Get Mystery Box with random crypto!

መልካም… '…መቼም ያን ሊማሊሞ፣ አርበረከቴ ግራካሱ የመሰለ እኝኝብላ የሆነ የዛሬውን ርዕሰ አንቀ | Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

መልካም…

"…መቼም ያን ሊማሊሞ፣ አርበረከቴ ግራካሱ የመሰለ እኝኝብላ የሆነ የዛሬውን ርዕሰ አንቀጼን እንዳነበባችሁ በላይክ አድራጊው ብዛት ገምቻለሁ። አይናችሁን እስትራፖ ሳላስየዘው አልቀርም። የሆነው ሆኖ የጻፍኩት ጊዜ አግኝተው የማንበብ ፍላጎት ላላቸው የቲጂ መንደር ጓደኞቼ ነው። ያው በል በል ሲለኝ፣ ግራ ትከሻዬንም ቀኝ ትከሻዬንም ሲሸክከኝ እና ሲያመኝ ጤና የለኝም አይደል? ለዚያ ነው ያስረዘምኩባችሁ። እስከ ነገ ድረስ ሌላ ነገር አልጽፍባችሁም። በመሃል ካልሸከከኝ በቀር ቃሌን እጠብቃለሁ ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ። ብጽፍስ ደግሞ ምን አለበት? ምን ክፋት አለው? አይደል…?

"…ለማንኛውም በሥራ ምክንያት ትናንት ያልገባንበት የቲክቶክ መንደራችንን ለመጎብኘት ገባ ብዬ ወጣ ለማለት ወደዚያው እየሄድኩ ነው። እስከዚያው በርዕሰ አንቀጹ ላይ ያላችሁን የራሳችሁን አስተያየት ለማንበብ ዝግጁ መሆኔን ስገልፅ ከፍ ባለ አክብሮት እና ትህትና ነው። (ወይ ትህትና እቴ)

• እየጻፋችሁ…እየሄዳችሁ…!