Get Mystery Box with random crypto!

ከላይኛው የቀጠለ… …ኃይል ስለመኖሩም ግን አላውቅም። የሰማሁት ነገርም የለም። (ጥርት ብሎ እ | Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ከላይኛው የቀጠለ… …ኃይል ስለመኖሩም ግን አላውቅም። የሰማሁት ነገርም የለም። (ጥርት ብሎ እንዲገለጽልኝ ግን ጸልዩልኝ ወይም የገባችሁ አስረዱኝ) በግሌ ግን እኔ በበኩሌ ከነ ጥርጣሬዬም ቢሆን የማርሸት የግሉ አድናቂ ነኝ። ንግግሩ፣ የቃላት አሰዳደሩ፣ ፍጥነቱ ሁሉ አፍ የማያስከድን ነው። አንደበተ ርቱዕም ነው። (በዐማራ ላይ ጄኖሳይድ አልተፈጸመም) የሚለው ሙግቱን ደጋግሜ ስሰማው ነገርየው ሊገባኝ ባይችልም ብቻ የጠራ ነገር የለኝም። ኦሮሙማው በጎጃም ይቀበራል። ጎጃም ፔርሙዳ ነው።

ሆ፦ ሸዋ

"…የሸዋም ለየት የሚል ባህሪ ነው ያለው። ከሌላው የዐማራ ክልል እንደሸዋ ቅጥቀጣ የደረሰበት ስለመኖሩ አላውቅም። ወያኔ የአጼ ዮሐንስን ለመበቀል፣ በጠላትነት የፈረጀችውን የሸዋ ሕዝብ ሽፍታ በማጥፋት ሰበብ ጄኖሳይድ የፈጸመችበት ገና ድሮ ጠዋት አዲስ አበባ ምኒሊክ ቤተ መንግሥት የገባች ጊዜ ነው። ቀድመው የነቁትን የሸዋ ዐማራው ፕሮፌሰር አሥራት ወልደየስን ቀርጥፋ የበላችውም በጠዋቱ ነው። እነ አጣዬን ከ10 ጊዜ በላይ ያቃጠለው ኦሮሙማም እንደ ሸዋ የፈጀው የለም። እነ ጃራ የሸዋ ዐማራን በግድ በኃይል ያሰለሙትም እዚያው ነው። ወያኔ እንኳ ከመቀሌ ተነሥታ የጁላ ጦር እየሸሸላት ያወደማት ሸዋን ነው። እናም ሸዋ በተለየ መልኩ ጫና ይበዛባታል።

"…ሸዋ ለ4 ኪሎ ቅርብ በመሆኑም የአገዛዙ ሙሉ ትኩረት እዚሁ ይሆናል። ሸዋ በሰሜኑ በኩል ከኦነግ፣ ከኦሮሞ መከላከያና በኦነግ መንፈስ ከሚመራው የወሃቢያ እስላሞች ጋር ይገጥማል። ሸዋ በምሥራቁ ክፍል የኦነግ፣ የኦሮሞ መከላከያና የኦሮሞ ሚሊሻ ከኦሮሚያ ልዩ ኃይልና ኦነግ ሸኔ ጋር ይገጥመዋል። መንዝ፣ መሃል ሜዳ፣ መራቤቴ፣ ደራም ያለው ዐማራ ከኦሮሞ ልዩ ኃይል፣ ከኦነግ ሸኔና ከመከላከያው ጋር ነው የሚገጥመው። ያ ውኃ አይገባው ድንጋይ የዐማራ አድማ ብተናና የአማራ ሚሊሻም በብአዴን እየተነዳ የሸዋዎች ተጋጣሚ እንደሚሆን ይጠበቃል። ከላይ እንዳልኩት ሸዋ ለማዕከላዊ መንግሥቱ፣ ለሀገሪቱ መናገሻ ከተማ ለ4ኪሎም ቅርብ ስለሆነ ዱላውም የዚያኑ ያህል ይበዛበታል። ነገር ግን ሁሉንም የሚመጣበትን ከመመከት በቀር ሌላ አማራጭ የለውም።

"…ይሄ በዐማራ ክልል የሚገኙ ዐማሮች የሚጠብቃቸው ግጥሚያ ሲሆን ከክልሉ ውጪና በውጭ ሀገር የሚገኙ ዐማሮች የሚገጥማቸውን ዐውደ ውጊያ ደግሞ በስሱ አብረን ለማየት እንሞክር።

• ከክልሉ ውጪ ያሉ ዐማሮች

ሀ፦ አዲስ አበባ

"…በአዲስ አበባ የሚገኘው ዐማራ በተለይ እዚያው አዲስ አበባ ከተማ ተወልዶ ያደገው ዐማራ የዘር ፖለቲካ ጨዋታው ምንም ሊገባው አልቻለም። እንዲገባው ስለማይፈልግም ሊገባው አይችልም። አዲስ አበባ ያለው ዐማራ ማንም ይግዛ ማን ሠርቶ፣ ተምሮ፣ በሰላም ውሎ መግባቱን ብቻ እንጂ ወደ ፖለቲካው አካባቢ ድርሽ ማለት የማይፈልግ ነው። ፖለቲካና ኮረንቲን በሩቁ ባይ ነው። ሀገሩን መውደዱን የሚገልጸው የኢትዮጵያ አትሌቶች፣ የብሔራዊ ቡድኑ ውድድር ሲኖርበት መደገፍ፣ ቴዲ አፍሮ ኢትዮጵያ የሚል ዘፈን ሲያወጣ በስሜት አብሮ ማንጎራጎር፣ ካምቦሎጆ ገብቶ ኢትዮጵያ የእኛ መመኪያ፣ ተከብረሽ የኖርሽው በአባቶቻችን አም፣ እናት ኢትዮጵያ የደፈረሽ ይውደም ብሎ ዘጠና ደቂቃ በድራፍት ኃይ በአቼኖና በአዳነ እየተመራ መጨፈር ይመስለዋል። እናም ጣጣ የለውም።

"…ቀበሌ መታወቂያ ለማውጣት መሰቃየቱን በገንዘብ ኃይል ለመፍታት መሞከሩንም እንደ ብልጠት፣ እንደ አራድነት የሚያይ ነው የአዲስ አበባ ዐማራ። ቀበሌ፣ ወረዳ፣ ክፍለከተማ፣ ክልል፣ ፓርላማ ገብቶ መሥራት ይሸክከዋል። ቀበሌውንም ፓርላማውንም ለክፍለ ሀገር ልጆች ለቆላቸው እሱ ፍዳውን ይበላል። ፖለቲካ እንደሆነ አይገባውም። እናቱን የሴፍቲ ኔት ተጠቃሚ አድርጎ ከዚያ በሚመጣ የምጽዋት ዘይት እየበላ ልክ ደህና ቤተሰብ እንዳለው ሰው በአደባባይ ሲጎርር ጉራውን ሲቸረችር ይውላል። እሱ አራዳ ነው። እየመጡ ነው ብሎ በመጨፈር ለፋኖ ደሙን የሰጠ ይመስለዋል። ሀገሪቷ ግልብጥብጥ ብትል አርሰናል አይሸነፍበት፣ ማንችስተር ነጥብ አይጣልበት እንጂ ደንታው አይደለም። ፖለቲካው ቡናና ጊዮርጊስን አዲስ አበባ ላይ እንዳይጋጠሙ አድርጎ ዱባይ ወስዶ ሲያጣልዝ እሱ አይገባውም። የሰው መሰባሰብ ችግር ይፈጥርብኛል ብሎ ጨዋታ ከአዲስ አበባ ማራቁን አይባንንም።

…ድሉ የዐማራው ነው። የተደራጀ ዐማራ ያሸንፋል። ድሬደዋ፣ ሀረር ሕብረታቸው ደስ ይላል። ደቡብም እንደዚያው። የሚያሰጋው ጋምቤላ ኢሉአባቦራ ነው። ባሌና አሩሲ ከተደራጀ አይደፈርም።

ሂ፦ ዳያስጶራው ዐማራ

"…ኬንያም፣ ጅቡቲም ያለው ስደተኛ ያው ዳያስጶራ ነው የሚባለው። ቅርብ አፍሪካ ያሉት ቢፈሩ አይፈረድባቸውም። ደቡብ ሱዳን፣ ሱዳንና ናይሮቢ ሆኜ ብቃወም የሚጠብቀኝን አስባችሁታል? እናም በእነሱ መፍረድ አይቻልም። ባህር ተሻግሮ አውሮጳና አሜሪካ የገባው ግን ያስቀኛል። በአየርም፣ በባህርም የመጣው ስደተኛ ዐማራ ፍርሃቱ ዘርፈ ብዙ ነው። አንዳንዳንዱ ዐማራ የተሰደደው ርቦት ነው። እናም ሠርቶ ሲያገኝ ማምሻ ዕድሜውን ሀገሩ ገብቶ በሸነና ብሎ መሞት ስለሚፈልግ ስለ ቦለጢቃው አያገባውም። በቃ ሆዱን እንዳሳደደ ይኖራል። ውስኪ በ30 ዩሮ፣ ቢራ በሳንቲም መጠጣት የልጅነት ሕልሙን እንደማሳካት ስለሚቆጥረው ለቦለጢቃው ደንታ የለውም። እንዲህ ዓይነቱ ሰው እንኳን በሀገሩ ጉዳይ ከቤተሰቡ ጭምር አድራሻውን ሰውሮ ነው እንደ ጅብ ተደብቆ እየበላ የሚሞተው። ሲበዛ ሆዳም፣ ራብ ያጠቃው ነው።

"…ይሄ ሆዳም ዐማራ ሴትም ከሆነች ቲክቶክም፣ ዩቱዩብም ላይ በአውሮጳና በአሜሪካ ርካሽ የሆነውን ምግብ እየሠሩ እየበሉ በራብ ለሚሰቃየው ወገናቸው የምግብ ጥያቄአቸው እንደተመለሰ በማሳየት ሲያስጎመጁ ይውላሉ። ቁርስም፣ ምሳም፣ ራትም ሲበሉ፣ ቡናም ጭማቂም ሲጠጡ Live ቀርበው ይለፋደዳሉ። ራብና ጠኔ ከሀገር ያስወጣቸው ስለሆኑ በቀል ላይ ናቸው። ውራጅ ጨርቅ፣ ሜካፕ ተቀብተው ሀብታም ሀብታም ይጫወታሉ። ሀገር ቤት ለእረፍት ሄደው ወር የማያቆይ ሳንቲም ያላቸው ሁሉ፣ እቁብ ጥለው የአውሮጵላን ትኬት ቆርጠው ዛር ወጥቶ ተንቀጥቅጦ የሚሄደው ሁላ በማኅበራዊ ሚዲያው ላይ ሲያክት አይጣል ነው። አመንዝራ፣ ሆዳም፣ መሃይም ስደተኛ ዐማራው ለቦለጢቃው ደንታ የለውም።

"…የተማረ፣ ደኅና ቦታ ደርሷል የሚባለው ዐማራ ድሮ በኢህአፓ ጊዜ፣ ከዚያም በዲቪ የሄደው፣ ቀደም ብሎ የወጣው፣ ወጥቶም ራሱን በትምህርት አሻሽሎ የእውቀት ወረቀትም፣ ገንዘብም ያለው ነው። እሱ ደግሞ ድሮ ላይ ተቸንክሮ የቀረ ነው። ዐማራ ሆኖ ከኢትዮጵያዊነቴ አልወርድም በማለት 1960 ላይ ተቸንክሮ የቀረ ነው። አሁንም አብዮተኛ ነው። ኢህአፓው ኢህአፓ፣ ደርጉም ያው ደርግ ነው። እናም የቦለጢቃ ጨዋታው አልገባውም። የገባቸው ደግሞ ገሚሶቹ ጩሉሌ ናቸው። አራዶች። በትምህርት ያጡትን ሀብት በትግሉ ስም ቀፍለው ፏ ብለው የሚልዮን ዶላር ቤት እና ቴስላ መኪና እየነዱ ይኖራሉ። ቦለጢቃውን በሩቁ የሚሉት ዳያስጶራዎች ለእነዚህ አጭቤዎች ገንዘቡን ወርውረው እነርሱ ድራሻቸውን ያጠፋሉ። እናም አጭቤው እየከበረ፣ ትግሉ እየከሰረ ይሄዳል።

"…እንጂ ዳያስጶራው ዐማራ መገፋፋቱን፣ ተቸንካሪነቱን፣ ጎጠኝነቱን፣ መንደርተኝነቱን ትቶ እንደ ዐማራ ተደራጅቶ ቢነሣ ተአምር ነው የሚሠራ የነበረው። አገዛዞች ደግሞ ሆዳም አማራውን በሽታ ነው የሚያውቁት። ሆዳምና መሃይም ዐማራ ለአምባገነኖች ምቹ አፈር ነው። መሃይም እና ሆዳም ዐማራን ኤምባሲ መጋበዝ ብቻ በቂ ነው። አምባሳደሩ ከደወለለት ክርስቶስን ያገኘ ነው የሚመስለው… ከታች ይቀጥላል…