Get Mystery Box with random crypto!

ከላይኛው የቀጠለ… …ማወዛገብም ሊሆን ይችላል! የቼሪ እና አስረስ ጨዋታ ማለቴ ነው! የሆነው | Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ከላይኛው የቀጠለ… …ማወዛገብም ሊሆን ይችላል! የቼሪ እና አስረስ ጨዋታ ማለቴ ነው! የሆነው ሆኖ. . .ምክንያቱ ከላይ ከተጠቀሱት አንዱ ይሁን ወይም ሌላ ፍፃሜው ግን አጓጊ ነው! ይልና ይሄንኑ የታደሰ ወረደን መግለጫ መነሻ በማድረግ የፌደራል መንግሥቱ እና የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ከስምምነት መድረሳቸውን በማተት ሌላ ትንተና ይሰጣል። አደገኛውንና በከባዱ የተመከረበትን ምክርም የሚያሳይ ምልክትም ይሰጣል።

"…ታዲያ የፌደራል መንግሥቱ እና የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር በትግራይ ክልል ፖሊስ፣ የዐማራ ፋኖን ከመሬቱ በማንፃት የራሱንን አስተዳደራዊ መዋቅር እንዲገነባ ከፈቀደ ይህም በምዕራብ ትግራይ ይቀጥላል ማለት ነው። ይህ ሆነ ማለት ደሞ የፕሪቶሪያው ስምምነት ተተግብሯል ማለት ነው!! በዚህም የፋኖ ኃይል ላይ ከፍተኛ ስጋት የሚፈጥር አጋርነት ሲሆን ለፌደራሉ መንግስሥት ደግሞ የዓለም መንግሥታት የሚለቁትን የዶላር ገንዘብ ይለቀቅለታል ማለት ነው።

"…ነገር ግን የሻብዕያ ልጅ የሆነው ፋኖን ይላል "ነገር ግን የሻብዕያ ልጅ የሆነው ፋኖን የፌደራሉ እና የትግራይ ኃይል በጋራ ጥምረት የሚመቱት ከሆነ እና የምዕራብ ትግራይ ጉዳይም እንደ ደቡብ ትግራይ በትግራይ ሠራዊት የሚፈታ ከሆነ የኤርትራ እና የኢትዮጵያ ቀጠናዊ ቆርሾ ከፍ ይላል ማለት ነው። ይህ ከሆነ ደግሞ የዓለም መንግሥታት በአፍሪካ ቀንድ በዚህ ሰዓት ውጥረት ለማስተናገድ ፍቃደኛ ስለማይሆኑ አንዱ ኃይል በዓለም መንግሥታት ይመታል ማለት ነው።

"…የኢትዮጵያ መንግሥት የዓለም መንግስታትን ፍላጎት በፕሪቶሪያው ስምምነት የሚያስፈፅም ከሆነ የኤርትራ ጉዳይ ከኢትዮጵያ ጋር ሳይሆን ከዓለም መንግሥታት ጋር ስለሚሆን ጨዋታው በትግራይ መንግሥት እና በፌደራል መንግሥቱ ስምምነት ወቅት ተጠናቅቋል በማለት በጓዳ ተመክሮ የወሰኑበትን ጉዳይ ይዘረግፈዋል። ዐማራ ከትግሬ ጋር ፍቅር ይኖረኛል ብለህ መጃጃሉን ትተህ በእነሱው የጭካኔ መስመር ሄደህ መብትህን እንድታስከብር እመክርህሃለሁ። ሲያዩት የሚከብድ የሚመስል ቢሆንም ዓረቡም ሆነ እነ አሜሪካ ተደርበው ቢገቡ ሱማሌና አፍጋኒስታን ድል የነሱትን ኃይል የዐማራ ፋኖ ያቅተዋል ተብሎ አይታሰብም። ስለዚህ ከዚህ የትግሬዎቹ ትንተና ተነሥተን ትግሬም አቢይም የሚፈልጉትን ፍላጎት ለሟሟላት ዐማራውን ተጠቃቅሰው ጭዳ ለያያደርጉት መጨረሳቸውን ዐወቆ በዚያው ልክ መዘጋጀት ያስፈልጋል።

• ድል ከዐማራው ፋኖ…!
• ድል ለተገፋው ለዐማራው ሕዝብ…!

• ድርጅቱ ዘመዴ ነኝ አሸበርቲው ከራየን ወንዝ ማዶ…!