Get Mystery Box with random crypto!

ከላይኛው የቀጠለ… '…በሰሜን ወሎ ራያ ዐማራው ከፊት ከትግሬ ኃይሎች እና ከኦሮሞው መከላከያ | Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ከላይኛው የቀጠለ… "…በሰሜን ወሎ ራያ ዐማራው ከፊት ከትግሬ ኃይሎች እና ከኦሮሞው መከላከያ ጋር፣ ከኋላው ከደነዙ የብአዴን አድማ ብተናና ምስኪኑ ሚሊሻ ከፍ ያለ ጦርነት ይጠብቀዋል። የኦሮሞ ብልፅግናም ሆነ ብአዴን እስከ አሁን በፋኖ ላይ ያላገኙትን ድል በዚህ ግንባር ሊያገኙ ያሰፈስፋሉ። ተጠቃቅሰው ራያና ወልቃይትን እንዳላስወረሩ ይሄ ሕዝብ ዥል፣ ዥልጥ ስለሚመስላቸው አቢይ አህመድ በለገሰ ቱሉና ብአዴን በክልል መንግሥቱ ስም ዐማራ በሕወሓት ተደፈረ ብለው መግለጫ ያወጣሉ። ሕዝቡም፣ ፋኖውም የሕወሓትን ወረራ ለመመከት ከክልሉ የፀጥታ ኃይልና ከከሃዲው መከላከያ ጋር ይሰለፍ ብለው ያውጃሉ። እንደ አገኘሁ ተሻገርም መሳሪያ ያለህ በመሳሪያ፣ መሳሪያ የሌለህ በገጀራ ህወሓትን መክት፣ የማረከው መሣሪያም የራስህ ይሆናል ውሰደው ሁላ ይሉታል። እናም እሺ ብሎ እነርሱን አምኖ ወደ ውጊያ የሚገባ ፋኖ ሲያገኙ በጥይትም፣ በፈንጂም፣ በድሮንም ከፊትም ከኋላም በመደምሰስ በውጊያ ያልቻሉትን በዘዴ ከመሃል አስገብተው ሳንድዊች ሊያደርጉት ቋምጠዋል። የወልድያው ስብሰባም በዚሁ አግባብ መፈጸሙም መረጃ ወጥቷል። የኦሮሙማው አየር ኃይልም አሁን ከትግሬ ጦርና ከመከላከያው ጋር ለመግጠም እጅብ ብሎ ይመጣል ብሎ ጓጉቶ የሚጠብቀውን የዐማራ ፋኖ በድሮን ሊያጠቃው ዝግጅቱን ጨርሷል። የጦር ጀቶችም የድሮን በራሪዎችም ወደ አፋር ሰመራ ገብተው በተጠንቀቅ ቆመዋል። የዐማራ ፋኖ ግን የሴራ ቦለጢቃውን ነቅቶበት ጆሮ ዳባ ልበስ ብሎ አኩርፎ በገፍ ሊቀላቀለው የሚመጣውን ሚሊሻም ሆነ አድማ ብተና ተቀብሎ ኃይሉን በማጠናከር ሕዝቡን ከያዘ ለትግሬም ጦር ሆነ ለኦሮሙማው መከላከያ ዋጋቸውን ለመስጠት እምብዛም አይቸገርም። ከመ ጤፍ…

ሁ፦ ሰሜን ወሎ ዋግ ኽምራ ሰቆጣ

"…የዐማራ ፋኖ በዚህ ግንባርም ከሦስት ኃይሎች ጋር ይጋፈጣል። ከትግሬ ኃይል፣ ትግሬና ኦሮሞ ካዘጋጁት የአገው ሸንጎ ኃይልና ከኦሮሙማው መከላከያ ጋር ውጊያ ይጠብቀዋል። የአገው ሸንጎ የሚባለው ራሱ የትግሬ ጦር ሌላኛው ክንፍ ስለሆነ ያው ስም የቀየረ ትግሬ ነውና አያሳስብም። እናም ይሄን ኃይል ለመመከት ከወዲሁ ከላስታ ጀምሮ ያለው የዐማራ ሕዝብ ለአርማጌዶኑ ጦርነት መዘጋጀት አለበት። የቤት ሥራው ከወዲሁ ተሠርቶ ማለቅ አለበት። የትግሬ ጦር ሲሸነፍ የአገው ሸንጎም አብሮ ነው የሚሸነፈው። የሚበተነውም።

ሂ፦ ደቡብ ወሎ

"…በዚህ ግንባር የዐማራ ፋኖ የሚጠብቀው የኦሮሙማው የመከላከያ ሠራዊት፣ የብአዴን አድማ ብተና ብቻ አይደሉም የሚጠብቁት። በደቡብ ወሎ የሃይማኖት ውጊያም ሊኖር ይችላል። በእነ ሙጂብ አሚኖ በጀት ወሎን ክልል እናደርጋለን ብለው በየመስጊዱ ጭምር ከሚፎክሩት፣ የዐማራ ፋኖን የክርስቲያኖች ስብስብ ነው ከሚለው የወሎ ኅብረት ፅንፈኛ የወሃቢይ እስላሞች ጋር ጦርነት ይጠብቀዋል ብዬ እሰጋለሁ። በጁንታው ጦርነት ወቅት ከዐማራ ፋኖ ጋር ገጥሞ ይዋጋ የነበረው የሐሰን ከሪሙ ቡድንም በዚሁ ቡድን መጠለፉም አይረሳ። ኮምቦልቻ አካባቢ ከከሚሴ የሚነሣ የኦነግ ጦርም ከኦሮሙማው መከላከያና ከወሎ ፅንፈኛ ዐማራ ጠል የወሓቢያ እስላሞች ጋር ፍልሚ ይጠብቀዋል። ምንአልባት ህወሓት እስከደሴ ድረስ መጥታ ከዚያ የወሎ ክልልነት ተመቻችቶ ኦሮሙማው በሠራው ካርታ መሠረት ወሎን ልክ እንደ አውራ ጎዳና ለመጠቅለል ይሞክራል። ነገር ግን በዐማራ ክልል ከዐማራ ፋኖ በቀር አሸናፊ አካልም ሓሳብ የለም። አይኖርምም።

ሃ፦ ሰሜን ጎንደር

"…በጠገዴ፣ በማይ ፀብሪ እና በአዲአርቃይ የኦሮሞው መከላከያ ሠራዊት እና የትግሬው ኃይል ጋር ይገጥማል። በወልቃይት ደግሞ አርማጌዶን በሉት ከበድ ይላል ተብሎ ይጠበቃል። የወልቃይቱ ኮሎኔል ከብልፅግና ጋር ከሆነ ወልቃይትን አስረክቦ ወደ ካደው ሕዝብ ወደ ጎንደር መጥቶ የገነባውን ህንፃ እያከራየ ዘጭ ብሎ ይኖራል። ምክንያቱም ኮሎኔሉ የሀገር መከላከያ ሠራዊት ላይ መተኮስ ወንጀል ነው ብሎ በአደባባይ ፋኖን ያወገዘ ሰው ስለሆነ አሁን መከላከያ ውጣ ሲለው እምቢ ይላል ተብሎ ይጠበቃልን? የኦሮሞው መከላከያ፣ የትግሬው ኃይልና ሱዳን የተሰደደው ገዳዩ የትግሬ የሳምሪ ቡድንም አሁን አንድ ላይ ሊሠለፉበትም ይችላል። የኦሮሞ ብልፅግና፣ የአማች ፖለቲካ ተጋቢዎችም የዋዛ አይሆኑበትም። በውስጥ ያለው የትግሬ ወለዱ የፖለቲካው ቅማንትም ሌላው ፈተና ሊሆንበት ይችላል። የሆነው ሆኖ በዚያ አካባቢ መለኮታዊ ጣልቃገብነት ከሌለ በቀር ትርምስምሱ ይወጣል። ደፍርሶም ግን ይጠራል። ሌላ አማራጭ ስለሌለው ዐማራም የግዱን ያሸንፋል። እንደ ራያ፣ እንደ አላማጣው ብዙ የብልፅግና ባለሥልጣናት ከወልቃይት እስከጎንደር ተቀርጥፈው የሚበሉበት ጊዜም የቀረበ ይመስላል።

ሄ፦ ደቡብ ጎንደር

"…ትልቁ ግዙፍ የዐማራው ፈተና የሚገኘው በደብረ ታቦር ነው። ደብረታቦር መከላከያው፣ የአማራ አድማ ብተናና ፖሊስ ብቻ አይደለም የሚገኘው። በደቡብ ጎንደር ወያኔ እስከአሁን አለች። አልሞተችም። አልጠፋችም። ከሁሉም የዐማራ ክልል የወያኔ ሴል እስከ አሁን ድረስ ሳይወገድ እንዳለ የአመራር ስፍራውን ሳይለቅ የተቀመጠው ደቡብ ጎንደር ነው። በሰሜን ጎንደር ወኪል፣ በጎጃምም ወኪል ነው ወያኔ ያላት። የፖለቲካው ቅማንት እና የፖለቲካው አገው ሸንጎ ሰዎች በወሳኝ ሥፍራ በሥልጣን ላይ ያሉ ቢሆንም በደቡቡ ጎንደር ግን ይበዛሉ። አጥብቆ ወያኔን ናፋቂ ዐማራ መሳይ በዐማራ ላይ የተሾመ ጉግማንጉግ ነቀርሳ የሆነ ፀረ ዐማራ ኃይል የሚገኘው በዚሁ አከባቢ ነው ይባላል። ወያኔ በመቀሌም ሳይቀር ሞታ በደቡብ ጎንደር ግን እንዳለች ነው ያለችው ይላሉ። እናም የዐማራ ፋኖ በደቡብ ጎንደር ከአፍቃሬ ወያኔ ብአዴን ኃይል፣ ከሚሊሻውና ከአድማ ብተናው ጋር የኦሮሙማውን መከላከያ ደርቦ ለመግጠም የሚዘጋጀው ከወያኔ ርዝራዥ ወያኔ ዐማሮችም ጋር ጭምር ነው።  ይሄ ግድ ነው በቃ።

ህ፦ ጎጃም

"…የጎጃም ዐማራም እንዲሁ በዛ ያለ የጦር ግንባር ነው የሚጠብቀው። ፖለቲካ ወለዱ አገው ሸንጎና የኦሮሙማው መከላከያ ኃይል እንዳለ ሆኖ ልክ እንደ ደቡብ ጎንደር አፍቃሬ ወያኔው ብአዴን ከነ ርዝራዡ ያለበትም ስፍራ ነው። መቀሌ ድረስ ትግሬ ተርቧል ብሎ ጤፍ ጭኖ 90 ዓመቱ ትግራይ ድረስ እያነከሰ የሚሄድ ጎጃሜ ስታይ ትደነግጣለህ። ይኸው የተላከው ዱቄት ስንቅ ሆኖት ትግሬ ወደ ራያ ሲገባ ሽማግሌው ጎጃሜ ምን ሊሉ ይችላሉ ብለህ አትሰብ። የዐማራ ሚሊሻና የአድማ ብተና ተብዬውን ከመከላከያው ጋር በጎጃም ከዐማራው ፋኖ ጋር ይገጥማል። የጉምዝ ኃይሎች ከኦነግ ጋር ሆነው እንደ አዲስ ካልተነሡበት በቀር በዚያ በኩል ስጋት ቢኖረኝም ስጋቴ ግን የቀነሰ ስጋት ነው።

"…ቅሬታ ካላመጣ ለምን እንደሆነ ባላውቅም ወያኔ በሩቅ ሆና ወሎን አልፋ እንደምንም ከጎጃም ፋኖ ጋር የመገናኘት እድል ቢኖራት የሚመኙና የሚናፍቁ ትግሬዎችን እያየሁ መሆኔ እያስገረመኝ ነው። አርበኛ ዘመነ ካሴ ከሚናገረውና ከሚሰጠው መግለጫ ተነሥቼ ለወያኔ መራር ጥላቻ እንዳለው ብገምት ብረዳም አብዛኛዎቹ የወያኔ ሰዎች ግን በጎጃም ፋኖ አመራሮች በተለይ ለጠበቃ አስረስ ማሬና ለማርሸት ያላቸውን ክብር ሳይ ይሄ ክብር ከምን እንደሚመነጭ ሊገባኝ ባለመቻሉ ቅዥብርብር ሲያደርገኝ ይኖራል። የሆነ ተንኮል ይኖርበት ይሆንን ብዬም እጠይቃለሁ? የሆነው ሆኖ እንደ ስትራቴጂም ሆነ፣ እንደ ታክቲክም ይዘውት እንደሁ ባላውቅም የወያኔ ሰዎች ግን እንደምንም ብለው ከጎጃም ፋኖዎች ጋር ኅብረት ለመፍጠር ሲላለጡ እያየሁ ነው። ምን አልባትም ልክ እንደ ደቡብ ጎንደሩ በጎጃም ፋኖ ውስጥም አፍቃሬ ወያኔ … ከታች ይቀጥላል…