይቀበራል። ጎጃም ፔርሙዳ ነው።

ሆ፦ ሸዋ

"…የሸዋም ለየት የሚል ባህሪ ነው ያለው። ከሌላው የዐማራ ክልል እንደሸዋ ቅጥቀጣ የደረሰበት ስለመኖሩ አላውቅም። ወያኔ የአጼ ዮሐንስን ለመበቀል፣ በጠላትነት የፈረጀችውን የሸዋ ሕዝብ ሽፍታ በማጥፋት ሰበብ ጄኖሳይድ የፈጸመችበት ገና ድሮ ጠዋት አዲስ አበባ ምኒሊክ ቤተ መንግሥት የገባች ጊዜ ነው። ቀድመው የነቁትን የሸዋ ዐማራው ፕሮፌሰር አሥራት ወልደየስን ቀርጥፋ የበላችውም በጠዋቱ ነው። እነ አጣዬን ከ10 ጊዜ በላይ ያቃጠለው ኦሮሙማም እንደ ሸዋ የፈጀው የለም። እነ ጃራ የሸዋ ዐማራን በግድ በኃይል ያሰለሙትም እዚያው ነው። ወያኔ እንኳ ከመቀሌ ተነሥታ የጁላ ጦር እየሸሸላት ያወደማት ሸዋን ነው። እናም ሸዋ በተለየ መልኩ ጫና ይበዛባታል።

"…ሸዋ ለ4 ኪሎ ቅርብ በመሆኑም የአገዛዙ ሙሉ ትኩረት እዚሁ ይሆናል። ሸዋ በሰሜኑ በኩል ከኦነግ፣ ከኦሮሞ መከላከያና በኦነግ መንፈስ ከሚመራው የወሃቢያ እስላሞች ጋር ይገጥማል። ሸዋ በምሥራቁ ክፍል የኦነግ፣ የኦሮሞ መከላከያና የኦሮሞ ሚሊሻ ከኦሮሚያ ልዩ ኃይልና ኦነግ ሸኔ ጋር ይገጥመዋል። መንዝ፣ መሃል ሜዳ፣ መራቤቴ፣ ደራም ያለው ዐማራ ከኦሮሞ ልዩ ኃይል፣ ከኦነግ ሸኔና ከመከላከያው ጋር ነው የሚገጥመው። ያ ውኃ አይገባው ድንጋይ የዐማራ አድማ ብተናና የአማራ ሚሊሻም በብአዴን እየተነዳ የሸዋዎች ተጋጣሚ እንደሚሆን ይጠበቃል። ከላይ እንዳልኩት ሸዋ ለማዕከላዊ መንግሥቱ፣ ለሀገሪቱ መናገሻ ከተማ ለ4ኪሎም ቅርብ ስለሆነ ዱላውም የዚያኑ ያህል ይበዛበታል። ነገር ግን ሁሉንም የሚመጣበትን ከመመከት በቀር ሌላ አማራጭ የለውም።

"…ይሄ በዐማራ ክልል የሚገኙ ዐማሮች የሚጠብቃቸው ግጥሚያ ሲሆን ከክልሉ ውጪና በውጭ ሀገር የሚገኙ ዐማሮች የሚገጥማቸውን ዐውደ ውጊያ ደግሞ በስሱ አብረን ለማየት እንሞክር።

• ከክልሉ ውጪ ያሉ ዐማሮች

ሀ፦ አዲስ አበባ

"…በአዲስ አበባ የሚገኘው ዐማራ በተለይ እዚያው አዲስ አበባ ከተማ ተወልዶ ያደገው ዐማራ የዘር ፖለቲካ ጨዋታው ምንም ሊገባው አልቻለም። እንዲገባው ስለማይፈልግም ሊገባው አይችልም። አዲስ አበባ ያለው ዐማራ ማንም ይግዛ ማን ሠርቶ፣ ተምሮ፣ በሰላም ውሎ መግባቱን ብቻ እንጂ ወደ ፖለቲካው አካባቢ ድርሽ ማለት የማይፈልግ ነው። ፖለቲካና ኮረንቲን በሩቁ ባይ ነው። ሀገሩን መውደዱን የሚገልጸው የኢትዮጵያ አትሌቶች፣ የብሔራዊ ቡድኑ ውድድር ሲኖርበት መደገፍ፣ ቴዲ አፍሮ ኢትዮጵያ የሚል ዘፈን ሲያወጣ በስሜት አብሮ ማንጎራጎር፣ ካምቦሎጆ ገብቶ ኢትዮጵያ የእኛ መመኪያ፣ ተከብረሽ የኖርሽው በአባቶቻችን አም፣ እናት ኢትዮጵያ የደፈረሽ ይውደም ብሎ ዘጠና ደቂቃ በድራፍት ኃይ በአቼኖና በአዳነ እየተመራ መጨፈር ይመስለዋል። እናም ጣጣ የለውም።

"…ቀበሌ መታወቂያ ለማውጣት መሰቃየቱን በገንዘብ ኃይል ለመፍታት መሞከሩንም እንደ ብልጠት፣ እንደ አራድነት የሚያይ ነው የአዲስ አበባ ዐማራ። ቀበሌ፣ ወረዳ፣ ክፍለከተማ፣ ክልል፣ ፓርላማ ገብቶ መሥራት ይሸክከዋል። ቀበሌውንም ፓርላማውንም ለክፍለ ሀገር ልጆች ለቆላቸው እሱ ፍዳውን ይበላል። ፖለቲካ እንደሆነ አይገባውም። እናቱን የሴፍቲ ኔት ተጠቃሚ አድርጎ ከዚያ በሚመጣ የምጽዋት ዘይት እየበላ ልክ ደህና ቤተሰብ እንዳለው ሰው በአደባባይ ሲጎርር ጉራውን ሲቸረችር ይውላል። እሱ አራዳ ነው። እየመጡ ነው ብሎ በመጨፈር ለፋኖ ደሙን የሰጠ ይመስለዋል። ሀገሪቷ ግልብጥብጥ ብትል አርሰናል አይሸነፍበት፣ ማንችስተር ነጥብ አይጣልበት እንጂ ደንታው አይደለም። ፖለቲካው ቡናና ጊዮርጊስን አዲስ አበባ ላይ እንዳይጋጠሙ አድርጎ ዱባይ ወስዶ ሲያጣልዝ እሱ አይገባውም። የሰው መሰባሰብ ችግር ይፈጥርብኛል ብሎ ጨዋታ ከአዲስ አበባ ማራቁን አይባንንም።

…ድሉ የዐማራው ነው። የተደራጀ ዐማራ ያሸንፋል። ድሬደዋ፣ ሀረር ሕብረታቸው ደስ ይላል። ደቡብም እንደዚያው። የሚያሰጋው ጋምቤላ ኢሉአባቦራ ነው። ባሌና አሩሲ ከተደራጀ አይደፈርም።

ሂ፦ ዳያስጶራው ዐማራ

"…ኬንያም፣ ጅቡቲም ያለው ስደተኛ ያው ዳያስጶራ ነው የሚባለው። ቅርብ አፍሪካ ያሉት ቢፈሩ አይፈረድባቸውም። ደቡብ ሱዳን፣ ሱዳንና ናይሮቢ ሆኜ ብቃወም የሚጠብቀኝን አስባችሁታል? እናም በእነሱ መፍረድ አይቻልም። ባህር ተሻግሮ አውሮጳና አሜሪካ የገባው ግን ያስቀኛል። በአየርም፣ በባህርም የመጣው ስደተኛ ዐማራ ፍርሃቱ ዘርፈ ብዙ ነው። አንዳንዳንዱ ዐማራ የተሰደደው ርቦት ነው። እናም ሠርቶ ሲያገኝ ማምሻ ዕድሜውን ሀገሩ ገብቶ በሸነና ብሎ መሞት ስለሚፈልግ ስለ ቦለጢቃው አያገባውም። በቃ ሆዱን እንዳሳደደ ይኖራል። ውስኪ በ30 ዩሮ፣ ቢራ በሳንቲም መጠጣት የልጅነት ሕልሙን እንደማሳካት ስለሚቆጥረው ለቦለጢቃው ደንታ የለውም። እንዲህ ዓይነቱ ሰው እንኳን በሀገሩ ጉዳይ ከቤተሰቡ ጭምር አድራሻውን ሰውሮ ነው እንደ ጅብ ተደብቆ እየበላ የሚሞተው። ሲበዛ ሆዳም፣ ራብ ያጠቃው ነው።

"…ይሄ ሆዳም ዐማራ ሴትም ከሆነች ቲክቶክም፣ ዩቱዩብም ላይ በአውሮጳና በአሜሪካ ርካሽ የሆነውን ምግብ እየሠሩ እየበሉ በራብ ለሚሰቃየው ወገናቸው የምግብ ጥያቄአቸው እንደተመለሰ በማሳየት ሲያስጎመጁ ይውላሉ። ቁርስም፣ ምሳም፣ ራትም ሲበሉ፣ ቡናም ጭማቂም ሲጠጡ Live ቀርበው ይለፋደዳሉ። ራብና ጠኔ ከሀገር ያስወጣቸው ስለሆኑ በቀል ላይ ናቸው። ውራጅ ጨርቅ፣ ሜካፕ ተቀብተው ሀብታም ሀብታም ይጫወታሉ። ሀገር ቤት ለእረፍት ሄደው ወር የማያቆይ ሳንቲም ያላቸው ሁሉ፣ እቁብ ጥለው የአውሮጵላን ትኬት ቆርጠው ዛር ወጥቶ ተንቀጥቅጦ የሚሄደው ሁላ በማኅበራዊ ሚዲያው ላይ ሲያክት አይጣል ነው። አመንዝራ፣ ሆዳም፣ መሃይም ስደተኛ ዐማራው ለቦለጢቃው ደንታ የለውም።

"…የተማረ፣ ደኅና ቦታ ደርሷል የሚባለው ዐማራ ድሮ በኢህአፓ ጊዜ፣ ከዚያም በዲቪ የሄደው፣ ቀደም ብሎ የወጣው፣ ወጥቶም ራሱን በትምህርት አሻሽሎ የእውቀት ወረቀትም፣ ገንዘብም ያለው ነው። እሱ ደግሞ ድሮ ላይ ተቸንክሮ የቀረ ነው። ዐማራ ሆኖ ከኢትዮጵያዊነቴ አልወርድም በማለት 1960 ላይ ተቸንክሮ የቀረ ነው። አሁንም አብዮተኛ ነው። ኢህአፓው ኢህአፓ፣ ደርጉም ያው ደርግ ነው። እናም የቦለጢቃ ጨዋታው አልገባውም። የገባቸው ደግሞ ገሚሶቹ ጩሉሌ ናቸው። አራዶች። በትምህርት ያጡትን ሀብት በትግሉ ስም ቀፍለው ፏ ብለው የሚልዮን ዶላር ቤት እና ቴስላ መኪና እየነዱ ይኖራሉ። ቦለጢቃውን በሩቁ የሚሉት ዳያስጶራዎች ለእነዚህ አጭቤዎች ገንዘቡን ወርውረው እነርሱ ድራሻቸውን ያጠፋሉ። እናም አጭቤው እየከበረ፣ ትግሉ እየከሰረ ይሄዳል።

"…እንጂ ዳያስጶራው ዐማራ መገፋፋቱን፣ ተቸንካሪነቱን፣ ጎጠኝነቱን፣ መንደርተኝነቱን ትቶ እንደ ዐማራ ተደራጅቶ ቢነሣ ተአምር ነው የሚሠራ የነበረው። አገዛዞች ደግሞ ሆዳም አማራውን በሽታ ነው የሚያውቁት። ሆዳምና መሃይም ዐማራ ለአምባገነኖች ምቹ አፈር ነው። መሃይም እና ሆዳም ዐማራን ኤምባሲ መጋበዝ ብቻ በቂ ነው። አምባሳደሩ ከደወለለት ክርስቶስን ያገኘ ነው የሚመስለው… ከታች ይቀጥላል…
69.2K viewsedited  12:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-17 15:41:39 ከላይኛው የቀጠለ… "…በሰሜን ወሎ ራያ ዐማራው ከፊት ከትግሬ ኃይሎች እና ከኦሮሞው መከላከያ ጋር፣ ከኋላው ከደነዙ የብአዴን አድማ ብተናና ምስኪኑ ሚሊሻ ከፍ ያለ ጦርነት ይጠብቀዋል። የኦሮሞ ብልፅግናም ሆነ ብአዴን እስከ አሁን በፋኖ ላይ ያላገኙትን ድል በዚህ ግንባር ሊያገኙ ያሰፈስፋሉ። ተጠቃቅሰው ራያና ወልቃይትን እንዳላስወረሩ ይሄ ሕዝብ ዥል፣ ዥልጥ ስለሚመስላቸው አቢይ አህመድ በለገሰ ቱሉና ብአዴን በክልል መንግሥቱ ስም ዐማራ በሕወሓት ተደፈረ ብለው መግለጫ ያወጣሉ። ሕዝቡም፣ ፋኖውም የሕወሓትን ወረራ ለመመከት ከክልሉ የፀጥታ ኃይልና ከከሃዲው መከላከያ ጋር ይሰለፍ ብለው ያውጃሉ። እንደ አገኘሁ ተሻገርም መሳሪያ ያለህ በመሳሪያ፣ መሳሪያ የሌለህ በገጀራ ህወሓትን መክት፣ የማረከው መሣሪያም የራስህ ይሆናል ውሰደው ሁላ ይሉታል። እናም እሺ ብሎ እነርሱን አምኖ ወደ ውጊያ የሚገባ ፋኖ ሲያገኙ በጥይትም፣ በፈንጂም፣ በድሮንም ከፊትም ከኋላም በመደምሰስ በውጊያ ያልቻሉትን በዘዴ ከመሃል አስገብተው ሳንድዊች ሊያደርጉት ቋምጠዋል። የወልድያው ስብሰባም በዚሁ አግባብ መፈጸሙም መረጃ ወጥቷል። የኦሮሙማው አየር ኃይልም አሁን ከትግሬ ጦርና ከመከላከያው ጋር ለመግጠም እጅብ ብሎ ይመጣል ብሎ ጓጉቶ የሚጠብቀውን የዐማራ ፋኖ በድሮን ሊያጠቃው ዝግጅቱን ጨርሷል። የጦር ጀቶችም የድሮን በራሪዎችም ወደ አፋር ሰመራ ገብተው በተጠንቀቅ ቆመዋል። የዐማራ ፋኖ ግን የሴራ ቦለጢቃውን ነቅቶበት ጆሮ ዳባ ልበስ ብሎ አኩርፎ በገፍ ሊቀላቀለው የሚመጣውን ሚሊሻም ሆነ አድማ ብተና ተቀብሎ ኃይሉን በማጠናከር ሕዝቡን ከያዘ ለትግሬም ጦር ሆነ ለኦሮሙማው መከላከያ ዋጋቸውን ለመስጠት እምብዛም አይቸገርም። ከመ ጤፍ…

ሁ፦ ሰሜን ወሎ ዋግ ኽምራ ሰቆጣ

"…የዐማራ ፋኖ በዚህ ግንባርም ከሦስት ኃይሎች ጋር ይጋፈጣል። ከትግሬ ኃይል፣ ትግሬና ኦሮሞ ካዘጋጁት የአገው ሸንጎ ኃይልና ከኦሮሙማው መከላከያ ጋር ውጊያ ይጠብቀዋል። የአገው ሸንጎ የሚባለው ራሱ የትግሬ ጦር ሌላኛው ክንፍ ስለሆነ ያው ስም የቀየረ ትግሬ ነውና አያሳስብም። እናም ይሄን ኃይል ለመመከት ከወዲሁ ከላስታ ጀምሮ ያለው የዐማራ ሕዝብ ለአርማጌዶኑ ጦርነት መዘጋጀት አለበት። የቤት ሥራው ከወዲሁ ተሠርቶ ማለቅ አለበት። የትግሬ ጦር ሲሸነፍ የአገው ሸንጎም አብሮ ነው የሚሸነፈው። የሚበተነውም።

ሂ፦ ደቡብ ወሎ

"…በዚህ ግንባር የዐማራ ፋኖ የሚጠብቀው የኦሮሙማው የመከላከያ ሠራዊት፣ የብአዴን አድማ ብተና ብቻ አይደሉም የሚጠብቁት። በደቡብ ወሎ የሃይማኖት ውጊያም ሊኖር ይችላል። በእነ ሙጂብ አሚኖ በጀት ወሎን ክልል እናደርጋለን ብለው በየመስጊዱ ጭምር ከሚፎክሩት፣ የዐማራ ፋኖን የክርስቲያኖች ስብስብ ነው ከሚለው የወሎ ኅብረት ፅንፈኛ የወሃቢይ እስላሞች ጋር ጦርነት ይጠብቀዋል ብዬ እሰጋለሁ። በጁንታው ጦርነት ወቅት ከዐማራ ፋኖ ጋር ገጥሞ ይዋጋ የነበረው የሐሰን ከሪሙ ቡድንም በዚሁ ቡድን መጠለፉም አይረሳ። ኮምቦልቻ አካባቢ ከከሚሴ የሚነሣ የኦነግ ጦርም ከኦሮሙማው መከላከያና ከወሎ ፅንፈኛ ዐማራ ጠል የወሓቢያ እስላሞች ጋር ፍልሚ ይጠብቀዋል። ምንአልባት ህወሓት እስከደሴ ድረስ መጥታ ከዚያ የወሎ ክልልነት ተመቻችቶ ኦሮሙማው በሠራው ካርታ መሠረት ወሎን ልክ እንደ አውራ ጎዳና ለመጠቅለል ይሞክራል። ነገር ግን በዐማራ ክልል ከዐማራ ፋኖ በቀር አሸናፊ አካልም ሓሳብ የለም። አይኖርምም።

ሃ፦ ሰሜን ጎንደር

"…በጠገዴ፣ በማይ ፀብሪ እና በአዲአርቃይ የኦሮሞው መከላከያ ሠራዊት እና የትግሬው ኃይል ጋር ይገጥማል። በወልቃይት ደግሞ አርማጌዶን በሉት ከበድ ይላል ተብሎ ይጠበቃል። የወልቃይቱ ኮሎኔል ከብልፅግና ጋር ከሆነ ወልቃይትን አስረክቦ ወደ ካደው ሕዝብ ወደ ጎንደር መጥቶ የገነባውን ህንፃ እያከራየ ዘጭ ብሎ ይኖራል። ምክንያቱም ኮሎኔሉ የሀገር መከላከያ ሠራዊት ላይ መተኮስ ወንጀል ነው ብሎ በአደባባይ ፋኖን ያወገዘ ሰው ስለሆነ አሁን መከላከያ ውጣ ሲለው እምቢ ይላል ተብሎ ይጠበቃልን? የኦሮሞው መከላከያ፣ የትግሬው ኃይልና ሱዳን የተሰደደው ገዳዩ የትግሬ የሳምሪ ቡድንም አሁን አንድ ላይ ሊሠለፉበትም ይችላል። የኦሮሞ ብልፅግና፣ የአማች ፖለቲካ ተጋቢዎችም የዋዛ አይሆኑበትም። በውስጥ ያለው የትግሬ ወለዱ የፖለቲካው ቅማንትም ሌላው ፈተና ሊሆንበት ይችላል። የሆነው ሆኖ በዚያ አካባቢ መለኮታዊ ጣልቃገብነት ከሌለ በቀር ትርምስምሱ ይወጣል። ደፍርሶም ግን ይጠራል። ሌላ አማራጭ ስለሌለው ዐማራም የግዱን ያሸንፋል። እንደ ራያ፣ እንደ አላማጣው ብዙ የብልፅግና ባለሥልጣናት ከወልቃይት እስከጎንደር ተቀርጥፈው የሚበሉበት ጊዜም የቀረበ ይመስላል።

ሄ፦ ደቡብ ጎንደር

"…ትልቁ ግዙፍ የዐማራው ፈተና የሚገኘው በደብረ ታቦር ነው። ደብረታቦር መከላከያው፣ የአማራ አድማ ብተናና ፖሊስ ብቻ አይደለም የሚገኘው። በደቡብ ጎንደር ወያኔ እስከአሁን አለች። አልሞተችም። አልጠፋችም። ከሁሉም የዐማራ ክልል የወያኔ ሴል እስከ አሁን ድረስ ሳይወገድ እንዳለ የአመራር ስፍራውን ሳይለቅ የተቀመጠው ደቡብ ጎንደር ነው። በሰሜን ጎንደር ወኪል፣ በጎጃምም ወኪል ነው ወያኔ ያላት። የፖለቲካው ቅማንት እና የፖለቲካው አገው ሸንጎ ሰዎች በወሳኝ ሥፍራ በሥልጣን ላይ ያሉ ቢሆንም በደቡቡ ጎንደር ግን ይበዛሉ። አጥብቆ ወያኔን ናፋቂ ዐማራ መሳይ በዐማራ ላይ የተሾመ ጉግማንጉግ ነቀርሳ የሆነ ፀረ ዐማራ ኃይል የሚገኘው በዚሁ አከባቢ ነው ይባላል። ወያኔ በመቀሌም ሳይቀር ሞታ በደቡብ ጎንደር ግን እንዳለች ነው ያለችው ይላሉ። እናም የዐማራ ፋኖ በደቡብ ጎንደር ከአፍቃሬ ወያኔ ብአዴን ኃይል፣ ከሚሊሻውና ከአድማ ብተናው ጋር የኦሮሙማውን መከላከያ ደርቦ ለመግጠም የሚዘጋጀው ከወያኔ ርዝራዥ ወያኔ ዐማሮችም ጋር ጭምር ነው።  ይሄ ግድ ነው በቃ።

ህ፦ ጎጃም

"…የጎጃም ዐማራም እንዲሁ በዛ ያለ የጦር ግንባር ነው የሚጠብቀው። ፖለቲካ ወለዱ አገው ሸንጎና የኦሮሙማው መከላከያ ኃይል እንዳለ ሆኖ ልክ እንደ ደቡብ ጎንደር አፍቃሬ ወያኔው ብአዴን ከነ ርዝራዡ ያለበትም ስፍራ ነው። መቀሌ ድረስ ትግሬ ተርቧል ብሎ ጤፍ ጭኖ 90 ዓመቱ ትግራይ ድረስ እያነከሰ የሚሄድ ጎጃሜ ስታይ ትደነግጣለህ። ይኸው የተላከው ዱቄት ስንቅ ሆኖት ትግሬ ወደ ራያ ሲገባ ሽማግሌው ጎጃሜ ምን ሊሉ ይችላሉ ብለህ አትሰብ። የዐማራ ሚሊሻና የአድማ ብተና ተብዬውን ከመከላከያው ጋር በጎጃም ከዐማራው ፋኖ ጋር ይገጥማል። የጉምዝ ኃይሎች ከኦነግ ጋር ሆነው እንደ አዲስ ካልተነሡበት በቀር በዚያ በኩል ስጋት ቢኖረኝም ስጋቴ ግን የቀነሰ ስጋት ነው።

"…ቅሬታ ካላመጣ ለምን እንደሆነ ባላውቅም ወያኔ በሩቅ ሆና ወሎን አልፋ እንደምንም ከጎጃም ፋኖ ጋር የመገናኘት እድል ቢኖራት የሚመኙና የሚናፍቁ ትግሬዎችን እያየሁ መሆኔ እያስገረመኝ ነው። አርበኛ ዘመነ ካሴ ከሚናገረውና ከሚሰጠው መግለጫ ተነሥቼ ለወያኔ መራር ጥላቻ እንዳለው ብገምት ብረዳም አብዛኛዎቹ የወያኔ ሰዎች ግን በጎጃም ፋኖ አመራሮች በተለይ ለጠበቃ አስረስ ማሬና ለማርሸት ያላቸውን ክብር ሳይ ይሄ ክብር ከምን እንደሚመነጭ ሊገባኝ ባለመቻሉ ቅዥብርብር ሲያደርገኝ ይኖራል። የሆነ ተንኮል ይኖርበት ይሆንን ብዬም እጠይቃለሁ? የሆነው ሆኖ እንደ ስትራቴጂም ሆነ፣ እንደ ታክቲክም ይዘውት እንደሁ ባላውቅም የወያኔ ሰዎች ግን እንደምንም ብለው ከጎጃም ፋኖዎች ጋር ኅብረት ለመፍጠር ሲላለጡ እያየሁ ነው። ምን አልባትም ልክ እንደ ደቡብ ጎንደሩ በጎጃም ፋኖ ውስጥም አፍቃሬ ወያኔ … ከታች ይቀጥላል…
70.7K viewsedited  12:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-17 15:41:17 "ርዕሰ አንቀጽ"

"…የበሻሻው አራዳ ልቡሰ ሥጋው ከሃዲ ውሸታም ደም አፍሳሹ እቡዩ አህመድ በሊቀ ሰይጣናቱ በክፉ ጨካኙ በዳንኤል ክብረት መሰሪ የይሁዳ ምክር ኖረውም የማይጠቅሙትን የዐማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድሩን አረጋ ከበደን ጨምሮ ለሱሙ ወሳኝ የሚባሉትን ዋና ዋኖቹን የዐማራ ክልል ባለ ሥልጣናት በፕሪቶሪያው የኦህዴድና የህወሓት ስምምነት መሠረት በፌደራል መንግሥቱ ይሁንታ በመከላከያው ድጋፍ "ህወሓት ራያ አላማጣ ወረዳዎችን በሚያስረክቧት ወቅት" እኛ በሀገር ውስጥ በልነበርንበት ጊዜ ነው" የሚል ምክንያት እንዲኖራቸው ለማድረግ በመምከር "በዐማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር የሚመራ የዐማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን የቦርድ አመራሮችና የሚዲያ ሓላፊዎችን ያካተተ ልዑክ ከአፕሪል 12/2024 ወይም ከሚያዝያ 4/2016 ዓም ጀምሮ ለተከታታይ 16 ቀናት ለሥራ ጉዳይ በሚል ምክንያት ወደ ሰሜን አሜሪካ እንዲሄዱ ተደርገዋል። የዐማራው ወኪሎች በቆይታቸው ወቅት ወጪያቸውን የአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት እንደቻላቸው የተነገረ ሲሆን ለቀን አበል የሚሆን የኪስ ገንዘብም ከዚያው ከፈረደበት የዐማራ ሕዝብ ኪስ ካቋቋመው ከአሚኮ በጀት ላይ ለእያንዳንዳቸው በዶላር እንዲከፈላቸው ነው የተደረገው ተብሏል። አሁን ሀገረ አሜሪካ እንዲሄዱ የተገደዱት የክልሉ ባለ ሥልጣናት ሄደው በላስ ቬጋስ ከተማ የሚገኙ ሲሆን በዚያም በቬጋስ በሸነና እያሉ እንደሆነ ነው የተሰማው። ላስቬጋስ ካዚኖ ቤት ተገብቶ 8 ሺ ዶላር ምን ልትጠቅማቸው ነው?

"…ቀደም ሲል አቢይ አሕመድ እነ አቶ ተመስገን ጥሩነህ ያሉበት ኮሚቴ በማቋቋም፣ አረጋ ከበደና ቡድኑ በአገው ሸንጎው በአቶ ሰማ ጥሩነህ ተጠርንፎ ህወሓት መጀመሪያ ራያን፣ ቀጥሎ ደግሞ ወልቃይትን እንድትረከብ ከህወሓት ጋር እንዲስማሙ አደረገ። ከሕዝቡ ለሚነሣብን ተቃውሞስ ምን እንመልሳለን ለሚለው ስጋታቸውም የተሰጣቸው መልስ "የዐማራ ሕዝብ ምንም አያመጣም። ትንሽ የአፍ ድለላ ማድረግ ብቻ ፀጥ ለማሰኘት በቂ ነው። ዐማራ ስለ ፍቅር፣ ስለ አንድነት ከተሰበከ ይሸነፋል። ይተወዋል። ስለ ዐማራ ሕዝብ እኛ አለን ስለ ሕዝቡ አታስቡ። ለእሱ እሱን ዝም ለማሰኘት እኛ በሚገባ ተዘጋጅተናል። አስቸጋሪ የሚሆኑ የዐማራ ብልጽግና ሰዎች ካሉም እርምጃ ይወሰድባቸዋል። የዐማራ ብልጽግና ሰዎች አኩርፈው የሚሄዱበት መጠጊያ እንዳይኖራቸውም ተደርጓል። እሺ ብለው ለእኛ ከታዘዙ መልካም እምቢ ካሉም ግን ወይ በእኛ አልያም በፋኖው ይበላሉ። እናም ስለ ሕዝቡ አታስቡ በማለት ነው ወደ አማሪካ የሸኟቸው። ንግድ ባንክም በታዘዘው መሠረት፦

1ኛ፦ ለአረጋ ከበደ የዐማራ ክልል መስተዳድር 8350$ 2ኛ፦ ለይርጋ ሲሳይ የአሚኮ ቦርድ ሰብሳቢ 8350$
3ኛ፦ ለአህመዲን መሐመድ የአሚኮ ምክትል ቦርድ ሰብሳቢ 8350$
4ኛ፦ለመንገሻ ፋንታሁን የአሚኮ ቦርዳባል 7450$
5ኛ፦ሙሉጌታ ሰጥዬ የአሚኮ ዋና ሥራ አስፈፃሚ 8350
5ኛ፦ለግዛቸው ሙሉነህ የአሚኮ አማካሪ 7450$
6ኛ፦ለተሾመ ውዱ የአሚኮ ምክትል ስራ አስፈጻሚ 6850$
7ኛ፦አንዳርጌ መዓዛ የርዕሰ መስተዳድር ፕሮቶኮል ሹም 6850$ ያህል ገንዘብ ነው በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ባህርዳር ቅርንጫፍ ከሚገኘው የኮርፖሬሽናችን የባንክ ሂሳብ ቁጥር ተቀናሽ ሆኖ ሰጥቷቸው "ጎሽ የእኛ አንበሶች፣ መልካም የበሸነና ጊዜ ይሁንላችሁ። አቶ ገዱን ካገኛችሁት በዚያው ሰላም በሉልን በማለት ነው የሸኟቸው።

"…በትናንቱ የምሥራቅ ዐማራ ፋኖ መግለጫ በተራ ቁጥር 1 ላይ እንደተጠቀሰው "የዐማራ ሕዝብ በብአዴን መሪነት የሚመጣ ውርደት እንጅ ነጻነት የሌለ መሆኑን ካወቀ ውሎ አድሯል፡፡ ይሁን እንጅ በዋና ዋና ከተሞች የሚታየው መዘናጋት ዋጋ የሚያስከፍለን በመሆኑ ዘላቂ ነጻነቱን ለማረጋገጥ ፍጹም መራራ ትግል በማድረግ ትግሉን ማቀጣጠል አለበት፡፡ የዐማራ ሕዝብ በመስዋዕትነቱ ወደእናት ግዛቶቹ የመለሳቸውን እነ ራያ ወልቃይትን አሳልፎ እየሰጠ ያለውን ብአዴን፣ ገጠር ከተማ ሳይል የፈራረሰ መዋቅሩን ጨርሶ ግብዓተ መሬት ለማስገባት ሁሉም በያለበት እንዲፈንን (ፋኖ እንዲሆን) የትግል ጥሪያችንን እናቀርባለን በማለት የጠቀሱትንም የምንመለከተው የብአዴንን አይረቤነት ሁሉም የሚረዳው መሆኑን ነው።

"…የሚገርመው ደግሞ እነ አረጋ ከበደን በላስቬገስ ተቀብሎ እንዲያስተናግዳቸው በአቢይ አሕመድ የታዘዘው ግለሰብ ኤርትራዊ ባለሃብት መሆኑ ነው። ሻአቢያ፣ ወያኔ እና ብልፅግና አሁንም ቁማር ላይ ናቸው ማለት ነው። ከድሮ ጀምሮ ከጥንትም ሁሌ እንደምለው "የመለስ ዜናዊን ቡድን የበሉት ሻአቢያ፣ አቢይ አሕመድና የዓድዋው ወያኔ በመጨረሻ ግንባር እየፈጠሩ መገለጣቸው እውን መሆኑን ነው። የዋህነት ብቻ ሳይሆን በብዙ ደንታ ቢስ፣ ዳተኛ፣ ቸልተኛ፣ ሰነፍ ጅልነት እና ፈሪ ቦቁባቃ የተሞላው የዐማራ ቦለጢቀኛም የሚሆነውን እያየ አፉን ለጉሞ ተቀምጧል። አሁን ላይ ምድር ላይ ያለው ዐማራ ጥሩ ነው። አየር ላይ ያለው ዐማራም አሁን ከበፊቱ የተሻለ ቢሆንም አሁንም ግን ይቀረዋል። ዐማራም እንደ ትግሬ እና ኦሮሞ ቦለጢቀኞች ጨካኝ፣ ከሃዲ፣ አረመኔ ካልሆነ በቀር ሕዝቡን በቀላሉ መታደግ የሚችል አይመስለኝም።

"…የራያው ወረራ በዚያ የሚቆም አይደለም። አይቆምም። ጠለምት፣ ከዚያ ወልቃይት ልክ በራያው መንገድ ነው ከዐማራው ፈልቅቀው ለመውሰድ የተዘጋጁት። ብልጽግናን አምነው በራያ፣ በወልቃይት እና በጠለምት ከሕዝባቸው ወኪል ከዐማራ ፋኖ ጋር የተቀያየሙ በሙሉ የሚጠብቃቸው ሞት ብቻ ነው። ካልሸሹ ወያኔ፣ ከሸሹ ብልፅግና ይገድላቸዋል። የሚሞተው የብልፅግና ባለ ሥልጣን ዐማራ ስለሆነ ችግር የለም። ዐማራ ብልጽግና ሆነ፣ ብአዴን ሆነ፣ አብን ሆነ፣ ተራ ሕዝብ ሆነ ሞቱ ጣጣ አያመጣም። ለዚህ ነው ብልፅግናን አምኖ የራያ አስተዳዳሪ ሆኖ የሄደው የደብረታቦር ዩኒቨርስቲው አቶ ደርበው፣ የቅርብ ጊዜ ሙሽራው የጫጉላ ጊዜውን ያልጨረሰውን ሰው የህወሓትን ወደ ራያ መግባት ተከትሎ የደፉት፣ የገደሉት። በዚህ ሰው ሞት ሚስቱና ቤተሰቦቹ ያዝናሉ። ህወሓት እና ብልፅግና ይደሰታሉ። በሰውየው ሲሳደድ የኖረው፣ የከረመው ፋኖም ሥራው ያውጣው ባይ ነው። ደመ ከልብ በሉት። ይኸው ነው ወልቃይት ላይም የሚከሰተው። መዝግቡልኝ። 

"…ከዚህ ተነሥቼ ለዐማራ የእኔ የዘመዴ ምክር የሚከተለው ነው። ዐማራ በቀጣይ ከፊቱ ብዙ የጦር ግንባሮች ከብዙ ኃይሎችም ጋር ከባድ ጦርነት ይገጥመዋል ብዬ እጠብቃለሁ። ለሁሉም የጦር ግንባሮች ግን እኩል መዘጋጀት ይኖርበታል። ዐማራ ሰፊም ጀግናም ሕዝብ ስለሆነ ከተናበበ አሸናፊነት የእጁ ነው የሚሆነው። ዐማራ ከበፊቱ በተሻለ ቁመና ላይ እንደሚገኝ የታወቀ ነው። እንደ በፊቱ በጥቂት ሰዎች የሚታገል አይደለም። በሀገረ መንግሥቱ ተስፋ የቆረጠ እና ወደ አባት ሀገር ዐማራ ፊቱን ያዞረ ዕልፍ ዐማራ የዐማራ ትውልድ ስለተፈጠረ አያሳስብም። ፈተናው እንዳለ የተረዱ ምሑራን፣ ነጋዴዎች፣ ተማሪዎች፣ የመንግሥት ሠራተኞች፣ ወጣቶች፣ ሴቶች፣ ገበሬዎች፣ የመከላከያ፣ የፌደራል ፖሊስ አባላት፣ የዐማራ ልዩ ኃይል እና ሚኒሻዎች የዐማራ ፋኖን ተቀላቅለው ዐማራ ትግሉን በብረት ጀምሯል። እናም ገና ለጋው የዐማራ ትግል ገና ከአሁኑ ሀገሪቷን ሽባ አድርጓት ተገኝቷል። መሀል ሰፋሪው፣ ሰነፉ፣ ደንታ ቢሱና ባንዳው ዐማራም ሲመርረው ትግሉን መቀላቀሉ አይቀርም። እናም ዐማራ ውሎ ሲያድር ወጥሮ በመመከት ሃቅ ስላለው ሁሉንም ጠላቶቹን ያሸንፋል። እኔ በዐማራ መቼም ተስፋ አልቆርጥም። የጦር ግንባሮቹንም እጠቅሳለሁ።

ሀ፦ ሰሜን ወሎ ራያ … ከታች ይቀጥላል…
73.4K views12:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-17 14:54:43
መልካም…

"…ከምስጋናው ቀጥሎ የሚከተለው ርዕሰ አንቀጹ ነው አይደል…? አዎ… ትክክል ነው።

"…ነገር ግን የዛሬው ርዕሰ አንቀጼን ማሳጠር፣ መግታት አቃተኝ። ውስጤ እየፈላ የሚንተከተከውን ሁሉ ጻፍኩኝ። ስጋቴን፣ ፍርሃቴን፣ ደግሞም ተስፋዬን እንደ ኢዩ ጩፋ፣ እንደ ዳንሳም ባይሆን ነገር ግን ቀኝ ትከሻዬን የሸከከኝን ሁሉ በመጻፌ ጦማሩ ረዘመ፣ የሊማሊሞን ተራራ መሰለብኝ። እናም ወዳጆቼ ይሄን ዝልግልግ ተልባ መሳይ ርዕሰ አንቀጽ ልጥፍላችሁ ይቅር፣ ወይስ ከፋፍዬ ላቅርበው?

• ምን ትላላችሁ…? ምንስ ትመክሩኛላችሁ…?
79.2K views11:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-17 10:25:43
“…ከአንድ አፍ በረከትና መርገም ይወጣሉ። ወንድሞቼ ሆይ፥ ይህ እንዲህ ሊሆን አይገባም። ምንጭስ ከአንድ አፍ የሚጣፍጥንና የሚመርን ውኃ ያመነጫልን? ወንድሞቼ ሆይ፥ በለስ ወይራን ወይስ ወይን በለስን ልታፈራ ትችላለችን? ከጨው ውኃም ጣፋጭ ውኃ አይወጣም።” ያዕ 3፥10-12

"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?

"… መልሱ እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ
86.3K views07:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ