Get Mystery Box with random crypto!

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

የሰርጥ አድራሻ: @zemedkunbekelez
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 407.60K
የሰርጥ መግለጫ

"ይህ የቴሌግራም ቻናሌ ግንቦት1/2011ዓም የተከፈተ ነው። የእኔን የስልክ ወጪ ጨምሮ አገልግሎቴን መደገፍ የምትፈቅዱ ጓደኞቼ በ
👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia እና
👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል ማገዝ ትችላላችሁ። በተረፈ ለቤተ ክርስቲያኔና ለኢትዮጵያ ሀገሬ የሚጠቅመውን ሁሉ አበረክት ዘንድ አብዝታችሁ ጸልዩልኝ።

Ratings & Reviews

4.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 269

2022-09-02 13:45:34 የከንቲባው ፍጻሜ…!!

• ቆይቼ የአስተያየት መስጫውን ሰንዱቅ እከፍትላችኋለሁ። እስከዚያው እያነበባችሁ ቆዩኝ።

"…በሰሜን ሸዋ በሸዋሮቢት ከተማ በትናንትናው ምሽት የከተማዋ ከንቲባ አቶ ውብሸት አያሌው ባልታወቁ ሰዎች ተመተው መገደላቸው ይታወሳል። ከአቶ ውብሸት በተጨማሪ የአቶ ውብሸት ባለቤትም የተመቱ ሲሆን ነገር ግን ለከፍተኛ ህክምና ወደ ደብረብርሃን ይሁን ወደ አዲስ አበባ ለጊዜው ወዳልታወቀ ሥፍራ ለህክምና መላካቸው እንጂ እስከአሁን የሞታቸው ዜና አልተሰማም።

"…የሸዋሮቢት ከተማ የተለየያዩ ከንቲባዎችን አስተናግዳ ታውቃለች። ከአቶ ውብሸት በፊት አቶ ቴዎድሮስ እና ወሮ ሉባባ የሚባሉ ሁለት ከንቲባዎችም ተሾመው ነበሩ። አቶ ቴዎድሮስ በፋኖዎች የፌስቡክ ገፅ ውስጥ ገብተው በኮመንት መስጫ ሳጥኑ ላይ " አንድ ሞርታር ይዞ መጎረር አይከብድም?" ብለው አስተያየት ከሰጡ በኋላ በደረሰባቸው ውግዘት ተደናግጠው ሥልጣን ለቀው አሁን ሰላማዊ ሰው ሆነው ብስክሌት እየነዱ በሰላም መኖር ከጀመሩ ሰነባብተዋል ነው የሚባለው። ወሮ ሉባባም በሁሉ ዘንድ ተወዳጅ የነበሩና በእድገት ወደ ዞን ያደጉ ሴት ከንቲባ ነበሩም ይላሉ አስተያየት ሰጪዎች። ቀጥሎ የመጡት አቶ ውብሸት ነበሩ።

"…አቶ ውብሸት የተረከቡት የሸዋሮቢት ከተማ ህዝብ በጁንታው የደቀቀ፣ በኦነግ ሴቶቹ የተደፈሩባት፣ ንብረት የተዘረፈባት፣ ዕልፍ ጀግኖች የወደቁባት፣ በአጠቃላይ የኢኮኖሚዋም፣ የሥነ ልቦናም ድቀት የገጠማት፣ ሆደባሻ ከተማን ነበር። ለዚህ በዘርፈ ብዙ ሀዘን ለተመታ ከተማ ህዝብ ደግሞ የሚያስፈልገው የሚያጽናና፣ የሚያበረታታ፣ ለሥራ የሚያፋጥን፣ የሥነ ልቦና ህክምና የሚሰጥ ሰው ነበር መመደብ የነበረበት።

"…መንዝን በቤተሰብ የሚያስተዳድረው አቶ ግርማ የጅብጥላ ግን ይሄን ትእቢተኛ ሰው መደበ። ህዝቡን ሰብስቦ የሚደነፋበት፣ አሳይሃለሁ፣ እቆርጥሃለሁ፣ እፈልጥሃለሁ እያለ እንደ ከንቲባ ሳይሆን እንደ ጀነራል የሚያደርገው፣ ከወፈሩ አይፈሩ ሆኖ ጮማው አዕምሮውን ደፍኖበት በጦርነቱ የሞቱ የፋኖና የሚሊሻ ቤተሰቦች ላይ ሳይቀር እንደግርማ የጅብጥላ ሲያቅራራ ከረመ ይላሉ አስተያየት ሰጪዎች።

"…ከዚህም አልፎ ዐቢይን ተሳደባችሁ ብሎ የሸዋ ሮቢትን ወጣቶች በጅምላ ፈጃቸው። በቅርቡም ሁለት ወጣቶችን አስገደለ። ግርማ የሺጥላ ለዚህ ጀብዱ ቪ8 መደበለት። በዐማራ ልዩ ኃይልም እንዲጠበቅ ተደረገ። በቃ ሚጢጢዬ አምባገነን ሆነ። ትናንት ምሽት ግን ውብሸት ባልታወቁ ሰዎች ተገደለ። አብረውት የነበሩትና ግርማ የሺጥላ የመደበለት የዐማራ ልዩ ኃይል አባላት ፖሊሶችም ጥለውት ሸሹ። አላዳኑትምም። አልተከላከሉለትምም። ሚስቱም ተመታች። ቨ8ቱም ቀረ። የግርማ የጂብጥላም ሞራል አብሮ ደቀቀ። ዐማራን ለማዋረድ ይደክም የነበረው አንደበትም ተዘጋ።

"…ከንቲባው ባለፈው የሸዋሮቢት ወጣቶችን ከረሸነ፣ ካስረሸነ በኋላ የሟች ቤተሰቦች ሀዘን እንዳይቀመጡ አስደረገ። ከለከለ። ሁሉም አዘኑበት። ለዚህ ተግባሩም የመንዙ ግርማ የጅብጥላ ጀግና ብሎ ጠራው። አሞካሸውም። ዛሬ በከንቲባ ውብሸት መኖሪያ ቤት ለቅሶ የሚደርሰው አንድም ሰው ጠፋ። ወዳጄ የሸዋ ህዝብ አይጥላህ። እንዲያውም በከንቲባው ሞት የተነሣ ግርማ የጂብጥላ ጦር ይልካል ተብሎ ተጠብቆ የነበረ ቢሆንም ከተማዋ የተለመደ ሰላማዊ እንቅስቃሴዋን ቀጥላለች። ቀጣዩ ከንቲባም ከውብሸት ትምህርት የወሰደ እንደሚሆን ይታመናል ይላሉ ሸዋሮቢቶች።

"…አሁን ከዘመነ ህወሓት ጀምሮ 30 ዓመት ሙሉ ብአዴን ሆነው ዐማራ ህዝብ ላይ ያላገጡ ነውረኞች ደንግጠዋል ይላሉ። አያ ግርማ የጂብጥላም ጠባቂ ቁጥር ይጨመርልኝ ብሏልም ተብሏል። በጠባቂ ብዛት ግን አይዳንም። ቤተሰቡ ያለቀበት፣ የታሠረበት ዐማራ፣ የዐማራ ፋኖ ከሸዋሮቢት ትምህርት የወሰደም ይመስላል። ሃዘን ከገባ አይቀር ብአዴኖች ቤትም ይግባ እንጂ ያሉም ይመስላሉ። አባቱ የተገደለበት፣ ወንድሙ የተገደለበት፣ የታሰረበት ሁላ በቀጣይ ወደ ምሥራቅ ወደ ሸዋሮቢት መመልከቱም አይቀርም። ጎን ለጎን ኦነግም አስወግዶት ቢሆንስ የሚሉም አሉ።

"…የሆነው ይሄ ነው…!! የሞቱትን የዐማራ ወጣቶች ግን ነፍሳቸውን ይማር። በቀጣይ እንዲሁ ዘገባ ሲኖር አቀርብላችኋለሁ።

#ማሳሰቢያ፦ ከእንግዲህ ወዲህ በፔጄ ላይ እገሌ ታሰረ፣ እገሌ ታፈነ ብዬ የማልዘግብ መሆኔ ይታወቅልኝ። እንደበግ መነዳት ዜና አይሆንም። ውሻው ሰውዬውን መንከሱ ዜና አይሆንም። የተለመደ ነው። ዜና የሚሆነው ሰውዬው ውሻውን የነከሰ እንደሆን ነው።

"… ጠብቁኝ ቆይቼ እመለሳለሁ…!!
12.4K views10:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-02 13:31:19
የከንቲባው ፍጻሜ…!!

"…ለጊዜው የምጠቀመው፣ ሃሳቤንም የምገልፀው፣ መልእክቶቼንም የማስተላልፈው በዚህ የቴሌግራም ቻናሌ ብቻ ነው። ከዚህ ውጪ አንድም ፌስቡክ የማልጠቀም መሆኔም በግልጽ ይታወቅልኝ። ተናግሬአለሁ። ከአጭበርባሪዎች ተጠበቁ።

http://t.me/ZemedkunBekeleZ

https://t.me/zemede_Discussion
19.2K views10:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-02 12:01:24 "…ቁጥራቸው አይታወቅም። እርሻና ልጆች ትተው ሊቀመንበሩ በጭካኔ የሚልካቸው ናቸው። መሬትም ሚስቱም የምትወረስ ብዙ ሚሊሻ ነው። ስንቅ የላቸውም። ወታደሩም ልዩ ኃይሉም ሬሽን አለው። ሚሊሻው ግን ያሳዝናል። ሦስት ቀን እህል ያልቀመሱ አሉ። ጫማቸው ኤርጌንዶ ነው። እሱ ተበጣጥሶ እግራቸው ነፍሮ ማየት ያሳዝናል። እናም ቢያንስ የሆዳቸው ነገር እና የተተኳሽ፣ የጫማቸው ነገር ቢታሰብበት መልካም ነው።

፰ኛ፦ የበጀት እጥረት

"…አምና በነበረው ጦርነት የህዝብ የደጀን ተሳትፎ እጅግ ግሩም ነበር። በሃገር ውስጥም ከሃገር ውጪም እንደዚያው። ነገር ግን ቀለብላባው እና ንኩ ጠቅላይ ሚንሥትር ተብዬው ለገና የመጡትን ዳያስፖራዎች ውሻ ፈትቶ ለቅቆ ካባረራቸው በኋላ ዳያስጶራውም በብልጽግና መንግሥት አኩርፎ እስከአሁን እንቅስቃሴ የለም። ይሄን ያስተባብሩ የነበሩት እነ ታማኝ በየነንም መንግሥት ውሻ አድርጎ አንገቱንም ቅስሙንም ሰብሮ ስለላካቸው የሉም። ዳያስጶራው አፍሯል። ድጋፉም ሙሉ ለሙሉ በሚባል ደረጃ ቀጥ ብሏል።

"…በሃገር ውስጥም አምና ክልሎች፣ ከተማ አስተዳደሮች፣ የመንግሥት ሠራተኞች በሙሉ ከደሞዛቸው ሳይቀር እያዋጡ ይደግፉ ነበር። እነ አዳነች አቤቤ ሁላ ግምባር ድረስ ሄደው ስንቅ ሲያቀብሉ፣ ከዚህም የተነሣ እነ ፋሲል የኔዓለም "ዳግማዊ ጣይቱ" ሲሏቸው እንደነበር ይታወሳል። ዘንድሮ ግን ወፍ የለም። ህዝቡም በመንግሥቱ ላይ ስላኮረፈ ጭጭ ምጭጭ ብሏል። ይሄ ነገር ከባድና አደገኛ ነው። ባለሃብቱም አይመለከተኝ የሚል ስሜት ያለው ይመስላል። አርቲስቱም ተደብቋል። እብድ መሪ ያላት ሃገር እንዲህ ናት።

"…የዐማራ ክልል አሁንም ይሄ ፍዳ የወደቀበት ሆኗል። በጀቱ በሙሉ ለጦርነቱ እየዋለ ነው። የሆስፒታል አልጋ በቁስለኞች ተሞልቷል። ሃኪሞች እዚያ ርብርብ ላይ ናቸው። ክልሉ በጀቱን በጊዜ ጨርሶ እጁን አጣጥፎ ከመቀመጥ ውጪ ሌላ አማራጭ ያለው አይመስልም። ኦሮሚያ ግን ልማት ላይ ነች። በጀቷንም በአግባቡ እየተጠቀመች ነው። እናም ይሄ ነገር በቶሎ ቢታሰብበት እና የፌደራሉ መንግሥት ልዩ የሆነ በጀት ለዐማራ ክልል ቢመድብ ይላሉ ወዳጆቼ። እናንተስ ምን ትላላችሁ? ተወያዩበት።

በተረፈ፦ ኢትዮጵያ ታሸንፋለች።

• ድል ለሃገሬ መከላከያ…!!
• ድል ለዐማራ ልዩ ኃይል…!!
• ድል ለዐማራ ፋኖ…!!
• ድል ለዐማራ ሚሊሻ…!!
• ድል ለአፋር ልዩ ኃይል…!!
• ድል ለአፋር ሚሊሻ…!!
• ነፃነት ለትግራይ ህዝብ…!!
• ሞት ለወያኔ እና ለልጆቿ ለብአዴንና ለኦህዴድ…!!
39.0K views09:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-02 12:01:23 የዐርብ ጠዋት ጦማር…!!

• የጥንቃቄና የማስተካከያ ጥቆማ የያዘ ጦማር ነው። አንዳንዱን ባይሰሙት የሚፈልጉ ይኖራሉ። ነገር ግን ቢመርም መስማቱ ፈውስ ነው። ለመከላከያው አድርሱልኝ።

"…ጦርነቱ አስከፊ ነው። አሰቃቂም ጭምር ነው። ከዚህም ከዚያም ይህ ነው የማይባል በቁጥር የማይገለፅ ሰው እያለቀ ነው። ወንድ የተባለ ከዚህም ከዚያም እየወደቀ ነው። በተለይ ደግሞ ከትግሬ ወገን የሚያሳዝነው እረገፈ ያለው ከህፃናት አንሥቶ ወጣት፣ ሽማግሌ፣ ጭምር መሆኑ ነው። አሁን ከዚያኛው ትውልድ የቀሩት ቢቆጠሩ 20 አይሞሉም። ህዝቡ እየተዋደቀ፣ እየረገፈ ያለው ለእነዚህ 20 ለማይሞሉ በቃኝ ለማያውቁ አረመኔ ጨካኞች ሲል መሆኑም ያሳዝናል።

"…በኢትዮጵያ ወገን እስከአለፈው እሁድ ድረስ በተለይ በቆቦ ግንባር የተዘበራረቀ አሰላለፍ ስለነበረ ከኢትዮጵያ ወገን ብዙ ምርኮኛና ቁስለኛ መመዝገቡን የሚደርሱኝ መረጃዎች ያሳያሉ። ሆስፒታሎች ሞልተው መንገድ ዳር ዳስ ተሠርቶም ህክምና ለመስጠት እየተሞከረ ነው። ከእሁድ ዕለት ወዲህ ግን አሰላለፉ በመቀየሩ ወታደሩ ከጥምር ጦሩ ከዐማራ ልዩ ኃይል እና ከዐማራ ፋኖ እንዲሁም ከዐማራ ሚኒሻ ጋር በመናበብ ከመከላከል ወደ ማጥቃት ተሸጋግሯል። በዚህም የተነሣ እጅግ ጠንካራ የተባሉ የህወሓት ምሽጎች እየተደረማመሱ ነው። ይሄ በእጅጉ ደስ የሚያሰኝ ነው።

"…ነገር ግን በሌላ በኩል በሰቆጣ ግምባር በህክምና አሰጣጥ በኩል በአንዳንድ ዐማራ ጠል በሆኑ የመከላከያ ኃላፊዎች ዘንድ እየታየ ያለው አረመኔያው የሆነ የጭካኔ ተግባር ከወዲሁ ይስተካከል ዘንድ በመከላከያ ውስጥ እንደ ሃገር የሚያስቡ አካላት ይናገራሉ። ምክሩን ተቀብሎ ማስተካከል ደግሞ የመከላከያ ሓላፊነት ነው።

፩ኛ፦ ቁስለኞችን እኩል ያለማየት፦

"…ይሄ ነገር እየተደጋገመ ነው። አብሮት እንዲዋጋ፣ እንዲዋደቅ ይጠራውና ፋኖው ሲቆስል ለፋኖ በጀት የለኝም፣ አላክምም ብሎ የቆሰለሉ ፋኖዎች ህክምና እንዳያገኙ ማድረግ ፀያፍ ነው። ይህን ትእዛዝ ጥሰው የቆሰለ ፋኖ ሲያክሙ የተገኙ ሃኪሞች በመከላከያ አዛዦች ሲዘለፉ፣ ሲሰደቡ ማየቱም ያሳፍራል። እንኳን ፋኖ የጠላት ጦር እንኳ ቢሆን ህክምና አይከለከልም። (ለሃኪሞቹ ደኅንነት ስል የመከላከያ ሓላፊዎቹን የድንፋታ ቪድዮ አዘገየዋለሁ)

፪ኛ፦ ያልታወቀ የመሳሪያ ክምችት፦

"…የሆስፒታሉን ስም አልገልፀውም። ነገር ግን ከሆስፒታሉ ጀርባ ማንነቱ ያልታወቀ ከፍተኛ መሳሪያ ክምችት አለ። መሳሪያው የወገን ጦር መሳሪያ ነው። መሳሪያው ተቀጣጣይ ፈንጂዎችንም ያካተተ ነው። በየጊዜውም የሚጨምርም ነው። እናም በተቻለ መጠን የመሳሪያ ክምችቱ ከሆስፒታሉ አካባቢ ቢርቅ መልካም ነው። ከፈነዳ ጥፋቱ ከባድ ስለሆነ ከወዲሁ ቢታሰብበት።

፫ኛ፦ ያልጠራ መከላከያ፦

"…በትግራይ ድንበር አካባቢ የሚገኙ ነዋሪዎች ትግርኛ ተናጋሪዎችም ጭምር ናቸው። ይሄን የማያውቁ ወይም አውቀው ማስተዋል የተሳናቸው አንዳንድ የመከላከያ ሓላፊዎች ከሆስፒታሉ ሆነው በስልክ ከወዲያኛው የህወሓት ሓይል ጋር ሲያወሩ፣ መረጃም ለጠላት ሲሰጡ እየታዘቡ ነው። ሓኪሞች። ይሄ ነውር ነው። እንትና በየትኛው ግንባር ነው የተሰለፈው? በዚያ ግምባር ነፍጠኛ ስለሚበዛ አምልጥ፣ በዚህ ግምባር አጥቁ፣ በዚህ እና በዚያ ግምባር የተሰለፈው መድፍ ሲሰማ የሚበተን የቅርብ ምሩቅ ነው። እያሉ ከወዲያኛው ጠላት ጋር የሚያወሩ አሉ። በተለይ ትግራይ ቆይተው የመጡ ቢጠነቀቁ መልካም ነው። አልያም እንደ ደብረ ታቦሩ ሰውዬ ስልካቸውን ጠልፎ እርምጃ መውሰድ ነው። አለበለዚያ የወገን ጦር ይጎዳል።

፬ኛ፦ ማታለል፦

"…በሆስፒታሎች ቀላል ቁጥር የሌላቸወረ በጣም ብዙ የመከላከያ አባላት ምንም አይነት አካላዊ ጉዳት ሳይደርስባቸው የቆሰሉ መስለው ጦርነቱን በመፍራት ብቻ የጓደኛቸውን ደም ተቀብተው የተመቱ መስለው ይመጣሉ። ይሄ የሚገጥም ቢሆንም በዚህ መጠን ግን አላየንም። ወይ የወታደራዊ ሥልጠና ጉድለት ነው። ወይም ደግሞ ተልእኮው ሌላ ነው። እናም ቢስተካከል።

ይህ ሲባል የወያኔ ጦር ደፋር ነው ማለት አይደለም። ወያኔ ህጻናትን ሳይቀር፣ ነፍሰጡር እመጫት ሳይቀር ሥነ ልቦናቸውን በኢትዮጵያና በዐማራ ህዝብ ጥላቻ ሰልባ፣ መርዝ ስትግታቸው፣ በዘፈን፣ በቀረርቶ ሁላ ስትነሽጣቸው ከርማ በመጨረሻም የሚያሳብድ ሀሺሽ እየሰጠች እንደምትማግዳቸው ይታወቃል። የእኛን ከዚያ ማወዳደር አይገባም። ቢሆንም ግን መመርመር ያስፈልጋል።

"…የወገን ጦር ድጋፍ ይፈልጋል። ህዝቡ ደጀን ሲሆን ወታደሩ ይደፍራል። የሙዚቃ ዝግጅት አንደኛው ወታደር ማጀገኛ መንገድ ነው። ድሮ የታወቁ ሙዚቀኞች ግንባር ድረስ ሄደው የሚዚቃ ሥራ በመሥራት ያበረታቱ ነበር። አሁን ያ አይታይም። ሙዚቀኞች በግንባር ሳሉ መሰዋታቸው ሁሉ ይታወሳል። እናም አሁን ያ የለም። ስለዚህ ወታደሩ ከነ ድብርቱ ነው ለውጊያ የሚላከው። በዚህ ላይ የዘር ፖለቲካው ጉዳይ አለ። እናም ቢታሰብበት።

፭ኛ፦ የመረጃ ዝርክርክነት

"…እንዴት እንደሆነ ባናውቅም በግልጽ የህውሓት ወታደሮች የሀገር መከላከያን ልብስ ለብሰው ማታ መረጃ ይዘው ይወጣሉ። ከማን ጋር እንደሚገናኙ ግን አይታወቅም። መከላከያ ውስጡን ቢያጸዳ መልካም ነው።

፮ኛ፦ የዩኒፎርም መመሳሰል

“…ከኦሮሚያ ክልል ሰልጥነው የመጡ አንዳንድ ሳይሆን በብዛት ለዐማራ ያላቸው ጥላቻ ከትግሬው የበለጠ ሆኖ እየተየ ነው። የቆሰለው ወታደር "ወይኔ በማያገባኝ መጥቼ ለነፍጠኛ ስል ቆሰልኩ፣ ትግሬና ዐማራ በተጣላ እኔ ምን ቤት ነኝ እያለ የሚብሰከሰክ ሲታይ ነገርየው ምንድነው ትላለህ። ባለፈው ጦርነትም፣ በአሁንም ገና ጦርነቱ ሳይጀመር ወደ ትግሬ ገብተው እጅ የሰጡም አሉ። የቆዩትም አሁን ያንኑ ዩኒፎርም ለብሰው የወገን ጦር መስለው እየገቡ ነውና በዚህ በኩል ጥብቅ ቁጥጥር እና ፍተሻ ቢደረግ መልካም ነው።

፮ኛ፦ በሞባይል ስልክ እየቀረጹ መዋጋት

"…አንዳንድ ወታደሮች ውጊያውን ትተው ቲክቶክ ሁላ ሲሠሩ ማየት ይደንቃል። በቤተ ክርስቲያን ዝማሬ ሲዘመር ጭብጨባ ትተው የማያዩትን ቪዲዮ ሲቀርጹ እንደሚውሉ ሴቶች በጦር ግንባርም ከጠላት ጋር እየተዋጉ ቪድዮ መቅረጽ እጅግ አደገኛ ነው። አንዳንዶች ቀጥታ ስርጭት ስለሚያስተላልፉም ለወገን ጦር ጉዳት ነው። በሰቆጣ ግንባር ግን የመከላከያ ሓላፊዎች ወደ ውጊያው የሚገቡ ወታደሮችን ስልክ ለቅመው መዝግበው ሲያስቀምጡ ታየተዋል። ይሄ የሚበረታታ ነው። በሁሉም ግምባሮች እንዲህ የሚድያ ሥራ የሚሠሩ ብቻ ፈቃድ ያላቸው ቢዘግቡ መልካም ነው። ወታደሩ ሬሳ ቀርጾ ለናትናኤል መኮንን እና ለእኔ ለመላክ ከሚጣደፍ ውጊያው ላይ ቢያተኩር መልካም ነው።

፯ኛ፦ የዐማራ ሚሊሻን በተመለከተ

"…የዐማራ ሚሊሻ አደረጃጀት የለውም። የቀበሌውን ሊቀመንበር ትእዛዝ ተቀብሎ የሚመጣ የዋህ ገበሬ ነው። የጦር መሣሪያውም ኋላቀር ነው። ብአዴኖች ፍፁም አረመኔዎች መሆናቸው የሚያስታውቀው በሽተኛ ሚሊሻ እዚያው ሄደህ አንድ ወያኔ ገለህ ሙት ብለው መላካቸው ነው። ይሄ ነውር ነው። ኃጢአትም ግፍም ወንጀልም ነው።

ሚሊሻው የተተኳሽ እጥረትም አለበት። በቁጥር ያለችውን ጥይት ከጨረሰ በቃ ከመሞት ውጪ ተስፋ የለውም። መገናኛ ሬድዮ የለውም። ከልዩ ኃይሉ፣ ከመከላከያው እና ከፋኖው ጋር ተደርቦ የሚገባ ነው። የትምህርት ዝግጅት የለም። ጦሩ ሲበተን ወዴት እንደሚሄዱም አያውቁም። መከላከያውን ያከብሩታል፣ ይፈሩታል፣ ይኮሩበታል። እናም የታዘዙትን ሁሉ " እሺ ጌታዬ ብለው ከመፈጸም በቀር ሌላ አያውቁም።
37.9K views09:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-02 11:51:39
የዐርብ ረፋድ ጦማሬ ነው።

"…ጦርነቱ መቆሙ አይቀርም። አንድ ቀን አንዱ ሲደክመው መቆሙ አይቀርም። ነገር ግን እስከዚያው ትግሬና ዐማራ ተጨፋጭፎ ቁጥሩ መቀነስ አለበት። በትግሬ በኩል እንደምታዩት አሮጊቷ አዛውንት እናት እንኳ ሳይቀሩ ነው የተሰለፉት። ለዝርፊያም፣ ለግድያም። ይሄ የጥላቻ ፖለቲካ የወለደው ክፉ ደዌ ነው።

"…በሁለቱም በኩል ሞትም ቁስለኛም የትየለሌ ነው። ሃኪም ቤት ሞልቶ መንገድ ዳር ዳስ ተሠርቶ እየተካመ ነው። ለማንኛውም ዘንዶ ጥምጥም፣ ሊማሊሞ የመሰለ ጦማሬን ከታች አንብቡልኝ። ከደበራችሁ አጫጭሩ ጦማር እስኪለጠፍ ባላየ ባልሰማ እለፉት።



የምጠቀመው፣ ሃሳቤን የምገልፀው፣ መልእክቴንም የማስተላልፈው በዚህ ቴሌግራም ቻናሌ ብቻ ነው። ከዚህ ውጪ ፌስቡክ የማልጠቀም መሆኔም ይገለፅ፣ ይታወቅልኝ። ተናግሬአለሁ።

http://t.me/ZemedkunBekeleZ

https://t.me/zemede_Discussion
42.3K views08:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-02 00:48:24
"…ነገ ጠዋት በአንደኛው የጦር ግንባር እየተፈጸመ ስላለ ዘግናኝ አፀያፊ ግፍ በአጭሩ ጀባ እላችኋለሁ።

"…መረጃው ለዐማራ ልዩ ኃይልና ለዐማራ ፈኖ እንዲሁም ለዐማራ ሚሊሻ ነው የሚጠቅመው።

• ደኅና እደሩ…!!
77.3K viewsedited  21:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 22:38:28
እንባና ሳቅ… ዋይታና ጭፈራ…!!

"…በሰሜን ኢትዮጵያ ዐማራ እና ትግሬ በእሳት ይጨፋጨፋል። በመሃል ሃገር በአዲስ አበባ ደግሞ የትግሬና የዐማራ ሴት ብብቷን እስኪያልባት ድረስ አቅሏን ስታ ትጨፍራለች። ምንአይነት የከፍት አዕምሮ እንደታደለ ህዝቡ ይገርማል። ኦሮሞዋ አዳነች አቤቤና የኦነጉ ሊቀመንበር ኦቦ ቀጀላ መርዳሳ ደሞ ሙድ ይይዙባቸዋል። ቀላል ይቀልዱባቸዋል በማርያም።

"…እየጨፈራችሁ ዐማራና ትግሬዎች…!!
"…አስጨፍሯቸው ኦሮሞዎች…!!
83.9K views19:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 22:19:19
የወግ ኽምራ መረጃ…!!

"…በዛሬው የውጊያ ውሎ በኮረም አቅጣጫ የህውሀት ኃይሎች የተወሰኑ ሾልከው በመግባት የላበላን ዋናውን መንገድ ለመዝጋት መክረው እንደነበር ተነግሯል። ሐሙሲት ከሚባል ቀበሌ በደቡብ በኩል ውጊያ ነበር። አብዛኛው የህወሓት ጠንካራ ምሽጎች በሃገር መከላከያ፣ በዐማራ ፋኖና፣ በዐማራ ልዩ ኃይል ፍርስርሳቸው መውጣቱም ተነግሯል።

"…ከእኛም ወገን በውጊያው ላይ ቆሰሉ የመከላከያ አባላት ሰቆጣ ሆስፒታል እየገቡ ነው። የህወሓት ጦር አሁን ተመትተው ወደኋላ ማፈግፈጋቸውም ተነግሯል።

"…እነ አሜሪካ ለህዝቡ የለገሱት የእርዳታ ስንዴም በየምሽጎቹ ተበትኖ መገኘቱም ተመልክቷል። አቤቱ ጌታ ሆይ ትግሬ ግን ከምድር ላይ አለቀ። ተዉ የሚልም ጠፍቷል። ከእልቂት ምን እንደሚያተርፉ መድኃኔዓለም ይወቅ። ምን እንደሚሻልም መድኃኔዓለም ይወቅ።

"…እየሞታችሁ…!!
84.2K views19:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 22:16:46
ዋግ ኽምራ የጦር ውሎ…!!

"…ንጋት 12:00 ሰዓት ጀምሮ ህወሓት ወደ ዋግ ኽምራ ሰቆጣ ለመግባት ከሰቆጣ ፋጥዝጊ ከሚባል ተራራ ላይ ሁና ወደ ዝቋላ ወረዳ ቀዳሚት ቀበሌ ከባድ መድፍ በመተኮስ የተለመደ ትንኮሳዋን ትጀምራለች። ነገር ግን እንደ ቆቦው ግንባር በርግጎ የሚሸሽ፣ የሚፈረጥጥ፣ የማይናበብ የኢትዮጵያ ሠራዊት በዚህኛው ግንባር አልገጠማትም። እንዲያውም አጸፋውን አከበዱባት።

"…በውጊያው ያ ድሮ ኢትዮጵያ በምታውቀው፣ መሸነፍ፣ መበርገግ፣ መሮጥ በማያውቀው ጀግና ስንለው በኩራት ደረታችንን ነፍተን በምንመሰክርለት በኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዎትና ጀግኖቹ በዐማራ ልዩ ኃይል፣ በዐማራ ፋኖ እና በዐማራ ሚኒሻዎች ጽኑ ተጋድሎ ህወሓትን በመመከት እስከ ቀኑ 10 ሰዓት ድረስ ውጊያው መቆየቱም ተነግሯል። ከ10ሰአት በኋላ ግን በሰቆጣ የከባድ መሣሪያ ድምፅ አልተሰማም።

"…ህወሓት በ3 አቅጣጫዎች ነበር መድፍ ስትተኩስ የዋለችው። 1ኛ ወደ ዝቋላ ቀዳሚት ቀበሌ። 2ኛ አበርገሌ ወረዳ፣ 3ኛ ፃግብጂ ወረዳ። የፃግብጅ ድልድዩን ሰብረውት የነበረ ቢሆንም ያ ድሮ የምናውቀው መመኪያችን የምንለው፣ የሃገር ኩራት የሃገር መከላከያ ሰራዊታችን ጊዜያዊ ድልድይ በአስቸኳይ በመሥራት ጥራሪን ተሻግሮ ወደ ኮረም መስመርም አልፏል። ገስግሷልም።

"…ጥምር ጦሩ ማታ አበርገሌ ጠዋት መቀሌ ነው የምገኘው እያለ ሲሆን ወደ ኮረም ከገሰገሰና ኮረም ከገባ ግን ወልድያን እይዛለሁ ብሎ በወጥመድ ውስጥ የተቀረቀረው የህወሓት ሰራዊት የመማረክ ዕድል ካልገጠመው በቀር ለወሬ ነጋሪም መትረፉን እንጃ ነው የሚሉት የመረጃ ምንጮቼ። በአፋር በኩል ደግሞ መቀሌ 50 ኪሎሜትር ነው የሚርቀው።

"…ይህ የእኔ የዘመዴ መረጃ ነው።

• ድል ለኢትዮጵያ ሠራዊት…!!
• ለዐማራ ልዩ ኃይል…!!
• ድል ለዐማራ ፋኖ…!!
44.9K views19:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 20:43:02
የትግሬዎች የእስር ዜና

"…በወጡበት በዚያው ይቀራሉ ተብለው ይጠበቁ የነበሩትና ወደ ሃገር ቤት የመመለስ ዜናቸው መሰማት ከጀመረ በኋላ ከላይ በወረደ መመሪያ ነው በሚል ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ ታስረው የተፈቱ በዘር ትግሬ የሆኑ በሙሉ እንዲታሰሩ መወሰኑ ተነግሯል።

"…በዚህም መሠረት በትናንትናው እለት ከዚህ በፊት ምንም ክስ ያልነበረበት ሊቀ ጠበብት ኤልያስ ተጫነ እና እስክንድር ወደ ማዕከላዊ ተወስደወ መታሰራቸው ተነግሯል። ትናንትም ዛሬም የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ ልዩ ጽ/ቤትም በብልፅግ የፖሊስ ኃይል ተከቦ መዋሉም ተሰምቷል።

"…ከመንግሥት አካባቢ ባገኘሁት መረጃ ይታሠሩ ዘንድ ውሳኔ ከተላለፈባቸው መካከል አዲስ አበባ የመሳለሚያ ልጅ የሆኑትና የብፁዕ ወቅዱስ ልዩ ጽ/ቤት ቤት ሓላፊ
መልአከ ሕይወት አባ ኃይለገብርኤል ነጋሽ (ቆሞስ) መልአከ ገነት አባ ኪዳነ ማርያም ደስታ(አቡነ ቀሲስ) መምህር ሙሴ ኃይሉ የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ተጠሪ ፕሮቶኮላቸው፣ መምህር ልሳነ ወርቅ ደስታ ገብረሕይወት የብፁዕ ወቅዱስ ፓትሪያርክ ልዩ ጽ/ቤት ጉዳይ አስፈፃሚ፣ መልአከ ሰላም አባ ኪሮስ ወልደ አብ፣ አባ ተስፋሥላሴ ዘርአይና ሌሎችም ትግሬዎች እንደሆኑ ተነግሯል።

"…የእስሩ ምክንያት በዋነኝነት ከሃገር ለህክምና ሲወጡ በቦሌ ያዋረዳቸው መንግሥት ፓትርያርኩ ተናደው በዚያው ይቀራሉ ብሎ አስቦ የነበረ ቢሆንም ነገር ግን ቅዱስነታቸው መንበሬን ጥዬማ የትም አልሄድም ብለው ለመመለስ መወሰናቸው ስላበሳጨው ነው የሚሉም አሉ። ዛሬም እስሩ ቀጥሎ ምክንያቱ ባይታወቅም ጎጃሜው ሊቀ ማዕምራን ፋንታሁን ሙጬም በዛሬው ዕለት ከረፋዱ 5ሰዓት ላይ ከቢሮው ውስደው እንዳሰሩት ተሰምቷል። በዚህ አካሄዳቸው በንዴት ፓትርያርኩን እንዳይተናኮሏቸውም እሰጋለሁ። እያመመው መጣ አለ አዝማሪው።

"…ትግሬዎች አይዟችሁ። እየታሰራችሁ…!!
64.1K views17:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ