Get Mystery Box with random crypto!

ከላይኛው የቀጠለ… …መንግሥት ያከበረው፣ የወደደው ሁላ ነው የሚመስለው። የአሜሪካ ጳጳሳትና | Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ከላይኛው የቀጠለ… …መንግሥት ያከበረው፣ የወደደው ሁላ ነው የሚመስለው። የአሜሪካ ጳጳሳትና ካህናት ዋነኛ ችግራቸው ይሄ ነው። ኤምባሲ ለእነርሱ የመንግሥተ ሰማያት ያህል ነው። እንቅልፍ ሁላ አይወስዳቸውም። ጥግረራዋ እየዋለች ኤምባሲ ራት የምትጠራ አንዲት ሴት ዐውቅ ነበር። በእነ ዶር አምባቸው ሞት በተለይ አሜሪካ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ዋነኛ አጋፋሪ ሆና የምትታይ። የብልፅግና ደጋፊ። ከእሷ ብሶ እኔኑ ትሰድበኝ ነበር። የኖ ሞር ዋነኛም ነበረች። አቤት ስትጠላኝ ለጉድ ነበር። አሁን ምኗን ብልፅግና እንደቀነደሸባት አላውቅም ውኃ ገብታ የወጣች አይጥ መስላ… 

"…በዳያስጰራ የሚገኘው አክቲቪስት፣ ጋዜጠኛ እና ሚዲያም መገምገም ነው ያለበት። የዐማራ ጠላቱ ሁላ የዐማራ ስም ይዞ ሚድያ በዐማራ ስም ነው የሚያንቀሳቅሰው። መጥራት አለበት። ጋዜጠኞቹና ሚዲያዎቹ ፕሮፌሽናል ሥራ ለመሥራት አልታደሉም። ጋዜጠኛው የፖለቲካ ፍላጎቱን ይዞ ነው የሚመጣው። ከሙያዊ ትንተናና መረጃ ከመስጠት ይልቅ ለዐማራ ፋኖ ማኒፌስቶ ሁላ የሚያዘጋጁ አይቻለሁ። እገሌ የሚባለውን ፋኖ ካልተቀላቀላችሁ ገንዘብ አንሰጥም የሚል ጋዜጠኛ እንዴት የዐማራን ትግል በፕሮፓጋንዳ ፈቅ ሊያደርገው ይችላል ተብሎ ይገመታል። የመንደራቸውን ፋኖዎች ብቻ ሲያወድሱ፣ ፋኖው ሲጣላና ሲከፈል ለአንዱ ወገን አድልተው ሌላውን የሚወቅጡ እያሉ ከባድ ነው ነገሩ። የሆነው ሆኖ ፖለቲከኞቹም፣ ጋዜጠኛና አክቲቪስቱም ሂስ ግለሂስ አውርዶ አንድ ከመሆን በቀር አማራጭ የላቸውም። ሺ ተከታይ ያላቸው የዐማራ ቲክቶከሮች የከፋፋይነት ትንተና መሬት ላይ ችግር አይፈጥርም ባይባልም የከፋ አደጋ ግን የለውም። ሞጣ ብሪጅ ስቶንሁላ… የለንደን ፋኖን ተመልከት።

"…የዐማራ አንድነት ለዐማራ ማሸነፍ ወሳኝ ነው። የሚደንቀው ምን መሰላችሁ ይሄን ሁሉ ግሪሳ የዐማራ ጠላት ኃይል የሚገጥመው የዐማራ ፈኖ በሎጀስቲክ በኩል ተተኳሽ ጥይት የሚያቀርብለት ሀገርም ሆነ ድርጅት የለም። ከላይ ከሰማይ ፈጣሪ፣ ከምድር ሕዝቡና ነፍጡ ብቻ ነው የፋኖ መተማመኛው። ተተኳሽ የሚያገኘው ከኦሮሞና ከትግሬ ሠራዊት ነው። በተቃራኒው ግን ለትግሬው ኃይል የርዳታው መጠን ተቆጥሮም፣ ተለክቶም አያልቅም። ምዕራባውያን በርዳታ ስም ቀለብም ተተኳሽም ያቀርቡለታል። አሜሪካ እንደ ስለት ልጅ ነው ዋይዋይ የምትልለት። የተባበሩት መንግሥታት በቀን 10 ጊዜ ስብሰባ ሊቀመጥለት ሁላ ይችላል። እንግሊዝን ጨምሮ የአውሮጳ ኅብረት መቀሌ ድረስ ተመላልሰው እነ ደጺን ጉንጫቸውን እያሻሹ "ኡሙንዱኖ ኢሹ" አይዞኝ ኤሊፖፕ እናመጣላችኋለን ሁሉ ሊሏቸው ይችላሉ። የምዕራባውያን የዜና ማሰራጫዎች በሙሉ ለጣሊያን የሚደግፉ እስኪመስሉ ድረስ ነው የሚጮሁላቸው። ቴዎድሮስ አድሃኖም ስለ ኮቪድ መግለጫ እየሰጠ በመሃል ቆሞ ስለትግራይ ሊያለቅስ ሁላ ይችላል። ይሄ አልበቃ ብሎም አረቦቹ ለኦሮሙማው ኃይል ከድሮን እስከ ሮኬት ድረስ ያስታጥቁታል። አቢይ በአሁኑ ረመዳን ቤተ መንግሥት ለጠራቸው መጅሊሶች "ኢንሻ አላህ ዱአ አድርጉልኝ፣ ሰአውዲ አረቢያ በገንዘብ ከረዳችኝ ኢትዮጵያን የአረብ ሊግ አደርጋታለሁ፣ በሽሪአ ሕግም ትተዳደራለች። ትግሉን ግፉበት" ሲል የተደመጠው የኦሮሙማው አገዛዝ ቁንጮ አቢይ በቢልዮን የሚቆጠር በጀት ከዐረብ ተቀብሎ ለትግሬ ይለቃል። ተተኳሽና የአየር ሽፋን በመስጠትም ያግዛል። የትግሬና የብልጽግና አክቲቪስቶች፣ ጋዜጠኞችና ፖለቲከኞችም ግንባር ፈጥረው ዐማራው ላይ የፕሮፓጋንዳ ዘመቻቸውን ይከፍታሉ። የመጨረሻው የዋንጫ ጨዋታ ስለሆነም ግርግሩ ይበዛል፣ ይከብዳልም። ዐማራው ግን ጆሮ ዳባ ልበስ ብሎ ፅዳቱ ላይ መበርታት ነው ያለበት። ትኩረቱን ከ4 ኪሎ አለመንቀል። ሁሉንም እንደ አመጣጡ መመለስ። ብአዴን የተባለ በሙሉ እረፍት ማሳጣት። የወልድያው አቶ መስፍን ላይ የተፈጸመው ለዚህ ምስክር ነው። በጥፋቴ ቤተሰቤን አስፈጅቼ ነበር። በጣም ይቅርታ እስኪል ያደረሰው የቦንቡ ውርጅብኝ ነው። የዐማራ ብልጽግና፣ የብአዴን ሰዎች እረፍት ካጡ ነገሩ ሁሉ ይቀለላል። አሸወይና ነው የሚሆነው።

"…በራያ ላይ የነበረው የብልፅግና አመራር ገሚሱ ወደኋላ ወደ ወልድያ ይሰደዳል። ገሚሱ ደግሞ በወያኔም፣ በመከላከያም፣ በፋኖም ይገደላል። የዐማራ ብልጽግናን አምኖ አብሮ ማዘጥዘጥ መጨረሻው ሞት ነው። ዕድል የቀናው ነው ስደት እንኳ የመውጣት ዕድል የሚያገኘው እንጂ በቀረ አቢይ አሕመድን አምኖ ኦሮሙማውን እና ወያኔን የሚያገለግሉ፣ ሕዝባቸውንም ዘላለም ባሪያ አድርገው እንዲገዛ ያስደረጉ የሚያስደርጉ ብአዴኖች በሙሉ የሰቡቱ ፍሪዳዎች ናቸውና ይበላሉ። ብልፅግና አሁን በራያ ተጀመረውን የራሱን ገረዶች አርዶ መብላት ካልነቁና በጊዜ ካልባነኑ፣ ወደ ሕዝብ ማዕቀፍ ካልገቡ ይኸው መበላት በወልቃይትም ይቀጥላል። ብልፅግናን ደግፎ እንጀፍ እንጀፍ ሲል የከረመው ሁላ አይኑ እያየ፣ ጆሮው እየሰማ ይበላል። ስም አጠራሩም ይጠፋል። ቢሰደድ እንኳ በተሰደደበት ሀገር ቀና ብሎ ለመሄድ እጁና ግንባሩ በሰው ደም የጨቀየ ስለሆነ ይሸታል፣ ይጠነባል፣ ይከረፋል። ከሰው መቅረብ አይችልም። እንደ ጎበጠ፣ በብቸኝነትም እንደማቀቀ፣ ከሰው ሳይቀላቀል እንደ መርገም ጨርቅ እንደተቆጠረ ይኖራል። በዚያው ይሞታል።

"…አሁን ሸዋ የሸዋ ፋኖ ወደ አንድ እየመጣ ነው። ጨርሷል። የጎንደር ፋኖንም ከብዙ ድካም በኋላ ወደ አንድ ለማምጣት እንቅልፍ አጥተን በስተመጨረሻ በትናንትናው እለት ለማቀራረብ ተሳክቶልናል። ዐዋጅ ማወጅ ነው የሚቀራቸው። ከምር ሆኗል። ወደ አንድነቱ ያልመጡ በጎጃም ያሉ ጦሮችም አሁን ልዩነታቸውን አጥበው፣ አስወግደውም የግድ ወደ አንድ ቢጠቃለሉ ሸጋ ነው የሚሆነው። በጎጃም ከአንድነቱ ያልገቡ ስላሉ፣ ስለየሚቀሩም ይሄን የምለው። በጎጃም አንድነት ላይ የደከማችሁ ሰዎች አሁንም ግዙፍ ጦር ያላቸውን የፋኖ አደረጃጀቶችን ጊዜ ወስዳችሁ ወደ አንድ ብታመጧቸው መልካም ነው። ጎጃም በተለይ ዳሞት ስለ ተጋድሎው አይነገርም። አይወራምም። ጎጃም ጥሩ ላይ ነው ያለው። ከአደባባይ ፉከራ ባሻገር በዓይን የሚታይ ተጋድሎ በማድረግ ግንባር ቀደም ሆኖ በታሪክ ተመዝግቧል። ጎንደር፣ ወሎ፣ ሸዋም እንደዚያው። አሁን ግን የጦር ግንባሩ በዛ ያለ ስለሆነ ከምን ጊዜውም በላይ አንድነት ወሳኝ ነው። በውጭ ያለውም ዐማራ አንድ ላይ ከመቆም በቀር ሌላ አማራጭ የለውም። በመሬት ላይ ያለው ዐማራም አላማጣ ሲያዝ ወደ ቆቦ፣ ቆቦ ሲያዝ ወደ ደሴ መሸሹን ትተህ ወስነህ እንደ ትግሬ እንደ ሕዝብ ተነሥ። ከአቢይ ጋር ተስማምቶ ሊወጋህ የመጣን ከሃዲ የትግሬ ሠራዊት ከወያኔ ትግሬ ጋር አንድ ላይ ሆነን ሠርተን አቢይን እናወርደዋለን ብለህ አትጃጃል። ህወሓት ሳትኖር የትግሬ ሕዝብ የሚመራው ፖለቲካም ቢሆን እንኳ እሺ ይሁን ይታሰብበት፣ ይመከርበትም ይባል ነበር። አሁን ግን በጭራሽ አይታሰብም። አትጃጃል።

"…አቢይ ዐማራ እና ትግሬን እያጫረሰ በዚህ መሀል ግዙፍ ጦር ያዘጋጃል። ትግሬና ዐማራን በልቶ በሻሻ ካረገ በኋላ ከዚያ የቀሩትን እነ አፋርን፣ ሱማሌን፣ ደቡብን ወዘተ በአስተማማኝ መልኩ በሻሻ ያደርጋል። ከዚያ የነጻነት ሃውልቱን አምቦ ላይ ያቆማል። ይሄ ነው ቃሉ። ስለዚህ አሁን እነ አቢይ ጉዞ ወደ ደቡብ አድርገው ሟች ወታደር ይመለምላሉ። ለኦሮሞ አሁን ታማኝ ኃይሉ የደቡብ ጴንጤው ነው። በአዲስ አበባ በቀን ሥራ ላይ፣  በህዳሴ ግድብ የጉልበት ሥራ ላይ ጭምር እንዲሠሩ የሥራ ዕድል ሳይቀር የተመቻቸላቸው የደቡብ ጴንጤዎች ናቸው። የደቡብ ጴንጤው በየቸርቹ ነው በፓስተሮቹ የብልጽግና ወንጌል … ከታች ይቀጥላል