Get Mystery Box with random crypto!

የትግሬዎች የእስር ዜና '…በወጡበት በዚያው ይቀራሉ ተብለው ይጠበቁ የነበሩትና ወደ ሃገር ቤት የ | Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

የትግሬዎች የእስር ዜና

"…በወጡበት በዚያው ይቀራሉ ተብለው ይጠበቁ የነበሩትና ወደ ሃገር ቤት የመመለስ ዜናቸው መሰማት ከጀመረ በኋላ ከላይ በወረደ መመሪያ ነው በሚል ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ ታስረው የተፈቱ በዘር ትግሬ የሆኑ በሙሉ እንዲታሰሩ መወሰኑ ተነግሯል።

"…በዚህም መሠረት በትናንትናው እለት ከዚህ በፊት ምንም ክስ ያልነበረበት ሊቀ ጠበብት ኤልያስ ተጫነ እና እስክንድር ወደ ማዕከላዊ ተወስደወ መታሰራቸው ተነግሯል። ትናንትም ዛሬም የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ ልዩ ጽ/ቤትም በብልፅግ የፖሊስ ኃይል ተከቦ መዋሉም ተሰምቷል።

"…ከመንግሥት አካባቢ ባገኘሁት መረጃ ይታሠሩ ዘንድ ውሳኔ ከተላለፈባቸው መካከል አዲስ አበባ የመሳለሚያ ልጅ የሆኑትና የብፁዕ ወቅዱስ ልዩ ጽ/ቤት ቤት ሓላፊ
መልአከ ሕይወት አባ ኃይለገብርኤል ነጋሽ (ቆሞስ) መልአከ ገነት አባ ኪዳነ ማርያም ደስታ(አቡነ ቀሲስ) መምህር ሙሴ ኃይሉ የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ተጠሪ ፕሮቶኮላቸው፣ መምህር ልሳነ ወርቅ ደስታ ገብረሕይወት የብፁዕ ወቅዱስ ፓትሪያርክ ልዩ ጽ/ቤት ጉዳይ አስፈፃሚ፣ መልአከ ሰላም አባ ኪሮስ ወልደ አብ፣ አባ ተስፋሥላሴ ዘርአይና ሌሎችም ትግሬዎች እንደሆኑ ተነግሯል።

"…የእስሩ ምክንያት በዋነኝነት ከሃገር ለህክምና ሲወጡ በቦሌ ያዋረዳቸው መንግሥት ፓትርያርኩ ተናደው በዚያው ይቀራሉ ብሎ አስቦ የነበረ ቢሆንም ነገር ግን ቅዱስነታቸው መንበሬን ጥዬማ የትም አልሄድም ብለው ለመመለስ መወሰናቸው ስላበሳጨው ነው የሚሉም አሉ። ዛሬም እስሩ ቀጥሎ ምክንያቱ ባይታወቅም ጎጃሜው ሊቀ ማዕምራን ፋንታሁን ሙጬም በዛሬው ዕለት ከረፋዱ 5ሰዓት ላይ ከቢሮው ውስደው እንዳሰሩት ተሰምቷል። በዚህ አካሄዳቸው በንዴት ፓትርያርኩን እንዳይተናኮሏቸውም እሰጋለሁ። እያመመው መጣ አለ አዝማሪው።

"…ትግሬዎች አይዟችሁ። እየታሰራችሁ…!!